TIKVAH-ETHIOPIA
#Sidama " ... እንዲዘጉ በተወሰነባቸዉ 17 ኮሌጆች ልጆቻችሁን ከማስተማር ተቆጠቡ " - የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በሲዳማ ክልል የሚንቀሳቀሱ ኮሌጆችና የሙያ ማሰልጠኛዎች በአብዛኛዉ ከደረጃ በታች መሆናቸዉ ተከትሎ 17 ኮሌጆች #መዘጋታቸዉ ተገለጸ። የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ኮሌጆችና የሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር ባካሄደዉ…
በሲዳማ ክልል የተዘጉ ኮሌጆች ዉስጥ እየተማሩ የሚገኙ ተማሪዎች ዕጣፋንታ ምንድን ነዉ ?
በሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በኩል 17 ያክል ኮሌጆች መዘጋታቸዉን ተከትሎ በተማሪዎችና ወላጆች በኩል የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተሰንዝረዋል።
ወደ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪዎች እና ወላጆች ከተላኩ ጥያቄዎች መካከል ዋነኛው " በኮሌጆች ዉስጥ ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች እጣፋንታ ምንድን ነዉ ? " የሚል ነበር።
ለዚህ ጥያቄ ምላሻቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ሀላፊው አቶ ፍስሀ ፍቶላ ፤ በነዚህ የተዘጉ ኮሌጆች የነበሩ ተማሪዎች መረጃ ተጠናቅሮ በቅርብ ወዳሉ ኮሌጆች እንደሚዘዋወሩ ገልጸዋል።
ለነዚህ ኮሌጆች ከ1 አመት በፊት #ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ መቆየቱን የገለፁት አቶ ፍስሀ ይህ ቆይታ የተማሪዎችን ጉዳይ ለመጨረስ እና ያለምንም ጉዳት ለማዘዋወር በቂ መሆኑን ገልጸዋል።
አሁን ላይ በክልሉ ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ዉሳኔ የተዘጉ ኮሌጆች ቅሬታቸዉን እያቀረቡ ስለመሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተረዳ ሲሆን ይህን ጉዳይ የምንከታተል ይሆናል።
የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ፦
* በክልሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ኮሌጆችና የሙያ ማሰልጠኛዎች በህገወጥ ስራ መሰማራታቸዉን፤
* 17 ኮሌጆች ስራ እንዲያቆሙ ሲወሰን ኮሌጆቹ በመላዉ ሲዳማ የጀመሯቸዉን የማስተማር ስራዎች አቁመዉ ፈቃዳቸዉን እንዲመልሱ እንደተናገራቸው፤
* ያላግባብ #ሳያስተምሩ_አስመርቀዉ ስራ ፈላጊና የሀገር ሸክም በማድረጋቸዉም በህግ ተጠያቂ እንደሚደረጉ፤ ቢሮዉ እጁ ላይ ያለዉን መረጃ ባፋጣኝ ለክልሉ ፍትህ ቢሮ እንደሚልክ፡
* ማህበረሰቡ እንዲዘጉ በተወሰነባቸዉ 17 ኮሌጆች ልጆቹን ከማስተማር እንዲቆጠብ፤
* ከዚህ በኋላ በመላዉ ሲዳማ ክልል ከገበያዉ በላይ የተማረ ሰዉ በመኖሩ የአካዉንቲንግ ማርኬቲንግና የሰዉ ሀይል አስተዳደር ትምህርቶችን መማርም ሆነ ማስተማር የተከለከለ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።
መረጃው በሀዋሳ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።
@tikvahethiopia