TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Success begins with the right mindset! 💡 Join Jasiri Talent Investor Programme - Cohort 5 and cultivate the entrepreneurial mindset needed to overcome challenges and seize opportunities. Surround yourself with a community that believes in your potential. Apply now at https://jasiri.org/application and embark on a journey of growth and success!
🎤 አዲስ አበባ
የዘመናችን የመጨረሻውን የ5G ኔትወርክ በአዲሱ የ5G ጥቅል ለመጠቀም ዝግጁ!!!?🏃‍♂️🏃‍♀️

ወርሃዊ የ5G ጥቅሎችን ከ10%_ተጨማሪ ጋር በቴሌብር ሱፐርአፕ፣ በማይ ኢትዮቴል ወይም በ*999# በመግዛት የአዲሱን ትውልድ ኔትወርክ ያጣጥሙ!

በአዲስ አበባ የ5G አገልግሎት የሚያስጠቅም ስልክ ያላቸውን ደንበኞቻችንን አገልግሎት ወደ 5G አሳድገናል ::

ለዝርዝር መረጃው: https://bit.ly/3RQ2McR

#አዲስ_ዓመት_አዲስ_ፍጥነት_ምቾት_እና_አኗኗር #5G
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#CARD: ይህን የ4 ደቂቃ መረጃ ዳሰሳ ጥናት በመሙላት የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት የምንሰራው የግንዛቤ ማስጨበጫ መመርያ ያግዙ።
👉 https://09u34jhg43098.typeform.com/to/nToapX9c

(የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል)
TIKVAH-ETHIOPIA
በቅበት ጉዳይ ምን ተባለ ? በስልጤ ዞን፣ ቅበት ከተማ ለተፈጠረው ችግር ፣ የዞኑ እና የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅተው በመሥራት፣ አስቸኳይ መፍትሄ ሊያበጁለት እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚደንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል። ችግሩን አስመልክቶ፣ ከዞንም ሆነ ከክልሉ እስልምና ጉዳዮች…
#ቅበት

ከአንድ ወር በፊት በቅበት ከተማ ተከስቶ የነበረውን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታታ ስምምነት ላይ መደረሱን ከስልጤ ዞን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ከዞን አስተዳደር በተገኘው መረጃ ፤ ስምምነት ላይ የተደረሰው የቅበት ከተማ አስተዳደር ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር ተባብረ ባዘጋጁት ውይይት ነው።

በዚሁ ውይይት ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን በመድረኩ ላይ የተሳተፉ አካላት ተከስቶ የነበረው አለመግባባት ሀይማኖታዊ መሰረት ያልነበረውና በግለሰቦች ችግር የተፈጠረ ነበር ብለዋል።

ለአለመግባባቱ መነሻ የሆኑ ምክንያቶችን ከስር መሰረቱ መፍታት የሁሉም ሀላፊነት መሆኑን የውይይቱ ተሳታፊዎች ያነሱ ሲሆን ሚዛናቸውን የሳቱ ትችቶችና ማህበረሰቡን በጠቅላላ የመፈረጅ አዝማሚያዎች ተገቢ እንዳልነበሩ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፤ በማናቸውም በኩል ያሉ ወንጀለኞች በአግባቡ እንዲጠየቁና በተለያየ መልኩ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ተገቢውን ፍትህ እንዲያገኙ በጋራ መስራት ይገባል ብሏል።

በዚሁ መድረክ የተፈናቀሉ ዜጎች ከአንድ ሳምንት በኋላ እንዲመለሱ የሚያስችል መግባባት ላይ ተደርሷል።

የግጭት መባባስ መንስኤ የሆኑ ጥፋተኞች፣ ዜጎችን ያፈናቀሉና ንብረት ያወደሙ ሰዎች በሕግ ተጠያቂ ይደረጋሉ ተሽሏል።

የወደሙ ቤቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ይገነባሉ ተብሏል። የቤቶችን ግንባታም በአንድ ሳምንት ጊዜ አጠናቅቆ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል።

የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አለመግባባቱን በዘላቁነት ለመፍታት የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ከአንድ ወር በፊት በቅበት በተፈጠረው ችግር የሰው ህይወ መጥፋቱ ንብረት መውደሙ፣ ዜጎችን ከቄያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ሲፌፓ

ሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።

አሁን ሀገር ካለችበት ሁኔታና ከተደቀነባት ፈተና ችግር አንፃር የተወሰኑ አስቻይ ሁኔታዎች ተፈጥሮ ሀገራዊ ምክክር ከማድረግ ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለ የሲዳማ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) ገልጿል።

ፓርቲው ፤ በየአከባቢው የሚደረጉ ጦርነቶችና ግጭቶች ቆመው ችግሮች በምክክርና በውይይት ብቻ መፈታት እንዳለበት አቋም መያዙን አሳውቋል።

ለዚህም የራሱን አስተዋፅዖ ለማድረግ ከውሳኔ ላይ መድረሱን ገልጿል።

በተጨማሪ የሲዳማን ህዝብ ፍላጎት በመወከል በሀገራዊ ምክክር መድረክ ላይ የሚሳተፍ ጠንካራ ፖለቲካ ፓርቲ የለም ያለው ሲፌፓ " በምክክር ሂደቱ ውስጥ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የህዝቡን ፍላጎት ማንፀባረቅ እንዳለብን አምንናል " ሲል አሳውቋል።

በመሆኑንም ፓርቲው በምክክር ሂደት ላይ ከወረዳ አንስቶ እስከ ሀገር ድረስ በበቂ ሁኔታ መሳተፍ የሚችልበት አግባብና በተለያዩ አስቻይ ሁኔታዎች ላይ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር በመነጋገር መስከረም 29/01/2016 ከኮሚሽኑ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊዉ አቶ ገነነ ሀሳና ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት መረጃ እንደገለጹት ስምምነቱ በርካታ ችግሮችን ለመቅረፍና የንግግርና የዉይይት መድረክ በመክፈት ክልላዊም ሆነ ሀገራዊ ክፍተቶችን ለማስተካከል እንደሚረዳ አመልክተዋል።

ስምምነቱን ተከትሎ ኮሚሽኑ በሲዳማ ክልል በሚያደርገዉ የዉይይት  መድረክ የበኩሉን ለማበርከት በወረዳ በዞን እንዲሁም ክልል ደረጃ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
" ከታች ጀምሮ የሚሰጠው ፈተና እንዲጠናከር ይደረጋል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከታች ጀምሮ የሚሰጠውን ፈተና ይጠናከራል አለ።

አገልግሎቱ ፤ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የገጠመውን የውጤት ማሽቆልቆል ለመቅረፍ ከታች ጀምሮ የሚሰጠው ፈተና እንደሚጠናከር ይደረጋል ብሏል።

" ለውጤት መቀነስ አንዱ ምክንያት ተማሪዎች በታችኞቹ የትምህርት ደረጃዎች በተገቢው ፈተና እየወሰዱ አለመምጣታቸው ነው " የሚለው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት " ይህም ተማሪዎች በየደረጃው ማወቅ ያለባቸውን እንዳያውቁ አድርጓል " ብሏል።

ይህ ሁኔታ በስተመጨረሻ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት እንዲያመጡ ማድረጉን አመልክቷል።

ችግሩን ለመቅረፍ ተማሪዎች በተገቢው ምዘና እንዲያልፉ እንደሚደረግ ያሳወቀው አገልግሎቱ ይህንም ለመተግበር በ8ኛ ክፍል የሚሰጠውን ፈተና ከማጠናከር ባለፈ በየትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን ምዘና ለማጠናከር ይሰራል ሲል አሳውቋል።

ከዚህ ባለፈ ግን ሁሉን አቀፍ የማሻሻል ስራዎች እንደሚያስፈልግ እና እንደሚሰራ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኤፍቢሲ በሰጠው ቃል አመልክቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" የ6 ተማሪዎች ህይወት አልፏል "

በትግራይ የ12ኛ ክፍል ፈተና ጨርሰው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የነበሩ ተማሪዎች በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

በርካቶችም ቀላል እና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ፈተናቸውን ጨርሰው ወደ ተንቤን እና አካባቢው ሲጓዙ የነበሩ ተማሪዎችን አስፋሮ የነበረ ኣውቶብስ በሀውዜን ወረዳ " ደብረ ሰላም " የሚባል አካባቢ ተገልብጦ የ6 ተማሪዎች ህይወት አልፏል።

በአደጋው ​​ከሞቱት 6 ተማሪዎች በተጨማሪ 53 ተማሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀውዜን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አሳውቋል።

የሀውዜን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና የመጋብ ጤና ጣቢያ የህክምና እና የአምቡላንስ ባለሙያዎች ተጎጂዎች ህክምና እንዲያገኙ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ተነግሯል።

ጉዳት የደረሰባቸው 29 ተማሪዎች በሀውዜን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና መጋብ ጤና ጣቢያ በህክምና ላይ ሲሆኑ ፤ 24ቱ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች ወደ አይደር ሪፈራል ሆስፒታል መላካቸውን ከቴሌቪዥን ትግራይ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
ብርቱ አጋር!!
ለስኬትዎ መዳረሻ ለህልምዎ እውን መሆን ብርቱ አጋር ነን

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ !!
ለጋራ ስኬታችን !!

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል
https://t.iss.one/Globalbankethiopia123
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቅልጥፍ ያለ አስተማማኝ የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፊያ መቷል! ዛሬውኑ M-PESAን አውርደን እንጠቀም።

#MPESASafaricomET #FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
ኤርዶጋን ምን አሉ ? የቱርክ ፕሬዝዳንት ሪሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ዙሪያ ይህን ብለዋል ፦ - በሲቪሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ወይም በሲቪል አካባቢዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ትክክል አይደለም፤ አንቀበለውም። - በእስራኤል ግዛት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ግድያ እንቃወማለን። - በጋዛ ውስጥ ንጹሃን  ያለየ ' #ጭፍጨፋ ' በፍጹም አንቀበልም። - አሳፋሪ ዘዴዎችን…
#እስራኤል #ፍልስጤም

ዛሬ አንድ ሳምንቱን የያዘውና ባለፉት ዓመታት ውስጥ ታይቶ አይታወቅም የተባለው እጅግ ደም አፋሳሹ የእስራኤል እና የፍልስጤሙ ሃማስ ጦርነት ቀጥሏል።

አጫጭር መረጃዎች ፦

- እስራኤል እየወሰደችው ባለው ጥቃት የሞቱ ፍልስጤናውያን ቁጥር 1,900 ደርሰዋል። ከሞቱት ውስጥ እጅግ በርከታ ህፃናት ይገኙበታል ተብሏል። 7,696 ሰዎች ደግሞ ተጎድተዋል።

- ሃማስ በሚፈፅመው ጥቃት በእስራኤል በኩል የሞቱ ሰዎች 1400 የደረሱ ሲሆን 3,418 ሰዎች ተጎድተዋል።

- በዌስት ባንክ ውስጥ 52 ሰዎች ሲገደሉ፣ 700 ተጎድተዋል።

- እስራኤል " ሃማስን እስከወዲያኛው አጠፋዋለሁ ፤ ላደረገው ድርጊትም ዋጋውን አስከፍለዋለው " እያለች ሲሆን አሁን ላይ እየወሰደች ያለው እርምጃ ገና መጀማሪያው እንዳሆነ ገልጻለች።

- እስራኤል በሰሜናዊ ጋዛ ያሉ ሁሉም ሲቪሎች በሰዓታት ውስጥ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቃለች። በሰሜናዊ ጋዛ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚገኙ ሲሆን ሀገራት እና ተቋማት እስራኤል ውሳኔዋን እንድታጥፍ እየጠየቁ ናቸው። እንደ ተመድ መረጃ በአስር ሺዎች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል።

- በጋዛ ላይ የነዳጅ፣ የምግብ፣ የውሃ እገዳው አሁንም እንደቀጠለ ነው።

- ሐማስ እስራኤል ላይ አሁንም የሮኬቶች ጥቃት መፈፀሙን ቀጥሏል።

- የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ የፍልስጤሙን " ሃማስ " በመደገፍ እንደሚሰለፍ አስታውቋል። ቡድኑ ጊዜው ሲደርስ ጦርነቱን ከሃማስ ጎን ሆኖ ለመሳተፍ ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ እንደሆነ ገልጿል። ባለፉት ቀናት በሊባኖስ በኩል አንዳንድ የግጭት ምልክቶች የታዩ ሲሆን እስራኤል ድንበሯን ጥሰው ሊገቡ ነበሩ ያለቻቸውን ሰዎች በድሮን መታ መግደሏ ተነግሯል።

- ሐማስ አግቶ ከወሰዳቸው ሰዎች ውስጥ 13 እስራኤላውያንን እና የውጭ አገራት ዜጎች እስራኤል በጋዛ እያደረገችው ባለችው የአየር ጥቃቶች መገደላቸው አሳውቋል።

- የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ወደ ጦርነቱ ቀጠና ሄደው ከእስራኤል ጠ/ሚ እስራኤል ውስጥ፣ ከፍልስጤሙ ፕሬዜዳንት ሞሀሙድ አባስ ጋር ዮርዳኖስ ውስጥ ተገናኝተው መከረዋል። በኃላም ወደ  አጋርናታችንን እናሳያለን ብለው ትላንት እስራኤልን ጎብኝተው ነበር። በኃላም ወደ ሳዑዲ አረቢያ አቅንተው ከሀገሪቱ አመራሮች ጋር ስለጦርነቱ መክረዋል።

- ጦርነቱ እንዲቆም እና መሄጃ ለጠፋባቸው ፍልስጤማውያን ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ በተለያዩ ወገኖች ጥሪዎች እየቀረቡ ይገኛሉ።

More  @BirlikEthiopia

https://t.iss.one/+LM-bJ8NzZMcxMjA8
#እንድታውቁት

" በዓለማችን በየ2 ደቂቃ ልዩነቱ  በማህፀን በር ካንሰር ምክንያት ሴቶች ህይወታቸውን ያጣሉ " - የዓለም ጤና ድርጅት

የማህፀን በር ካንሰር (Cervical Cancer) ፦

- የማህፀን በር ካንሰር በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ  ካንሰሮች በገዳይነቱ በዓለም 4ኛ ላይ የተቀመጠ ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ ከጡት ካንሰር ቀጥሎ 2ኛ ላይ ተቀምጧል::

- ይህ የካንሰር ዓይነት 99.7% መነሻው (Human papilloma virus)  የተባለ ቫይረስ ሲሆን ከሰው ወደ ሰው በጾታዊ ግንኙነት ጊዜ የሚተላለፍ ነው፡፡  ይህ የቫይረስ ዓይነት ከ200 በላይ ዓይነቶች ሲኖሩት የማህፀን በር ካንሰር የሚያመጡት ጥቂቶቹ ሲሆኑ HPV 16 እና HPV 18 የተባሉት ዋነኞቹ ናቸዉ፡፡

- ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት በላይ የሆኑ ሴቶች ላይ፣ የበሽታ መከላከል አቅማቸው የቀነሰ እንደ ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ያለባቸው ሰዎች፣ ከአንድ ሰው በላይ ጋር ግንኙነት ሚያደርጉ እና የአባላዘር በሽታ ያለባቸው  ሴቶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው።

-  ለብዙ ጊዜ ምልክት ሳያሳይ በሰውነት ውስጥ ሊቆይ ይችላል፡፡

  ምልክቶቹም-
▪️ከግንኙነት በዃላ በብልት በኩል መድማት
▪️የወር አበባ ካለቀ በዃላ እና በሁለት የወር አበባ ጊዜ መካከል ያለ መድማት
▪️በብልት በኩል ያልተለመደ ጠረን ያለው ፈሳሽ መዉጣት
▪️ከ Menopause (ማረጥ) በኋላ የሚኖር የማህፀን መድማት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

- በዓለማችን በየ 2ደቂቃ ልዩነቱ  በማህፀን በር ካንሰር ምክንያት ሴቶች ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡ ከ90 በላይ የሚሆኑት ደግሞ እንደኛ በመካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ላይ ነው፡፡

- ይህንን ደግሞ ታዳጊ ሴቶች የማህፀን በር ካንሰር ክትባትን በመከተብ እንዲሁም እድሜያችው 21 እና በላይ የሆኑ ሴቶች ቢያንስ በየ3 ዓመቱ ቅድመ ምርመራ በማድረግ መከላከል ይቻላል፡:

- ይህ በሽታ በአግባቡ በሚደረግ ቅድመ ምርመራ በጊዜ ከተገኘ በህክምና የመዳን አድሉ ከፍተኛ ነው።

▫️ስለዚህ ታዳጊ ሴቶችን  ክትባቱን በማስከተብ እና እድሜያቸው ከ21 አመት በላይ የሆኑ ሴቶች ደግሞ  በየ3 አመት ሚደረገውን ቅድመ ምርመራ በማድረግ በበሽታው ምክንያት የሚከሰት የጤና መጓደልን እና ሞትን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ይቻላል፡፡

#WHO #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " የሚቋረጥ የትራንስፓርት አገልግሎት የለም ፤ ባንኮች ግን ለሁለት ቀን ዝግ ይሆናሉ " - የትግራይ አርበኞች ኮሚሽን ምክር ቤት የትግራይ የአርበኞች ኮሚሽን ም/ቤቱ በትግራይ ክልል ደረጃ የታወጀው " የሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን " ስነ-ሰርአት አስመልክቶ መስከረም 29/2016 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ ስብሰባው የህክምናና የትራንስፓርት አገልግሎት የማይቋረጥ ሲሆን የባንከ አገልግሎት ግን…
#ትግራይ

" በጦርነቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፣ መምህራን ፣ አምራች አርሶ አደሮች፣ ሃኪሞችን ጨምሮ ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሰውተዋል  " - ጊዜያዊ አስተዳደሩ

በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች በትግራዩ  ደም አፋሳሽ ጦርነት ስለ ተሰው ታጋዮች " እንደ ተራ ነገር የሚነገረው ቁጥር የሃቅ መሰረት ስለሌለው ትርጉም አንሰጠውም " አሉ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ።

ፕረዚደንቱ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ስነ-ሰርአት በይፋ መታወጅ አስመልክተው ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም ለክልሉ የመንግስት ፣ የግልና የውጭ ሚድያዎች ሰፊ ቃለ-መጠይቅና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ፤ በክልሉ በተካሄደው ደም አፋሳሽና እልህ አስጨራሽ ጦርነት የተሰው ታጋዮች ቁጥር እንዲገልፁ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ " ... በትግሉ ስለተሰውት ታጋዮች ቁጥር ብዙ ተረት ነው የሚወራው ፤ የተሰውት ታጋዮች ቁጠር እንገልፃለን። ለጊዜው ግን መግለፁ አስፈላጊ ሆኖ ስላልታየን እናቆየዋለን "  ብለዋል። 

" ... ለትግራይ ህልውና የተከፈለ ዋጋ የሚመጥነው ደረጃና ዋጋ መስጠት አለብን ሲባል ለያንዳንዱ የተሰዋ ታጋይ ፤ ለያንዳንዱ የተሰዋበት ቤተሰብ የክብር የምስክር ወረቀት ልከናል " ያሉት አቶ ጌታቸው ፤ " የተሰውት ታጋዮች ቁጥር በእጃችን ይገኛል። ከቁጥሩ ባሻገር ግን እጅግ ከባድና ውድ ዋጋ ከፍለናል። ለህልውናችን የተከፈለ በመሆኑም  ግን የሚያስቆጨን አይሆንም ሊባል ይችላል " ሲሉ አክለዋል።

አቶ ጌታቸው ፤ " ብዙ ልጆቻችን ከፍለናል። ጠላቶች (ፕሬዜዳንቱ ጠላቶች ያሏቸውን በስም አልገለጿቸውም) የኛ የመስዋእት ኪሳራ በማብዛት የነሱ ለማሳነስ እንደማነፃፀሪያ በማቅረብ ብዙ ይናገራሉ። በበኩሌ አሁን ካለው የተሰዋ ታጋይ ቁጥር ሩብ ፤ ከሩብ በታች ፤ አንድ መቶኛው እንኳን ብንከፍል ዋጋው ከባድ ነው የሚል እምነት አለኝ። " ብለዋል።

" አልተሳካልንም እንጂ ያለ አንድ ታጋይና ያለ አንድ ወጣት መስዋእት ፣ ራሳችን በራሳችን የማስተዳደር መብታችን የምናረጋግጥበት ዕድል ቢኖር እመርጥ ነበር " ሲሉ አክለዋል።

ፕሬዜዳንቱ በስም ያልጠሯቸውና " ጠላቶች " ሲሉ የጠሯቸው ኃይሎች " አሁን ላይ መጥራት በጀመሩት የተዛባና የተጋነነ ቁጥር በመደናገር ሌላው ያልሆነ ቁጥር ሲጠራ ቢውል ለኔ 20 ሺህ ተባለ ፣ 10 ሺህ ተባለ ፣ ህልውናችን ለማረጋገጥ አንድ ሰው ይሰዋ 20 ሺህ ዋጋው እጅግ ከባድ ነው " ብለዋል።

" በተሰውት ታጋዮች ዝርዝር ፦
- የዩኒቨርስቲ መምህራንና ተማሪዎች ፣
- ጥሩ አምራች አርሶ አደሮች
- ሃኪሞች ሁሉም አይነት የህብረተሰብ ክፍሎች አሉ። በአጠቃላይ ትግራይን በሰላም ጊዜ ወደ ተሻለ የእድገት ደረጃ የማሸጋገር አቅም የነበራቸው በመስዋእትነት አጥተናል " ያሉት አቶ ጌታቸው ፤ " ይህንን መስዋእትነት ዋጋ መስጠት እንዳለ ሆኖ ፤ ቁጥሩ ጠላት በሚለው ደረጃ እንዳልሆነ መረዳቱ ስጋታችን ቀንሶ ያረጋጋናል " ማለታቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

የትግራይ ሰማእታት የሃዘንና የክብር ቀን ሰነ-ሰርዓት ከጥቅምት 3 አስከ 5 በተለያዩ ዝግጅቶች ታጅቦ በመካሄድ  ፤ ጥቅምት 6/2016 ዓ.ም " በሃዘን አንገታችን እንደፋም "  በሚል መሪ ቃል በሚካሄድ የህዝብ ሰልፍ እንደሚጠቃለል ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል።   

መረጃው በቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ የተዘጋጀ ነው።

@tikvahethiopia