TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አማራ በአማራ ክልል ለወራት ከቀጠለው የትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ በርካቶች በድሮን ጥቃት መገደላቸው እና በክልሉ ከፍርድ ውጭ ግድያዎች መቀጠላቸውን ዛሬ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከተላከልን መግለጫ መረዳት ችለናል። ከኢሰመኮ በደረሰን መግለጫ ፤ ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ የአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች በተለያየ ደረጃና ጊዜ የትጥቅ ግጭት ተካሂዶባቸዋል። …
" ሪፖርቱ የመንግሥትን እንቅስቃሴ አውድ ከግምት ያላስገባ፣ በበቂ መረጃ ላይ ያልተመሠረተ እና ከእውነታ ያፈነገጠ ነው " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የአማራ ክልል የሰብዓዊ ሁኔታን በተመለከተ ያወጣውን መግለጫ " ከእውነታው ያፈነገጠና ሚዛናዊነት የጎደለው ነው " አለ።

ዛሬ መግለጫ የሰጡት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አግልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ  ኢሰመኮ በአማራ ክልል ጉዳይ ያወጣው ሪፖርት የመንግሥትን እንቅስቃሴ አውድ ከግምት ያላስገባ፣ በበቂ መረጃ ላይ ያልተመሠረተ እና ከእውነታ ያፈነገጠ ነው ብለዋል።

በተጨማሪ ፤ መንግሥት ክልሉ ወደ ሰላማዊና መደበኛ እንቅስቃሴ እንዲመለስ ያደረገውን ጥረት ከግምት ያላስገባ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

" መንግሥት ገለልተኛ ተቋማት እንዲኖሩ የሚፈልገው የተዛቡ መረጃዎች አንዲታረሙ እና ዴሞክራሲ እንዲጠናከር አስቦ ነው " ያሉት ሚኒስትሩ " ነገር ግን እነዚህ ገለልተኛ ተቋማት በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ ባሉ የተዛቡ መረጃዎች ከተጠለፉ የምንፈልገውን ዴሞክራሲ ልንገነባ አንችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ፤ ኢሰመኮ የሚያወጣቸውን መረጃዎች ከትክክለኛ መንጭ በመረዳት እና ትክክለኛውን አውድ ከግምት ያስገባ መሆን እንሚገባው ገልጸዋል።

ከሰሞኑን ያወጣውን መግለጫም ቆም ብሎ እንዲገመግም አሳስበዋል።

መንግሥት በአማራ ክልል ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት እና የዜጎችን በሕይወት የመኖር መብት ለማረጋገጥ ጥንቃቄ የተሞላባቸው እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በዛሬው መግለጫቸው ወቅት ተናግረዋል።

ኢሰመኮ ከቀናት በፊት በላከልን መግለጫ ፤ በአማራ ክልል ለወራት ከቀጠለው የትጥቅ ግጭት ጋር በተያያዘ በርካቶች በድሮን ጥቃት መገደላቸው እና በክልሉ ከፍርድ ውጭ ግድያዎች መቀጠላቸውን ፣ እንዲሁም በመንግሥት ኃላፊዎች ላይ ግድያ መፈፀሙን አሳውቆ ነበር።

በተለይም #የአየር /#ድሮን መሣሪያን ጨምሮ በከባድ መሣሪያዎች ጥቃት የተነሳ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ፣ ሰዎች መኖሪያ አካባቢያቸውን ጥለው መሸሻቸውን የኢሰመኮ መግለጫ ያስረዳል።

በተለይም በመጥተህ ብላ ከተማ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት የአንድ አመት ከ7 ወር ህፃንን ጨምሮ በርካቶች መገደላቸውን ፣ በደብረ ማርቆስ በተመሳሳይ በድሮን 8 ሲቪል ሰዎች መገደላቸውን ፤ እንዲሁ በደንበጫ በከባድ መሳሪያ ሲቪሎች መገደላቸውን በመግለጫው አሳውቋል።

ኢሰመኮ በመግለጫው ላይ ቀጥሏል ባለው ከፍርድ ውጭ ግድያ ግጭት በተካሄደባቸው አካባቢዎች የመንግሥት የጸጥታ አካላት በመንገድ ላይ ወይም ቤት ለቤት ፍተሻ በማድረግ ከያዟቸው በርካታ ሲቪል ሰዎች ውስጥ ፦ " ፋኖን ትደግፋላችሁ " ፤ " ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ " ፤ " መሣሪያ አምጡ "፤  " የተኩስ ድምጽ ስለተሰማበት አቅጣጫ መረጃ ስጡ " በሚልና ይህንን በመሰሉ ምክንያቶች ከሕግ ውጭ የሆኑ ግድያዎች መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ተዓማኒ መረጃዎች መገኘታቸውን ገልጿል።

ከዚህ ባለፈ ፤ በየደረጃው የሚገኙ ሲቪል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች፣ ግድያዎችና እገታዎች በታጠቁ ኃይሎች መፈፀማቸውን ኢሰመኮ በመግለጫ አሳውቆ ነበር።

ኢሰመኮ ልኮት የነበረው ሙሉ መግለጫ በዚህ ይገኛል፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/82610

@tikvahethiopia