" የግብረሰዶም ድርጊትን የተላመዱና የሚለማመዱ በውጭ የሚኖሩ #ብሩንዲያውያን ወደ ሀገር ቤት እንዳይመለሱ " - የቡሩንዲው ፕሬዜዳንት
ቡሩንዲ በሀገሯ ግብረሰዶምን በፍፁም እንደማትቀበል አሳወቀች።
የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ቡሩንዲ ሀገራቸው ግብረሰዶምን በፍፁም እንደማትቀበል አሳውቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ በጋዜጠኞች ተጠይቀው ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከግብረሰዶም ጋር ታያይዞ " ሃያላኑ ሃገራት ለአፍሪካ ሀገራት እርዳታ እየለገሱ ለግብረሰዶማውያን መብት የመስጠት ግዴታን የሚያስቀምጡ ከሆኑ እርዳታቸውን እዛው መያዝ አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል።
ግብረሰዶም በቡሩንዲ ወንጀል ነው ያሉት ፔሬዝዳንቱ ይህ ወንጀል እስከ ሁለት አመት እስር እንደሚያስቀጣ ገልፀዋል።
" በግሌ እንደዚህ አይነት ሰዎችን (ግብረሰዶሞችን) ቡሩንዲ ውስጥ ካየን ስታዲየም ውስጥ አስገብተን በድንጋይ መውገር አለብን ብዬ አስባለሁ፤ ይህንን ለሚያደርጉ ደግሞ ሃጢያት አይሆንም " ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ በአፍሪካ አህጉር ከ30 በላይ ሀገራት ይህን ድርጊት የማይቀበሉ እና ወንጀል መሆኑን ያስታወሱ ሲሆን የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል በማጣቀስ " አምላክ ግብረሰዶምን ይቃወማል " ብለው በሀገራቸው ድርጊቱን በፍፁም እንደማይቀበሉት አስረድተዋል።
የዚህ አይነት የድርጊት መብት እንዲከበር ከምዕራባውያን ሀገራት ግፊት የሚደረግበትን መንገድ አስመልክቶ የተጠየቁት ፕሬዝዳንቱ ይህንን የሚመርጡ ሰዎች ወደ ምዕራቡ ዓለም ሄደው እነዚያን ልማዶች እንዲያደርጉ አስጠንቅቀው ድርጊቱ ከሀገሪቱ እና ከአህጉሪቱ ባህል እና እሴት ውጪ በመሆኑ በጭራሽ በሀገራቸው እንማይፈቀድ አስጠንቅቀዋል።
" ሰይጣንን የመረጡ እና የግብረሰዶም ድርጊትን የተላመዱና የሚለማመዱ በውጭ የሚኖሩ #ብሩንዲያውያን ወደ ሀገር ቤት እንዳይመለሱ " ሲሉም አክለዋል።
በግብረሰዶማዊነት ጉዳይ በሌሎች በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የተጠናከረ ህግ እያወጡ ሲሆን የጋና የፓርላማ አባላት ድርጊቱ በሶስት አመት እስራት የሚያስቀጣ ህግ እና የድርጊቱ ተከራካሪ ሆነው ዘመቻ የሚያደርጉ ሰዎችን እስከ 10 አመት እስራት ሊያስቀጣ የሚችል ህግ እያወጡ መሆኑ ተዘግቧል።
ኡጋንዳም ከእድሜ ይፍታህ እስራት እስከ #ሞት ድረስ የሚያስቀጣ ጠንካራ ህግ ማውጣቷ የሚዘነጋ አይደለም።
Via @TikvahethMagazine

#መልዕክት
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፌል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳሳት ፦
" . . . የክርስቶስን መወለድ በአግባቡ ለማክበር ለሰው ልጆች ሕይወት፣ ለእግዚአብሔር ቤተክርስቲያንና ለእርሱ ቅዱስ ስፍራዎች ክብርን እንስጥ፡፡
ከራስ ወዳድነት መንፈስ እንውጣ በመላው አገራችን #ሞት_ይብቃ፣ #ሰላም_ይስፋፋ፡፡
የተራቡ ፣ የተጠሙ ፣ የታረዙ ፣ የተበደሉ፣ የታመሙና የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን እናስታውስ፡፡
ከጎናቸው እንሁን እንርዳቸው እናጽናናቸው፡፡ ለኛ ምን ይደረግልን ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ምን እናድርግ እንበል፤ መጠጊያ ለሌላቸው መሸሸጊያ እንሁንላቸው፡፡
የሚገለሉ ባይተዋርነት እንዳይሰማቸው እናድርግ፡፡ ዘመዳቸው እንሁን፡፡ ምክንያቱም የልደት በዓል ክርስቶስ ዘመዳችን እንደሆነ የሚያበሥረን በዓል ነውና፡፡
በልደት ምስጢር ማንም እንግዳ ሊሆን አይገባውም፡፡
እግዚአብሔር ከጥንት ጀምሮ ጠንካራ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ በግብጽ ባርነት ሳላችሁ በመገለል፣ በመማረር ኖራችኋል፡፡ ስለሆነም እንግዳ እንዳታማርሩ ይላል፡፡ ይህ ትልቅ የፈጣሪ ትዕዛዝ ነው፡፡ ሁላችንም ልናቀርበው የሚገባው ጥያቄ የሚከተለው ነው፡፡
‹‹እንግዳ አባርሬ ይሆን››? እንግዳን ከሚያዋርድ ሐሳብ፣ ትምህርት፣ መልዕክት ጋር ተባብሬ ይሆን? የእኔ ባሕል ሙሉ ስለሆነ ሌላውን መጫን፣ ማግለል አለብኝ ብዬ ይሆን ? ይህ ዓይነት ሐሳብ ከእግዚአብሔር ቃል እንደሚርቅ ተረድቼ ይሆን? ከእንደዚህ ዓይነት ሐሳብ ለመውጣትስ ምን ማድረግ ይገባኛል ልበል፡፡
ከዚህ ሐሳብና ይህ ዓይነት ሐሳብ ከሚገለጥባቸው ተግባራት ነፃ መውጣት የምንችለው ወደ ገና በዓልና ወደ ትንሣኤ ምስጢር ስንቀርብ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ሰማይና ምድር ከእኛ ጋር አብረው ለታላቁ ጌታ ታላቅ የምስጋና መዝሙር ይዘምራሉ፡፡ "
(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

#AddisAbaba #ጋብቻ #ፍቺ #ልደት #ሞት
በአዲስ አበባ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት አፈፃፀም ከባለፉት ዓመታት በከፍተኛ ቁጥር የላቀ የኩነት እና የዲጂታል ምዘገባ መመዝገቡን የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።
ኤጀንሲው ፤ ከ393 ሺህ በላይ የዲጂታል ምዝገባ እና ከ210 ሺህ በላይ የኩነት ምዘገባ መደረጉን ነው የገለጸው።
ከተመዘገበው ጠቅላላ ኩነት ፦
➡ 181 ሺ 983 ልደት፣
➡ 16,933 ጋብቻ፣
➡ 2,813 ፍቺ
➡ 8,761 ሞት ሲሆን ከዚህም ውስጥ በአንድ ዓመት ገደብ ውስጥ የተመዘገበው ፦
* አዲስ ጋብቻ 5,171
* በፍርድ ቤት በተከናወነ በአንድ ዓመት ግዜ ውስጥ የተመዘገበ ፍቺ 1,296
* ሞት 2,312 መሆኑ ታውቋል።
ከ2015 ዓመት በንፅፅር ሲታይ ፦ አዲስ ልደት በ65%፣ ፍቺ በ106.7% እንዲሁም ሞት በ25.29% ጭማሪ ብልጫ ያሳየ ሲሆን ጋብቻ በ5% የቀነሰ መሆኑ ተገምግሟል።
በነዋሪነት አገልግሎት ዘርፍ ለ393,303 ነዋሪዎች በአዲስ፣ በምትክ፣ በእርማት እና በእድሳት የመታወቂያ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን 311 ሺ 446 (93%) የዲጂታል መታወቂያ መሆኑ በአፈፃፀሙ የተሻለ አድርጓታል።
በተጨማሪም በዚሁ ዘርፍ 76,299 የያላገባ ማስረጃ እንዲሁም 15,369 የመሸኛ (Clearance ) አገልግሎት በከተማዋ ተሰጥቷል።
ከተመዘገበው ኩነት ትንተና በዕድሜ ሲታይ ፦
☑ ልደት
6% ከ1 ዓመት በታች፣
28% ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት፣
26% ከ6 ዓመት እስከ 17 ዓመት እንዲሁም
40% ከ17 ዓመት በላይ መሆናቸው ትንተናው ያመላክታል፡፡
☑ ጋብቻ
72.8% የሚሆነው ተገቢ ከ18 - 40 ዓመት
27.2% የሚሆነው ከ41 በላይ መሆኑ ትንተናው አሳይቷል።
☑ ሞት
0.01% ከተወለደ ከ28 ቀን እስከ 1 ዓመት የተከሰተ ሞት፣
0.6% ከተወለደ ከ2 ዓመት እስከ 17 ዓመት የሞተ፣
22.9% ከተወለደ ከ18 ዓመት እስከ 40 ዓመት የሞተ፣
28.5% ከተወለደ ከ41 ዓመት እስከ 60 ዓመት የሞተ፣
35% ከተወለደ 61 ዓመት እስከ 80 ዓመት የሞተ፣
12% ከተወለደ 81 ዓመት እስከ 100 ዓመት የሞተ፣
0.9% ከተወለደ ከ100 ዓመት በላይ የሞተ መሆናቸው ያመላክታል፡፡
በስድስት ወራት አፈፃፀም በከተማው የዲጂታል ምዝገባ እና ልደት ምዝገባ የተሻለ አፈፃፀም የታየባቸው መሆኑ ተነግሯል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ዓለማየሁ ምንም እንኳን የተሻለ አፈፃፀም ቢኖርም ፤ አገልግሎቱን በጥራት ከመስጠት አንፃር የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን ከአፈፃፀሙ እኩል ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የቀሪ ወራት አቅጣጫ ነው ብለዋል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM

#ሞስኮ
ዛሬ አርብ ታጣቂዎች በሩስያ ፣ ሞስኮ ወደሚገኝ ህዝብ ወዳለበት ትልቅ የሙዚቃ ኮንሰርት አዳራሽ በመግባት አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ በመተኮስ በርካታ ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል።
የአካል ጉዳት የደረሰባቸውም አሉ።
አንዳንድ ሪፖርቶች እስካሁን ድረስ ባለው በትንሹ 40 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ100 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን ጠቁመዋል።
በአዳራሹ ውስጥ ሰዎች ተሰባስበው የነበረው ለአንድ የሙዚቃ ድግስ ነበር።
ታጣቂዎቹ ቦንብም ሲወረውሩ ነበር የተባለ ሲሆን አዳራሹ ያለበት ህንፃ በእሳት ሲያያዝ ታይቷል።
የሩሲያ ሀገር ውስጥ ስለላ አገልግሎት ከጥቃቱ በኋላ #ሞት እና #የአካል_ጉዳት መድረሱን አረጋግጧል ፤ የሟቾች ቁጥርን ግን አልገለጸም።
የሩስያ ጤና ሚኒስቴር የተጎዱ ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን አሳውቋል።
በስፍራው የነበረ አንድ ጋዜጠኛ ፥ ታጣቂዎቹ አውቶማቲክ መሳሪያ እየተኮሱ መግባታቸውን ፤ የእጅ ቦምብ / ተቀጣጣይ ቦምብ ሲወረውሩም እንደነበር ገልጿል።
ጋዜጠኛው ፤ " በአዳራሹ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ለ15 እና 20 ደቂቃዎች እራሳቸውን ከጥይት ለመከላከል ወለል ላይ ተኝንተው እንደነበር በኃላ ሁኔታው ጋብ ሲል እና የፀጥታ ኃይል ሲመጣ መውጣታቸውን አስረድቷል።
የሩስያ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ድርጊቱን " የሽብር ተግባር " ብሎታል።
እስካሁን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ ወይም ሩስያ ይህ አካል ነው ያለችው የለም።
ቪድዮ ፦ ከሩስያ የማህበራዊ ሚዲያዎች

#ሞት_ተፈርዶበታል !
ከአባቱ ጋር በገባበት " #የጥቅም_ግጭት " መላው ቤተሰቦቹን በጥይት ገድሎ ሊጨርስ የነበረው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ተፈረደበት።
ተከሳሽ ከፍታ ካፋላ ይባላል።
በጋርዱላ ዞን የሃይበና ቀበሌ ነዋሪ ነው።
ግለሰቡ ቤተሰቦቹ በሚኖሩበት በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ሠገን ገነት ቀበሌ በመሄድ በ4 ቤተሰቦቹ ላይ የጥይት እሩምታ ይከፍታል።
በዚህም ሶስቱን ሲገድል አንዱን አቁስሏል።
በጥይት እሩምታ የገደላቸው ፦
- #አባቱ
- #እናቱ
- #አጎቱ ሲሆኑ የመቁሰል አደጋ የደረሰበት የ9 አመት ታናሽ ወንድሙ ነው።
ግለሰቡ ይህን ፈጽሞ ከአካባቢዉ ቢሰወርም የጸጥታ ኃይሉ ከማህበረሰቡ ጋር ተባብሮ ባደረገዉ ክትትል ከ5 ወራት በኋላ ሊያዝ ችሏል።
ፖሊስም ስራውን አጠናቆ ለፍርድ ቤት አቅርቧል።
ተከሳሹም ፤ ከወላጅ #አባቱ ጋር በገባበት ' የጥቅም ግጭት ' ምክኒያት ወንጀሉን እንደፈጸመ ለፍርድ ቤቱ አምኖ ቃሉን ሰጥቷል።
ይህም ቃሉም ከቀረበበት የሰውና የሰነድ ማስረጃ ጋር ተዳምሮ የፍርድ ሂደቱን ቀላል እንዳደረገዉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።
በዚህም በኃላ ጉዳዩን ሲመረምር የነበረዉ የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተከሳሽ ከፍታ ካፋላ #በሞት እንዲቀጣ ወስኗል።
በተከሳሹ ላይ የተጣለው #የሞት_ፍርድ በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሲጸድቅ ነው ተፈጻሚ የሚሆነው።
#TikvahEthiopiaFamilyHW