TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
ኤርዶጋን ምን አሉ ?

የቱርክ ፕሬዝዳንት ሪሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት ዙሪያ ይህን ብለዋል ፦

- በሲቪሎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ወይም በሲቪል አካባቢዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ትክክል አይደለም፤ አንቀበለውም።

- በእስራኤል ግዛት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ግድያ እንቃወማለን።

- በጋዛ ውስጥ ንጹሃን  ያለየ ' #ጭፍጨፋ ' በፍጹም አንቀበልም።

- አሳፋሪ ዘዴዎችን በመጠቀም የሚካሄደው ግጭት ፣ ጦርነት ሳይሆን ' ጭፍጨፋ ' ነው።

- ማንኛውም አካል ፍልስጤማውያንን 🇵🇸 ለመቅጣት ዓላማ ካላቸው ውሳኔዎች መራቅ አለበት።

- ሽምግልና እና ፍትሃዊ ዳኝነትን ጨምሮ የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን።

በእስራኤል እና በፍልሥጤሙ ሃማስ መካከል ቅዳሜ የጀመረው ደም አሳፋሽ ግጭት ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ሃማስ ወደ ቴላቪቭ እና ማዕከለኛው እስራኤል ሮኬቶችን ሲያስወነጭፍ ውሏል።

እስራኤል የምትወስደውን የአስፀፋ እርምጃ አጠናክራ ቀጥላለች። ሠራዊቷን ጋዛ ድንበር ላይ በማከማቸት ላይ እንደሆነችና የምድር ጥቃት ሊደረግ እንደሚችል እየተጠበቀ ይገኛል። የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይም ወደ " ጋዛ ለመግባት ዝግጅት ላይ ነን " ማለታቸው ተዘግቧል።

በጦርነቱ ሌሎች ኃይሎች እንዳይሳተፉበት ተሰግቷል ፣ የሊባኖሱ ሄዝቦላህ " አሜሪካ እስራኤል የምትፈፅመው ጥቃት አጋር ናት " ያለ ሲሆን ለሚፈፀመው ግድያ፣ ወንጀል እና ጋዛ ላይ ለተደረገው ከበባ ተጠናቂነት አለባት ብሏል።

#አሜሪካ እና አጋሮቿ የ " ሂዝቦላህ " የታጠቀ ኃይልን " ከእስራኤል ጋር ጦርነት ውስጥ ለመግባት አትሞክር አርፈህ ተቀመጠ " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የየመኑ " ሁቲ ኃይል " አሜሪካ በቀጥታ ጦርነቱ ላይ ወታደራዊ ተሳትፎ ካደረገች ከወንድሞቻችን (ሃማስ) ጋር በመሆን ጦርነቱን እንቀላቀላለን በሚሳኤል እና ድሮን እንዲሁም በሌሎች አመራጮች የታገዘ ጥቃት እስራኤል ላይ እንከፍታለን ሲሉ ዝተዋል።

More 👉 @BirlikEthiopia

https://t.iss.one/+LM-bJ8NzZMcxMjA8
#አሜሪካ

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አንደኛ ዓመትን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

አንቶኒ ብሊንከን ምን አሉ ?

- ብሊንከን በደፈናው #ኢትዮጵያ እና #ኤርትራ ጠብ ከሚያጭሩ ድርጊቶች እንዲቆጠቡና የአካባቢውን አገራት ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ማክበር አለባቸው ብለዋል።

- የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ክልል ሙሉ ለሙሉ መውጣትን እንዳለባቸው ገልጸዋል።

- ስምምነቱን ተከትሎ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መመሥረቱን ጨምሮ የተወሰዱ በጎ እርምጃዎችን አሜሪካ እንደምትደግፍ አሳውቀዋል።

- ህወሓት ኃይሎቹ ከባድ መሳሪያቸውን ፈትተው ተዋጊዎች ማሰናበት በተጀመረበት ጊዜ በትግራይ ውስጥ ዘላቂ ሰላም ለማስፍን ተጨማሪ እርምጃዎች መውሰድ ያስፈልጋል። ለዚህም የኤርትራ ኃይሎች ሙሉ ለሙሉ መውጣት አለባቸው ብለዋል።

- ብሊንከን አሜሪካ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎችም አካባቢዎች ያሉት ግጭቶች እንደሚያሳስባት ገልጸዋል። ያለው ነገር  በቀላሉ ሊታወክ የሚችለውን የኢትዮጵያን ሰላም አደጋ ላይ እንደጣለው አመልክተዋል።

- በአገሪቱ በተለያዩ ወገኖች የቀጠለው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና ጥቃት፣ " የመርዛማ ንግግሮች " መስፋፋት በጦርነቱ ምክንያት የሳሳውን ማኅበራዊ ትስስር የበለጠ እየሸረሸረው መሆኑን ገልጸዋል። ለዚህም ፦
🔹አስተማማኝ የሽግግር ፍትሕ፣
🔹ሐቀኛ እና አካታች ብሔራዊ ምክክር በመላዋ አገሪቱ ተግባራዊ እንዲሆን እንዲሁም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚካሄዱትን ግጭቶች ለመፍታት ውይይት እንዲደረግ አስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል።

#BBC
#SecretaryofStateAntonyJBlinken

@tikvahethiopia
#TOYOTA

ቶዮታ / Toyota ዓለም አቀፍ የመኪና አምራች ኩባንያ በዓለም ገበያ በዋነኝነት #በአሜሪካ የተሸጡ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎቹን  ከገበያ ላይ እንዲሰበሰቡ አዟል።

ቶዮታ እንዲሰብሰቡ ያዘዘው ከ2020 እስከ 2022 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የተመረቱ ተሽከርካሪዎችን ሲሆን ተሽከርካሪዎቹ የ " ኤርባግ " ደህንነት ችግር አለባቸው ተብሏል።

ከ2020 እስከ 2022 ወደ ገበያ የቀረቡ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎች (በዋነኝነት #አሜሪካ) ከ " ኤርባግ " ጋር በተያያዘ ችግር እንዳለባቸው ተደርሶበታል።

ችግሩ በፊት ለፊት ተሳፋሪ መቀመጫ በኩል በስህተት ከተሰራ የ " ኤርባግ ሴንሰር " ጋር የሚያያዝ ሲሆን ምናልባትም በአደጋ ጊዜ " ኤርባጉ " አገልግሎት ላይሰጥ ይችላል። ይህ አደጋ በሚፈጠር ጊዜ ኩዳቱ እንዲጨምር ያደርጋል።

ቶዮታ የትኞቹ ሞዴሎች ይሰብሰቡ አለ ?

#ቶዮታ

ኮሮላ (2020 - 2021)
ራቭ4 ፣ ራቭ4 ሃይብሪድ (2020 - 2021)
ሃይላንደር፣ ሃይላንደር ሃብሪድ (2020 - 2021)
አቫሎን ፣  አቫሎን ሃይብሪድ (2020 - 2021)
ካምሪ፣ ካምሪ ሃብሪድ (2020 - 2021)
ሴና ሀይብሪድ (2021)

#ሌክሰስ

ES250 (2021)
ES300H (2020-2022)
ES350 (2020-2021)
RX350 (2020-2021)
RX450H (2020-2021) የተሰኙ ከ2020 እስከ 2022 ላይ የተመረቱት የ " ኤርባግ " ችግር ስላለባቸው ይሰብሰቡ ብሏል።

ከላይ የተጠቀሱት ተሽከርካሪዎች ያላቸው ሰዎች ኤርባጋቸውን #እንዲያረጋግጡ እና ችግር ካጋጠማቸው እስከ ቀጣዩ የካቲት ወር ድረስ እንዲመልሱለት ቶዮታ ጥሪ አቅርቧል።

የቶዮታ ተሽከርካሪዎች ችግር እንዳለባቸው የታወቀው የጃፓን ትራንስፖርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ ተሽከርካሪ እምራች ኩባንያዎች ላይ ባደረገው #ምርመራ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎ የቶዮታ ኩባንያ አክስዮን ዋጋ ቅናሽ አሳይቷል።

ምርመራው ከቶዮታ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ ዳይሀትሱ በተሰኘው ኩባንያ ላይም ተመሳሳይ ችግር መታየቱን ገልጿል።

ከ87 ዓመት በፊት ኪቺሮ ቶዮታ በተባለ ግለሰብ የተመሰረተው ቶዮታ የተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ አሁን ላይ በዓመት 10 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎችን በማምረት ላይ ይገኛል።

ከ360 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉት ቶዮታ ኩባንያ 300 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት እንዳለው የኩባንያው ዓመታዊ ሪፖርት ያስረዳል።

#ጥቆማ ፦ ከደህንነት ጋር በተያይዘ በተለይም በአሜሪካ እንዲሰበሰቡ የታዘዙ ተሽከርካሪዎችን ቼክ ለማድረግ https://www.nhtsa.gov/recalls በዚህ አድራሻ መጠቀም ይቻላል። የመኪናውን መለያ ቁጥር (VIN) በማስገባት ማወቅ ይቻላል።

Credit - #AlAiN / #Reuters / #Toyota_News_Room

@tikvahethiopia
#አሜሪካ

" የዋሽንግተን አጠቃላይ የመሳሪያ ሽያጭ መጠን 238 ቢሊየን ዶላር ደርሷል " ተባለ።

አሜሪካ በፈረንጆቹ 2023 ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ሽያጭ አስመዝግባለች።

" የዋሽንግተን አጠቃላይ የመሳሪያ ሽያጭ መጠን 238 ቢሊየን ዶላር ደርሷል " የተባለ ሲሆን፤  ይህም በ2022 ከነበረው የ50 በመቶ ብልጫ ማሳየቱ ተመላክቷል።

ለሽያጩ መጨመር የሩሲያ ዩክሬን #ጦርነት ከፍተኛ ድርሻ አለው የተባለ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ የአሜሪካ መከላከያ ኩባንያዎች ለውጭ ሀገራት በቀጥታ ያደረጉት ሽያጭ እንደሆነ ነው።

ፖላንድ የአሜሪካን የጦር መሳሪያ በመግዛት ቀዳሚ ሀገር እንደሆነች ለተቀናጀ የአየር እና የሚሳኤል መከላከያ የውጊያ ትዕዛዝ ስርዓትም 4 ቢሊየን ዶላር ማውጣቷ ተመላክቷል።

"አሜሪካ ለውጭ ያቀረበችው የጦር መሳሪያ ሽያጭ ባለፈው ዓመት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ሲል ፖለቲኮ ዘግቧል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን በዚህ ይከታተሉ ፦ https://t.iss.one/+LM-bJ8NzZMcxMjA8

@ThiqaMediaEth
TIKVAH-ETHIOPIA
#PurposeBlack ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ምን አለ ? - የቢጂአይ ኢትዮጵያ የዋናው መሥሪያ ቤት ሽያጭ ውልን በውልና ማስረጃ በኩል ለመፈጸም ዝግጁ ነን። - ቢጂአይ ኢትዮጵያ የመንግስትን ግዴታ ቀድሞ ባለመወጣቱ በውል እና ማስረጃ መፈራረም አልተቻለም። ከታክስ ጋር በተያያዘ ክሊራንስ አልጨረሱም። - ቢጂአይ ብዙ ማሟላት ያለበትን ዶክመንት አላሟላም። በዚህ ምክንያት በውል እና ማስረጃ ለመፈራረም…
#PurposeBlack

የፐርፐርዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አፈፃሚ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ በአሁን ሰዓት #አሜሪካ ሀገር እንደሚገኙ ተነግሯል።

" አሜሪካ የሚገኙት ለስራ ነው " ያለው ድርጅቱ የፊታችን ሀሙስ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱና መግለጫም እንደሚሰጡ አመልክቷል።

ዛሬ መግለጫ ሰጥተው የነበረው የድርጅቱ የቦርድ አባል እና የህግ አማካሪ ዶ/ር ኤርሚያስ ብርሃኑ ናቸው።

ፐርፐዝ ብላክ ከቤቶቹ ግንባታ እና ከአክሲዮን ባለቤቶች ጋር በተያያዘ ምን አለ ?

- ለቤቶች ግንባታ ሌላም መሬት መግዛቱን ገልጿል።

- አሁን በገባው ቃል መሰረት ቤቶቹን በሚቀጥሉት 5 አመታት ሰርቶ እንደሚያስረክብ አመልክቷል። 

- " #ወሰን " አካባቢ ለቤቶች ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተጥሏል ብሏል።

- የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያን አክሲዮኖች የገዙ ዜጎች ብራቸው #እንደማይመለስ ገልጿል። ነገር ግን ባለ አክሲዮኖች አክሲዮናቸውን መሸጥ ይችላሉ ብሏል።

- በአሁኑ ሰዓት ድርጅቱ ለ1 ሺ ባለ አክሲዮኖች የአክሲዮን ሽያጭ ካደረገ በኋላ የአክሲዮን ሽያጭ ማቆሙን ገልጿል።

- በተለዩ ቦታዎች መሬት እና ንብረትን ከግለሰቦች በመግዛት ፣ መሬት እና ንብረቱን አፍርሶ በመስራት እና ከባለሃብት ጋር አብሮ በማልማት በ3 አማራጮች ግንባታ ለመጀመር የሚጠቀማቸው አማራጮች መሆናቸውን አሳውቋል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
#ኢራቅ

የኢራቅ ፓርላማ #ግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል።

በአዲሱ ሕግ መሠረት ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት ሊታሰሩ ይችላሉ።

በአዲሱ ሕግ ፦

➡️ የግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤

➡️ ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ፤

➡️ ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና የሚያደርጉ ዶክተሮችን፤

➡️ " ሆን ብለው " እንደ #ሴት የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ።

የሕጉ ዓለማ ፥ " የኢራቅን ማህበረሰብ ከሞራል ዝቅጠትና ግብረ ሰዶማዊነት ከሚያደርሰው አደጋ ለመጠበቅ ነው " ተብሏል።

ረቂቁ መጀመሪያ ላይ ግብረሰዶማውያን #በሞት እንዲቀጡ የሚል የነበረው ቢሆንም በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ተቃውሞ መሻሻሉ ነው የተሰማው።

የኢራቅ ፓርላማ አባል የሆኑት አሚር አል-ማሙሪ ፥ " አዲሱ ሕግ #ኢስላማዊ እና ማህበረሰባዊ እሴቶችን የሚቃረኑ ልዩ ጉዳዮችን ለመዋጋት ትልቅ እርምጃ ነው " ብለዋል።

#አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መ/ ቤቷ በኩል ሕጉን ፤ " ለሰብአዊ መብትና ነፃነት ጠንቅ ነው " በማለት ሕጉን ተቃውማለች።

" ሕጉ የኢራቅን ኢኮኖሚ የሚያቀዛቅዝ እና የውጭ ኢንቨስትመንትን የመሳብ አቅምን ያዳክማል" ብላለች።

የምዕራቡ ዓለም ሀገራት ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም ሕጉን ተቃውመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ምንጮች #ቢቢሲ እና #ሮይተርስ መሆናቸውን ይገልጸል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢራን የሂሊኮፕተር አደጋ የሞቱት እነማን ናችው ? - የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ - የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚር አብዶላሂያን - የተብሪዝ መስጂድ ኢማም አያቶላህ አልሃሸሚ - የምስራቅ አዘርባጃን ግዛት አስተዳዳሪ ማሊክ ራህማቲ - የፕሬዝዳንቱ ጥበቃ ኃላፊ ማሄዲ ሙሳቪ - የሄሊኮፕተሩ አብራሪ፣ - የሂሌኮፕተሩ ረዳት አብራሪ - ቦዲጋርድ - የበረራ አስተናጋጅ በትላንቱ የሂሊኮፕተር…
#ኢራን

" ...አሜሪካ በአቪየሽን ዘርፍ ላይ የጣለችው ማዕቀብ ለአደጋው መንስዔ ነው " - ሙሐመድ ጃቫር ዛሪፍ

የኢራን የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሙሃመድ ጃቫር ዛሪፍ ፣ የኢራን ፕሬዝዳንት እና ሌሎች ከፍተኛ የኢራን ባለስልጣናት ላይ ለደረሰው የሄሊኮፕተር አደጋ አሜሪካን ተጠያቂ አድርገዋል።

ሙሃመድ ጃቫር ዛሪፍ ፣ " #አሜሪካ በአቪየሽን ዘርፍ የጣለችው ማዕቀብ ለአደጋው መንስዔ ነው " ብለዋል፡፡

ከኢራን ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ደረጉት ዛሪፍ ፣ " ማዕቀቡ ኢራን #አዳዲስ የአቪየሽን ምርቶችን መግዛት እንዳትችል አድርጓታል " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ጥሩ የሚባል ግንኙነት እንደሌላት ይታወቃል።

ትላንት የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ እና ሌሎች ባለልስጣናት ግድቦችን መርቀው ከከፈቱ በኋላ ወደ ታብሪዝ እያመሩ ሳሉ የነበሩበት ሂሊኮፕተር ከተራራ ጋር ተጋጭቶ ሁሉም ህይወታቸው አልፏል።

አደጋው በደረሰበት አካባቢ ላይ እጅግ አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ እንደነበርም ተገልጿል።

More ➡️ @thiqaheth
#አሜሪካ

ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ ፤ በሉዊዚያና ግዛት ከታች አንስቶ እስከ ዩኒቨርሲቲ ባሉ በሁሉም የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ አስርቱ ትዕዛዛት እንዲለጥፉ ታዟል።

ትላንት ደግሞ የኦክላሆማ ግዛት በአስቸኳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንዲጀመር አዟል።

የግዛቱ ትምህርት ቢሮ በግዛቱ ያሉ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች መጽሐፍ ቅዱስን በትምህርት ስርዓታቸው በአስቸኳይ እንዲያካትቱና እንዲያስተምሩ መመሪያ አስትላልፏል።

በግዛቱ የትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ ሪያን ዋልተርስ የተላከ መመሪያ " አፋጣኝ እና ጥብቅ ተፈጻሚነትን " የሚፈልግ አስገዳጅ ድንብ ነው ይላል።

ዋልተርስ " መጽሐፍ ቅዱስ ታሪካዊና ባህላዊ መሠረት ነው "  ብለዋል።

" ያለ መጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ እውቀት የኦክላሆማ ተማሪዎች የአገራችንን መሠረት በትክክል መረዳት አይችሉም " በማለት ነው በአስቸኳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንዲሰጥ መታዘዙን ያመለከቱት።

በግዛቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ይተገበራል።

ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ እያንዳንዱ ክፍል መጽሐፍ ቅዱስ ሊኖረው ይገባል ተብሏል። ሁሉም አስተማሪዎች በክፍሉ ውስጥ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ማስተማር እንዳለባቸው ታዟል።

የሲቪል መብት ተሟጋች ድርጅቶች ግን ይህንን ውሳኔ ተቃውመዋል።

ሃይማኖት እና መንግሥት መለያየት አለባቸው ብለዋል።

አንድ መንግሥትን ከሃይማኖት መለያየት እንዳለበት የሚሰራ ተቋም ፥ " የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ሰንበት ትምህርት ቤቶች አይደሉም " ብሏል።

" ሪያን ዋልተርስ የተሰጠውን የመንግሥት ስልጣንን አላግባብ በመጠቀም ሃይማኖታዊ እምነቱን በሌሎች ላይ ለመጫን እየተጠቀመበት ነው። ይህ እኛ ባለንበት ሊሳካ አይገባም " ብሏል ተቋሙ።

በአሜሪካ የሃይማኖት ነፃነትን ለማስጠበቅ የሚሰራው ኢንተርፌይዝ አሊያንስ ፤ " መመሪያው ግልጽ በሆነ መልኩ ሃይማኖትን መጫን ነው " ሲል ገልጾታል።

" እውነተኛ የእምነት ነፃነት ማለት የትኛውም የሃይማኖት ቡድን አመለካከቱን በሁሉም አሜሪካውያን ላይ እንዳይጭን መከላከል ነው " ብሏል።

#BBC #CNN

@tikvahethiopia