#ETHIOPIA #USA
ዓለም አቀፍ ለጋሾች ያቆሙት የምግብ ርዳታ ይቀጥል ዘንድ በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን መካከል የስልክ ውይይት ተደረገ።
የሚኒስቴር መ/ቤቱ ቃል አቀባይ ማት ሚለር እንዳሳወቁት ብሊንከን ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር የስልክ ውይይት አድርገዋል።
በዚህ ውይይት ወቅትም ፤ ዓለም አቀፍ ለጋሾች ያቆሙት የምግብ ርዳታ ይቀጥል ዘንድ ፣ የሰብአዊ ሁኔታ ቁጥጥር ተሻሽሎ ስለሚቀጥልበት አሠራር ላይ ተወያይተዋል።
በተጨማሪ አንተኒ ብሊንከን፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታ " አሳስቦኛል " ሲሉ ተናግረዋል።
በሁለቱ ክልሎቹ ያሉትን ችግሮች #በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት፣ የፖለቲካ ውይይትንና የሰብአዊ መብቶች መከበር አስፈላጊነትን አጽንዖት ሰጥተውበታል።
እውነተኛ ፣ ታማኝ እና ሁሉን አካታች የሽግግር ፍትሕ ሒደትን ለመፍጠር እየተከናወነ ያለውን ሥራ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመልካም እንደተቀበሉት ተጠቁሟል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፣ በአፍሪካ ቀንድ ስለሚታየው የጸጥታ ተግዳሮት፣ እንዲሁም አንዲት፣ ሰላማዊት እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማየት ያላቸውን የጋራ ግብ አስመልክቶም እንደተወያዩ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤትን ዋቢ በማድረግ ቪኦኤ ዘግቧል።
@tikvahethiopia

#ሺርካ
✦ " 11 የአንድ ቤተሰብ አባላት (አያት ፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ ፣ የ39 ቀን ጨቅላ) ጨምሮ 17 ስዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል " - የቲክቫህ ቤተሰብ አባል
✦ " ከሟቾቹ ውስጥ ከ70 ዓመት አዛውንት እስከ 26 ቀን ህጻን ነፍሰጡር እናቶች ይገኙበታል " - ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ (ለቪኦኤ)
✦ " ጥቃቱን ያደረሰው አሸባሪው ሸኔ ነው " - የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን (ለቪኦኤ)
✦ " እኛ ንፁሃን ላይ ጥቃት አላደረስንም " - የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ለቪኦኤ)
✦ " ባለሞያ መድበን ምርመራ ጀምረናል " - ኢሰመኮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ፤ ሺርካ ወረዳ ፤ በተፈጸመ ጥቃት ንጹሐን ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መሞታቸውን እና የዐይን እማኞችና መልክታቸውን ያደረሱ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።
አንድ #የአካባቢው ነዋሪ የቤተሰባችን አባል በላኩልን መልዕክት ፤ " ህዳር 13 /2016 በግምት ከምሽቱ 2:30 አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ እና በታጠቁ ኢ - መደበኛ ሀይሎች በሽርካ ወረዳ ሶሌ ዲገሉ ጉና እና ጢጆ ለቡ በተባሉ የገጠር ቀበሌዎች በተፈፀመ ጥቃት 11 የአንድ ቤተሰብ አባላት (አያት ፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ ፣ የ 39 ቀን ጨቅላ) ጨምሮ 17 ስዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ በተመሳሳይ ሰዓት በተፈፀመ በሌላኛው ጥቃት ደግሞ 11 በድምሩ 28 ሰው ሲልፍ ሁለት ህፃናት ደግሞ ቆስለው ህክምና ላይ ይገኛሉ " ሲሉ ገልጸዋል።
ቪኦኤ አማርኛ አገልግሎት ክፍል በጉዳዩ ላይ በሰራው ዘገባ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ሦስት ቀበሌዎች ሐሙስ ህዳር 13 እና ሰኞ ህዳር 17 ቀን በተፈጸመ ጥቃት #36_ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል።
ከሟቾቹ ገሚሶቹ የሁለት ቤተሰብ አባላት መሆናቸውን በዘገባው ጠቅሷል።
ቃላቸውን የሰጡ አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉ ነዋሪ ፤ " ህዳር 13 ለ 14 አጥቢያ ለቡ በተባለው ቀበሌ ላይ 11 ሰው አንድ ላይ ሰብስበው እነዚህ ታጣቂዎች አንድ ላይ ረሽነዋል። ሶሌ ዲገሉ በተባለው ቀበሌ ደሞ 17 ሰው አስሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው ሰብስበው ረሽነዋል። እነዚህ 17ዱ በአንድ ጉድጓድ 11ቱ በአንድ ጉድጓድ ተቀብረዋል። የዚህን ሀዘን ሳንጨርስ እንደገና በሦስተኛው ቀን ለቡ በተባለው ቀበሌ የአንድ ቤተሰብ አባላት 8 ሰዎች ረሽነዋል። እነዚህም በአንድ ጉድጓድ ተቀብረዋል " ሲሉ ተናግረዋል።
ነዋሪው አክለው፤ " ከእነዚህ ከሟቾቹ ውስጥ ከ70 ዓመት አዛውንት እስከ 26 ቀን ህጻን ነፍሰጡር እናቶች ይገኙበታል" ያሉ ሲሆን " የሦስቱ ቦታ ጥቃቶች በተመሳይ መልኩ ቤት እየገቡ አንድ ቦታ ያሉ ሰዎችን መረሸን ነው። ህጻን የለም አዋቂ የለም ገብተው መረሸን ነው። የአማርኛ ስም ያላቸው፣ የአማራ ስም ያላቸውና የኦርቶዶክስ እምነት አማኝ ላይ ያተኮረ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ጥቃቱን ማን እንደፈጸመ የተጠየቁት ነዋሪው " ምንም የሚታወቅ ነገር የለም የታጠቁ ኃይሎች ናቸው እከሌ ልንላቸው አንችልም። " ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።
የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ፣ ለጥቃቱ መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ ከሚጠራው (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ተጠያቂ አድርገዋል።
ኃላፊው ለቪኦኤ በሰጡት ምላሽ " በሽርካ ወረዳ ሶሌ ዲገሉ፤ ጢጆ ለቡ፤ ሲላ ዋጂ አሸባሪው ሸኔ ንጹሐን ላይ ጥቃት ፈጽሟል። ከ2 ዓመት ህጻንን እስከ አቅመ ደካማ ሴቶችን ላይ አነጣጥሮ እኔ ባለኝ መረጃ የ27 ሰዎች ህይወት አልፏል " ብለዋል።
አክለውም " ይኼ አሸባሪ ቡድን ባሳለፍነው ሳምንት ቡኖ በደሌ ጨዋቃ ወረዳ ላይ በኢትዮጵያ የጸጥታ አካል በተወሰደበት እርምጃ ብዙ ኃይሉ ሙትና ቁስለጫ በመሆኑ ይሄንን ለመበቀል ብሎ በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ይሄንን ጥቃት ፈጽሟል።" ሲሉ ከሰዋል።
በመንግሥት " ኦነግ ሸኔ " የተባለውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው የታጠቀ ኃይል ቃል አቀባይ የሆኑት ኦዳ ታርቢ ለቪኦኤ ኦሮምኛ ክፍል በሰጡት ምላሽ ውንጀላውን #አስተባብለዋል፡፡
" እኛ ኃይላችን በተባለው አከባቢ #በሰላማዊ ሰዎች ላይ የወሰደው እርምጃ፤ ያጠፋው የሰላማዊ ሰዎች ህይወትም የለም። ከህዳር 14 - 17 ድረስ በሥርዓቱ ኃይል ብዙ ሰው ተገሏል፤ ብዙ ቤትም ተቃጥሏል። ይህም በምስራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ነው የተፈጸመው አዛውንቶችም ተገለዋል። ይህንን ለማድበስበስ ነው ጣታቸውን በእኛ ላይ የሚጠቁሙት " ሲሉ ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ግን ይህ ኃይል የሚፈጸጸምማቸውን ጥቃት መካድ ባህሪው ነው ሲሉ ገልጸውታል።
አስተያየታቸውን የሰጡን የቲክቫህ ቤተሰቦች ፤ " እዚሁ ወረዳ ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ግድያ እንደነበረ ቢታወቅም በአካባቢው ያሉ የመንግስት ታጣቂዎች ለጉዳዩ የሰጡት ትኩረት አነስተኛ ስለነበር ይህ ሁሉ ሰው ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ተጨፍጭፈዋል። የአካባቢው ህዝብም በአካባቢው ለመኖር ዋስትና ስለሌለው አካባቢውን ለቆ ለስደት እየተዳረገ ነው፡፡" ሲሉ ተናግረዋል።
በኦሮሚያ ክልል ፤ ምሥራቅ አርሲ ዞን ፤ ሽርካ ደረሰ ስለተባለው ጥቃት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ( #ኢሰመኮ ) ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን የኮሚሽኑ የክትትልና ምርመራ ስራ ክፍል ሲኒየር ዳይሬክተር ሚዛኔ አባተ (ዶ/ር)፣ " መረጃ ደርሶናል እያየነው ነው " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።
" አሁን ላይ በዝርዝር የምናገረው ነገር የለም። ነገር ግን እኛ ጉዳዮች እንደዚህ በሚደርሱን ሰዓት ጉዳዩን የሚከታተል ባለሙያ እንመድባለን፣ በዚህም ምርመራ እናደርጋለን። ያ ነገር የተጀመረ መሆኑን ነው መናገር የምችለው " ሲሉ ገልጸውልናል።

#መልዕክት
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዜዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ፦
" . . . በዓለማችን #የሰላም ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ በሆነበት በአሁኑ ጊዜ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ስናከብር እግዚአብሔር በራሱና በሰው ልጆች መካከል፤ እንዲሁም በሰው ልጆች መካከል የነበረውን ጥል አስወግዶ ሰላምን ለማውረድ ያደረገውን ማሰብ ብቻ ሳይሆን የክርስቶስን ምሳሌነት ለመከተል መወሰንን ይጨምራል፡፡
በተለይም በአሁኑ ጊዜ በአገራችን የሚታዩት ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ተወግደው ሰላም እንዲሰፍንና አገራዊ አንድነት እንዲረጋገጥ መላው የአገራችን ሕዝቦችና ሕዝበ ምዕመኑ እንደወትሮው የእግዚአብሔር አምላካችንን ጣልቃ ገብነት ተግተው መለመንና አቅም የፈቀደውን ሁሉ ለማድረግ መዘጋጀት ይጠበቅባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በአገራችን በተለያዩ ቦታዎች ለሚነሱ አዳዲስ ግጭቶችም ሆነ ለሰነበቱት አለመግባባቶች ዋነኛ መፍትሔ ሊሆን የሚችለው #በሰላማዊ_መንገድ ተቀራርቦ መመካከርና መነጋገር ብቻ እንደሆነና የትጥቅ ፍልሚያ ሰላም ሊያመጣ እንደማይችል ታምናለች፡፡
የሰው ልጆች አብረው በሰላምና በፍቅር እንዲኖሩ የሰላም ወንጌልን ትሰብካለች፡፡ ከሰላም እጦት የተነሳ የሚፈጠረውን ሞትና እንግልት ትቃወማለች፤ በበኩልዋም ችግሮች ሲፈጠሩ ለእርቅና ለሰላም ጥረቶች የምትጠየቀውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆንዋንም በየጊዜው ስትገልጽ ቆይታለች፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱም ራስዋ በየጊዜው በተለያዩ ታጣቂ ኃይላት መካከል በሚከሰቱ ግጭቶች ቀጥታ ተጠቂ የሆነችባቸው አጋጣሚዎች በርካታ ናቸው፡፡
ለዚህም በቅርብ ጊዜ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቄለም ወለጋ ዞን በጊዳሚ ወረዳ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በጸሎት ላይ በነበሩ ንጹሐን ምዕመናኖቻችን ላይ የደረሰው የጅምላ ግድያ በማሳያነት ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያኒቱ በጊዜው ድርጊቱን ከመቃወምና ከማውገዝ ባሻገር ሁኔታውን አስመልክቶ ክትትል እንዲደረግና ለህዝብ ይፋ እንዲሆን ጥሪ ማድረግዋ የሚታወስ ነው፡፡
አያይዛም እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት ላንዴና ለመጨረሻ ለማስወገድ የትጥቅ ፊልሚያዎችን አቁሞ ለሰላማዊ ምክክር ዕድል መስጠት ብቸኛ አማራጭ እንደሆነም አስታውሳለች፡፡
አሁንም ይህንኑ ጥሪ ደግማ ደጋግማ ማሰማትዋን ትቀጥላለች፤ ምዕመናንዋንም በዚሁ መስመር በጸሎት በማትጋት ላይ ትገኛለች፡፡ በእግዚአብሔር ተስፋ አይቆረጥም፤ እርሱ የምህረት ፊቱን ይመልስልናል፤ ሰላሙንም በእርግጥ ይሰጠናል፡፡ "
(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)