TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጥምረት የፊልም ፌስቲቫል #3ኛው ቀን መርኃግብር ዛሬም ይቀጥላል!

ዛሬ በሚኖረን መርኃግብር፦

#በአዲስ አበባ ፦  "እኝህ ጀግና ገበሬ በሳቅ ገደሉኝ እና ይኸው ተጋብተናል" የተሰኙ 4 ዶክመንተሪዎች ለዕይታ ይቀርባሉ።
📍በጣሊያን ባህል ማዕከል 🕒 ከ 11፡ 00 ሰዓት ጀምሮ በሮች ይከፈታሉ።

#በአዳማ ፦ "ኢሬቻ የሰላም እና የአብሮነት እሴት"
📍በኦሊያድ ሲኒማ 🕒 ከ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በሮች ይከፈታሉ።

#በባህርዳር ፦ "ባህላዊ የግጭት አፈታት በአባ ገዳዎች"
📍በሙሉዓለም አዳራሽ 🕒 ከ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በሮች ይከፈታሉ።
ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን 👉  https://t.iss.one/TimretEth
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጋምቤላ በጋምቤላ ክልል በተከሰተ የፀጥታ ችግር የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ። በክልሉ ሰሞኑን በተከሰተ የፀጥታ ችግር ምክንያት ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ላልተወሰነ ጊዜ የሚተገበር የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን የክልሉ ካቢኔ አሳውቋል። የክልሉ መንግሥት የፀጥታ ችግሩን መነሻ በዝርዝር ከመናገር ተቆጥቧል። ነገር ግን ከዛሬ ጀምሮ ከተመደቡ የጸጥታ ኃይል በስተቀር ከምሽቱ…
በጋምቤላ የተደረገው የሰዓት ዕላፊ ማሻሻያ እስከ ስንት ሰዓት ነው ?

በጋምቤላ ክልል በፀጥታ ችግር ሰዓት ዕላፊ ገደብ ተጥሎ እንደነበር ይታወሳል።

በክልሉ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 12:00 ሰዓት ላልተወሰነ ጊዜ የሚተገበር የሰዓት እላፊ ገደብ ነበር የተጣለው።

አሁን ላይ ግን ሁኔታዎች እየተሻሻሉ በመምጣታቸው የሰዓት ገደቡ ማሻሻያ ተደርጎበታል።

በዚህም መሰረት ፦

- የባለ ሁለትና ባለሶስት እግር ባጃጅና ሞተር ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 12:00 ስዓት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12:30 እንዲሰሩ ተብሏል።

- ሰዎች እስከ ምሽት ሶስት ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ ይችላሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert በጋምቤላ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለት ቦታዎች እንዲሰጥ ተወሰነ። በጋምቤላ ክልል ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ እና በጋምቤላ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንደሚሰጥ የክልሉ መንግስት አስታውቋል። የክልሉ መንግሥት ፤ " በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ብቻ ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው…
#Gambella

በጋምቤላ መምህራን ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ተፈታኝ ተማሪዎች " የጤና እክል " ገጥሟቸው እንደነበር የክልሉ የመንግስት አሳውቋል።

ተፈታኞቹ ትላንት ምሽት ከ1:30 ጀምሮ ወደ ጋምቤላ አጠቃላይ ሆስፒታል አቅንተው ተገቢው ህክምና እየተደረገላቸው ነው ተብሏል።

ተፈታኞቹ የገጠማቸው የጤና እክል መነሻው " የምግብ መመረዝ " አልያም " የተበላሸ ምግብ መብላት " መሆን አለመሆኑን በማጣራት ላይ ክልሉ አሳውቋል።

ሆስፒታል ከገቡ ተማሪዎች መካከል ለህይወት የሚያሰጋ የጤና እክል የደረሰባቸው እንደሌሉ የገለፀው ክልሉ አብዛኞቹ አገግመው ወደ ፈተና ማዕከላቸው መመለሳቸውን አመልክቷል።

በአሁኑ ሰዓትም ህክምና በመከታተል ላይ ያሉ ተፈታኞች እንደሚገኙ የተጠቆመ ሲሆን በህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ክልሉ አሳውቋል።

" የተፈታኝ ወላጆች ልጆቻቸው በመልካም ጤንነት ላይ የሚገኙ በመሆናቸው እንዳይደናገጡ " ያለው የጋምቤላ ክልል " ምክንያቱ ምን እንደሆነ የህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡትን መረጃ ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን " ብሏል።

በጋምቤላ ክልል በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ እና በጋምቤላ መምህራን ትምህርትና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንዲሰጥ መወሰኑ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በክልል ትግራይ የሚገኙ አባቶች የቅዱስ ሲኖዶስን ውግዘት " ቅቡልነት የለውም ፤ በጉዟችንም ላይ ምንም ተፅእኖ የለውም " አሉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በክልል ትግራይ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ጉዳይ ባካሄደው አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ይታወሳል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ እጅግ አሳዛኝ ኢ-ሲኖዶሳዊ የሆነ አስነዋሪ፣ ሕገ-ወጥ፣ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ጥሰት በመፈጸም ሲመት ፈፅመዋል ፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያንን በማታለል የክህደት እና የኑፋቄ ተግባር ፈፅመዋል ያላቸውን 4 ብፁዓን አባቶች አውግዞ፤ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር እንደለያቸው ገልጿል።

በተጨማሪ ፤ የኤጲስ ቆጶስነት ሹመት ያገኙትን 9 መነኮሳት ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸው ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት ተሽሮ በቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያ በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ አውግዞ ለይቷቸዋል፡፡

እንዲሁም አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤልና መ/ር ተስፋዬ ሐደራ ተወግዘው ከቤተክርስቲያን ተለይተዋል ብሏል።

ከዚህ ባለፈ ቅዱስ ሲኖዶስ " መንበረ ሰላማ "  የሚለው ስያሜ ሕገወጥ መሆኑን ገልጾ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ትውፊትም ሆነ በቀደምት አብያተ ክርስቲያናት ትውፊት የማይታወቅ፣ ሃይማኖታዊ መሠረት የሌለው፣ ከቀኖና የወጣ፣ አስተዳደራዊ መዋቅርን የሚያዛባ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም ብሏል።

በዚህ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ዙሪያ በትግራይ ያሉ አባቶች ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ሲኖዶሱ  ፤ በትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን መንበረ ሰላማ ቤተክህነት ብፁኣን ኣበው ፣ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ኤጲስ ቆጳሳት እና አገልጋዮች ላይ አስተላለፍኩት ያለው ውግዘት " ከንቱ እና ቅቡሉነት የሌለው " ነው ብለዋል።

" ይህ ከንቱ ውግዘት የመንበረ ሰላማ ጉዞ ላይ ምንም አይነት ተፅእኖ እንደሌለው እና ለአፍታም ቢሆን የሚቆም ነገር እንደሌለ እንገልፃለን " ብለዋል።

ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ከማዕከል የተነጠሉት በትግራይ የሚገኙት አባቶች " የትግራይ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን መንበረ ሰላማ ቤተክህነት " በሚል አቋቁመው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
#Amhara

እጅግ አስከፊ ከነበረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ገና ያላገገመው አማራ ክልል ዳግም የግጭት ቀጠና እየሆነ መምጣቱና የፀጥታውም ሁኔታ አሳሳቢ የሆነ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገልጿል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በ " ፋኖ " የታጠቁ ኃይሎች እና በ " መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች " መካከል በተከሰቱ ግጭቶች የሰዎች ህይወት አልፏል፤ ጉዳትም ደርሷል።

በተለይ ከጥቂት ወራት ወዲህ " የክልሉና የአማራ ህዝብ ህልውና ከፍተኛ አደጋ ላይ ወድቋል " ፣ " መንግሥት የክልሉን ልዩ ኃይል መልሶ ለማደራጀት የሚያደርገው እንቅስቃሴን እንቃወማለን " የሚሉ ወገኖች ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ ገብተዋል።

በዚህም በአንዳንድ አካባቢዎች አለመረጋጋቶችና የሰላም መደፍረስ እየተበራከቱ መጥተዋል።

ከሰሞኑን ግን በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ጠንከር ያሉ ከባድ የተኩስ ልውውጦች እና ግጭቶች መኖራቸውን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

ንፁሃን ዜጎች የተጎዱባቸው ቀጠናዎች ያሉ ሲሆን በተለያዩ መስመሮችም መንገዶች በመዘጋታቸው እንቅስቃሴዎች ተስተጓጉለዋል።

ጥቃት አድራሾቹ " ያልታወቁ ኃይሎች " በሚባሉ አካላትም የመንግሥት የፀጥታ እና አመራር አካላት እየተገደሉ ተገኝተዋል።

በታሪካዊቷ ጥንታዊቷ ላሊበላ አካባቢ በነበረ ግጭትም በረራ መስተጓጎሉ ተሰምቷል።

የክልሉ አስተዳደር ፤ እርስ በእርስ በመገዳደል ዘላቂ በሆነ መንገድ ክልሉ ይጎዳል እንጂ መፍትሄ አያመጣም ብሏል።

ያለው ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ሁለንተናዊ ችግር በክልሉ ይከሰታል የሚለው የክልሉ አስተዳደር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ እና በውይይት እንፍታው ሲል ጥሪ አቅርቧል።

የሀገር መከላከያ ሠራዊት በበኩሉ ፥ አባላቱ በአማራ ክልል ባሉ በሁለት ስፍራዎች ድንገተኛ ጥቃት ተፈጽሞባቸው እንደነበር አሳውቆ ፤ " በፋኖ ስም እየተንቀሳቀሱ ሰላም በሚያውኩ ላይ እርምጃ ይወሰዳል " ሲል አሳውቋል።

የሀገሪቱ ምክትል ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን ፤ በአማራ ክልል የሚታየው የፀጥታ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አመልክተው ጥያቄዎች ሁሉ በሰላማዊ መንገድ እና በውይይት ሊፈቱ ይገባል ብለዋል።

የተቃዋሚ ኃይሎች በበኩላቸው መንግሥት በክልሉ እያካሄደ ካለው ዘመቻ እንዲቆጠብ እየጠየቁ ይገኛሉ።

ለአብነት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ፤ የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር " በአማራ ሕዝብ ላይ ወረራ ፈፅሟል ብለዋል። ከዚህ ባለፈም የንፁኃን ግድያ እየፈፀመ ነው " ሲሉ ከሰዋል።

" ይህ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳስባለሁ ያሉት " የህ/ተ/ም/ቤት አባሉ ፤ መንግስት የቴሌኮም አገልግሎቶችን በመዝጋት ጭምር በአማራ ክልል በከባድ መሣሪያ ታግዞ በንፁኃን ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀመ በመሆኑ የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ እንዲሁም ሚዲያዎች እንድታወግዙና አገዛዙ ላይ ጫና እንድታሳድሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ #የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥን የሚያመልከቱ መረጃዎችን ለማግኘት ችለናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ስፔን ዜጎቿ ወደ አማራ ክልል ከመጓዝ እንዲቆጠቡ አሳሰበች።

ስፔን አዲስ አበባ ባለው ኤምባሲዋ ለዜጎቿ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ሰጥታለች።

ሀገሪቱ በአማራ ክልል በተፈጠረው አለመረጋጋት የስፔን ዜጎች ወደ አካባቢው ከመጓዝ እንዲቆጠቡ አሳስባለች።

በጥንታዊቷ እና ታሪካዊቷ " #ላሊበላ " የሚገኙ ስፔናውያን ከሆቴላቸው ወይም ከቤታቸው እንዳይወጡ እና አዲስ አበባ የሚገኘውን ኤምባሲ እንዲያነጋግሩ (0911219403) ጥሪ አቅርባለች።

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በሰላም ስምምነት እንዲቋጭ ከተደረገ በኃላ በጦርነቱ ምክንያት እጅግ ተዳክሞ የነበረው የላሊበላ የቱሪዝም እንቅስቃሴ የተወሰነ መነቃቃት ማሳየቱን ተከትሎ የተለያየ ሀገራት ዜጎች ላሊበላን ለመጎብኘት ወደ ስፍራው ሲያቀኑ ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በአማራ ክልል ብዙ አካባቢዎች የኢንተርኔት ግንኙነቶች መቋረጣቸውን አረጋግጠናል " - ካርድ

" የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል / ካርድ " በአማራ ክልል የተለያዩ አከባቢዎች የበይነመረብ አገልግሎት መቋረጡን ማረጋገጥ መቻሉን አመልክቷል።

" የበይነመረብ ግንኙነትን ማቋረጥ ግጭቶችን ለመከላከል እና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን አይበጅም " ያለው ካርድ እገዳው እንዲነሳ ጥሪ አቅርቧል።

በአማራ ክልል ብዙ አካባቢዎች የኢንተርኔት ግንኙነቶች መቋረጣቸውን ያመለከተው ካርድ  የኢንተርኔት ግንኙነቶቹ መቋረጥ ሰሞኑን ከተባባሱ ግጭቶች ጋር በተያያዘ እንደሆነ መገመት ይቻላል ብሏል።

ድርጅቱ ፤ የበይነመረብ ግንኙነቶችን ማቋረጥ ለግጭቶች መፍትሔ አያመጣም የሚል አቋሙን ከዚህ ቀደም ደጋግሞ መግለፁን አስታውሶ " ይህ እርምጃ ይልቁንም የመረጃ መታፈን ከማስከተል ባሻገር ግጭቶቹን ለመቆጣጠር የሚወሰደው እርምጃ ያልተመጣጠነ እንዲሆን ዕድል ይሰጣል " ሲል አስረድቷል።

ስለሆነም፣ መንግሥት የበይነመረብ ግንኙነቶችን ማቋረጡን እንዲያቆም እና ለግጭቶቹ ዘላቂ ፣ ሁሉን አካታች መፍትሔ እንዲያፈላልግ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia