TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " በጦርነቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፣ መምህራን ፣ አምራች አርሶ አደሮች፣ ሃኪሞችን ጨምሮ ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሰውተዋል " - ጊዜያዊ አስተዳደሩ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በትግራዩ ደም አፋሳሽ ጦርነት ስለ ተሰው ታጋዮች " እንደ ተራ ነገር የሚነገረው ቁጥር የሃቅ መሰረት ስለሌለው ትርጉም አንሰጠውም " አሉ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ።…
#Update
በትግራይ የተለያዩ ከተሞች በጦርነቱ ህይወታቸው ላለፈ ወገኖች የጥዋፍ ማብራት ስነስርዓት ተከናውኗል።
በተለይም በክልሉ መዲና መቐለ ሰማዕታት ሃውልት እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመቐለ ነዋሪ በተገኘበት ነው ስነስርዓቱ የተከናወነው።
ፎቶ / ቪድዮ ፦ ከመቐለ፣ ዓዲግራት ፣ ማይጨው ፣ ሽረ እንዳስላሴ (በቴሌቪዥን ትግራይ)
@tikvahethiopia

አንጋፋዋ አርቲስት ሀሎ ዳዌ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።
አርቲስት ሀሎ ዳዌ በኦሮሞ የኪነጥበብና የትግል ታሪክ ውስጥ አንጋፋ ከሆኑ አርቲስቶች አንዷ ናት።
አርቲስት ሀሎ ዳዌ ባደረባት ሕመም ምክንያት ለረጅም ጊዜ በህክምና ስትረዳ ብትቆይም ማገገም ባለመቻሏ ዛሬ በአዳማ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ከ #ኦቢኤን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia
አርቲስት ሀሎ ዳዌ በኦሮሞ የኪነጥበብና የትግል ታሪክ ውስጥ አንጋፋ ከሆኑ አርቲስቶች አንዷ ናት።
አርቲስት ሀሎ ዳዌ ባደረባት ሕመም ምክንያት ለረጅም ጊዜ በህክምና ስትረዳ ብትቆይም ማገገም ባለመቻሏ ዛሬ በአዳማ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ከ #ኦቢኤን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የትግራይ አካባቢዎች ከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ ናቸው።
ጥቅምት 2 በይፋ የታወጀው የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት ተከትሎ የክልሉ ከተሞችና ገጠሮች በከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ ይገኛሉ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በትግራይ ያለው የሃዘንና የመርዶ ስነ-ሰርአትና ተዛማጅ ጉዳዮች አፈፃፀም በሚከተለው ሪፓርታዥ አጋርቶናል።
ዓርብ ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም ከሰዓት በኃላ በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ የሃዘንና የክብር ስነ-ሰርአቱ መታወጅ ተከትሎ ከ1:00 ሰዓት አመሻሽ ጀምሮ ከማይጨው እስከ ሸራሮ በ500 ኪሎ ሜትር ርቀት አከባቢ የሚገኙ ከተሞች ሰማእታት የሚዘክር ሻማ ያበሩ ሲሆን ፤ በሌሊቱ በቤተከርስትያንና በመስጊዶች ቅዳሴና ፀሎት እንዲሁም ዱዓ ሲያደርጉ አድረዋል።
ጥቅምት 3 ጠዋት 12:00 ሰዓት የክልሉ ባንዴራ ዝቅ ብሎ ሲውለበለብ ፤ በመቐለ ጥቅምት 3 ከምሽቱ 1:00 ሰማእታትዋ ለማሰብ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንትና ካቤኔያቸው ፣ የህወሓት ሊቀመንበርና የከተማው ነዋሪ በተገኘበት ጥዋፍ አብርታለች።
የሃዘንና የክብር ስነ-ሰርአቱ ለማስፈፀም የወጣ መመሪያ የሚከለክላቸው ነገሮች ተፈፃሚነታቸው ከጥቅምት 3 ጀምሮ መሆኑ በመመሪያ የተቀመጠ ቢሆንም እንደ መጠጥ ቤት የመሳሰሉ አገልግሎት ሰጪዎች በራሳቸው ፍላጎት ጥቅምት 2 ከሰአት በኃላ ጀምሮ ዘግተዋል።
ጥቅምት 2 ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በተሰው ቤተሰቦች መኖሪያ ይፋዊ የመርዶ ስነ-ሰርአት የተካሄደ ሲሆን የመርዶ ስነ-ሰርአቱ የሚያከናውኑት ፦
- የአገር ሽማግሌ
- የሃይማኖት አባቶች
- ታጋዩ ሲሰዋ በአጠገቡ የነበረ የአይን ምስክር
- ከነባር ታጋይ የተወጣጡ ኮሚቴ ሲሆኑ ቤተሰቡ ሲያረዱ ከመንግስት የተላከ የክብር መግለጫ የምስክር ወረቀትና የትግራይ ባንዴራ በመስጠት ነው።
መርዶ ከተነገረ በኃላ የተሰዋ ታጋይ ቤተሰብ ኮሚቴው አረጋግቶ በማጀብ እና በመምራት መርዶ ወደ ተነገሩ ሌሎች ቤተሰቦች ጋር በማቀላቀል ወደ መሰባሰብያ ቦታ ወስደዋቸዋል።
ከጥዋቱ 12:30 በየአከባቢው መርዶ የተነገረው ሁሉም ወደየ መገናኛ ቦታ ተሰባሰበ። በቦታው ደርሶ ልክ 1:00 ሰአት ከጠዋቱ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የሚኖር ትግራዋይ በሚድያ የሚመራ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል።
ከህሊና ፀሎት በኋላ የተሰዋ ቤተሰብ አባል እንደየ እምነቱ ወደ ሚመለከተው የማምለክያ ቦታ በህዝብ ታጅቦ ተጓዘ።
በእምነት ማስፈፀምያ ቦታ እንደየ እምነቱ የሚሰጠው ፀሎተ ፍትሃት፣ ዱዓና መፅናኛ የሃይማኖት አስተምህሮ ከተሰጠ በኃላ ከጊዚያዊ አስተዳደሩ የተላከ መልእክት በንባብ ቀርቧል።
በቤተ እምነት የተካሄደው ፍፃሜ ከተጠቃለለ በኃላ የሰማእታት ቤተሰብ በህዝቡ በመታጀብ ወደየ ቤታቸው ተመልሰዋል።
በየሃይማኖት ማምለኪያ ቦታዎቹ ከሚፈፀም ስነ-ሰርአት ጎን ለጎን በትግራይና ድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት የተላለፈ በሰማእታት የመታሰብያ ሃወልት በክብር መዝገብ ፅሁፍ የማኖርና የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ስነ-ሰርአት ተከናውኗል።
መቐለ ጨምሮ ማይጨው፣ መኾኒ፣ ዓዲጉዶም፣ ውቕሮ፣ ዓብዪ ዓዲ፣ ዓዲግራት፣ ዓድዋ፣ አክሱም፣ ሽረ፣ ሸራሮና ሌሎች ከተሞች በከፍተኛ የሃዘን ድባብ ውስጥ ሲሆኑ እንደ ባንክ የመሳሰሉ አገልግሎት ሰጪዎች የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአቱ ለማስፈፀም አስመልክቶ በወጣ መመሪያ መስረት ዝግ ሆነው ውለዋል።
የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት በተለያዩ ፕሮግራሞች በመቀጠል ጥቅምት 6 በህዝባዊ ሰልፍ እንደሚጠቃለል የወጣው መርሃ ግብር ያስረዳል።
መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው ከመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።
ፎቶ፦ ከላይ ተያይዟል