TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጅግጅጋ የሆነው ምንድነው ?

ከሰሞኑን በጅግጅጋ ከተማ እጅግ አሰቃቂ የተባለ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈፅሟል።

የአስገድዶ መድፈር ወንጀሉ የተፈፀመባት የ9 ዓመት ህፃን ልጅ ስትሆን ይህ ድርጊት ከተፈፀመባት በኃላ የድርጊቱ ፈፃሚዎች የደፈሯትን ልጅ ገድለዋታል።

ከዚህ አሰቃቂ ድርጊት በኃላ ወንጀሉን የፈፀሙ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ እንደቻሉ ተገልጿል።

ነገር ግን ከዚህ የወንጀል ድርጊት ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎችን በመያዙ ሂደት ላይ ሰዎችን ለይቶ በአፈሳ የማሰር ድርጊት እንደነበር ቃላቸውን የሰጡ የጅግጅጋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የጅግጅጋ ነዋሪ በሰጡት ቃል ፤ ከህፃኗ መደፈር ድርጊት ጋር በተያያዘ ሰኞ 4 ተጠርጣሪዎች ቢያዙም በከተማው ሰፊ አፈሳ ሲደረግ ነበር ብለዋል።

በተለይም ከደቡብ አካባቢ የመጡ ልጆች በድርጊቱ ላይ በመጠርጠራቸው ይህን መሰረት ያደረገ እስር ሲፈፀም እንደነበር ገልጸዋል። ድርጊቱ እስከ ትላንት ድረስ መቀጠሉን ጠቁመዋል።

አንድ ሌላ ነዋሪ ድርጊቱ እጅግ በጣም አሰቃቂና አስደንጋጭ እንደነበር ገልጸው ከተጠርጣሪዎች አያያዝ ጋር በተያያዘ በፀጥታ ኃይሎች የተፈፀመው ድርጊት ተገቢ አይደለም ብለዋል።

" ተጠርጣሪዎችን በልዩነት ማሰር እየተቻለ ሰዎች በአፈሳ ወደ ማቆያ ሲገቡ ነበር ይህ ተገቢ ያልሆነ አካሄድ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላ አንድ ነዋሪ ደግሞ ፤ " እሁድ እለት አንድ ልጅ ተደፈራ ከተገደለች በኃላ ድርጊቱን የፈፀሙ ግለሰቦች ተይዘው ለህግ ቀርበዋል " ብለዋል።

" ይሄ ጥሩ ነው " ያሉት እኚሁ ነዋሪ ነገር ግን ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የለላቸውን ሰዎች ፓሊስ በጅምላ በማፈስ ማሰረሱን ፣እና መደብደቡን ጠቁመዋል።

በነበረው ሁኔታ የሰዎች ህይወት ማለፉን እንደሰሙ ገልጸዋል።

በተለይ ከደቡብ የመጡ ወጣቶችን መታወቅያ በማየት እስር ፣ ድብደባ ሲፈፀም ነበር ይህን የሚመለከተው አካል ይወቀው ሲሉ ገልጸዋል።

የሶማሌ ክልል መንግሥት ግን ከአሰቃቂው የወንጀል ድርጊት በኃላ ተፈፅሟል የተባለው ድርጊት #አሉባልታ እና #ሀሰተኛ ነው ብሏል።

የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አብድቃድር ረሽድ ፤ " በሱማሌ ክልል የሌላ ክልል ተወላጆች እየታፈሡ እየታሰሩ ፣እየተገደሉ ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው አሉባልታ ወሬ ነው " ያሉ ሲሆን የሚንገረው ሁሉ ውሸት ነው ብለዋል።

" የሶማሌ ህዝብ ሰፊ ህዝብ ነው አቃፊ ነው ፣ ከየትኛውም ህዝብ ጋር የመኖር ባህል ያለው ማህበረሰብ ነው ፤ የሌላ ኢትዮጵያዊ ተወላጅ የማሳደድ፣ የመግደል ባህል ፈፅሞ የለውም የሚነገረው ሁሉ ውሸት ነው፤ የሶማሌ ህዝብን ስም ለማንቋሸሽ የሚሰራ ፕሮፖጋንዳ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" የህግ አካላት ቦታው ላይ ሳይደርሱ ሁከት ለመፍጠር ሙከራ ተደርጎ ነበር " ያሉት ኃላፊው የህግ አካላት የዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ የወሰዱት እርምጃዎች ነበሩ ብለዋል።

" እነዛም መቆያ አካባቢዎች ለደህንነታቸው ስጋት የቆዩ አካላት በማጣራት ወደመደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ ትላንት በፀጥታ አካላት መመሪያ ተሰጥቷል። " ሲሉ ተናግረዋል።

" በሶማሌ ክልል ምንም ችግር የለም ሰላም ነው ፤ የሶማሌ ህዝብ አቃፊ ነው " ያሉት ኃላፊው የፖለቲካ አጀንዳ በማድረግ ተቃውሞ በመፍጠር ብጥብጥ ለመፍጠር ፣ በክስተቶች ላይ ክስተት በማጋነን ፣ እከሌ ተገደለ፣ እከሌ ዘሩ እንዲህ ነው በማለት ለፖለቲካ የሚጠቀሙ ኃይሎች አሉ " ብለዋል።

" የሶማሌ ክልል ሰላም ነው ፤ ሁሉም ወደ መደበኛው ስራ ተመልሷል " ሲሉ አክለዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የተሽከርካሪዎች_ጨረታ_ጉምሩክ_ኮሚሽን_አዳማ_.pdf
ውዝግብ የፈጠረው የበርካታ ተሽከርካሪዎች ጨረታ !

" ' የጉምሩክ ኮሚሽን ' የገንዘብ ሚኒስቴርን ውሳኔ በመጣስ 237 መኪኖችን ለሐራጅ አወጣብን " - ከሰደት ተመላሾችና 10 የሚደርሱ የአገር ውስጥ አስመጪዎች

" በግልፅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት ተሽከርካሪዎች ህጋዊ ስርዓቱን በአግባቡ በተከተለ መልኩ ነው። ' ህጋዊ ስርዓቱን አልተከተለም ' በሚል የሚሰራጩት መረጃዎች ሀሰተኛ ናቸው ፤ #ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩ አካላትን በህግ አግባብ እንጠይቃለን " - ጉምሩክ ኮሚሽን

ከሰሞኑን የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ፅ/ቤት ያወጣው የበርካታ ተሽከርካሪዎች ጨረታ ውዝግብ የፈጠረ ሆኗል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሬታ አለን ያሉ ከሰደት ተመላሾችና የአገር ውስጥ አስመጪዎች ፤ " ጉምሩክ ኮሚሽን የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔን በመጣስ 237 ተሽከርካሪዎች ለሐራጅ አወጣብን " በሚል ከሰዋል።

ጉምሩክ ኮሚሽን በበኩሉ ፤ " ምንም አይነት የህግ ጥሰት አልፈተፈፀም ህጉን እና አሰራሩን በተከተለ መልኩ ነው ተሽከርካሪዎቹ ለጨረታ የቀረቡት " ሲል አሳውቋል።

ያንብቡ 👇 https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-11-24

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይፈለጋል #Wanted " ... ሟች ያሳድጉት የነበረው መሀመድ ሽኩር አበባው ፤ ሼህ አብዲ ያሲንን በመግደል ወንጀል ተጠርጥሮ ይፈለጋል " - ፖሊስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፤ ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የሚጠረጠረው መሀመድ ሽኩር አበባው የተባለ ግለሰብ መሆኑን ገልጿል። ግለሰቡ #እጁን_እንዲሰጥም ፖሊስ አሳስቧል። ፖሊስ ተጠርጣረው ያለበትን የሚያውቅ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪውን አስተላልፏል።…
#ይፈለጋል #Wanted

ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የሚጠረጠረው መሀመድ ሽኩር አበባው በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትሉን አጠናክሮ መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

አንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ተጠርጠሪው እንደተያዘ በማስመሰል የሚያሰራጩት መረጃ #ሀሰተኛ መሆኑን አስታውቋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጠርጣሪው ሳይያዝ እንደ ተያዘ አድርጎ መረጃ ማሰራጨት ተገቢ እንዳልሆነ የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ መሀመድ ሽኩር አበባው ያለበትን የሚያውቅም ሆነ ማነኛውም መረጃ ያለው በስልክ ቁጥር 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ ቁጥር 991 መረጃ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
" ለ ' ህወሓት' የሰጠነው ምንም አዲስ እውቅና የለም " - የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ

በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ለ "ህወሓት" እውቅና ስለ መሰጠቱ የሚሰያጨው መረጃ #ሀሰተኛ መሆኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በማህበራዊ ትስስር ገፆች በተለይም በፌስቡክ ለ " ህወሓት " እውቅና ስለመሰጠቱ #ሀሰተኛ_መረጃዎች እየተሰራጩ መሆኑን በተደረገ ቅኝት ማየት መቻሉን የገለፀ ሲሆን ለ " ህወሓት " የተሰጠ እውቅና #እንደሌለ ቢሮው ገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትላንትናው እለት ፦
- ለወሎ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ
- ለኩሽ ህዝቦች ብሔራዊ ንቅናቄ
- ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ ለተባሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መስጠቱን አሳውቋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ለ "ህወሓት" እውቅና ተሰጠ ተብሎ የሚሰራጨው #ሀሰተኛ_መረጃ ፥ መረጃውን የእውነት ለማስመሰል እየተደረገ ያለ ሙከራ መሆኑን የቦርዱ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያስረዳ ሲሆን " ለህወሓት የሰጠነው ምንም አዲስ እውቅና የለም " ብሏል። 

ማንኛውም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድን የተመለከተ መረጃ በቦርዱ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ እስካልወጣ ድረስ መረጃዎቹ ሀሰተኛ መሆናቸውንና ቦርዱን የማይወክሉ መሆኑን እንዲታወቅልኝ ሲል ቦርዱ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ🚨

" ማህበረሰቡ ያለበትን #የቤት_እጦት እና ፍላጎት በመገንዘብ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከኢትዮ - ቴሌኮም ጋር በመተባበር 100 ሚሊዮን ብር መድቦ እየሰራ ነው " እየተባለ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰራጨው መረጃ ፍጹም #ሀሰተኛ ነው።

በማህበራዊ ሚዲያው የሚዘዋወረው መልዕክት አጭበርባሪዎች ህብረተሰቡን #ለማጭበርበር የፈጠሩት ነው።

" ሼር ብቻ እያደረጋችሁ የቤት ባለዕድለኛ ሆኑ ፣ ተሸለሙ " የሚሉት መልዕክቶች በሁለቱም ተቋማት እውቅና የሌላቸው የአጭበርባሪዎች ስራ ናቸው።

" ቤት ታገኛላችሁ ሼር አድርጉ " እንዲህ የሚባል ነገር የለም።

ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦቻችን ፤ መሰል #በውሸት የተሞሉ የማጭበርበሪያ ስልቶችን እንድትጠነቀቁ ከዚህ ቀደም በዛ ያሉ መልዕክቶች ተለዋውጠናል ፤ በቂ እውቀትም አላችሁ።

ምናልባት እንዲህ ያለን ሀሰተኛ መልዕክት አምኖ የሚጭበረበር ወዳጅ ዘመንድ እንዳይኖራችሁ አስገንዝቧቸው።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia