TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ፍልስጤም #እስራኤል

በጋዛ በሚገኝ ሆስፒታል ላይ በተፈፀመ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገደሉ።

ሃማስ ጥቃቱን እስራኤል ነው የፈፀመችው ብሏል።

የእስራኤል መከላከያ ደግሞ " ኢስላሚክ ጂሃድ " የተባለው ቡድን እስራኤል ላይ ያስወነጨፈው ሮኬት ዒላማው ሳይሳካ ቀርቶ የተፈጠረ ነው ብሏል።

ትላንት ጋዛ ውስጥ በሚገኘው "አልአህሊ ባፕቲስት ሆስፒታል " ላይ በደረሰ የአየር ጥቃት በትንሹ 500 ሰዎች መገደላቸውን በጋዛ  የሚገኘው ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሃማስ ጥቃቱን እስራኤል ነው የፈፀመችው ብሏል። ጥቃቱን " የጦር ወንጀል ነው" ሲል ገልጾ " ሆስፒታሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ የታመሙ እና የቆሰሉ ሰዎች ነበሩበት ብሏል።

የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ፤ በጋዛ የሚገኘው ሆስፒታል የተመታው ባያልተሳካ የ " እስላሚክ ጂሃድ " ቡድን ሮኬት ነው ብሏል።

ያልተሳካ ሮኬት ያስወነጨፈው ይኸው ቡድን ለሆስፒታሉ መመታት ተጠያቂ ነው ሲል ገልጿል።

" እኛ ሆስፒታሉ ላይ ጥቃት አልፈፀምንም " ብሏል።

የ " ፍልስጤም እስላሚክ ጂሃድ " ድርጅት የእስራኤል ክስ ሀሰተኛ እና ምንም መሰረት የሌለው የተለመደ ቅጥፈት ነው ብሏል። እስራኤል ከተለመደው ጭፍጨፋ ተጠያቂነት ለማምለጥ በፍልስጤማውያን እና ' ኢስላሚክ ጂሃድ ' ላይ ጣቷን ለመጠቆም የፈጠረችው ሀሰተኛ ፈጠራ ነው ሲል ገልጿል።

" ፍልስጤም እስላሚክ ጂሃድ " እኤአ 1981 የተመሰረተ ሲሆን በጋዛ እና ዌስት ባንክ ውስጥ ይንቀሳቀሳል።

በሌላ በኩል ፤ የፍልስጤም ፕሬዜዳንት ማሃሙድ አባስ በሆስፒታሉ ላይ በተፈፀመው ጥቃት እና በጠፋው የሰው ህይወት ምክንያት የ3 ቀን ሀዘን አውጀዋል።

በሆስፒታል ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ሀገራት እና ተቋማት እያወገዙ ይገኛሉ። በተለያዩ ከተሞችም እስራኤልን የሚያወግዙ ሰልፎች እየተደረጉ ይገኛሉ።

ዓለም ለጋዛ ሆስፒታል ለደረሰው ጥቃት ምን ምላሽ ሰጠ ?

እስራኤል የአየር ጥቃቱን ፈፅማለች ብለው የከሰሱና ያወገዙ ፤ በጉዳቱ ሀዘናቸውን የገለፁ ፦

🇪🇬 የግብፅ ፕሬዝዳንት
🇯🇴 የዮርዳኖስ ንጉስ
🇸🇾 የሶሪያ ፕሬዝዳንት
🇨🇺 የኩባ ፕሬዝዳንት
🇮🇶 የኢራቅ መንግስት
🇸🇦 የሳዑዲ አረቢያ መንግስት
🇹🇷የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
🇻🇪 የቬንዙዌላ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
🌍 የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሃላፊ
🇮🇷 የኢራን ፕሬዝዳንት (እስራኤል ብቻ ሳትሆን አሜሪካም ጭምር ከእስራኤል ጋር ሀላፊነት ትወስዳለች ብለዋል)

ጥቃቱን ያወገዙ ነገር ግን ማንንም ያልወቀሱ ፤ ይልቁንም ምርመራ እንዲደረግ የጠየቁ ፦

🇪🇺 የአውሮጳ ዲፕሎማሲ ኃላፊ
🇫🇷 የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት
🇳🇱 የኔዘርላንድስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
🇪🇸 የስፔን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
🇬🇧 የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት
🇯🇵 የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
🇺🇸 አሜሪካ ማንም ሳትከስ ነገር ግን ስለ ተፈጠረው ሁኔታ ተጨማሪ መረጃዎችን ሰበስባለሁ ብላለች።

" ማስረጃ አቅርቢ " - ሩስያ

🇷🇺 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስራኤል በጥቃቱ ላይ የለሁበትም ካለች የሳተላይ ምስሎችን በማስረጃነት ታቅርብ ብሏል።

እኤአ ጥቅምት 7 ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ ባደረሰችው ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ከ3,200 በልጠዋል።

በእስራኤል ውስጥ በሃማስ ጥቃት የተገደሉ ከ1,400 በላይ ሰዎች ሆነዋል።

More 👉 @Birlikethiopia