TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥያቄ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ወ/ሮ ከድጃ ያሲን ፦ " ... የብልሹ አሰራር ከማስወገድና የፀረ-ሌብነት ትግልን ከማጠናከር አንፃር መንግሥት በየደረጃው ተጠያቂነትን ለማስፈን ምን ያህል ቁርጠኛ ነው ? በፀረ-ሌብነት ትግሉ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ምን ይጠበቃል ? ሰፊ የሀብት ብክነት እና ሌብነት በሚታይባቸው ለምሳሌ እንደ #መሬት_አስተዳደር፣ #ገቢዎች፣ #የጉምሩክ_አገልግሎት ፣ ትላልቅ…
#ጥያቄ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ባርጠማ ፍቃዱ ፦

" የሀገራችን የኢትዮጵያ ህዝብ የባለፈው ምርጫ አካሄድ ምንም ይሁን ምን እርሶንና ፓርቲዎን መርጦ መንግሥት ከመሰረተ ሁለት አመት አገባደን ሶስተኛ አመት ይዘናል።

በዚህ ምርጫ የተፎካካሪ ፓርቲዎች በአግባቡ በተወዳደሩበት ቦታ በአብዛኛው ህዝቡ ፓርቲዎን አምኖ ሳይሆን ለእርሶ በነበረው እምነትና ፍቅር የመጡበትም ጊዜ ውስብስብ እና ያደረና የገነነ የብሄርተኝነት ችግር እግር ተወርች ጠንፎ ይዟቸዋል ፦
- እድል እንስጣቸው ፣
- እሳቸው ጊዜ ሲያገኙ ቃል የገቡልንን ሁሉ ይፈፅሙልና ፓርቲያቸውንም ያጠሩታል ፣
- የዴሞክራሲ ተቋማት ጠንካራ ሆነው እንዲወጡ ያደርጋሉ ፣
- ፍትህ ያሰፍናሉ፣
- መፈናቀል፣ ስደት ፣ውርደት ያስቀሩልናል
- የስራ አጥ ቁጥር ይቀንሳሉ ፣
- የዜጎችን ደህንነት ያስጠብቃሉ፣
- የኑሮ ውድነትም ይቀንሱልናል በጥቅሉ ከንግግራቸውና አንዳንድ ከወሰዷቸው እርምጃዎች አንፃር የተሻለ ሊለውጡ ሀገራችንን የሚያሻግሩት እሳቸው ናቸው በሚል ነበር።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በእውነት እኔም በግሌ እምነት ነበረኝ። ብዙ ለውጥና ውጤቶችን አይቻለሁ። የህዳሴው ግድብ እውን ሆኖ ማየት፣ በሀገር ገበታ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ያሉ አፈፃፀሞች፣ ሰፋፊ የግብርና ስራዎች ጅማሮዎች ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም ከምንም በላይ ግን ፦

∘ ዜጎች እየሞቱ ነው፤ እየተፈናቀሉ ፣ እየተሰደዱ ነው።

∘ ዜጎች ለዘመናት ከኖሩበት ቄዬ በላይ ላያቸው ቤት ይፈርስባቸዋል፤ ተሰደዋል።

∘ ብዙ ዜጎች እስር ላይ ይገኛሉ የፍርድ ሂደቱም የተዛባ፣ የተንዛዛና የተጓተተ ነው።

∘ ሀገራችን ከጦርነት ልትላቀቅ አልቻለችም ፣የትግራይ ጦርነት በሰላም ቢቋጭም በሌላ በኩል በሌሎች አካባቢዎች ጦርነት ተፋፍሟል፣ በሰላም ለመፍታት የተኬደበት ርቀት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፤ እልህ መጋባትም ይታይበታል።

∘ እውነተኛው እና ጤነኛው የንግዱ ማህበረሰብ ከንግዱ እየወጣ ነው። ህገወጡ እያበበ፣ ሀገሪቱ ጥቂት ህገወጥ ከበርቴዎች እንዳሻቸው የሚሆኑባት እየሆነች ነው።

∘ የፋይናንስ ተቋማት እየከሰሙ ያሉበት፤

∘ የባንክ ማናጀሮች ከበላይ ተቋሞቻቸው በጥቅም ትስስር ምክንያት በአቅም ማነስ እና በሙስና መቆጣጠር ያለበት ተቋም በቸልታ የሚያይበት 10 ሺህ ብር እንኳን ለማግኘት ችግር የሆነበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን። እርምጃ ሲወሰድ አይታይም።

∘ የኑሮ ውንድነቱ ዜጎች ሳይወዱ በግድ ጎዳና እያስወጣ ነው።

∘ የኢትዮጵያውያን የአኗኗር ሁኔታ እጅግ ተለያይቷል። መንግስት እና ህዝብ ጀርባ ለጀርባ እየሆነ መጥቷል።

∘ የዜጎችን እንቅስቃሴ የሚገድብ አስጊ ሁኔታ ላይ እንገኛለን።

ክቡር ፕሬዚዳንት በንግግራቸው አማላይ የሆኑ የ3 ዓመት የኢኮኖሚ እቅድ አቅርበዋል። ነገር ግን የኢኮኖሚ እድገት ከላይ ተዘረዘሩ ችግሮች ባሉበት ሁኔታና ሌላው ቀርቶ የፓርቲዎ አባላት እርስ በእርሳቸው በማይተማመኑበት ሁኔታ እንዴት ሊሳካ ይችላል ?

እነዚህን ለማረም ምን አይነት የመፍትሄ ሀሳብ ይዘው ቀርበዋል ?

ሀገር እና መንግሥትዎን እንዴት ሊታደጉ አስበዋል ? "

@tikvahethiopia