TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.46K videos
209 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በዓሉ #በሰላም ተጠናቋል " - ግብረ ኃይሉ

የ2016 የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል የገዳ ስርአቱን በጠበቀ መልኩ #በሰላም መከበሩን የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል።

ግብረ ኃይሉ ፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ተገኝተውበታል ያለድ የዘንድሮው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በሰላም ተከብሮ #መጠናቀቁን ገልጿል።

የነገው የሆራ አርሰዴ ኢሬቻ በዓለም በተመሳሳይ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ህብረተሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ እና ለፀጥታ ኃይሉ እገዛውን እንዲያጠናክር ተጠይቋል።

@tikvahethiopia
ቪድዮ፦ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በረራ ላይ ሳለ #መስኮቱ_መገንጠሉን ተከትሎ አንድ የአሜሪካ አየር መንገድ አውሮፕላኑን ከበረራ አግዶታል።

የአሜሪካው አላስካ አየር መንገድ በቁጥር 65 የሆኑ 737 ማክስ 9 አውሮፕላኖቹን አግዷል።

እገዳው በበረራ ወቅት የአንደኛው አውሮፕላን መስኮት ተገንጥሎ አውሮፕላኑ በአስቸኳይ ለማረፍ ከተገደደ በኋላ ነው።

አርብ ዕለት በኦሬጎን ግዛት ከፖርትላንድ ከተማ ተነስቶ ወደ ካሊፎርኒያ ሲበር የነበረው አውሮፕላን የገጠመውን አደጋ ተከትሎ ከ35 ደቂቃዎች በረራ በኋላ በመነሻው ለማረፍ ተገዷል።

አየር መንገዱ በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩት 177 ተሳፋሪዎች እና ሠራተኞች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው አውሮፕላኑ #በሰላም አርፏል ብሏል።

የአደጋው መንስዔ እስኪጣራ ድረስ ሁሉንም 737 ማክስ 9 አውሮፕላኖች በጊዜያዊነት ከበረራ እንዳገደ አየር መንገዱ አስታውቋል።

ይህ ቦይንግ ሰራሹ አውሮፕላን ባለፉት ዓመታት መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

ከአምስት ዓመት በፊት #በኢትዮጵያ እና #ኢንዶኔዢያ ባጋጠመ አደጋ ምክንያት ከበረራ ታግዶ የነበረው ይህ ማክስ 737 ዝርያ መሆኑ ይታወቃል። #BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ' በኃይል ይዣለሁ ፣ ይዣለሁ ማለቱ ፍጹም ሰላም አያመጣም " - ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዜዳንት የሆኑት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ፥ " በወረራ " ተይዘዋል ያሏቸውን የትግራይ ክልል ግዛቶችን በሰላም ስምምነቱ መሰረት ነጻ እንዲወጡ እና የአካባቢዎቹ ሰላምና ደህንነት ተረጋግጦ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ ቄያቸው እንዲመለሱ የማድረግ ኃላፊነት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት…
" ስጋት ፈጥሮብናል " - ኤምባሲዎቹ

ሰሞነኛውን የሰሜን ኢትዮጵያን ጉዳይ አስመልክቶ በአዲስ አበባ የሚገኙት ፦
- የካናዳ፣
- የፈረንሳይ፣
- የጀርመን፣
- የጣሊያን፣
- የጃፓን፣
- የእንግሊዝ እና የአሜሪካ ኤምባሲዎች የጋራ አጭር መግለጫ አውጥተዋል።

በዚህም ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ " #አወዛጋቢ " በሆኑት አካባቢዎች ከሰሞኑን የተፈጠረው ግጭት " ስጋት ፈጥሮብናል " ብለዋል።

ሁሉም ወገኖች የታጣቂ ኃይሎች ትጥቅ ማስፈታት ፣ ብተና እና መልሶ ማቋቋም /#DDR / እንዲሁም ተፈናቃዮችን #በሰላም ወደ ነበሩበት መመለስ ላይ አበክረው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

" ውጥረቱ እንዲረግብ እና #ሰላማዊ_ሰዎች ጥበቃ እንዲደረግላቸው እናሳስባለን " ብለዋል።

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እና የተወሳሰቡ የፖለቲካና የጸጥታ ቀውሶችን ለመፍታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ውይይት ማድረግ ብቸኛው መንገድ ነው ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #EOTC " የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻ አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ ፤ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው " - ቅዱስነታቸው ግንቦት ወር ላይ የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀመረ።   የጉባኤውን መጀመር አስመልክቶ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ…
#EOTC #ETHIOPIA

ብፁዕ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፦

" የማኅበረሰባችን ችግር በቤተ ክርስቲያን ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ በሀገር ደረጃ እየቀጠለ ያለው አለመግባባትም ለጠቅላላ ማኅበረ ሰባችን ፈተና ከሆነ ውሎ አድሮአል፤ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ምንጭ ከሆኑትም አንዱና ዕድል ሰጩ ይህ ሀገራዊ አለመግባባት ነው።

በዚህ አለመግባባት ምክንያት ገዳማውያን መነኮሳት፤ መምህራን ካህናት ምእመናን አብያተ ክርስቲያናት ከባድ የሆነ ጉዳት ደርሶባቸዋል ፤ #በሰላም_ወጥቶ_መግባትም_አጠራጣሪ_ሆኖአል ፤ ይህንን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረትም ጎልቶ አይታይም፡፡

በመሆኑም ይህ ክሥተት እውን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን መፍታት የማንችል ሰዎች ነን ወይ ? ለኛስ ከኛ የበለጠ ማን ይመጣልናል ? የሚለውን ጥያቄ ልናነሣ ግድ ነው። ስለዚህ ለሀገር ህልውናና ድኅነት የሚበጅ ነገር እንዲመጣ ቤተ ክርስቲያን ባላት ሃይማኖታዊና ሰብአዊ ኃላፊነት ጠንክራ መስራት ይጠበቅባታል። "

#ኦርቶዶክስተዋሕዶ #ኢትዮጵያ
#የግንቦት_ርክበ_ካህናት_ቅዱስ_ሲኖዶስ_ምልአተ_ጉባኤ

@tikvahethiopia
#OROMIA #PEACE

" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ... ለሰላም ክፍት ነን ድርድሮችም እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም ቢሆን ያሉ ችግሮች #በሰላም እንዲፈቱ መንግሥት #ለድርድር ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።

የክልሉ መንግሥት አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በአዲስ አበባ እንደመከሩ ተነግሯል።

በምክክሩ ላይ የተገኙት የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈሰ ውይይቱ ልማትና ጸጥታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

በውይይቱ ፦

- የልማት ስራ ያለ ሰላም ውጤት አልባ እንደሆነ / ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነ ፤

- ሰው ሰርቶ የሚበላው ፣ ወልዶ የሚስመው ሰላም ሲኖር እንደሆነ አጽንኦተ ተሰጥቶበታል ብለዋል።

" ሰላም ለመንግሥት ብቻ የተተወ ስላልሆነ እንዴት ነው አብሮ መስራት የሚቻለው ? " የሚለውም መነሳቱን አስረድተዋል።

" መንግሥት እና ሸኔ የጀመሩት ድርድር ፤ በተለያየ ምክንያት አኩርፈው ጫካ የገቡ ነፍጥ ያነገቡ ጓዶች አሉ ፤ መንግሥት በሆደ ሰፊነት ዛሬ ነገ ሳይል እነዚህን አካላት ጠርቶ በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር አለበት ይህ ሲደረግ ደግሞ ለሰዎቹ እውቅና ተሰጥቶ የህግ ከለላ ተሰጥቶ ነው ውይይት መደረግ ያለበት " የሚለውም መነሳቱን ገልጸዋል።

" በመንግሥት በኩል ' ዛሬም ቢሆን ክፍት ነው እንነጋገራለን ፣ ችግሮችን በጋራ ተነጋግረን እንፈታለን ' የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን " ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ አሁንም ቢሆን የክልሉ መንግሥት በውይይት ያምናል ብለዋል።

" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ሙሉ ትኩረታችን ወደ ሰላም ማምጣት ነው ያለብን። የፈለግነውን ነገር በአዳራሽ መወያይት ይቻላል። ጥረቶች ብዙ ነው ያደረግነው አሁንም ለሰላም ክፍት ነን እኛ 3ኛ ዙር ይሁን፣ 5ኛ ዙር ይሁን ፣ 10ኛ ዙር ድርድሮች እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " ብለዋል።

#Ethiopia
#Oromia #VOA

@tikvahethiopia