#ትግራይ
መሻሻል ታይቶበት የነበረው የትግራይ ከተሞች የፀጥታ ሁኔታ እንደገና አሳሳቢነቱ መጨመሩ ተነግሯል።
በአንድ ሳምንታ ብቻ በሁለት ከተሞች ሁለት ሰዎች በሰለት በመወጋት እና በድንጋይ በመመታት ተገድለዋል።
በአሰቃቂ አገዳደል ህይወታቸው ያለፈው የዓዲግራት እና የሽረ እንዳስላሰ ከተሞች ወጣት ነዋሪዎች ናቸው።
የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል እስከ አሁን ባለው መረጃ በሟቾች ተጠርጥሮ አስከ አሁን በቁጥጥር ስር የዋለ የለም።
ሟች የዓዲግራት ከተማ ነዋሪ ደስታኣለም ነጋሽ ከቤተሰቡ አምሽቶ ወደ ቤቱ በመኪና ሲጓዝ ፤ የመኪና መንገድ በድንጋይ ዘግተው በማውረድ ዘራፊዎቹ ሲገድሉት አብሮት የነበረ ሌላ ሰው ሊያመልጥ ችሏል።
ግድያው የተፈፀመው ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ሰዓት አከባቢ ነው።
ሟች ወጣት ጋይም የሽረ እንዳስላሰ ከተማ ነዋሪ ነበር። ከጓደኞቹ ሲዝናና አምሽቶ ወደ ቤቱ ሲጓዝ በከተማው ቀበሌ 02 ልዩ ቦታ ማይ ሎሚን ሆቴል በተባለ አከባቢ በስለት ወግተው በድንጋይ ደብድበው ጥለውት አመልጠዋል።
ወጣት ጋይም ህይወቱ ሳታልፍ ሰዎች ደርሰው ወደ ሆስፒታል ሊመውሰድ ቢጥሩም የደረሰበት ድብደባ ከባድ ነበርና መትረፍ አልቻለም። አሰቃቂ ግድያው የተፈፀመው ታህሳስ 8/2016 ዓ.ም ነው።
ታህሳስ 9 እና 10/2016 ዓ.ም የአክሱም ከተማ ነዋሪ የአይን እማኞች እንደሚሉት ከምሽቱ 1:00 ሰዓት አከባቢ የተደራጁ ሌቦች ሁለት ሰዎች በመደብደብ 25 ሺህ ብር ቀምተዋቸዋል።
ታህሳስ 9 /2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ ቀበሌ 17 ልዩ ቦታ ዕዳጋ ብዕራይ (የበሬ ገበያ) በቡድን በመሆን በሬ ሰርቀው ለማረድ ሲሞክሩ ባሰማው ድምፅ በመፍራት ዘራፊዎቹ ሲያመልጡ በሬው በፓሊስ እጅ ገብቶ ባለቤቱ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
የተለያዩ የትግራይ ከተሞች ነዋሪዎች " ከሚታወቁት የማይታወቁት የዝርፍያና የግድያ ወንጀሎች በርካታ ናቸው " ይላሉ ፤ ስለሆነም የከተሞች የፀጥታ ጉዳይ እጅግ በጣም ትኩረት እንደሚሻ በአፅንኦት አሳስበዋል።
የትግራይ ፓሊስ ኮሚሽን በዚህ ዙሪያ የሚለው ካለ ለማስተናገድ ዝግጁን የሚሰጠው መግለጫ ካለም ተከታትለን እናቀርባለን።
መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia

ሁሉም የሚመርጠን በምክንያት ነው! ባሉበት ሆነው የአፖሎ ዲጂታል ባንክን በመጠቀም አነስተኛ ብድር ያለምንም ማስያዣ በአነስተኛ የአገልግሎት ክፍያ ይውሰዱ፡፡
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#Apollodigitalbank #loan #apolloloan #instantloan
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ

በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የበአል ገበያው ሞቅ ሞቅ እያለ ነው እርስዎም በዚህ ከ400 በላይ የሃገር ውስጥ እና የውጭ ሃገር አምራቾች ምርታቸውን በሚያቀርቡበት እና በታዋቂ ድምጻውያን በደመቀው ባዛር ላይ ለበዓሉ የሚሆንዎን ለመሸመት እና ዘና ለማለት ብቅ ካሉ የመግቢያ ትኬቱን በቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/fpgu4m ወይም *127# ሲቆርጡ 5% ያሻዎን በቴሌብር ሲሸምቱ ደግሞ እስከ ብር 2,500 ላለው የአየር ሰዓት እና ጥቅል የሚገዙበት 10% ተመላሽ አለዎት!
ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ፈተናው በ3 የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ይሰጣል " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከ16 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ሠራተኞች ነገ አርብ ታኅሣሥ 12/2016 ዓ.ም. ለፈተና ይቀመጣሉ። ይህን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከ11ዱ…
#Update
➡ " ' ፈተና አለ ' ተብለን ስንገላታ ከዋልን በኃላ ' ቀርቷል ' አሉን " - የመንግሥት ሰራተኞች
➡ " ፈተናው በመሰረዙ #ይቅርታ እንጠይቃለን " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ለመንግሥት ሰራተኞች ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና አለመሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል።
ቅሬታቻውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ የአስተዳደሩ ሰራተኞች " ፈተና አለ " ተብለው ቀኑን ሙሉ ሲንከራተቱ ከዋሉ በኃላ " ፈተናው ቀርቷል " መባላቸውን ገልጸዋል።
ሰራተኛው ይሰጣል የተባለውን ፈተና ሲጠባበቅ ከዋለ በኃላ አንድም ግልፅ ምክንያት ሳይነገር አመሻሽ ላይ " ቀርቷል " መባሉ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል።
" ለተፈጠረው መጉላላትና የስነልቦና ጉዳት ማነው ተጠያቂው ? " ሲሉም ጠይቀዋል።
ፈተናው ለምን እንደቀረ በይፋ የተሰጣቸው ማብራሪያ እንደሌለ ሰራተኞቹ አክለዋል።
በሌላ በኩል ፤ ለ " ካፒታል ጋዜጣ " ቃላቸው የሰጡ የመንግሥት ሰራተኞች በመፈተኛ ቦታቸዉ ተገኝተው ሳይፈተኑ ለረዥም ሰዓታት በፌዴራል ፖሊስ መጠበቃቸውን ተናግረዋል።
ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ 4 እና 5 ኪሎ ለመፈተን ወደ ተቋሙ ከ6:30 ጀምሮ በተመደቡበት መፈተኛ ክፍል ቢደርሱም እስከ ቀን 11:30 ድረስ ከፌዴራል ፖሊስ በስተቀር ማንም ፈታኝ ባለመምጣቱ ከረዥም ሰዓታት እንግልት በኃላ እንዲበተኑ ተደርገዋል።
በቅርቡ ለሚተገበረዉ የሰራተኞች ድልድል ሲባል ከ14 ሺህ በላይ የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኞች ለፈተና እንደሚቀመጡ መነገሩ ይታወቃል።
- የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር፣
- ቤቶች ልማት እና አስተዳደር፣
- ትራንስፖርት፣
- ፐብሊክ ሰርቨሲ እና ሰው ሀብት ልማት፣
- ፕላን እና ልማት፣
- ሥራ እና ክህሎት፣
- ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮዎች
- ቤቶች ኮርፖሬሽን ጨምሮ አጠቃላይ ከ13 ሺህ በላይ ሰራተኞች ፈተናዉን አልወሰዱም።
በወቅቱ ረዥም ሰዓታት ፈተናዉን በመጠባበቃቸዉ ምክንያት የጩኸት ድምፅ ያሰሙ ሰራተኞች ለእስር መዳረጋቸውን እና የተለያዩ እንግልቶች እንደደረሰባቸው ለጋዜጣው ተናግረዋል።
በምን ምክንያት እንደሆነ ባይታወቅም ፈተናው ወደሌላ ቀን መራዘሙን እንደሰሙ ሰራተኞቹ ጠቁመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ ከሚኖሩ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች መካከል ተመሳሳይ የብሔር ማንነት ያላቸው አመራሮች ብዛት ከ40 በመቶ እንዳይበልጥ ሊያደርግ መሆኑ መነገሩ ይታወሳል።
ተጨማሪ . . .
የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ምዘና ፈተናውን እንደሚያዘጋጁ ከተገለፁት ሁለት ተቋማት አንደኛው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፈተናው #መሰረዙን በደብዳቤ አሳውቋል።
ዩኒቨርሲቲው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ፦
* ለአመራሮች፣
* ባለሙያዎች
* ሰራተኞች ፈተና እንዲሰጥ ኃላፊነት እንደተሰጠ አስታውሷል።
ሆኖም በተከሰተ " የፈተና ቴክኒካዊ ችግር " ምክንያት በ12/04/2016 ዓ.ም ሊሰጥ ታቅዶ የነበረው ፈተና መሥጠት እንዳልተቻለ ከይቅርታ ጋር ገልጿል።
የተዘጋጀው ፈተና ደህንነት ችግር ያላጋጠመው መሆኑን ግን አመልክቷል።
በማንኛውም በጋራ በመስማማት ቀን ይሄንኑ ፈተና ለመሥጠት እንደሚቻል ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባገኘው መረጃ አስተዳደሩ ፈተናው የሚሰጥበትን ቀን በቅርብ ያሳውቃል።

#Update ➡ " ' ፈተና አለ ' ተብለን ስንገላታ ከዋልን በኃላ ' ቀርቷል ' አሉን " - የመንግሥት ሰራተኞች ➡ " ፈተናው በመሰረዙ #ይቅርታ እንጠይቃለን " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ለመንግሥት ሰራተኞች ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና አለመሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል። ቅሬታቻውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ የአስተዳደሩ ሰራተኞች " ፈተና አለ " ተብለው ቀኑን ሙሉ ሲንከራተቱ…
#AddisAbaba #ፈተና
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፦
" የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ፦
* ለአመራሮች ፣
* ለባለሙያዎች
* ለሰራተኞች ፈተና እንዲሰጡ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ኃላፊነት ሰጥቷል።
ሆኖም ግን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና በቴክኒክ ችግር ምክንያት በመሰረዙ #ይቅርታ ጠይቋል።
ቀጣይ የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ምዘና ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ #በቅርብ የምናሳውቅ ይሆናል። "

#SafaricomEthiopia
ለስራ ቀናት በ1GB ፤ ለሳምንቱ መጨረሻ ደግሞ በ5GB እንበሽበሽ! በ60 ብር ብቻ 150% ተጨማሪ ዳታ እናግኝ! ቅዳሜና እሁዳችንን አስደሳች ለማድረግ *777*4# በመደወል ጥቅሉን እንግዛ!
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/
ቴሌግራም- https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC
#FurtherAheadTogether

#የመምህራን_ቅሬታ #ምላሽ
ለ487 ' የአዲአርቃይ ወረዳ ' መምህራን የ22 ወራት የደረጃ ዕድገት ደመወዝ አለመከፈል ቅሬታ ማሳደሩን የሰሜን ጎንደር ዞን መምህራን ማኅበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቋል።
የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ፤ " በበርካታ ችግር ውስጥ ያለ ወረዳ ነው እንደሚታወቀው እናም በጀት ይዘን #መክፈል አልቻልንም። ስለዚህ መምህራን እስኪከፈላቸው ድረስ በትዕግስት ይጠብቁን " የሚል ምላሽ ሰጥቶናል።
የሰሜን ጎንደር ዞን የመምህራን ማኅበር ሊቀመንበር አቶ ሀብታሙ አቸነፍ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
- የመምህራንን #የመልካም_አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት ዝግጁ የሆነ የፖለቲካ የመንግሥት አመራር ባለመፈጠሩ ምክንያት 487 የአዲአርቃይ ወረዳ መምህራን ከጥር 1/2014 ዓ.ም እስከ አሁን ድረስ በጊዜ ቆይታ የደረጃ እድገት ክፍያ አልተከፈላቸውም። ይህ በመምህራን ዘንድ ከፍተኛ የሆነ የቅሬታ ምንጭ ሆኖብናል።
- ለመምህራን ከጥር 01/2014 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 01 ቀን 2015 ዓ.ም የደረጃ እድገታቸው እንደሚያድግና ለእድገታቸው የሚሆን በጀት ጥር 1 ቀን 2014 ዓ.ም በሥማቸው ተይዞ ነበር። ይህንን በጀት ' አዘዋውረን ለሰላም ማስከበር አውለነዋል' ነው የሚለው የአስተዳደር ምክር ቤቱ።
- ጥያቄያችንን #በተደጋጋሚ አቅርበን ምላሽ የሚሰጥ የመንግሥት አካል አላገኘንም።
- ባለፈው ዓመት በወረዳው ላይ በነበረ አንድ ጉባኤ ' የመምህራን ጥያቄ ትክክለኛ ጥያቄ ነው፣ በአዲሱ በጀት ዓመት ጥያቄውን እመልሳለሁ ' የሚል ምላሽን ሰጠ #አስተዳዳሪው። በዚህ ዓመት ደግሞ ፦
* ሀምሌ፣
* መስከረም፣
* ጥቅምት ወራት ላይ ተጠየቀ አሁን የመጨረሻው ውሳኔ ' እኔ በጀቱን አላውቅም ፣ በወቅቱ የነበረውን አስተዳዳሪ በጠየቃችሁ ፣ እኔ አሁን የምከፍልበት ኮንዲሽን የለም ' የሚል ምላሽ ነው የተሰጠው ፤ በዚህ መምህራን በጣም #ተበሳጭተው ነው ያሉት።
- መምህራን አንድ ላይ ሰብሰብ ብለው ለመጠየቅ ሲሄዱ 'እናስራችኋለን፣ እንመታችኋለን' የሚል ተፅእኖ አለ።
- በወቅቱ የነበረው ችግር የሁላችንም ችግር ቢሆንም ደመወዝ ቀጥታ ተከፋይን አንስቶ ' ለሰላም ማስከበር ' በሚል ላለአስፈላጊ ጥቅም ማዋል ተገቢ አይደለም። ላለአስፈላጊ ጥቅም ነው የዋለበት ያልኩት ፤ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ኮማንድ ፖስት የትዕዛዝ አቅጣጫ ተሰጥቶ የነበረው ሁሉም ደመወዝ ለሰላም ማስከበር ይሆናል የሚል ሳይሆን፣ 'የሥራ ማስኬጃ 40%ን ተጠቀሙ' የሚል ስለነበር ነው።
- እንደ 'ሰሜን ጎንደር ዞን' ብዙ ወረዳዎች ተሳትፈዋል በጦርነቱ። ጠለምት ተሳትፏል፣ ዳባት ተሳትፏል ነገር ግን አንድም ከበጀት ጋር የተያያዘ ደመወዝ የተነሳበት ወረዳ የለም። በዞናችን አሥር ወረዳዎች አሉ ሙሉ በሙሉ የደረጃ ዕድገታቸውን እየከፈሉ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። #አዲአርቃይ ግን እንዲህ አይነት ችግር ገጥሞናል።
- ያልተከፈለውን የደረጃ እድገት ምን ያህል እንደሆነ አላሰላሁትም፣ ግን ቢያንስ ለ487 መምህራን ዝቅተኛ 800፣ ከፍተኛ እስከ 2,000 ብር የደረጃ እድገት ያገኛሉ። ነገር ግን ይኸው እንግዲህ አሁን ጥር ወር ሲገባ 2 ዓመታት ሊሆነው ነው ሳይከፈል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦ " የመምህራኑን #የደረጃ_እድገት ደመወዝ ለምን እስካሁን ድረስ አልተከፈለም ? " ሲል የአዲአርቃይ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አረቡ ጆርጌ ጠይቋል።
አቶ አረቡ ጆርጌ " አሁን ያለበት ሁኔታ በበርካታ ችግር ውስጥ ያለ ወረዳ ነው እንደሚታወቀው እናም በጀት ይዘን #መክፈል አልቻልንም። ስለዚህ መምህራን እስኪከፈላቸው ድረስ በትዕግስት ይጠብቁን " ሲሉ መልሰዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ " መምህራኑ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም እንዳልተከፈላቸው፣ በመጨረሻም በጀቱ ለሌላ ጥቅም እንደዋለ " እንደገለፁለት ለኃላፊው #በድጋሚ ጥያቄ አቅርቧል።
በተጨማሪ ፦
* ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ለምን ገንዘቡን አልከፈላችሁም ?
* አሁን ለመክፈልስ ምን የታሰበ ነገር አለ ? ብለን ጠይቀናቸዋል።
ኃላፊው " ኦሬዲ ጠይቀዋል በጀት ተይዞ እንደሚከፈል ብቻ ነው የነገርናቸው እንጂ ለዚህ የተመደበ #ለሌላ ጥቅም የዋለ ገንዘብ የለም " ብለዋል።
" መከፈሉ ግዴታ ነው፣ እንደ ተቋም እንደ አስተዳደር ምክር ቤትም ' አይከፈልም ' የሚል ማስተባበያ አይኖረንም ምክንያቱም ደመወዝ ስለሆነ " ያሉት ኃላፊው፣ " ለሁለት ዓመታት ያክል የገቢ መሰብሰብ ችግር ስለነበር በጦርነቱ ምክንያት በጀቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጫና ነው ያሳደረው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ስለዚህ እኛም አሁን የያዝነው ፕሮግራም ሙሉውን እንኳ ባይከፈል እየተከፈለ (የአመቱን ወደ 6 ወራት፣ የ6 ወራቱን ወደ ሦስት ወራት እየተደረገ በጀት እየያዝን እንከፍላለን እንጂ አይከፈልም የሚል አቋም የለም። ተገቢነትም የለውም " ብለዋል።
መረጃው በአ/አ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተጠናቅሮ የቀረበ ነው።

" ኢትዮጵያ የ ' ብሪክስ ' ቡድንን የተቀላቀለችው በዋናነት በወቅታዊ የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ማዕቀቦች ጫና ነው " - የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር የባለሙያዎች ዳሰሳ
ከ5 ሺህ 500 በላይ የኢኮኖሚ ባለሙያዎችን ያቀፈው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ‘ የኢትዮጵያ ብሪክስ ቡድንን መቀላቀል ጥቅም እና ስጋት ’ን የፈተሸ የባለሙያዎች ዳሰሳ አድርጎ በዋና መስሪያ ቤቱ ይፋ አድርጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በአካል ተገኝቶ በተከታተለው በዚህ ዳሰሳ የማህበሩ የምርምርና ፖሊሲ ትንተና ዳይሬክተር ደግዬ ጎሹ (ዶ/ር)፤ " በዳሰሳው 233 የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል " ብለዋል።
የግኝቱ ዋነኛ ነጥቦች ፦
- ከተሳታፊዎች መካከል :
* 49% የሚሆኑ ባለሙያዎች ኢትዮጵያ የብሪክስ ቡድንን የተቀላቀለችው በፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማዕቀቦች ተገፍታ ነው ብለዋል።
* 47% የሚሆኑት አዳጊ ኢኮኖሚ ስላላት ነው ብለዋል።
* 45.5% የጂኦፖለቲካዊ ምክንያቶችን አንስተዋል።
* 41% እና 39% እንደቅደም ተከተላቸው ከምዕራባውያን ጋር የግንኙነት መሻከር እና የውጭ ምንዛሪ እጥረትን በገፊ ምክንያትነት ጠቅሰዋል።
" ይሄ ትንሽ ተቃርኖ አለው። መንግስት የሚለው በራሳችን በጎ ተግባሯ (merits) ነው ይላል፤ ያመለከተችው በተፅዕኖዎቹ ነው፤ ለምን እንደተቀበሏት አይታወቅም። በእርግጥ ብሪክስ የተቀበላቸው ሀገራት በምን መስፈርት እንደገቡ ማንም አያውቀም " ሲሉ ዶ/ር ደግዬ ግኝቱን አስረድተዋል።
- ከተሳታፊ ባለሙያዎች ውስጥ ኢትዮጵያ ብሪክስን በመቀላቀሏ ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል ያሉት 51% ሲሆኑ 25% የሚሆኑት በተቃራኒው እንደሚሆን ገምተዋል።
- #ዶላርን ከግብይት ስርዓት ውጪ ለማድረግ ስለተያዘው የብሪክስ ዕቅድ በተመለከተ ይሳካል የሚሉት ብዙኀኑ ቢሆኑም ይህ እንዲሳካ እስከ 15 ዓመታት ይፈጃል ያሉት 67% ናቸው።
ዳሰሳው ሌላኛው የተመለከተው ጉዳይ ኢትዮጵያ ብሪክስን በመቀላቀሏ ከምዕራባውያን ወገኖች ስለምታጣቸው ጥቅሞች እና ስለሚኖሩት ጫናዎች ነው።
በዚህም፦
* ብድር እና ድጋፎችን ለማግኘት ትቸገራለች ወይም ትከለከላለች የሚሉ ባለሙያዎች 56% ናቸው።
* 43% የሚሆኑት በሂደት ላይ ለሚገኙ ፕሮጀክቶች ገንዘብ ለማሰራጨት ትቸገራለች ብለዋል።
* 40% የሚሆኑት የብር የመግዛት አቅም እንዲዳከም ግፊት ይደረግባታል ብለዋል።
- ጫናዎችን በተመለከተ 66% የሚሆኑት ከምዕራባውያን ዘርፈ ብዙ ጫናዎችን ሲገምቱ፣ በአባላቱ መካከል የእርስ በእርስ የፖለቲካ ፍላጎት ግጭቶች እንዲሁም የብሪክስ ልማት ባንክ የሆነው " ኒው ዲቨሎፕመንት ባንክ " አቅም ውስንነት በተከታይነት ስጋቶች ሆነው ተቀምጠዋል።
የባለሙያዎች ዳሰሳው ያስቀመጣቸው ምክረ ሃሳቦች ፦
☑ የኢኮኖሚ ባለሙያዎቹ ኢትዮጵያ በምዕራባውያን ቁጥጥር ስር ከሚገኙት ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እንዲሁም ከብሪክስ ጋር መስራት ግዴታዋ እንደሆነ ገልፀው፤ ለረጅም ዓመታት ከምዕራባውያን ጋር ከነበራት ትስስር አሁን እንደተፃራሪ ወደሚታየው ብሪክስ ቡድን ስትገባ የሁለቱን አሰላለፍ ጥቅምና ጉዳት በትኩረት ለይቶ መንቀሳቀስ ትኩረት እንደሚፈልግ ተገልጿል።
☑ እስከዛሬ ከምዕራባውያን የሚገኙ ጥቅሞችን ማካካስ ካልቻለ ተግዳሮቱ ይበዛል። የዶላርን የበላይነት መቀነስና ለንግድ የራሳቸውን ኖቶች መጠቀም የሚለውም ለኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ እጥረት የባሰ ራስምታት ስለሚሆን ከአባል ሀገራቱ የሚኖረውን አንድነትና ልዩነት በአግባቡ መፈተሽ ይገባል።
☑ ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስተማማኝነት ላይ ጥያቄ ያነሱ ሲሆን ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር የሚያሰራ የፋይናንስ ስርዓት ለመፍጠር መልሶ ማደራጀት ይፈልጋል ብለዋል።
#ቲክቫህኢትዮጵያ

#Tecno_Pop8 !
እያንዳንዱ ምስል በቀለማት ታጅቦ በከፍተኛ ጥራት ቁልጭ ብሎ እንዲታይ 6.6 ኢንች ሰፊ ስክሪን ከ90Hz ሪፍሬሽ ሬት ጋር በማጣመር አዲሱ Pop 8 ከTECNO ሞባይል ቀርቦሎታል።
ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Pop8 #TecnoMobile #TecnoEthiopia

#ግሎባል_ባንክ_ኢትዮጵያ
ቀለል ያለ ጥያቄ በመገመት ይሸለሙ!
የሽልማቱ ሕግጋትና ደንቦች፤
1. የሚያሸልመውን ትክክለኛ ጥያቄ ምላሽ የምንቀበለው በቴሌግራም ቻናላችን https://t.iss.one/Globalbankethiopia123 ብቻ ነው፡፡
2. የጥያቄውን ትክክለኛ ምላሽ ለሚያገኙ ቀዳሚ 10 ተወዳዳሪዎች ሽልማቱን የምንሰጥ ይሆናል፡፡
3. ትክክለኛውን ምላሽ ከጎል አስቆጣሪዎቹ ጋር በትክክል ለሚገምቱ መላሾች ተጨማሪ ቦነስ ሽልማት ያገኛሉ፡፡
4. ተወዳዳሪዎች ሽልማቶቹን ለማሸነፍ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን የቴሌግራም ገፅ ተከታይ መሆን አለባቸው፡፡
5. የጥያቄውን ትክክለኛ መልስ የምንቀበለው እስከ ቅዳሜ ማታ 1፡00 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
6. ከአንድ በላይ ግምት መስጠት ለሽልማት ብቁ አያደርግም፡፡
በሚቀርብዎ አማራጮች ያግኙን፡ https://bit.ly/3TkrrXD
ደንብ እና ሁኔታዎች ተፈጻሚ ናቸው፡፡
መልካም ዕድል!
ለጋራ ስኬታችን
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ

#EHRC
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለይም አዲሱ የክልል አደረጃጀት ተከትሎ የተለያዩ አስተዳደሮች እና መዋቅሮች መልሶ መቋቋም ወይም ተያያዥ ውሳኔዎች ሂደት ጋር የሚነሱ የደመወዝ መዘግየት እና ያለመከፈል የተመለከቱ አቤቱታዎችን፣ እንዲሁም ጥቆማዎችን መነሻ በማድረግ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።
ይህ በተመለከት ከላይ የተያያዘውን መግለጫ ልኮልናል።