TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EHRC

" በወልቂጤ ከተማ ጥቅምት 02 ቀን 2016 ዓ.ም. ለተከሰተው ሁከት እና የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ተጠያቂነት ማረጋገጥ፣ እንዲሁም ለተፈናቃዮች እና ተጎጂዎች አስፈላጊው ድጋፍ እና ካሳ ሊሰጣቸው ይገባል " - የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)

ከኢሰመኮ የተላከ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
Report_of_the_Ethiopian_Human_Rights_Commission_EHRC_and_the_Office.PDF
1.6 MB
#EHRC #UN #ሪፖርት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጽህፈት ቤት ከሐምሌ ወር 2014 ዓ/ም - መጋቢት ወር 2015 ዓ/ም ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች በሽግግር ፍትሕ ጉዳይ ላይ ከተጎጂዎችና ጉዳት ከደረሰባቸው ማኅበረሰቦች ጋር ባደረጉት ምክክር የተገኙ ግኝቶችን በተመለከተ ይፋ ያደረጉት ባለ 90 ገጽ ሪፖርት ከላይ ባለፈው ፋይል ተያይዟል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara #Merawi በአማራ ክልል ፤ በየጊዜው በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በመንግሥት የፀጥታ ኃይል መከላከያ እና በ " ፋኖ " ታጣቂ ኃይሎች መካከል ግጭቶች ይደረጋሉ። በእነዚህ ግጭቶችም በሁለቱም በኩል ከሚሞተው የግጭቱ ተካፋይ ባለፈ ንፁሃን ሰዎች ሰለባ እየሆኑ እንዳለ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ምንም እንኳን #መንግሥት ፤ " ከእውነታው ያፈነገጠ እና ሚዛናዊነት የጎደለው " ብሎ ቢያጣጥለውም የኢትዮጵያ…
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በአማራ ከልል ምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ በ20/05/2016 ዓ.ም በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች መካከል በነበረ ግጭት ከፍተኛ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች እንደደረሱት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

በእዚህ ግጭት ምክንያት በመርዓዊ ከተማ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ እንደነበር ፤ በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች ላይ ግድያ፣ የአካል ጉዳት፣ ድበደባ፣ ማስፈራራትና ሌሎችም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መፈፀማቸውን ገልጿል።

በአካባቢው በነበረው ግጭት ምክንያት ከ80 በላይ የሆኑ በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች የተገደሉ መሆኑን ከእነዚህም መካከል ሁለት ሴቶች እንደሚገኙበትና ለግድያው ምክንያት የነበረው በግጭቱ ወቅት የነበረው ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር አመልክቷል።

በተጨማሪም ቤት ለቤት በመዘዋወር ግድያ መፈጸሙን ከአካባቢው ካሰባሰብኳቸው መረጃዎች ለመረዳት ችያለሁ ብሏል።

በእዚህ ግጭት ወቅት አካል ጉዳተኞች ላይ ድብደባ የተፈጸመ መሆኑንና ከተገደሉ ሰዎች መካከል አንድ የ17 አመት ታዳጊ እንደሚገኝበት ከአካባቢ ከነበሩ የአይን እማኞች ለመረዳት እንደተቻለ ገልጿል።

ከአይን እማኞች አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት ፦
- ወንዶችን ቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ ወደመንገድ በማውጣት የጅምላ ግድያ መፈጸሙን፤
- ከ21/05/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሟቾች አስከሬን በመርዓዊ ከተማ ማሪያም ቤተክርስቲያን በጅምላ እየተቀበሩ የነበረ መሆኑን፤
- በከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ምክንያት የአካባቢው ነዋሪ አካባቢውን ለቆ እየወጣ መሆኑን አመልክቷል።

ኢሰመጉ ከላይ የተዘረዘሩትን ጉዳዮች በአካል በመገኘት ምርመራ በማድረግ ለማረጋገጥ እንዳልቻለ በመግለጫው አሳውቋል።

ይህንን ጉዳይ አስመልከቶ የአካባቢው የጸጥታው ሁኔታ ሲፈቅድ ተጨማሪ የምርመራ ስራን በማከናወን ዝርዝር መግለጫን እንደሚያዘጋጅ ይፋ አድርጓል።

እስካሁን በመንግስት በኩል የተሰጠ ምላሽም ይሁን መረጃ የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቀናት በፊት በመርዓዊ ጉዳይ ባዘጋጀው አንድ ዘገባ  ፦
* የክልሉ የኮሚዩኒኬሽን ምክትል፣
* የክልሉና የሰሜን ጎጃም ዞን ኮማንድ ፖስት፣
* የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ስለጉዳዩ ምን ምላሽ እንዳለቸው ለማወቅ እና ሃሳባቸውን ለማካተት ስልክ ቢደውልም ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሀሳባቸውን ለማካተት ሳይችል ቀርቷል።

በክልሉ ኮሚኒኬሽን በኩል ምላሽ ለማግኘት ለአንድ ኃላፊ ስልክ ብንደውልም ጥያቄውን በዝርዝር ከሰሙ በኋላ " ስብሰባ ላይ ነኝ መልሼ ደውላለሁ " ቢሉም አልደወሉም ፤ በድጋሚም ስልክ ሲደወል ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።

" እባክዎ ስልክዎን ያንሱና በኮሚዩኒኬሽን በኩል ያለውን የመርዓዊ ጉዳይ ማብራሪያ በመስጠት ኃላፊነትዎን ይወጡ " የሚል የፅሑፍ መልዕክት (SMS) ቢላክላቸውም ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ኮሚሽን ( #ኢሰመኮ ) ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ " መረጃው ደርሶናል (የመርዓዊ ጉዳይ) ። እያረጋገጥን ነው " ብለዋል።

አክለው ፣ " የጸጥታ ጉዳይ ስለሆነ ትንሽ መንቀሳቀስና መረጃ መሰብሰብ አስቸጋሪ ሊሆን ስለሚችል ሊዘገይ ይችላል። ግን እያጣራን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AmharaRegion #Gojjam ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላና ኧሌ ዞኖች ተነስተው ለደን ምንጣሮ ስራ ወደ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እያመሩ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ጎዛምን አካባቢ በ " ፋኖ ታጣቂዎች " የተያዙ የቀን ሰራተኞችን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረገ መሆኑን የምልመላና የቅጥር ሂደቱን የፈፀመው " ኒኮቲካ ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር አሳውቋል። የታገቱት ሰራተኞች ብዛታ 272…
#EHRC

ወደ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ለሥራ ሲያመሩ በአማራ ክልል ጎጃም ውስጥ ስለታገቱ ዜጎች ሰምቶ እንደሆነና መረጃው ይኖረው እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)ን ጠይቋል።

የተጀመረ ምርመራ ካለም ማብራሪያ ጠይቀናል።

አንድ የኮሚሽኑ አካል በሰጡት ምላሽ፣ “ መረጃው አለን። በሥራ ላይ ነን። ምናልባት እንግዲህ ፋይንዲንጎች ሲኖሩ እናሳውቃለን ” ሲሉ አረጋግጠዋል።

እኚሁ የኮሚሽኑ ባልደረባ ፤ “ መረጃው ደርሶናል ” ያሉ ሲሆን፣ ምርመራ ጀምራችኋል ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “ አዎ መረጃ የመሰብሰብና የማጣራት እንቅስቃሴ አለ ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን የተሰኘው ቀጣሪ ድርጅት ሰራተኞቹን በህጋዊ መንገድ እንደወሰዳቸው የገለጸ ሲሆን ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ጋርም የተለዋወጠው ደብዳቤ ስለመኖሩ ተነግሯል።

ታዲያ የነዚህን ሰራተኞች ጉዳይ በተመለከተ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዋኖ ምን አስተያየት እንዳላቸው ለማወቅ ስልክ ደውለን ነበር።

ኃላፊው ፤ ጥያቄውን በጽሞና ከሰሙ በኋላ ማብራሪያ ለመስጠት ቀጠሮ ቢሰጡም ፣ በሰጡት የቀጠሮ ሰዓት በተደጋጋሚ ስልክ ሲደወል ለማንሳትም ሆነ ስለጉዳዩ የፅሑፍ ምላሽ እንዲሰጡ ለተላከላቸው የፅሑፍ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ወደ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ እየተጓዙ ነው የተባሉና ጎጃም ውስጥ በፋኖ ታጣቂዎች ታግተዋል የተባሉ ሠራተኞች በቁጥር 272 እንደሆኑ ቀጣሪ ድርጅቱ ገልጿል።

ሠራተኞቹን ለማስለቀቅም ሽምግልናን ጨምሮ ሌሎች ጥረቶችን በስፍራው ተገኝቶ እያደረገ እንደሚገኝ አመላክቷል።

ቃላቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ የሰጡት ' የአማራ ፋኖ የጎጃም ቃል አቀባይ ነኝ ' ያሉት ፋኖ ማርሸት ፀሀዩ ፤ " ልጆቹ አውቀውም ይሁን ተጭበርብረው ጎጃም ውስጥ ወደሚገኘው የብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ሲወሰዱ እንዳገኟቸው " ገልጸዋል።

ሲመሯቸው የነበሩትም ወታደሮች እንደነበሩ ከተገኘው መታወቂያቸው ማረጋገጣቸውን ነገር ግን በቀጣይ ከ72 እስከ 100 ሰዓታት ውስጥ ለቀይ መስቀል ለማስረከብ እየተዘጋጁ እንደሆነ አሳውቀዋል።

መረጃው በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
#ሪፖርት

በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በግጭት ዐውድ ውስጥና ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች አሳሳቢነትና ሥጋቶችን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ሪፖርት አውጥቷል።

በሪፖርቱ ፦

- ከሕግ ውጭ ግድያ (በድሮን ጨምሮ) ፣ የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ፤
- የዘፈቀደ፣ ሕገወጥ፣ የጅምላና የተራዘመ እስራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፤
- እገታ
- አስገድዶ መሰወር እና ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ አስሮ ማቆየት
- የሀገር ውስጥ መፈናቀል ... ተዳሰዋል።

° በጸጥታ መደፍረስ፣
° ከመንግሥት አካላት ተገቢውን ምላሽና ትብብር በወቅቱ ባለማግኘት
° በሌሎች ምክንያቶች ምርመራቸውና ክትትላቸው የዘገዩና የተጓተቱ በርካታ ጉዳዮችን መኖራቸው ተገልጿል።

እነዚህን ጉዳዮች በመርመርና ክትትል በማድረግ በተገቢው ጊዜ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኮሚሽኑ የተላከለትን ዝርዝር ሪፖርት ከላይ አያይዟል፤ በጥሞና ያንብቡት።

ኢሰመኮ በግጭት ዐውድ ውስጥ እና ከዐውድ ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችንና ሥጋቶችን በአስቸኳይ ማቆም ይገባል ብሏል።

የአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎችን ጨምሮ ሁሉንም የትጥቅ ግጭቶች በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምና የሰብአዊ መብቶች መከበርን ማረጋገጥ እንደሚገባም አስገንዝቧል።

#EHRC
#Ethiopia #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Amhara

ኢሰመኮ፦

- ከየካቲት 15 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ/ም በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ (ዝቋላ ወገም፣ ፈረስ ቤት01፣ ገሳግስና ጉድባ ሰቀላ ቀበሌዎች) እና ሰከላ (አጉት፣ ጉንድልና አምቢሲ ቀበሌዎች እና ግሼ ዓባይ ከተማ) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል የተካሄዱ የትጥቅ ግጭቶችን ተከትሎ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ አካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ደርሷል።

- የካቲት 20/2016 በሰሜን ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው የጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የአብነት ተማሪዎች የዕለቱን ትምህርትና ጉባኤ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ አጠናቀው ወደ ማደሪያ ጎጇቸው ከገቡ በኋላ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አባላት ከሌሊቱ 6፡30 ሰዓት ገደማ ላይ ወደ ቦታው ደርሰው ተማሪዎችን “ #ውጡ ” እያሉ ተኩስ በመክፈት ቀድመው በወጡ #በ11_ተማሪዎች ላይ ግድያ እንደፈጸሙ፤ ሌሎች 8 ተማሪዎችንም ደግሞ በቁጥጥር ሥር አውለው ካሳደሩ በኋላ በማግስቱ ምንም ጥፋት የለባችሁም ብለው እንደለቀቋቸው ኢሰመኮ ለመረዳት ችሏል። በወቅቱ በአቅራቢያው የሚንቀሳቀስ የታጠቀ ኃይል እንዳልነበር ምስክሮች አስረድተዋል።

- መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ/ም በኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን የተነሱ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር #በኤፍራታና_ግድም እና #ቀወት ወረዳዎች በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ ንብረት መውደሙን፣ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን እና የቀንድ ከብቶችና ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች መዘረፋቸውን ኢሰመኮ ተረድቷል።

- መጋቢት 6 ቀን 2016 በአማራ ክልል፣ በባሕር ዳር ከተማ ዘንዘልማ አካባቢ አቶ ብርሃኑ ሽባባው አካል ፣ አቶ በላይ አካል እና አቶ ተሾመ ይበልጣል የተባሉ ነዋሪዎች አንዱ በሚሠራበት ሱቅ እና ሁለቱ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ " ኑ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ " በሚል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ መጋቢት 7 ቀን 2016 በባሕር ዳር ቀበሌ 14 በተለምዶ ጉዶ ባሕር አካባቢ #የፊጥኝ_እንደታሰሩ በጥይት ተገድለው ተገኝተዋል።

- በባሕር ዳር ዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ ጋጃ መስክ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ መጋቢት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት በተፈጸመ ጥቃት ሶላት ስግደት አከናውነው ወደ ቤታቸው እየተመለሱ የነበሩ የእስልምና ተከታይ 5 ሰዎች (4ቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ) ተገድለዋል።

- ሚያዝያ 7/2016 ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ አጎና ቀበሌ ላይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከእስቴ ወረዳ ወደ ላይ ጋይንት ወረዳ በመጓዝ ላይ እያሉ በአካባቢው ላይ በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች (#ፋኖ ) ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ታጣቂዎቹ አካባቢውን ጥለው እንደሸሹ #የመንግሥት_የጸጥታ_ኃይሎች ወደ ቦታው በመግባት 7 (1 ሴትና 6 ወንዶች) ሲቪል ሰዎች ላይ ከሕግ ውጪ ግድያ ፈጽመዋል። ከ15 በላይ የሚሆኑ የቆርቆሮ ክዳን ያላቸው መኖሪያ ቤቶች እና 3 የገለባ ቤቶችና ንብረት መቃጠላቸውን እንዲሁም ከ100 በላይ የሚሆኑ የቀበሌው ነዋሪዎች ወደ ሌላ አካባቢ የተፈናቀሉ መሆኑን የቀበሌው ነዋሪዎች እና ተጎጂዎች ገልጸዋል።

- ግንቦት 4/2016 ዓ/ም ከቀኑ ከ7፡00 ሰዓት አካባቢ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ ውስጥ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በጉሎ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ግቢ ውስጥ 2 ሲቪል ሰዎች ሲገደሉ አንድ ሴት መምህርትን ጨምሮ ሌሎች 9 ሲቪል ሰዎች የቆሰሉ መሆኑን ኢሰመኮ ተረድቷል።

#Amhara #EHRC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara ኢሰመኮ፦ - ከየካቲት 15 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ/ም በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ (ዝቋላ ወገም፣ ፈረስ ቤት01፣ ገሳግስና ጉድባ ሰቀላ ቀበሌዎች) እና ሰከላ (አጉት፣ ጉንድልና አምቢሲ ቀበሌዎች እና ግሼ ዓባይ ከተማ) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል የተካሄዱ የትጥቅ ግጭቶችን ተከትሎ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ አካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ደርሷል። - የካቲት 20/2016…
#Oromia

ኢሰመኮ ፦

- ታኀሣሥ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በግምት ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት አካባቢ በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጉዱሩ ወረዳ ውስጥ በተፈጸመ #የድሮን_ጥቃት
° በየነ ጢቂ፣
° ጉደታ ፊጤ፣
° ሀብታሙ ንጋቱ፣
° ታዴ መንገሻ፣
° ዳመና ሊካሳ፣
° ዱጋሳ ዋኬኔ፣
° ሕፃን አብዲ ጥላሁን
° ሕፃን ኦብሳ ተሬሳ የተባሉ 8 ሰዎች ተገድለዋል።

በተጨማሪም፦
• ስንታየሁ ታከለ፣
• ሽቶ እምሩ፣
• ተሜ ኑጉሴ
• አለሚ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በአካባቢው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ”) በሰፊው ይንቀሳቀስ የነበረ መሆኑን እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው በሚደረጉ ውጊያዎች አልፎ አልፎ #በድሮን_ይጠቀም የነበረ መሆኑን ኢሰመኮ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

- ጥር 9/2016 ዓ/ም በሰሜን ሸዋ ዞን ፤ ደራ ወረዳ የሀገር መከላከያ ሰራዊት #ለሌላ_ግዳጅ አካባቢውን ለቅቆ ይወጣል። ይህን ተከትሎም የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) ታጣቂዎች በማግስቱ አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በኋላ “ ለመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ምግብ ስታቀርቡ ነበር ” በማለት 01 ቀበሌ የሚገኘው ሳላይሽ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጥበቃ የነበሩት አቶ ስዩም ካሴን #በጥይት_በመምታት ገድሏል። አቶ ከበደ ዓለማየሁ የተባሉ ነዋሪን ከመኖሪያ ቤታቸው አስወጥተው ከወሰዷቸው በኋላ በአካባቢው ጫካ አስክሬናቸው ወድቆ ተገኝቷል።

- ጥር 13 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋት 2 ሰዓት ጀምሮ ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በምዕራብ ጉጂ ዞን፣ ገላና አባያ ወረዳ ኤርገንሳ ቀበሌ ለሚኖሩ ነዋሪዎች የኩፍኝ በሽታ ክትባት ለመስጠት በመጓዝ ላይ በነበሩ ሠራተኞች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የገላና አባያ ወረዳ አስተዳደር ጤና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊን ጨምሮ ሁለት ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል። እንዲሁም 3 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- ከየካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በአማራ ክልል ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ #የአማራ_ታጣቂ_ቡድኖች የኦሮሚያ ክልል ፤ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በሚገኙ አዋሳኝ ቀበሌዎች በሲቪል ሰዎች ላይ #በተከታታይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች ፦
➡️ 25 ሲቪል ሰዎችን ገድለዋል ፤ 
➡️ 4 ሲቪል ሰዎች ላይ የአካል ጉዳትን አድርሰዋል
➡️ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሲቪል (ሰላማዊ) ሰዎችን #አግተው ወስደዋል። በታጣቂዎቹ በተፈጸመ ጥቃት በርካታ የመኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል።

- በሰሜን ሸዋ ዞን ፤ ደራ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (በተለምዶው “ ኦነግ ሸኔ ”) ታጣቂዎች ከኅዳር ወር 2016 ዓ/ም ጀምሮ በወረዳው በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች በሲቪል ሰዎች ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች ፦
➡️ 15 ሲቪል (ሰላማዊ) ሰዎች #ተገድለዋል
➡️ ቁጥራቸው ለጊዜው በትክክል ያልታወቀ በርካታ ነዋሪዎችን #አግተው_ወስደዋል
➡️ በርካታ የቀንድ ከብቶችን ዘርፈዋል
➡️ መኖሪያ ቤቶችን አቃጥለዋል።

- መጋቢት 1/2016 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ስልካምባ ከተማ ላይ የኦሮሞ ነጸነት ሰራዊት (በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ”) ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት የወረዳው አበዪ ሄቤን ቀበሌ ነዋሪ የነበሩ አቶ ሹመቴ ፋርስ እና ወ/ሮ ተቀባ አበጋዝ የተባሉ አረጋዊያን በመኖሪያ ቤቶቻቸው ፊት ለፊት ተገድለዋል።

- መጋቢት 16/2016 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ባሉት ሰዓታት ማንነታቸው ያልታወቀ የታጠቁ ቡድኖች በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ 7 ሰዎችን ተኩሰው መግደላቸውን ለማወቅ ተችሏል። በዕለቱ በተፈጸመ ጥቃት የቀበሌው ነዋሪ የሆነ እና የምዕራብ አርሲ ሃገረ ስብከት የዶዶላ ደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆነ ግለሰብ ፣ ከባለቤቱ እና #ከ2_ልጆቹ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው እያሉ እንዲሁም ሌላ አንድ ዲያቆን ከባለቤቱ እና ከእህቱ ጋር በመኖሪያ ቤታቸው መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል። 

- መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም በዶዶላ ወረዳ በደነባ ቀበሌ በግምት ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ ላይ 4 የቀበሌው ነዋሪዎች ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ሰዎች/ቡድኖች በጥይት ተመተው ሲገደሉ 5 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

- የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ( በተለምዶ “ #ኦነግ_ሸኔ ” ) በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ አመያ ወረዳ ውስጥ “ የመንግሥት ሠራተኞች እና የመንግሥት ጸጥታ ኃይል አባላት ቤተሰቦች ናችሁ ” በሚል ወይም “ለመንግሥት አካላት ትብብር አድርጋችኋል” በሚል ምክንያት በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች በየካቲት እና ሚያዝያ ወራት በፈጸማቸው ተከታታይ ጥቃቶች በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ፣ አካል ጉዳት፣ እገታ፣ ንብረት ውድመት እና ዘረፋ ፈጽሟል።

ለምሳሌ ፦

👉 በወረዳው አቡዬ ጀብላል ቀበሌ የካቲት 7/ 2016 ዓ.ም. በፈጸመው ጥቃት 11 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፤ መኖሪያ ቤቶችንና ሞተር ብስክሌቶችን አቃጥሏል፤ የቀንድ ከብቶችን ዘርፏል።

👉 መጋቢት 27/2016 ዓ.ም. በወረዳው ቆታ ከተማ ላይ በፈጸመው ጥቃት 31 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል፣ 3 ሲቪል ሰዎችን አቁስሏል፣ የቀንድ ከብቶችንና ሌሎች ንብረቶችን ዘርፏል እንዲሁም ንብረቶችን አቃጥሏል።

👉 ሚያዝያ 8/2016 ዓ/ም በደራ ቲርቲሪ ቀበሌ ላይ ታጣቂ ቡድኑ በፈጸመው ጥቃት 2 ሲቪል ሰዎችን ገድሏል ፣ ከ100 በላይ የተለያዩ የቀንድ ከብቶች ዘርፏል።

👉 በሚያዝያ 13/2016 ዓ/ም በጎምንቦሬ አሊይ ቀበሌ 36 የቀንድ ከብቶችንና 3 የሞቶር ብስክሌት ዘርፏል።

#Oromia #Ethiopia #EHRC

@tikvahethiopia
#StateofEmergency #EHRC

" በእስር የቆዩ ሰዎች ሊለቀቁ ይገባል " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (#ኢሰመኮ) ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አተገባበር ጋር በተያያዘ በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ጠየቀ።

በአማራ ክልል በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች (በተለምዶ “#ፋኖ”) መካከል ከሚካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር ተያይዞ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የነበረው እና ጥር 24 ቀን 2016 ዓ/ም ለተጨማሪ 4 ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ ተፈጻሚነት አብቅቷል።

ይህንን ተከትሎ በእስር የቆዩ ሰዎችን የመልቀቅ ሂደት እንዲቀጥል ኢሰመኮ አሳስቧል።

ኮሚሽኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

ከአዋጁ ትግበራ ጋር የተስተዋሉ ክፍተቶችንና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያመላክቱ፣ እንዲሁም ምክረ ሐሳቦችን ያካተቱ ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ያደረገውን ጋዜጣዊ መግለጫ ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ የክትትልና የምርመራ ሪፖርቶች ይፋ ሲያደርግ የቆየ መሆኑ አስታውሷል።

በዚሁ አዋጅ አተገባበር ዐውድ ውቅጥ #በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ማድረግን ጨምሮ ወደ መደበኛው የሕግ አተገባበር ሂደት መመለስ፣ እንዲሁም በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ እና ሌሎችም ማኅበረሰባዊ #አገልግሎቶች እንዲመለሱ ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል።

#EHRC #Ethiopia #StateofEmergency

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Afar #Somali🚨

" የግጭቱ ማገርሸት ለሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀል ምክንያት ሆኗል " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር እና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት ማገርሸቱ ገልጿል።

ኮሚሽሙ ግጭቱ እንዳሳሰበውም አመልክቷል።

ኢሰመኮ በቅርቡ በሚያዚያ ወር የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ በሶማሊ ክልል ሽንሌ ዞን እና አፋር ክልል አዋሳኝ ያገረሸው ግጭት አሳሳቢ ነው ብሏል።

ግጭቱ ለሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀል ምክንያት እንዳሆነ ገልጿል።

በኮሚሽኑ የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሰኢድ ደመቀ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃል ፤ " የአሁኑ ግጭት የተጀመረው ከግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም 2024 ወዲህ ነው " ብለዋል።

" በግጭቱ የተወሰኑ ሰዎች ሞት፤ መፈናቀል እና የአካል ጉዳት፤ የንብረት መውደም እንደደረሰ ነው ያለው መረጃ በእኛ በኩል ግጭቱ እንዳገረሸ። በትክልል ስንት ሰው ሞተ፤ ቆሰለ የሚለውን ገና በምርመራ የምናጣራው ነው " ብለዋል።

" በአሁኑ ወቅት ግን ጠቅለል ባለ መልኩ የሰው መፈናቀል፤ ሞት እና ጉዳት እንዳለ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ኢሰመኮ ከሁለቱ ክልሎች የመንግስት አስተዳዳሪዎች ተረዳሁት ባለው መሠረት ፥ በሁለቱም ክልሎች በኩል የሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀሎች ተፈጽሟል።

በቅርቡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለተገኘው አዎንታዊ የሰላም ማስፈን ሂደት ሁለቱ ክልሎች ያሰጡትን አዎንታዊ ምላሽ ያደነቀው ኢሰመኮ፤ የተጀመረው የሰላም ጥረት እንዲቀጥል የፌዴራልም ሆነ የሁለቱ ክልሎች መንግስታት የቀጠለውን ግጭት እንዲያስቆሙት ጥሪውን አቅርቧል።

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የፌዴራል መንግስት አስቸኳይ የግጭት ማስቆም ጥረት እንዲያስደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የሁለቱ ክልሎች አስተዳዳሪዎች በቀጣይ ሕዝበ ሙስሊሙ ከሚያከብረው የኢድ አል-አደሃ በዓል አስቀድሞ ሰላም እንዲሰፍን ጥረት እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

#DWAmharic #EHRC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gambella ንፁሃንን " መረጃ ሰጥታችኋል " በሚል በአቃቂ ሁኔታ #እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ፤ ግድያው ላይም ተሳትፈዋል ከተባሉ ተከሳሾች ውስጥ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞ ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ በተከሰሱበት ክስ #ነጻ መባላቸው ተሰምቷል። ሌሎች የቀድሞ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና የልዩ ኃይል አዛዦችን ጨምሮ 12 ተከሳሾች ግን የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል። …
#EHRC #Gambella

“ ቪዲዮው የቆየ ነው ፤ ከሁለት ዓመት በፊት ነው ” - የኢሰመኮ ጋምቤላ ክልል ጽሕፈት ቤት

ባለፉት ሳምንታት ውስጥ አንድ እጅግ በጣም አሰቃቂ ቪድዮ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወር ቆይቷል።

እውነት ለመናገር በቪድዮ ላይ የሚታየው የጭካኔ ተግባር በቃላት የሚገለጽ አይደለም።

ቪድዮው የጋምቤላ ክልል የጸጥታ ልብስ የለበሱ አካላት ሰዎችን እጅግ በአሰቃቂ ሁኔታ በድንጋይ ጭምር ጭንቅላታቸውን እየፈጠፈጡ በጅምላ ሲገድሏቸው የሚያሳይ ለማየት የሚከብድ ዘግናኝ ቪዲዮ ነው።

ይህን ቪዲዮ የተመለከቱ በርካቶች ፣ “ እውነት እኛ ሀገር ነው ? እኛ ሀገር ከሆነስ ለዚህ ተግባር ተጠያቂነት እና ፍትሕ ተረጋግጧል ? ” በማለት በእጅጉ አዝነው ጠይቀዋል።

አብዛኛዎቹ ሰዎችም ቪዲዮው ከሰሞኑን የተፈጸመ ጥቃት አድርገውም የወሰዱ ነበሩ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ለጉዳዩ ቅርብ ናቸው ያላቸውን አካላት ስለቪድዮው ጠይቋል።

ይህንን ቪዲዮ ኮሚሽናችሁ ተመልክቶት ነበር ? በማለት የጠየቃቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጋምቤላ ክልል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አቤል አዳነ፣ “ ቪዲዮው የቆየ ቪዲዮ ነው። ከሁለት ዓመታት በፊት የነበረ ቪዲዮ ነው ” ብለዋል።

ሰኔ 7 / 2014 ዓ/ም “ የሸኔና ጋነግ ” ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ገብተው ጥቃት እንደፈጸሙ አስታውሰዋል።

በኋላ “ የክልሉ ልዩ ኃይሎች ‘ ኦነግ ሸኔ ቀርተዋል ’ ብለው የጠረጠሯቸውን ሰዎች በየቤታቸው እየሄዱ፣ እዛው ፓሊስ ኮሚሽን አካባቢ ወስደው ግድያ ፈጽመውባቸዋል ” ነው ያሉት።

“ ይህንን ቪዲዮ ጨምረን ሌሎችንም ምርመራ አድርገን የምርመራውን ሪፓርት ይፋ አድርገናል በሰዓቱ ” ብለዋል።

የኮሚሽኑ አስተያዬት የተካተተበትን ሪፓርትም ልከዋል። 

ግድያውን የፈጸሙት አካላት በሕግ ፊት ተጠያቂ ተደርገው ይሆን ? በማለት ላቀረብንላቸው ጥያቄ “ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎች አሉ ” ብለዋል።

ከፌደራል ፓሊስ ፣ ከፍትህ ሚኒስቴር የተውጣጣ አጣሪ መርማሪ ቡድንም ጋምቤላ መጥቶ ጉዳዩን እንደመረማረና ‘በጉዳዩ ላይ ተጠይቂ ናቸው’ ብሎ የሚያስባቸውን ሁሉ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ የፍርድ ሂደታቸው እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል።

ከነዚህም ውስጥ በወቅቱ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር የነበሩትና ምክትላቸውን ጨምሮ ሌሎችም እንዳሉበት አክለዋል።

ትላንትና ከሰኔ 7 ቀን 2014 የጋምቤላ ክስተት ጋር በተያያዘ ንፁሃንን " መረጃ ሰጥታችኋል " በሚል በአቃቂ ሁኔታ #እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል ፤ ግድያው ላይም ተሳትፈዋል የተባሉ ፦
➡️ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞ አመራሮች ፣
➡️ የልዩ ኃይል አዛዦች (ዋናውና ምክትሉ)
➡️ የተለያዩ የጸጥታ አባላት
የጥፋተኝነት ፍርድ እንደተላለፈባቸው ፤ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞ ዋና ኮሚሽነር አቡላ ኦባንግ ግን በተከሰሱበት ክስ #ነጻ መባላቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዶክተር ዳንኤል በቀለ የሥራ ጊዜ አበቃ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ የሥራ ጊዜ አብቅቷል። የሕዝብ ተወካዮች ም/ ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ ዋና ኮሚሽነሩን አሰናብተዋል። ዶክተር ዳንኤል በቀለ ሰኔ 25 ቀን 2011 ዓ/ም ነበር የተሾሙት። በአምስት ዓመታት የሥራ ቆይታቸው ተቋማቸው እጅግ በርካታ የሰብዓዊ መብት ሪፖርቶችን ለህዝቡ ይፋ አድርጓል። ዛሬ…
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ዓመታዊ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ሪፖርት ይፋ ያደርጋል።

የዛሬው ሪፖርት ለሦስተኛ ተከታታይ ዓመት የሚቀርብ ነው።

ሪፖርቱ ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ነው፡፡

ይኸው ሪፖርት በሚሸፍነው ጊዜ የነበረውን የሀገራዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ጠቅለል ባለ መልኩ ይቃኛል።

በትኩረት ዘርፎች (Thematic Areas) የተስተዋሉ እና የተለዩ ቁልፍ እመርታዎች፣ ዋና ዋና አሳሳቢ ጉዳዮች፣ ተግዳሮቶች እና ምክረ ሐሳቦችን ጨምሮ ልዩ ትኩረት የሚሹ የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮችም ተካትተዋል።

ላለፉት ዓመታት በርካታ የሰብዓዊ መብት ሪፖርቶችን ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ ሲመሩ የቆዩት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ የሥራ ጊዜያቸው በማብቃቱ ይሰናበታሉ።

(ዓመታዊ ሪፖርቱ እንደደረሰን እንልክላችኋለን)

@tikvahethiopia
የሴቶች_እና_የሕፃናት_ሰብአዊ_መብቶች_ሁኔታ_ዓመታዊ_ሪፖርት_ከሰኔ_ወር_2015_ዓ_ም_እስከ_ሰኔ_ወር.pdf
2.7 MB
#EHRC

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች እና የሕፃናት ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት ይፋ አድርጎ ነበር።

ይህ ሪፖርት ከሰኔ 2015 ዓ/ም እስከ ሰኔ 2016 ዓ/ም ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ነው።

በዚሁ የዓመታዊ ሪፖርት ፥ በግጭት ውስጥ ባሉ እና በትጥቅ ግጭት ውስጥ በቆዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች በተለያየ ጊዜ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ሴቶችና ሕፃናትን ፦

🔴 ለሞት ፣ ለአካል ጉዳት እንዲሁም ለወሲባዊ እና ጾታዊ ጥቃቶች መጋለጣቸው፤

🔴 በግጭት ዐውድ ውስጥ በቆዩት፦
° አፋር፣
° ቤኒሻንጉል ጉሙዝ
° ትግራይ ክልሎች በቂ መልሶ የማቋቋም ሥራ ባለመከናወኑ በሕክምና ተቋማት የውሃና ኤሌክትሪክ ፣ የሕክምና ቁሳቁስ ፣ የአምቡላንስ ፣ የመድኃኒት ፣ የክትባትና የምግብ አቅርቦት ውስንነት ምክንያት እናቶችና ጨቅላ ሕፃናት በቅድመ ወሊድ ፣ በወሊድ ፣ ድኅረ ወሊድ ፣ በድንገተኛ ወሊድ ወቅት ሊያገኙት የሚገባቸውን መሠረታዊ አገልግሎቶች እያገኙ ባለመሆኑ የእናቶችና ሕፃናት ሞት እየጨመረ መምጣቱ፣

🔴 በሀገሪቱ በቀጠሉ ግጭቶች እና በተፈጠረው የደኅንነት ሥጋት በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ በሺህዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው በአሳሳቢነት ተጠቅሰዋል፡፡

(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
የሀገር_ውስጥ_ተፈናቃዮች_የሰብአዊ_መብቶች_ሁኔታ_ዓመታዊ_ሪፖርት_ከሰኔ_ወር_2015_ዓ_ም_እስከ_ሰኔ.pdf
2.6 MB
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

በዚህም ሪፖርቱ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ ድጋፍ በአግባቡ ሊቀርብ እንዲሁም ደግሞ የሰብአዊ መብቶች መርሖችን ፣ የተፈናቃዮችን ክብር ፣ ደኅንነት እና ፍላጎት ያከበረ ዘላቂ መፍትሔ ሊመቻች እንደሚገባ አሳስቧል።

የኢሰመኮ ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ምን አሉ ?

" ኢትዮጵያ ውስጥ መፈናቀል በአብዛኛው እየተከሰተ ያለው በግጭቶች ምክንያት በመሆኑ ግጭቶችን በአፋጣኝ ሁኔታ በሰላማዊ መንገድ መፍታትና እንዳይባባሱ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ፤ መፈናቀልን ለመከላከል እና በዘላቂነት መፍትሔ ለመስጠት ወሳኝ በመሆናቸው ትኩረት ሰጥቶ መተግበር ያስፈልጋል።

በተፈጥሮ አደጋም የሚከሰት መፈናቀል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ በመምጣቱ ለቅድመ አደጋ መከላከል እና ለአደጋ ጊዜ ምላሽ አሰጣጥ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

የሰብአዊ መብቶች መርሖችን መሠረት ያደረገ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እንዲሁም የሽግግር ፍትሕ እና የሀገራዊ ምክክር ሂደቶች የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን መብቶችና ተሳትፎ በሚያረጋገጥ ሁኔታ እንዲተገበሩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል። "

(ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia