TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ

በነዳጅ የሚሠሩ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ውጪ ተገጣጥመው ወደ ሃገር ውስጥ በሚገቡ አውቶሞቢሎች ላይ የውጪ ምንዛሬ እቀባ ተደረገ።

የጉምሩክ ኮሚሽን በነዳጅ የሚሠሩ እና ሙሉ በሙሉ ውጭ ተገጣጥመው ወደ ሃገር  የሚገቡ አውቶሞቢሎች ላይ የውጪ ምንዛሬ እቀባ መጣሉን አሳውቋል።

ዕቀባው ያስፈላገበት ዋና ምክንያት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ እና በሃይብሪድ /በኤሌክትሪክ እና በነዳጅ/ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ ለማበረታት ነው ተብሏል።

አሰራሩ ፥ የአረንጓዴ ልማትን ተግባራዊ ለማድረግ እና ለነዳጅ እና በነዳጅ ለሚሰሩ አውቶሞቢሎች ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጪ ምንዛሬ ለመቀነስ ይረዳል ሲል ኮሚሽኑ አመልክቷል።

ይህ እቀባ #ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል ተገልጿል።

በነዳጅ የሚሠሩ አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎችን ወደ ሃገር ውስጥ የሚያስገቡ አስመጪዎችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ #ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከገቢዎች ሚኒስቴር ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
#ትኩረት🚨

ከሰሞኑን በርካታ ሰዎች በተለይ ትንንሽ ህጻናት በጉንፋን እና በጉንፋን መሰል የመተንፈሻ አካላት ህመም እየተያዙ ይገኛሉ።

ይህንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመክቶ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና እንስቲትዩት ያጋራ መግለጫ ልከዋል።

ምን አሉ ?

➡️ የጉንፋን ሕመም በተፈጥሮ የላይኛውን የመተንፈሻ የሰውነት ክፍሎች ማለትም አፍንጫን፣ ጎሮሮን እና የአየር መተላለፊያ ባንቧን የሚያጠቃ ተላላፊ ሕመም ነዉ።

➡️ ሪኖ ቫይረስ ለጉንፉን መከሰት ዋና ምክንያት ሲሆን፣ ኮሮና፣ ኢንፍሉዌንዛ፣ ፓራ ኢንፍሉዌንዛ፣ አር ኤስ ቪ(RSV) ቫይረሶች ደግሞ ለጉንፉን መሰል ህመሞች መከሰት ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸዉ። ከተጠቀሱት ቫይረሶችም ለጉንፋን ሕመም መከሰት 50 በመቶ ድርሻውን የሚይዘው ሪኖ ቫይረስ ነው፡፡ በደረቅ ነፋሳማ ወቅት የአፍንጫ የውስጠኛው ስስ ሽፋን “ ሙከስ መምብሬን ” ስለሚደርቅ የጉንፋን ሕመም እና ተላላፊነቱ ይጨምራል፡፡

➡️ የክረምት ወራት ወይም የዝናብ ወቅት ማብቃቱን ተከትሎ መስከረምን ጨምሮ በጥቅምትና ህዳር ወራት እንደዚህ አይነት ጉንፋን መሰል ህመም የሚጠበቅ ነው፡፡

➡️ ሕመሙ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በቫይረሱ የተጠቃ ሰው በሚያስልበት ወይም በሚያስነጥስበት ጊዜ እንደሆነና በተጨማሪም ሰዎች ቫይረሱ ያረፈበትን የበር እጀታ፣ ጠረጴዛ ወይም በሕመምተኛው የተነካካንን ሰው እጅ ከነኩ በኋላ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ሲነካኩ ቫይረሱ ለመተላለፍ በሚፈጠርለት ምቹ ሁኔታ ነው።

➡️ የጉንፋን ሕመም የመጀመሪያ ምልክቱ ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት ተላላፊ ሊሆን ይችላል፤ ሕመሙ ከጀመረ ከ 5 እስከ 10 ባሉት ቀናት ደግሞ ሕመምተኛው ቫይረሱን ያስተላልፋል።

➡️ ህመሙ አብዛኛዉን ጊዜ እስከ 2 ሳምንት ሊቆይ ይችላል። ምልክቶቹም እንደ ፦
° የአፍንጫ ፈሳሽ መብዛት፣
° ሳል፣
° ትኩሳት፣
° ራስ ምታትና ጉሮሮን መከርከር፣
° ማስነጠስ፣
° አይን ማሳከክ እና መቅላት፣
° ማስታወክ፣
° ከፍ ሲልም የትንፋሽ ማጠር፣
° ከፍተኛ ድካምና የምግብ ፍላጎት መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ።

➡️ ከመስከረም ወር ጀምሮ መሰል ህመም ተሰምቷቸው ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ናሙና ከሰጡት ታካሚዎች ውስጥ አር ኤስ ቪ የተገኘባቸዉ ቁጥር የመጨመር ሁኔታ ያሳያል፡፡ በዚሁ ወቅት የተከሰተው ጉንፋን መሰል ህመም (አር ኤስ ቪ) በተለይ በህጻናት ላይ በብዛት የተከሰተ ሲሆን ለዚህም ወቅቱ ትምህርት ቤት የተከፈተበት በመሆኑ ለበሽታው መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

➡️ ባለፈዉ 1 ወር ዉስጥ ተመርምረዉ አር ኤስ ቪ ከተገኘባቸዉ ታካሚዎች መካከል 84% ያክሉ እድሜያቸዉ ከ5 አመት በታች ነዉ። እንደዚሁም ባለፈዉ ሳምንት ለአር ኤስ ቪ ከተመረመሩት 81 ናሙናዎች 49 (60.5%) ያህሉ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

➡️ አስፈላጊው ጥንቃቄ ካልተደረገ በሽታው የመዛመት እድሉ ከፍ ሊል እንደሚችል፤ በተለይ ቀዳሚ ተጎጅ ሊሆኑ የሚችሉ እንደ ህጻናትና አረጋውያን ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች አና ተጓዳኝ የጤና ችግር እንደነ አስም፣ የስኳር በሽታ፣ ካንሰር እና ሌሎች ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያሉባቸው ሕሙማን ከፍተኛ ጥንቃቄ ልናደርግላቸው እና ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ አስፈላጊዉን ምርመራና ህክምና ሊያደርጉ ይገባል።

➡️ የጉንፋን ሕመም የጆሮ ኢንፌክሽን እና የሳንባ ምች ሕመምን ጨምሮ ለተለያዩ ሕመሞች ተጋላጭ ሊያደርግ ይችላል፡፡

ጉንፋን መሰል በሽታን የምንከላከልባቸው መንገዶች ምንድናቸው ?
° የእጅ ንጽህናን መጠበቅ፣
° ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ የአፍና አፍንጫ ጭምብል(ማስክ) ማድረግ
° በዕለት ኑሯችን የምንጠቀምባቸውን በከባቢዎቻችን የሚገኙ ቁሳቁሶችን ማጽዳት
° የብዙሃን ማጓጓዣ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶችን በመክፈት በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር በማድረግ የበሽታዉን የመተላለፍ ዕድል መቀነስ ይቻላል፡፡


#ማሳሰቢያ ፦ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስድና ጠንከር ያለ የበሽታው ምልክት የሚታይበት ሰው በፍጥነት በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምክር አና ዕርዳታ ማግኘት አለበት፡፡

#MoH #EPHI

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮ ኢንተርናሽናል ስተዲ ሴንተር ከፍተኛ ትምህርታቸውን በአለም አቀፍ ተቋማት መከታተል ለሚፈልጉ የግንዛቤ መርሃግብር አዘጋጅቷል።

የፊታችን ማክሰኞ ጥር 13 ከጥዋቱ 1 ሰዓት እስከ 6:30 ድረስ በአዲስ አበባ EISC አዘጋጅነት 65 ከሚሆኑ የNCUK  አጋር ዩኒቨርስቲዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ የሆኑት ተቋማት ተወካዮች እዚሁ አዲስ አበባ ተገኝተው የተማሪዎችን ጥያቄዎች ያስተናግዳሉ።

በመርሃግብሩ ለይ ተሳታፊ ለመሆን በዚህ ሊንክ ይመዝገቡ :
https://eisc.uk/universities-fair-2025/

#ማሳሰቢያ 1 : የፕሮግራሙ ተሳታፊ ለመሆን ምንም አይነት ክፍያ ተማሪዎች አይጠየቁም።

#ማሳሰቢያ 2 : ለትምህርት እድል ተብሎ የሚከፈል ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ የለም። ፕሮግራሙ ከማንኛውም አይነት ክፍያ ጋር የሚገናኝ አይደለም።