#EomMarket
አዲሱን የአዳማ ቅርንጫፍ በማስመልከት ሁሉም እቃዎች ላይ ልዩ ቅናሽ አድርገናል!
ETHIO ONLINE MARKET
☎️ 0929181818 / 0909868788
ይምጡ የሽያጭ ማእከሎቻችንን ይጎብኙ፤ ተደስተው ይመለሳሉ !
https://t.iss.one/EOMMarket
አድራሻችን፦
•ቁጥር 1:- መገናኛ, ቤተልሄም ፕላዛ
የሱቅ ቁጥር G-10 ( ግራውንድ )
•ቁጥር 2:- ሜክሲኮ, ኬኬር ህንፃ
የሱቅ ቁጥር #338
•ቁጥር 3:- አዳማ , German City
Mall, Ground G-27
𝕵𝖔𝖎𝖓 𝖔𝖚𝖗 𝖈𝖍𝖆𝖓𝖓𝖊𝖑 https://t.iss.one/EOMMarket

September 21, 2023
" አምቡላንስ ተሽከርካሪያችን በኃይል ተወስዷል " - ቀይ መስቀል
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አምቡላንስ ተሽከርካሪው በኃይል እንደተወሰደበት አሳወቀ።
ማኅበሩ ፤ የምዕራብ ጎጃም ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ንብረት የሆነ ማኅበሩ ለሰብዓዊ አገልግሎት የሚጠቀምበት ታርጋ ቁጥሩ " ET05-01107 " አምቡላንስ ተሸከርካሪ መስከረም 08 ቀን 2016 ዓ.ም ማንነታቸው ባልታወቁ የታጠቁ ኃይሎች እንደተወሰደ ገልጿል።
አምቡላንስ ተሸከርካሪው የተወሰደው በፍኖተ ሰላም ከተማ ከሚገኘው የቅርንጫፉ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲሆን የተወሰደውም በአስገዳጅ ሁኔታ ነው ብሏል።
ይህ ድርጊት ኢትዮጵያ የፈረመችውን ዓለም አቀፍ የጄኔቫ ሥምምነቶችን የሚፃረርና ከማህበሩ ዓላማ ውጪ መሆኑን ገልጿል።
ድርጊቱን የፈፀሙት አካላት አምቡላንሱን ለማህበሩ በመመለስ ለማኅበረሰቡ የተለመደውን ሰብዓዊ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል እንዲያሰርጉ ጠይቋል።
በመላው ሀገሪቱ በሰብዓዊ አገልግሎት የተሰማሩ የቀይ መስቀል ሠራተኞችና በጎፈቃደኞች እንዲሁም አምቡላንሶችና ሌሎች ተሽከርካሪዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉ፣ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ፣ ታጣቂ ኃይሎች ከእንደዚህ አይነት ድርጊት እንዲቆጠቡና ማኅበረሰቡም መሰል ድርጊቶችን እንዲያወግዝ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጠይቋል።
@tikvahethiopia

#አማራ
በአማራ ክልል ፤ ሰሜን ሸዋ ዞን ከ88,000 በላይ ለሚሆኑ ተፈናቃዮች የድጋፍ እጥረት ማጋጠሙ ተገልጿል።
በአማራ ክልል ደብረ ብርሃን፣ ሰሜን ሸዋ በመጠለያ ካምፓችና ከመጠለያ ውጪ በዘመድ ወዳጅ ቤት ተጠልለው ለሚገኙ ከ88,000 በላይ ተፈናቃዮች የድጋፍ እጥረት ማጋጠሙን የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ገልጿል።
እጥረቱ ያጋጠመው፣ በግጭት ምክንያትና መንግሥት የሚሰጠው ወርሀዊ ድጋፍ ገና ባለመሰጠቱ ነው ተብሏል።
" ከግጭቱ ጋር ተያይዞ የሚደግፉ አካላት እንደልባቸው ገብተው መደገፍ አልቻሉም " ሲሉ የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ቡድን መሪ አቶ ደረጀ ይነሱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
" አሁን የድጋፍ እጥረት አለ። ሁለተኛ ደግሞ አሁን የመስከረም ወር ድጋፍ ራሱ ማግኘት አለባቸው። የመስከረም ወር ድጋፍ ገና አልገባም። እየጠበቅን ነው " ብለዋል።
" በአብዛኛው ሰሜን ሸዋ ወረዳ ላይ በግጭት የተሞላ ስለሆነ ከኅብረተሰቡም ድጋፍ ማሰባሰብ አይታሰብም " ያሉት አቶ ደረጀ፣ " በመንግሥት የሚሰጠው የመስከረም ወር ድጋፍ እስካሁን መድረስ ነበረበት። ገና እየጠበቅን ነው " ሲሉ አስረድተዋል።
ድጋፉ እንዲገኝ ምን እየተደረ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ደረጀ ፣ " በእኛ በኩል ያለውን ነገር ችግሩን ለመንግሥት ማሳወቅ ነው። አሳውቀናል " ብለዋል።
በሌላ በኩል ፤ በመጠለያ ካምፕ ያለ ዕድሜ ጋብቻ መፈጸሙ፣ የሥጋ ዝምድና የሌላቸው ወንድና ሴት ተፈናቃዮች አንድ ላይ በመኖራቸው የመደፈር ጥቃት ይፈጸማል የሚል ሥጋት እንዳለ ተመላክቷል።
ያለ ዕድሜ ጋብቻን በተመለከተ አቶ ደረጀ በሰጡት ማብራሪያ፣ " ወይንሸት መጠለያ ካምፕ ዕድሜዋ 15 የሆነች ልጅ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ተፈጽሞ ነገሩ በፓሊስ ጣቢያ ተይዟል " ብለዋል።
አክለውም፣ " ባቄሎ መጠለያ ካምፕ ላይ ግን ሁለት ወንዶችና አንዲት ሴት (አባውራዎች ማለት ነው) በአንድ ቤት ውስጥ እንዲኖሩ ተደርገው ሴቷ ቀን ቀን እዚያው ቤት ትውላለች፣ ማታ ማታ ደግሞ ሌሎች ጓደኞቿ ጋ እየሄደች ነው የምታድረው። ይሄ ነገር ለመደፈር ጥቃት ሊያጋልጥ የሚችል ነው " ሲሉ ሥጋታቸውን ገልጸዋል።
ችግሩን ለመቅረፍም፣ በተለይ ቤተሰብ ያልሆኑ ሰዎች በአንድ ሼድ ውስጥ መቀመጥ በተለይ ባቄሎ መጠለያ ካምፕ የሥጋ ዝምድና የሌላቸውና አብረው የሚኖሩ ሰዎችን መለየት ያስፈልጋል የሚል ሀሳብ እንዳለ ጠቁመዋል።
" በእርግጥ ችግሩ በርካታ ነው። አንዳንዱ አንለይም የሚል አለ። በሌላ መልኩ ደግሞ የመጠለያ ችግርም ለመለየት የሚያመች አይደለም " ብለዋል።
በደብረ ብርሃን በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ከ25,000 በላይ፣ በሰሜን ሸዋ በሚገኙ የመጠለያ ካምፖች ከ63,000 በላይ በአጠቃላይ በሰሜን ሸዋ ዞን ከ88,000 በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ ተብሏል።
መረጃው የቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ አባል ነው።

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ #መርዶ
ደም አፋሳሹና አስከፊው የትግራይ ጦርነት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መቆሙን ተከትሎ የመርዶ አነጋገር በዘፈቀደ እየተካሄደ ነው በሚል መርዶውን በሚጠባብቁ ቤተሰቦችና በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ አስነስቷል።
የህዝቡን ቅሬታ ተከትሎ በተለያዩ ሚኒስትሪሚንግ ሚድያዎችና በማህበራዊ የትስስር ገፆች በርካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው።
ይህ ርእሰ ጉዳይ ሰፊ የመወያያ አጀንዳ ሆኗል። የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር የህዝብ ቅሬታዎች አንብቦና አድምጦ በጊዜ ሰሌዳ ያልተቋጨ " ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቂያለው '' ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በመርዶ አነጋገር ዙሪያ የሚነሱ የህዝብ ቅሬታዎችና የግዚያዊ አስተዳደሩ ምላሽ እንዲህ አቀናጅቶታል።
ዘመንፈስ ቅዱስ ዮሃንስ ፣ ክንፈ ሓዱሽ ፣ ወልዳይ ረታ ካሕሳይ ፣ ኣታኽልቲ ደጀኔ የተባሉት የትግራይ ክልል ነዋሪዎች በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባጋሩት አስተያየት " ታጋዮቹ ለትግራይ ህዝብ ድህንነት ሲሉ ክቡር መስዋእትነት ከፍለዋል " ያሉ ሲሆን ፣ የመርዶው አነጋገር ስነ-ሰርአት መንግስት በእቅድና በሚድያ በከፍተኛ ትኩረት ሊመራው ይገባል ብለዋል።
አስተያየት ሰጪዎቹ ፤ " ከልጆቻቸው ፣ ባልና ፣ ሚስቶቻቸው ለሁለት አመት ገደማ ሳይገናኙ በመቅረታቸው በአስከፊው ጦርነት ተሰውተዋል በሚል ዛሬ ነገ ይነገረናል በሚል እንቅልፍ ያጡት ቤተሰቦች መንግስት ቅጥ ባለው መንገድ በአጭር ጊዜ በመንገር እርማቸው እንዲያወጡ ማድረግ ይጠበቅበታል " ብለዋል።
ረዳት ፕሮፌሰር ክንፈ ተስፋይ የተባሉ ምሁር መንግስት መርዶው ከመንገሩ በፊት ፦
✔ መርዶ የሚነገረው የአእምሮ ዝግጅት እንዲያደርግ፤
✔ መርዶው ሲነገር እነማን መኖር እንዳለባቸው፤
✔ ልጆች የመርዶው ስሜት እንዳይጎዳቸው ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ፤
✔ መርዶው የሚነግር ሰው የተረጋጋና ከጭንቀት ሰሜት የራቀ መሆን እንዳለበት፤
✔ መርዶው በጠዋት እንዲከናወን፤
✔ ከመርዶው በኃላ ረጅም ጊዜ በሃዘን መቀመጥ ላልተፈለገ ስሜት ስለሚያጋልጥ ለቀናት መሆን እንዳለበት፤
የመሳሳሉ በሚድያ የተደገፉ የስነ-ልቦና ዝግጅቶች ማድረግ ተገቢ እንደሆነ መክረዋል።
የግዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ ከቀናት በፊት ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ዞንና ወረዳ አስተዳዳሪዎች ጋር በነበራቸው ስብሰባ እንዲሁም በጦርነቱ የተጎዱ አባላት እንክብካቤ ማእከል በይፋ ሲያስጀምሩ ስለ መርዶ ተናግረዋል ፦
" ... በመንግስት ደረጃ መርዶው ከመረጃ አሰባሰብና ከሪሶርስ በማያያዝ ነው እስከ አሁን ያዘገየነው። አሁን መረጃው አጠናቅረን ጨርሰናል የተሰውት ታጋዮች የተሟላ መረጃ ይዘናል። በዚህ በኩል የቀረ ነገር የለንም።
ባለፈው ሃምሌ ወር መርዶው እንዲነገር አቅድን ከክረምት የእርሻ ስራዎች እንደይጋጭ ብለን ነው ያቆየነው። ዋና ነገር ካለን የገንዘብ ሪሶርስ ነው ያያዝነው። መርዶ ነገረህ ለተጎዳ ቤተሰብ ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል። አሁንም ቢሆን ለድጋፍ የሚሆን የጠበቅነው ሪሶርስ አላገኘንም። ስለዚህ ከአሁን በኃላ ሪሶርስ እስከሚገኝ ብለን አንጠብቅም ።
መርዶ የሚነገራቸው ቤተሰቦች ድጋፍ እንደሚገባቸውና እንደሚደረግላቸው በማመን ቶሎ ብለን እናደርገዋለን ። ስለሆነም የተሰውት ታጋዮች በቀርቡ ክብራቸው በሚመጥን መልኩ ለቤተሰቦቻቸው መርዶ የመንገር ስነ-ስርአት ይቀጥላል..." ብለዋል ።
ፕረዚደንቱ አቶ ጌታቸው ረዳ ይህን ይበሉ እንጂ ይፋዊ ያልሆነ መርዶ የመንገር ሂደት ትግራይ ውስጥ እየተካሄደ እንደሆነ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ታዝቧል።
ትግርኛ - @tikvahethiopiatigrigna

#GoogleMaps
" ጉግል ማፕ " ፊሊፕ ፓክሰን የተባለ ግለሰብን በፈረሰ ድልድይ ላይ እንዲያሽከረክር በማመላከቱ ህይወቱን አጥቷል ያሉ ቤተሰቦች ጉግል ላይ ትላንት ክስ መሰረቱ።
በአሜሪካ ሰሜን ካሊፎርኒያ ግዛት ነው ክስተቱ የተፈጠረው።
የሟች ቤተሰቦች ጉግል #ወቅታዊው የስፍራውን ሁኔታ ባለመጠቆሙ የቤተሰባቸውን አባል መስከረም ወር ላይ ህይወቱ እንዲቀጠፍ ምክንያት ሆኗል በሚል ነው ወደ ፍርድ ቤት ያመሩት።
የፊሊፕ ፓክሶንስ ቤተሰቦች እንዳሉት " ጉግል ማፕ " በቸልተኝነት ከዛሬ 9 ዓመት በፊት ከአግልግሎት ውጪ የሆነ ድልድይን ማመላከት ባለመቻሉ ፓክሶን ህይወቱን አንጥቷል።
የሁለት ልጆች አባት የሆነው ፓክሰን ሴት ልጇቹን የጓደኛቸውን ልደት እንዲያከብሩ ወደ ቤቷ ወስዷቸው እየተመለሰ ሳለ ነበር አደጋው ያጋጠመው። ቤተሰቦቹ እንደመሰረቱት ክስ ከሆነ ፓክሰን #ለአካባቢው_አዲስ_ነበር።
ባለቤቱ ቀደም ብላ ልጇቿን ይዛ ስታሽከርክር እሱ ወደኋላ ቀርቶ የነበረ ሲሆን አካባቢውን ስለማያውቀው ጉግል ማፕን እየተከተለ ሲያሽከረክር ከ9 ዓመት በፊት በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት የፈረሰ ድልድይ ላይ ለማሽከርከር ሲሞክር ባጋጠመው አደጋ ህይወቱ አልፏል።
የአከባቢው ነዋሪዎች እ.ኤ.አ በ2013 የፈረሰውን ድልድይ በተመለከተ ያለውን መረጃ እንዲያስተካክል " ጉግል " ን በተደጋጋሚ መጠየቃቸውን ጉግል ላይ በተመሰረተው የክስ መዝገብ ላይ ሰፍሯል።
ክሱ ላይ ወደ ድልድዩ የሚወስደውን መንገድ የሚዘጉ ብረቶች መጥፋታቸው ተመላክቷል። ድልድዩን የመጠገን ኃላፊነት አለባቸው የተባሉ ሶሰት ተቋማት ላይም ክስ ተመስርቷል።
የጉግል ቃል አቀባይ የቀረበውን ክስ ኩባንያው እየተመለከተው እንደሆነ ተናግረዋል። ተቋሙ ለሟች ቤተሰቦች ሃዘን እንደተሰማው ገልጿል።
መረጃው የቢቢሲ እና ኤፒ ነው።

ካርድዎን ሳያስገቡ፤ ገንዘብዎን ያውጡ!
****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካርድዎን ኤቲኤም ማሽን ውስጥ ሳያስገቡ በማስጠጋት ብቻ
የይለፍ ቁጥርዎን አስገብተው ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ፡፡
የያዙት ካርድ እና ATM ማሽኑ ያለንክኪ እንደሚሠሩ የሚያሳየውን የሞገድ ምልክት (የዋይፋይ ምልክት) ልብ ይበሉ፡፡
#CBE #ATM #contactlesscards
#DigitalBanking #Ethiopia

" ወጪያቸው በመንግሥት የሚሸፈንላቸውን ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ሰጥተን እንቀበላለን " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ትምህርት ሚኒስቴር ከሚያስቀምጠው የመቁረጫ ነጥብ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል መገለጹ ይታወቃል፡፡ በሀገሪቱ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሆነው ዩኒቨርሲቲው፣ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን የሚቀበልበት መስፈርት…
#AAU
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሽግግር ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ በነባሩ አሰራር እንደሚቀጥል ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ተናግረዋል።
በዚህም የ2016 የትምህርት ዘመን ተማሪ ቅበላ ከዚህ ቀደም በነበረው ነባሩ ስርአት የሚከናወን ሲሆን ፤ አዲስ አሰራሮች ከመጡ በየጊዜው ይፋ እንደሚደረግ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አሳውቀዋል።
@tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሽግግር ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ በነባሩ አሰራር እንደሚቀጥል ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ተናግረዋል።
በዚህም የ2016 የትምህርት ዘመን ተማሪ ቅበላ ከዚህ ቀደም በነበረው ነባሩ ስርአት የሚከናወን ሲሆን ፤ አዲስ አሰራሮች ከመጡ በየጊዜው ይፋ እንደሚደረግ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አሳውቀዋል።
@tikvahethiopia
September 21, 2023
" የቀበሌ መታወቂያ ካላመጣችሁ እርዳታ አታገኙም ተብለናል " - ተፈናቃዮች
ከኦሮሚያ እና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተፈናቅለው በባሕር ዳር ከተማ አካባቢ የሚኖሩ ተፈናቃዮች የ " ቀበሌ መታወቂያ " ካላመጣችሁ እርዳታ አታገኙም በመባላቸው መቸገራቸውን ገለፁ።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የእርዳታ ድግግሞሽን ለመቀነስ ለባህር ዳር ተወላጅ ተፈናቃዮች ብቻ እርዳታ እንደሚሰጥ አመልክቷል። ሌሎችም ወደ ትውልድ ቀያቸው በመሄድ እርዳታ ሊያገኙ እንደሚችሉም ገልጿል።
ከ30 ዓመት በላይ ከኖሩበት ኦሮሚያ ክልል እንደተፈናቀሉ የገለፁ አንድ ተፈናቃይ " ንብረታችን ትተን፣ ህይወታችን ይዘን አገር አቋርጠን መጥተን አስፈላጊው እገዛ አልተደረገልንም " ብለዋል፡፡
ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ ተፈናቃይ ፤ በተመሳሳይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ነዋሪነት መታወቂያ ቢኖራቸውም " የባህር ዳር ከተማ መታወቂያ ስለሌለኝ እርዳታ አላገኘሁም " ብለዋል፡፡
የባህር ዳር መታወቂያ ባይኖረንም መንግስት እንደ ኢትዮጵያዊ ዜግነታችን ሊረዳን ይገባል ሲሉ ነው ተፈናቃዮቹ የተናገሩት፡፡
በተፈጠረው ችግር ምክንያት እርዳታ ካገኙ ወራት መቆጠራቸውን ነው ተፈናቃዮቹ በምሬት የሚናገሩት፡፡
ጉዳዩን በተመለከተ አንድ የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ስራ ኃላፊ ፤ ተፈናቃዮች ወደ ትውልድ ቦታቸው እየሄዱ እርዳታ እንዲወስዱ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቁመው ኮሚሽኑ የቀበሌ መታወቂያ የማደል ኃላፊነት ግን እንደሌለው ተናግረዋል፡፡
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አስራት ሙጨ ለፀጥታ ሲባል በአንድ ወቅት መታወቂያ መሰጠቱን ጠቁመው ሆኖም አሁን ያ እንደማይሰራ፣ ግን ደግሞ ተፈናቅለው ከሚመጡበት ክልል መታወቂያ ላይ ትውልድ ቦታቸው " ባሕር ዳር "ለሆኑ ተፈናቃዮች እርዳታው ይሰጣል፣ ሌሎችም በየትውልድ ቦታቸው ሄደው እርዳታ ማግኘት ይችላሉ ብለዋል።
መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

" ፈተናውን 98.6 በመቶ ተማሪዎች አልፈዋል "
በትግራይ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 98.6 ከመቶ ወደ ቀጣዩ ክፍል ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
ኮሮና ተከትሎ በትግራይ በተካሄደው ጦርነት ተቋርጦ የነበረው የመማርና የማስተማር ሂደት ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ በተሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በመውሰድ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎች ውጤታቸዉ ይፋ ሆኗል።
በትግራይ ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራትና ምዘና ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዳይሬክቶሬት አቶ ክንፈ ፍስሃ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከተፈታኞቹ 98.6 በመቶ ወደ ቀጣይ ክፍል ተሸጋገረዋል።
የነበረውን ክፍተት ለሞምላት የተሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በቂ ባለመሆኑ በ2016 ዓ.ም ለ9ኛ ክፍል ተማሪዎች በሚሰጠው ትምህርት ፤ ሁሉም መምህራንና የሚመለከታቸው አካላት ልዩ ትኩረት በመስጠት ተማሪዎቹ ለማብቃት ጥረት ማድረግ አለባቸው ብለዋል ዳይሬክተሩ።
በተያያዘ በክልሉ ትምህርት ቢሮና የፌደራል መንግስት ቅንጅት ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ መሆኑንና አገር አቀፍ ፈተና ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 2/2016 ዓ.ም እንደሚወስዱ ከትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
መረጃውን የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው ያደረሰን።

#InternationalDayofPeace
ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ የ " ሰላም ቀን " ነው።
እንደ ተባበሩት መንግሥታት እወጃ በየዓመቱ ይህ ቀን ማለትም መስከረም 21 እኤአ " የዓለም የሰላም ቀን " እየተባለ ይከበራል።
ኢትዮጵያ እና ሰላም ?
ያለፉት ዓመታት በሀገራችን #ኢትዮጵያ የሰላም እጦት በተለይ በግጭት ተሳታፊ ባልሆኑ ወገኖች ላይ ያሳረፈውን ጠባሳ ፣ በንፁሃን ላይ ማንነትን መሰረት አድርጎ በሚፈፀም ግድያና ማፈናቀል፣ ማሳደድ ምን አይነት አስከፊ ነገር እንደደረሰ ይታወቃል ፤ በተደጋጋሚም ተገልጿል ፤ ባይገለፅም ሁሉም ያውቀዋል።
ዛሬም ግን በጦርነት እና ግጭት ውስጥ ሆነው ሰላም እና ዘላቂ መረጋጋት እንዲሁም የወደፊት ብሩዕ ተስፋ የጠማቸው ዜጎች እልፍ አእላፍ ናቸው።
ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንዳልነው ዛሬም የምንለው ፤ በሰላም እጦት ከምናንም በላይ እየሚሰቃዩት ምንም ፖለቲካ የማያውቁ ታዳጊዎች፣ ህፃናት፣ ሴቶች ፣ አረጋውያን ፣ አዛውንቶች ፣ ታማሚዎች ናቸው።
በተለይ ተደጋጋሚ ግጭት በሚያስተናግዱ የሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ እነዚህ ወገኖች ምን ያህል የስቃይ ኑሮ እንደሚገፉ ለማሰብ ይከብዳል።
ህፃናትና ታዳጊዎች በከባድ ማሳሪያ ድብደባ ድምፅ፣ በተኩስ ልውውጥ፣ በሰዎች አስክሬን፣ ለቅሶና ዋይታ ውስጥ የሚያሳልፉት ህይወት ምን ያህል የከበደ እንደሆነ ማሰብ ቀላል ነው።
የህፃናቱን ጉዳይ ብናነሳ ፦ ትንሽ ድምፅ ሰምተው ከእንቅልፍ የሚነቁ ፣ የቤተሰብ ጭቅጭቅና ጩኸት የሚያስደነግጣቸው ፤ የከባባድ መሳሪያ ድምፆችን ሲሰሙ ምን ያህል እንደሚጎዱ መገመት ይቻላል። በተላይም ልጅ ያለው በደንብ ያውቀዋል።
ተማሪው ሰላም በመጥፋቱ ከትምህርት ገበታ መቅረቱ ፣ ከገዛ ቄዬው ተፈናቅሎ ሜዳ ላይ ያሉት ታዳጊዎች ፣ ተደፍረው ህይወታቸው የተመሰቃቀለ ሴቶች፣ ህክምና መድሃኒት አጥተው በህመም የሚሰቃዩ ወገኖች ከምንም በላይ በግጭት ፣በጦርነት ፣ በጥላቻ እና በመከፋፈል ውስጥ የሚያድገው ከታች ያለው ትውልድ ነገ ስለሀገሩና ስለህዝቡ ምን አይነት አመለካከት እንደሚቀረፅበት ለመግመት አያዳግትም።
በእርግጥ ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው ፤ የሰላም ዋጋ የሚታወቀውም ስናጣት ብቻ ነው ፤ ነገር ግን ሰላም ዛሬ ካልተሰራባት ነገ አትኖርም።
በዛሬው ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ማለት የሚቻለው ፦ ሰላምን ሊያደፈርስ የሚችልን ጉዳይ ቀድሞ በማወቅ ማስተካከል ፣ ህዝብን ማድመጥ፣ ዜጎችን ማክበር ፣ ሰው እንዳይሞት እንዳይፈናቀል ማድረግ፣ ዜጎችን እርስ በእርስ እንዲጠላሉ ከሚያደርግ ማንኛውም ቅስቀሳ መቆጠብ ፣ ችግር ሲኖር ከሴራ በነፃ መልኩ ቁጭ ብሎ ለመነጋገር ዝግጁ መሆን ፣ እርስ በእርስ በመከባበር ፣ የግጭት በሮችን ቀድሞ መዝጋት ሲቻል ያኔ ሰላም የፀናች ትሆናለች።
በዚህ ውስጥ እያንዳንዱ ዜጋ የአንዱ ጉዳት ፣ የአንዱ ሰላም ማጣት የሱ መሆኑን በማወቅ ዛሬ እሱ ሰላም መሆኑን ሳይሆን ነገን በማሰብ ስለ ሰላም ጥቅም ባገኘው አጋጣሚ መስበክ አለበት።
" ሰላም ! ሰላም ! " ስለተባለ ብቻ ሰላምን ማረጋገጥ አይቻልምና ለነገ ሰላም ዛሬ መስራት ያስፈልጋል።
#TikvahEthiopia #InternatioalPeaceDay

አቢሲንያ ባንክ ከወገን ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ Wegen Technology Solutions ጋር በመተባበር ወደ አገር ወስጥ ገንዘብ ማስተላለፍን ለማቀላጠፍ የተዘጋጀውን “Wegensend” የተባለውን ድረ-ገፅ ይፋ አድርጓል።
ይህ ድረ-ገፅ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ቤተሰቦቻቸውን እና ወዳጆቻቸውን ለመደገፍ ገንዘብ የሚልኩበትን መንገድ ያለምንም ክፍያ፣ አስተማማኝ እና ምቹ በሆነ መልኩ በማዘጋጀት የቀረበ ነው።
በቅርቡም ድረ-ገጹ በመተግበሪያ(APP) በአንድሮይድና አይኦኤስ ይቀርባል ፣ ይህም በተለያዩ አማራጮች በመገኘት ለብዙ ተጠቃሚዎች ተደራሽነትን ያረጋግጣል።
ገንዘብ የተላከላቸው ደንበኞች ገንዘባቸውን በአቢሲንያ ባንክ ሒሳባቸው እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ መቀበል የሚችሉባቸው አማራጮች ተመቻችትዋል።
የሀገራችንን ገንዘብ ዝውውር መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት እና የዳያስፖራው ማህበረሰብ በብዛት ሊጠቀምባቸው የሚችላቸውን አገሮች በመለየት ካናዳ፣ እስራኤል፣ ጣሊያን፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ስዊድን፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ (አሜሪካ) በወገን ሴንድ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ የሚላክባቸው አገሮች ናቸው።
ወደፊትም ብዙ አገሮችን ለመሸፈን እየተሠራ ሲሆን፣ አሁን ባለው የሥራ ፈቃድ ተጠቃሚዎች በአንድ ወር እስከ አምስት የሚደርሱ ግብይቶችን በማድረግ ለጓደኞቻቸው ወይም ለቤተሰባቸው በወር ውስጥ እስከ 1000 ዶላር መላክ ይችላሉ።
የአገልግሎት ክፍያው ነጻ መሆኑ ወገን ሴንድን ከአብዛኞቹ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶች የተለየ ያደርገዋል፡፡ ስለ ወገን ሴንድ (Wegensend) የበለጠ ለማወቅ ፡ [www.wegensend.com] [ድረ-ገጽን] ይጎብኙ።

September 22, 2023