በመላው ዓለም ኢንተርኔት ሊቋረጥ ይችላል ?
የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም ወይም በምህጻረ ቃሉ ናሳ ከሰሞኑ አንድ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።
የተቋሙ ማስጠንቀቂያም በሚቀጥለው ሳምንት በተለይም በፈረንጆቹ ጥቅምት 10 እና 11 ባሉት ቀናት ውስጥ ከባድ የጸሀይ መብረቅ ወይም ሞገድ ሊከሰት ይችላል ብሏል።
ይህን የናሳን ማስጠንቀቂያ መሰረት በማድረግ በመላው ዓለም ኢንተርኔት ሊቋረጥ ይችላል የሚሉ ዜናዎች በዓለም ላይ በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ።
ይህ ዜና በስፋት መሰራጨቱ ያሳሰበው ናሳም ኢንተርኔት በመላው ዓለም ይቋረጣል በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አስታውቋል።
ድርጅቱ አክሎም በሚቀጥለው ሳምንት በጸሀይ ሀይል ምክንያት ይፈጠራል በተባለው መብረቅ የኢንተርኔት አገልግሎት ሊቋረጥ የሚችልበት ምንም አይነት ግልጽ ስጋት የለም ብሏል።
የአሜሪካ መንግሥት ንብረት የሆነው ናሳ ስለ ጠፈር ሳይንስ የተለያዩ ጥናቶችን እና ግኝቶችን ለመላው ዓለም በማቅረብ ይታወቃል።
Credit - #AlAin_Amharic
@tikvahethiopia

#TOYOTA
ቶዮታ / Toyota ዓለም አቀፍ የመኪና አምራች ኩባንያ በዓለም ገበያ በዋነኝነት #በአሜሪካ የተሸጡ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎቹን ከገበያ ላይ እንዲሰበሰቡ አዟል።
ቶዮታ እንዲሰብሰቡ ያዘዘው ከ2020 እስከ 2022 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የተመረቱ ተሽከርካሪዎችን ሲሆን ተሽከርካሪዎቹ የ " ኤርባግ " ደህንነት ችግር አለባቸው ተብሏል።
ከ2020 እስከ 2022 ወደ ገበያ የቀረቡ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎች (በዋነኝነት #አሜሪካ) ከ " ኤርባግ " ጋር በተያያዘ ችግር እንዳለባቸው ተደርሶበታል።
ችግሩ በፊት ለፊት ተሳፋሪ መቀመጫ በኩል በስህተት ከተሰራ የ " ኤርባግ ሴንሰር " ጋር የሚያያዝ ሲሆን ምናልባትም በአደጋ ጊዜ " ኤርባጉ " አገልግሎት ላይሰጥ ይችላል። ይህ አደጋ በሚፈጠር ጊዜ ኩዳቱ እንዲጨምር ያደርጋል።
ቶዮታ የትኞቹ ሞዴሎች ይሰብሰቡ አለ ?
#ቶዮታ
➡ ኮሮላ (2020 - 2021)
➡ ራቭ4 ፣ ራቭ4 ሃይብሪድ (2020 - 2021)
➡ ሃይላንደር፣ ሃይላንደር ሃብሪድ (2020 - 2021)
➡ አቫሎን ፣ አቫሎን ሃይብሪድ (2020 - 2021)
➡ ካምሪ፣ ካምሪ ሃብሪድ (2020 - 2021)
➡ ሴና ሀይብሪድ (2021)
#ሌክሰስ
➡ ES250 (2021)
➡ ES300H (2020-2022)
➡ ES350 (2020-2021)
➡ RX350 (2020-2021)
➡ RX450H (2020-2021) የተሰኙ ከ2020 እስከ 2022 ላይ የተመረቱት የ " ኤርባግ " ችግር ስላለባቸው ይሰብሰቡ ብሏል።
ከላይ የተጠቀሱት ተሽከርካሪዎች ያላቸው ሰዎች ኤርባጋቸውን #እንዲያረጋግጡ እና ችግር ካጋጠማቸው እስከ ቀጣዩ የካቲት ወር ድረስ እንዲመልሱለት ቶዮታ ጥሪ አቅርቧል።
የቶዮታ ተሽከርካሪዎች ችግር እንዳለባቸው የታወቀው የጃፓን ትራንስፖርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ ተሽከርካሪ እምራች ኩባንያዎች ላይ ባደረገው #ምርመራ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።
ይህን ተከትሎ የቶዮታ ኩባንያ አክስዮን ዋጋ ቅናሽ አሳይቷል።
ምርመራው ከቶዮታ ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ ዳይሀትሱ በተሰኘው ኩባንያ ላይም ተመሳሳይ ችግር መታየቱን ገልጿል።
ከ87 ዓመት በፊት ኪቺሮ ቶዮታ በተባለ ግለሰብ የተመሰረተው ቶዮታ የተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ አሁን ላይ በዓመት 10 ሚሊዮን ተሽከርካሪዎችን በማምረት ላይ ይገኛል።
ከ360 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉት ቶዮታ ኩባንያ 300 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት እንዳለው የኩባንያው ዓመታዊ ሪፖርት ያስረዳል።
#ጥቆማ ፦ ከደህንነት ጋር በተያይዘ በተለይም በአሜሪካ እንዲሰበሰቡ የታዘዙ ተሽከርካሪዎችን ቼክ ለማድረግ https://www.nhtsa.gov/recalls በዚህ አድራሻ መጠቀም ይቻላል። የመኪናውን መለያ ቁጥር (VIN) በማስገባት ማወቅ ይቻላል።
Credit - #AlAiN / #Reuters / #Toyota_News_Room