TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጎንደር

° " የሽንኩርት ሽያጭ ዋጋ በኪሎ 60 ብር ነበር አሁን በእጥፍ አድጎ እስከ 120 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው " - የጎንደር ነዋሪ

° " በሚታየው የዋጋ ጭማሪ ምክንያት የዕለት ከዕለት ኑሮን መግፋት አስቸጋሪ ሆኖብኛል " - የጎንደር ነዋሪ


በጎንደር ከተማ ተከስቶ የነበረውን ግጭት መነሻ በማድረግ በኢንዱስትሪና በግብርና ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በመከሰቱ የዕለት ከዕለት ኑሯቸውን ለመምራት መቸገራቸውን ያነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡

ካነጋገርናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ወጣት አስተሪዮ አስማረ በሰጠው አስተያየት ቀደም የሽንኩርት ሽያጭ ዋጋ በኪሎ 60 ብር ነበር አሁን ዋጋው በእጥፍ አድጎ እስከ 120 ብር ድረስ እየተሸጠ ነው፡፡

የዘይትና የሌሎች የሸቀጥ ምርቶችም ላይም የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል፡፡

ታዲያ የዋጋ ንረት በመከሰቱ " የዕለት ከዕለት ኑሮዬን ለመምራት ተቸግሪያለሁ " ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

ሌላው በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡት የከተማዋ ነዋሪ አቶ ጎበዬ መኩሪያው ደግሞ በአካባቢው ተከሰቶ የነበረውን ግጭት ምክኒያት በማድረግ በግብርና ምርቶችና በሸቀጥ ምርቶች ላይ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል ይላሉ፡፡

የጤፍ ዋጋ በኪሎ 65 ብር ይሸጥ የነበረው አሁን ወደ 110 ብር አሻቅቧል፡፡

" በእያንዳንዱ የሸቀጥ ምርቶችም ላይም በተመሳሳይ የሽያጭ ዋጋቸው እየጨመረ ነው፡፡ ነጋዴዎች ያላግባብ ምርት ያከማቻሉ፡፡ ያላግባብ ዋጋ ይጨምራሉ፡፡ ነዋሪዎች ግጭት ይነሳል በሚል ስጋት እህል እየገዙ ያከማቻሉ፡፡ ይህ ሁሉ ተደማምሮ የዕለት ከዕለት ኑሮን መግፋት አስቸጋሪ ሆኖብኛል " ሲሉ አስተያየት ሰጭው ይናገራሉ፡፡

እየተደረገ ያለው የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ተገቢ ባለመሆኑ የሚመለከተው አካል ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይ ከሰሞኑን በነበረ አንድ መድረክ ላይ ፤ " በከተማዋ በኢንዱስትሪና በግብርና ምርቶች ላይ ያላግባብ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል፡፡ ይህ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ነዋሪዎችና የመንግሰት ሰራተኞችን አስመርሯል፡፡ በቀጣይ ችግሩን ለመፍታት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በትኩረት ይሰራል " ብለዋል፡፡

" የከተማ አስተዳደሩ ለዳሽን የሸማቾች ህብረት ስራ ዩኔን 20 ሚሊየን ብር ያለ ወለድ ብድር ሰጥቶ በመሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት የግብርና ምርቶችን የማሰራጨት ስራ እየተሰራ ነው " ያሉት ከንቲባው በቀጣይ ለመሰረታዊ የሸማቾች ህብረት ሰራ ማህበራት የሚደረገው ያለ ወለድ የገንዘብ ብድር ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፤ የማህበራትን አቅም የማሳደግ ስራም በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል።

ያለ አግባብ ምርት በሚያከማቹ ግለሰቦች ላይም ክትትልና ቁጥጥር ይደረጋል ብለዋል፡፡     

መረጃውን የጎንደር የቲክቫህ-ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል ነው የላከው።

@tikvahethiopia
#ጎንደር

° “ ውሃ ካጣን ከወራት በላይ ሆነን፤ እንኳን ለመታጠብ ለመጠጥም አልተገኘም ” - የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች

° “ ጉድጓድ ስናስቆፍር በ4 ወራት ይደርሳል ብለን አንድ ዓመት ከ8 ወራት ወስዷል ” - የከተማው ውሃና ፍሳሽ 


በአማራ ክልል የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ኢንተርን ሀኪሞች፣ የውሃ ችግር እንደፈተናቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የከተማው ነዋሪዎች በሰጡት ቃል፣ “ ውሃ ካጣን ከወራት በላይ ሆነን፤ እንኳን ለመታጠብ ለመጠጥም አልተገኘም። በአፋጣኝ መፍትሄ እንሻለን ” ብለዋል።

በከተማው የውሃ አቅርቦት እንደሌለ፣ በተለይ ህፃናት የውሃ ጥሙን መቋቋም እንዳልቻሉ፣ ሰው የክረምት ውሃ ለመጠጣት መገደዱን ነዋሪዎቹ አስረድተዋል። 

ከዚህ ባለፈ ነዋሪዎች የጉርጓድ ውሃ በሰልፍ የመጠቀም ደረጃ እንደደረሱ አመልክተዋል።

ለቅሬታው ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወርቅነህ አያል ፤ “ እውነት ነው። እንዲያውም ማህበረሰቡ ታጋሽ ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ አሁን ዝናብ ስለዘነበ ትንሽ ይቀንሳል እንጂ በአንድ ወር ነው ሰው ውሃ ሲያገኝ የነበረው። ግድቡ ሙሉ ለሙሉ ቆሞ ነበር። አሁን ትንሽ ውሃ ስለያዘ ምርት ስለጀመርን አሁን ወደ 25 ቀን እየወረደ ነው ” ብለዋል።

የኢንተርን ሀኪሞቹን ቅሬታ በተመለከተ፣ “ ሆስፒታል ላይ ግን 24 ሰዓት ነው የምንሰጠው። መብራትና አጠቃላይ ምርት ቆሞ ካልሆነ አይቋረጥም ” ነው ያሉት።

“ የማህበረቡ ቅሬታ ግን እውነቱን ለመናገር ከቅሬታ ባለፈ ሌላ ነገር ቢሉም አይፈረድባቸውም ትክክል ናቸው ” ያሉት አቶ ወርቅነህ፣ “ እንደዚህ ትዕግስተኛ የሆነ ማህበረሰብ የለም ” ሲሉ ተናግረዋል።

ችግሩ ከቆዬ ለምን በወቅቱ መፍትሄ እንዳልተቸረው ሲያስረዱም፣ “ ጉድጓድ ስናስቆፍር በ4 ወራት ይደርሳል ብለን አንድ ዓመት ከ8 ወራት ወስዷል። እንደዚህ አይነት ቻሌንጆች አሉብን ” ብለዋል።

ችግሩን ለመቀረፍ የገጠማችሁ ዋናው ችግር ምንድን ነው ? ለሚለው ጥያቄ የፋይናንስ ችግር እንዳለባቸው ገልጸው፣ ምን ያህል በጀት እንደሚያስፈልግ ከመናገር ግን ተቆጥበዋል።

“ ችግሩን መነሻ ተደርጎ የአጭር፣ የአስቸኳይ፣  የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜያት ተብሎ ስራዎች እየተሰሩ ነው። አንዳንዶቹን ቶሎ እናጠናቅቃቸዋለን ” ብለዋል።

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚበጀውን በተመለከተ፣ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበው፣ ማህበረሰቡ ላሳየው ታጋሽነት ምስጋና አቅርበዋል። 

ለነዋሪዎቹ ከሚያስፈልገው የውሃ መጠን እየቀረበ ያለው ምን ያህሉ እንደሆነ፣ ምን ያህል ጉድጓድ እየተቆፈረ እንደሆነ፣ ችግሩን በተጨባጭ እስከ መቼ ለመቅረፍ እንደታሰበ በቀጣይ መረጃ የምናደርሳችሁ  ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አብና🕯 " የ4ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል ፤ የ6 ሰዎች አስከሬን ሊገኝ አልቻለም ! " በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ልዩ ስሙ ኖላ በተባለ ቦታ ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ 10 ሰዎች ሞተዋል። የጠለምት ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋየ ወርቅነህ ምን አሉ ? " የ4 ሰዎች አስከሬን በፍለጋ ተገኝቷል ፤ የቀሪ 6…
#አማራ #ጎንደር🕯

በአማራ፣ ሰሜን ጎንደር ዞን 3 ወረዳዎች በመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ እና የተጎዱ ሰዎች ቁጥር በዛሬው ዕለት ጨምሯል።

ሟች ወገኖቻችን 23 ደርሰዋል።

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖቻችን ደግሞ  8 መድረሳቸው ተነግሯል።

ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወገኖቻችን አጠቃላይ ከ2 ሺህ 700 በላይ ናቸው።

አደጋው የደረሰው በዞኑ በጠለምት፣ በጃናሞራ፣ በአዲአርቃይና በየዳ ወረዳዎች በሚገኙ 11 የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ ነው፡፡

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሰሜን ጎንደር ኮሚኒኬሽን ነው።

#አማራ #ሰሜንጎንደር

@tikvahethiopia