TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Axum #Tigray

" በጦርነቱ ጊዜ እኮ #መከራው ከባድ ነበር !! "

ወ/ሮ በላይነሽ መኣሾ (የአክሱም ነዋሪ ለድምጺ ወያነ) ፦

" ሰላም በመሆኑ ጥሩ ነው ያለው።  ብርሃን አየን።

በሰላም እየተንቀሳቀስን ነው። #ሕጻናት እየተጫወቱ ነው።

ብዙ ለውጥ ነው ያለው።

በጦርነቱ ጊዜ እኮ #መከራው እጅግ ከባድ ነበር። አሁን በጣም በጣም ይሻላል ፤ ቢያንስ #እፎይ ብለን  መተኛት እንችላለን።

ቢሆንም ግን #የከፋው_ሰው_አለ ፤ ሰው የሚበላው የሚጠጣውን አጥቶ በጣም ከፍቶታል ፣ የመንግስት ሰራተኛውም ያለፉት ዓመታት ደመወዝ ባለመከፈሉ ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጦ ነው ያለው ፣ የተፈናቃዮች ነገርማ #አይወራም ፣ ሕጻናት ልጆች የሚበሉትን አጥተው በየከተማው #በልመና ነው ተሰማርተው ያሉት። "

#Ethiopia #TigrayRegion #Peace

@tikvahethiopia
#OROMIA #PEACE

" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ... ለሰላም ክፍት ነን ድርድሮችም እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም ቢሆን ያሉ ችግሮች #በሰላም እንዲፈቱ መንግሥት #ለድርድር ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።

የክልሉ መንግሥት አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በአዲስ አበባ እንደመከሩ ተነግሯል።

በምክክሩ ላይ የተገኙት የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈሰ ውይይቱ ልማትና ጸጥታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

በውይይቱ ፦

- የልማት ስራ ያለ ሰላም ውጤት አልባ እንደሆነ / ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነ ፤

- ሰው ሰርቶ የሚበላው ፣ ወልዶ የሚስመው ሰላም ሲኖር እንደሆነ አጽንኦተ ተሰጥቶበታል ብለዋል።

" ሰላም ለመንግሥት ብቻ የተተወ ስላልሆነ እንዴት ነው አብሮ መስራት የሚቻለው ? " የሚለውም መነሳቱን አስረድተዋል።

" መንግሥት እና ሸኔ የጀመሩት ድርድር ፤ በተለያየ ምክንያት አኩርፈው ጫካ የገቡ ነፍጥ ያነገቡ ጓዶች አሉ ፤ መንግሥት በሆደ ሰፊነት ዛሬ ነገ ሳይል እነዚህን አካላት ጠርቶ በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር አለበት ይህ ሲደረግ ደግሞ ለሰዎቹ እውቅና ተሰጥቶ የህግ ከለላ ተሰጥቶ ነው ውይይት መደረግ ያለበት " የሚለውም መነሳቱን ገልጸዋል።

" በመንግሥት በኩል ' ዛሬም ቢሆን ክፍት ነው እንነጋገራለን ፣ ችግሮችን በጋራ ተነጋግረን እንፈታለን ' የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን " ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ አሁንም ቢሆን የክልሉ መንግሥት በውይይት ያምናል ብለዋል።

" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ሙሉ ትኩረታችን ወደ ሰላም ማምጣት ነው ያለብን። የፈለግነውን ነገር በአዳራሽ መወያይት ይቻላል። ጥረቶች ብዙ ነው ያደረግነው አሁንም ለሰላም ክፍት ነን እኛ 3ኛ ዙር ይሁን፣ 5ኛ ዙር ይሁን ፣ 10ኛ ዙር ድርድሮች እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " ብለዋል።

#Ethiopia
#Oromia #VOA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መሪዎች በምን ጉዳዮች ላይ መከሩ ፤ ምንስ ተስማሙ ?

የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሙሀሙድ ዛሬ በአዲስ አበባ የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋል።

ከውይይቱ በኃላ የጋራ መግለጫ ወጥቷል።

ምን ተባለ ?

- በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

- በሁለቱ ሀገራት ህዝቦች መካከል ያለውን ወንድማማችነትና ግንኙነት በማጠናከር ላይ ገንቢ ውይይት አድርገዋል።

-  የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደነበረበት ለመመለስ እና በየመዲኖቻቸው ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ውክል እንዲኖር ለማድረግ ተስማምተዋል።

- መሪዎቹ ለቀጣናው መረጋጋት የሁለቱ ሀገራት የጋራ የእርስ በርስ እምነት ፣  መተማመን እና መከባበር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ትብብር እንደሚያስፈልግ አረጋግጠዋል።

- ቀጠናዊ ግንኙነቶችን ለማሻሻል፣ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር እና የጋራ እድገትን ለማስቀጠል በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።

- መሪዎቹ የጸጥታ ትብብር ማስቀጠልና ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል። በቀጠናው ፅንፈኛ ታጣቂ ሃይሎች እየፈጠሩ ያሉትን አሳሳቢና እየጨመሩ  ያሉ ስጋቶችን በመገምገም መሪዎቹ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን የሚደረገውን ትብብር ለማጠናከር ለጸጥታ ተቋሞቻቸው መመሪያ ለመስጠት ተስማምተዋል።

- በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ማጠናከር ያለውን ጠቀሜታ ላይ ተወያይተዋል ፤ አጽንኦትም ሰጥተዋል። የበለጠ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ትብብር በማድረግ የንግድ ልውውጥን ለማሳለጥ እና የጋራ ብልጽግናን ለመፍጠር የመሰረተ ልማት ትስስሮችን ለማስፋት ተስማምተዋል።

- ለአንካራው ስምምነት በጓደኝነት እና በአብሮነት መንፈስ ቁርጠኝነታቸውን ዳግም ያረጋገጡ ሲሆን  በስምምነቱ ላይ የታቀዱትን የቴክኒክ ድርድሮችን ለማፋጠንም ተስማምተዋል።


#Ethiopia #Somalia #Peace

@tikvahethiopia
#Peace🏳

ሃማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ለማድረግ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነገረ።

ሀማስ የስምምነት ፕሮፖዛሉን መቀበሉን በይፋ ሲያሳውቅ የእስራኤልም ይፋ ታደርጋለች ተብሎ እየተጠበቀ ይገኛል።

ሁለቱ አካላት ወደ ስምምነት እንዲመጡ አሜሪካ፣ ኳታር እና ግብፅ ለበርካታ ሳምንታት ሲሰሩ ነበር ተብሏል።

እንደ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የተኩስ አቁም ስምምነቱ በመጀመሪያው ዙር ለ6 ሳምንታት ይቆያል።

ሃማስ 33 ታጋቾችን ለመልቀቅ እስራኤል ደግሞ 1,000 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን ለመልቀቅ መስማማቷ በስፋት እየተነገረ ነው።

' አል አረቢያ ' አንድ ስማቸው ያልተገለጸ የእስራኤል ባለስልጣንን ዋቢ ለማድረግ ሀማስ ለተኩስ አቁም እና ታጋቾችን ለመልቀቅ መስማማቱን ፅፏል።

' አልጀዚራ ' ደግሞ እስራኤል ከስምምነቱ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ያልተፈቱና ያላለቁ ጉዳዮች እንዳሉ በመጠቆም የመጨረሻው ማጠቃለያና መፍትሄ በቀጣይ ሰዓታት ውስጥ እንደሚገኝ ዘግቧል።

ስምምነቱን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ያፀድቁታል ተብሎ ይጠበቃል። የእስራኤል መንግስት ነገ ድምጽ ይሰጣል።

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ትሩዝ በተባለው የማህበራዊ ሚዲያቸው ላይ " ስምምነት ላይ ተደርሷል ሀማስም ታጋቾችን ለመልቀቅ ተስማምቷል ፤ ታጋቾች በአጭር ጊዜ ነጻ ይሆናሉ " ብለዋል።

የሁለቱ ወገኖች ስምምነት ለ15 ወራት የዘለቀውን እጅግ በጣም አስከፊ ጦርነት ያስቆማል ተብሎ ትልቅ ተስፋ ተጥሏል።

የስምምነቱን መረጃን የሰሙ ፍልስጤማውያን ጋዛ ውስጥ እያነቡ አደባባይ ወጥተው ደስታቸውን እየገለጹ ነው።

ይህ ስምምነት እየተካሄደ በነበረበት ወቅት እስራኤል ጋዛ ቡሬጂ የስደተኞ ካምፕ ላይ በፈጸመችው ጥቃት በርካታ ፍልስጤማውያንን ገድላለች።

ባለፉት 15 ወራት በነበረው እጅግ አስከፊ ጦርነት ከ46 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ሲገደሉ 1,200 እስራኤላውያን ተገድለዋል 250 ታግተው ተወስደዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከአልጀዚራ፣ አል አረቢያ፣ ፍራንስ 24 ነው ያሰባሰበው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Peace🏳 ሃማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ለማድረግ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነገረ። ሀማስ የስምምነት ፕሮፖዛሉን መቀበሉን በይፋ ሲያሳውቅ የእስራኤልም ይፋ ታደርጋለች ተብሎ እየተጠበቀ ይገኛል። ሁለቱ አካላት ወደ ስምምነት እንዲመጡ አሜሪካ፣ ኳታር እና ግብፅ ለበርካታ ሳምንታት ሲሰሩ ነበር ተብሏል። እንደ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች የተኩስ አቁም ስምምነቱ በመጀመሪያው ዙር ለ6 ሳምንታት ይቆያል።…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ  ፦ #ሀማስ እና #እስራኤል የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸው መነገሩን ተከትሎ ፍልስጤማውያን ደስታቸውን ለመግለፅ በጋዛ አደባባይ ወጥተዋል።

" አላሁ አክበር ! አላሁ አክበር ! " ይህ በስምምነቱ መረጃ የተደሰቱ ፍልስጤማውያን ድምፅ ነው።

በርካቶች የሰላም ወሬ በመንፈሱ በደስታ አልቅሰዋል ፤ አንብተዋል ፤ ፈጣሪ ቀጣዩን ጊዜ ደግሞ የሰላም ያደርግላቸው ዘንድ ተማፅነዋል።

ፍልስጤማውያን ስምምነቱን ተከትሎ እስራኤል የያዘቻቸውን ያሰረቻቸውን ወገኖቻቸውን ትፈታለች ብለው ተስፋ አድርገዋል።

በአስከፊው ጦርነት እጅግ በርካታ ፍልጤማውያን ህጻናት፣ ሴቶች፣ እናቶች ፣ አዛውንቶች አልቀዋል። ላለፉት 15 ወራት የሰቀቀን ህይወት ሲገፉም ነበር።

ስምምነቱ ዘላቂ እና አስተማማኝ ሰላምን ያመጣ ይሆን ? በቀጣይ የሚታይ ይሆናል።

#ሰላም 😭 #Peace 🕊 #سلام

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቪድዮ  ፦ #ሀማስ እና #እስራኤል የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸው መነገሩን ተከትሎ ፍልስጤማውያን ደስታቸውን ለመግለፅ በጋዛ አደባባይ ወጥተዋል። " አላሁ አክበር ! አላሁ አክበር ! " ይህ በስምምነቱ መረጃ የተደሰቱ ፍልስጤማውያን ድምፅ ነው። በርካቶች የሰላም ወሬ በመንፈሱ በደስታ አልቅሰዋል ፤ አንብተዋል ፤ ፈጣሪ ቀጣዩን ጊዜ ደግሞ የሰላም ያደርግላቸው ዘንድ ተማፅነዋል። ፍልስጤማውያን ስምምነቱን…
#Peace🏳

ጋዛ ተኩስ አቁም ነገ ተግባራዊ ይሆናል።

የተኩስ አቁሙ ነገ ተግባራዊ እንደሚሆን የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ነገ በሀገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት ተኩል ላይ የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ እንደሚሆን አረጋግጧል።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ዛሬ ቅዳሜ የተኩስ አቁሙን አፅድቋል።

ተኩስ አቁሙ ስራ ላይ ሲውል 1,904 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስር ቤቶች እንደሚለቀቁ የእስራኤል መንግሥት አሳውቋል።

ሀማስ ደግሞ ከ98 እስራኤላውያን ታጋቾች መካከል 33ቱን ለ6 ሳምንታት በሚዘልቀው የተኩስ አቁም ወቅት ይለቃል።

ግብፅ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ ለመላክ እየተዘጋጀች ነው።

በሌላ በኩል ግን ሀማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ከተገለጸ በኃላ 122 ፍልስጤማውያን በእስራኤል መገደላቸውን የጋዛ የሰላማዊ ሰዎች ጥበቃ ኤጀንሲ ገልጿል።

እስካሁን በ15 ወራት ጦርነት የተገደሉት ፍልስጤማውያን ቁጥር 46,899 ደርሷል። 110,725 ሰዎች ታጎድተዋል።

መረጃው ከዶቼ ቨለ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia