TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ምረቃ በዛሬው ዕለት የተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ። - ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ - ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ - ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ - አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ - ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ - መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ - አሶሳ ዩኒቨርሲቲ - የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ - አርሲ ዩኒቨርሲቲ በየተለያዩ የትምህርት መስኮችና መርሀ ግብሮች ያስተማሯቸውን…
አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከአርሲ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተበረከተለት።

አንጋፋው አትሌት ፤ በአትሌቲክስ ዘርፍ ባበረከተው ሀገራዊ አስተዋፅኦ ነው የክብር ዶክትሬት የተበረከተለት።

ቀነኒሳ ሀገሩን ወክሎ በተካፈለባቸው ውድድሮች የሀገሩን #ኢትዮጵጵያን ስም ከፍ በማድረግ ታሪክ ፅፏል።

ከአትሌቲክሱ በተጨማሪ በሀገር ልማት እና በኢንቨስትመንት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል።

አትሌት ቀነኒሳ በቆጂ ሆቴል፣ በአሰላ ሆቴልና የገበያ ማዕከል፣ በአዲስ አበባ ሆቴል፣ በአዳማ የገበያ ማዕክል በማስገንባት ለአካባቢው እና ለሀገሩ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።

በዚህም ባበረከተውና እያበረከተ ባለው ስራ ከአርሲ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተበርክቶለታል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
የወላጆችን ጊዜ ቆጥቦ፤ ተማሪዎችን ከእንግልት ገላግሎ፤ የትምህርት ቤቶችን አሰራር ያዘመነውን ዘመናዊ ፤ቀላል እና ቀልጣፋ የብርሃን ስኩል ፔይ (school pay) አገልግሎት ይጠቀሙ!
#schoolpay #berhanbank #bank #finance #Stressfreebanking #bankinethiopia
#ብርሃን_ባንክ
እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በትግራይ ክልል ከነበረው ጦርነት ጋር በተያያዘ ከማዕከል ተነጥለው " የትግራይ መንበረ ሰላማ ከፍተኛ ቤተ ክህነት " በሚል እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ በትግራይ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች ከዚህ ቀደም በኣክሱም ከተማ የ10 ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ማሄዳቸው ይታወቃል። በዛሬው ዕለት ቅድስት ከተማ አክሱም ጽዮን የኤጲስ ቆጰሳቱን በአለ ሲመት እንደሚያከናውኑ አሳውቀዋል። ከትላንት በስቲያ ፤ የኢትዮጵያ…
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን " ሕገወጥ " እንደሆነ ገልጻ እንዲቆም ያሳሰበችው የትግራይ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ተፈፀመ።

" የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት " ዛሬ ሃምሌ 15 / 2015 ዓ.ም  በአክሱም ከተማ የኤጲስ ቆጶሳት በአለ ሲመት አከናውኗል።

በዚህም ፦
1. ንቡረ ዕድ መሓሪ - አቡነ ሊባኖስ
2. ቆሞስ አባ ዘሥላሴ - አቡነ ናትናኤል
3. ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ - አቡነ ኣረጋዊ
4. ቆሞስ አባ ኃ/ሚካኤል - አቡነ ዮሐንስ
5. ቆሞስ አባ ጽጌገነት - አቡነ ኣትናቴዎስ
6. አባ ኤልያስ - አቡነ ዕንባቆም ተብለው ተሰይመዋል።

ከጥቂት ቀናት በፊት በትግራይ ያሉ ብፁኣን አባቶች በትግራይ እና በውጭ ሀገር የሚያገለግሉ 10 ኤጲስ ቆጲሳትን መምረጣቸው አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሹመት እንቅስቃሴው ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ የሆነና ሕገወጥ ተግባር በመሆኑ እንዲቆም አሳስባ ነበር።

በትግራይ ባሉ የአህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንት እየተከተሉት ያለው አካሄድ ላለው ችግር መፍትሔ የማይሆን እንደሆነ በመግለፅ የፌዴራሉ እና ክልሉ መንግስት " ሕገወጡ " ን ሹመት በማስቆምና ሰላማዊ የውይይት መድረኮችን በማመቻቸት የበኩላቸውን ታሪካዊ ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርባ ነበር።

ፎቶ፦ ቴሌቪዥን ትግራይ / ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተፈታኞች በአካልም ይሁን በስነልቦና እራሳችሁን ዝግጁ አድርጉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መርሃ ግብርን ይፋ አድርጓል። በዚህም ፥ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሐምሌ 16 እና 17/2015 ዓ.ም ወደተመደቡበት ተቋም ይገባሉ። ሐምሌ 18/2015 ዓ.ም ገልጻ ይሰጣቸዋል። ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015…
" የፌዴራል ፖሊስ ለልጆቻችሁ #ሙሉ_ኃላፊነት ይወስዳል ፤ አስተማማኝ ጥበቃም ያደርግላቸዋል " - የጋምቤላ ትምህርት ቢሮ

ከሰሞኑን በጋምቤላ ክልል የፀጥታ ችግር መከሰቱና የሰዎች ህይወት ማለፉ ፣ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎም በክልሉ የሰዓት እላፊ ገደብ ታውጆ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

ካለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እንዴት ሊሆን ነው ? የሚለው የብዙሃን ጥያቄ ነው።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ፤ ሰሞነኛው የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ አንፃራዊ ሰላም እየታየበት በመሆኑ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፉ ብሔራዊ ፈተና ላይ እንዲሰጥ #ተወስኗል ሲል አሳውቋል።

ቢሮ ፤ ፈተናው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እንደሚሰጥ አረጋግጧል።

ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ በሚኖራቸው ቆይታ አስተማማኝ ጥበቃ ይደረግላቸዋልም ብሏል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ፤ " ሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ለማከናወን የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል " ያለ ሲሆን በዚህም መሰረት ወላጆች ተፈታኝ ልጆቻቸውን በወረዳ ማዕከል በተዘጋጁ የትራንስፖርት አገልግሎት በመጠቀም ወደ መፈተኛ ዩኒቨርስቲ እንዲልኩ ጥሪ አቅርቧል።

ቢሮው ፤ ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ በሚኖራቸው ቆይታ የፌዴራል ፖሊስ ሙሉ ኃላፊነት እንደሚወስድ እና አስተማማኝ ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ታጣቂዎቹ በለሊት ከነ #መሳሪያቸው ወደ ጫካ ገብተዋል " - ከንቲባ አቶ ጊሳ ዙፋህ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፤ ግልገል በለስ " የሰላም ጥሪ ተቀብለው መጡ " የተባሉ ታጣቂዎች ከነትጥቃቸው ወደ ጫካ ተመልሰው ገብተዋል።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ የግልገል በለስ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጊሳ ዙፋህ ለዶቼ ቨለ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

ከንቲባው ፤ ከሚያዚያ 24 ጀምሮ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የመጡ የሰላም ተመላሾች በከተማው ለ2 ወራት ያህል መኖራቸውን ገልጸዋል።

ከዛሬ ሁለት ቀን በፊት ወደ ተሀድሶ ስልጠና እንዲገቡ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ባለበት ሰዓት ባልታወቀ ምክንያት ታጣቂዎቹ በለሊት ከነ መሳሪያአቸው ወደ ጫካ መግባታቸውን አብራርተዋል፡፡

ታጣቂዎቹ በሰላማዊ መንገድ እንዲመለሱ ለማደረግ ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በመተከል ዞን ውስጥ የተከሰቱ የጸጥታ ችግሮችን እና የታጣቂዎችን እንቅስቃሴ ከፓርቲው ጋር ለማገናኘት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን እቃወማለሁ ብሏል።

ፓርቲው ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ሀይል እንደሌለው ገልጿል።

በቅርብ " የሰላም ተመላሽ " ተብለድ በመተከል ዞን ግልገል በለስ የነበሩ ታጥቂዎችን የጉህዴን ታጣቂዎች ናቸው በማለት " በድርጅቱ ስም መነገድ የሚፈልጉ " አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ፓርቲው አሳስቧል።

በካምፕ ውስጥ የነበሩ ከአንድ መቶ የሚበልጡ የሰላም ተመላሽ የተባሉ ታጣቂዎች ወደ ጫካ መመለሳቸውን ፓርቲው ገልጿል።
 
ፓርቲው፤ ከጥቅምት 9/2015 ዓ.ም አንስቶ ከመንግስት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሰረት በስሙ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎቹን በሰላማዊ መንገድ ትጥቅ እንዲፈቱ ማድረጉን አስረድቷል።

በተቀመጠው ስምምነት መሰረት በተዘጋጁ  ዘርፎች ወደ ስራ መሰማራታቸውንም አመልክቷታ።

በአሁኑ ጊዜ በፓርቲው ስም ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ሐይል አለመኖሩን አሳውቋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከፓርቲያቸው ጋር ግንኙነት የሌላቸው በርካታ ታጣቂዎች ከመንግስት ጋር በመስማማት በሰላማዊ መንገድ ወደ ካምፒ መግባታቸውን ያሳወቀው ጉህዴን " በሚያዚያ ወር መጨረሻም ወደ ግልገል በለስ ከተማ የገቡ ታጣቂዎች ከፓርቲው ጋር ግንኙነት የለላቸው እና መንግስት ያደረገላቸውን ሰላማዊ ጥሪ የተቀበሉ  ታጣቂዎች ናቸው " ብሏል።

በዞኑ እና ሌሎች ስፍራዎች የሚከሰቱ የጸጥታ ችግሮችን ከፓርቲው ጋር ለማገናኘት የሚደረጉ ጥረቶችን ተቀባይነት የላቸውም ያለው ጉህዴን " በታጣቂዎች ለሚደርሱት ጥቃቶችም ድርጅቱ ኃላፊነት አይወስድም " ሲል አስረግጧል።

በግልገል በለስ ከተማ ሰነ 30 ቀን 2015 ዓ.ም በታጣቂዎች በደረሰው ጥቃት ጸጥታ ሐይሎችን ጨምሮ 11 ሰዎች ህይወት ማለፉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል፡፡

#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ተፈታኞች በአካልም ይሁን በስነልቦና እራሳችሁን ዝግጁ አድርጉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መርሃ ግብርን ይፋ አድርጓል። በዚህም ፥ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሐምሌ 16 እና 17/2015 ዓ.ም ወደተመደቡበት ተቋም ይገባሉ። ሐምሌ 18/2015 ዓ.ም ገልጻ ይሰጣቸዋል። ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015…
ተፈታኞች ከነገ ጀምሮ ይገባሉ።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከነገ ሐምሌ 16 ጀምሮ ወደ ተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ።

ተፈታኝ ተማሪዎች ከሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች ወደ ተመደቡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች የሚጓዙት በተዘጋጅላቸው ተሽከርካሪዎች ነው።

ተፈታኞች ዩኒፎርማቸውን መልበስ ፤ ብርድልብስና አንሶላ ይዘው መገኝት ይጠበቅባቸዋል። 

ወደ መፈተኛ ተቋማት ቆሎ፣ ጭኮ፣ በሶ የመሳሰሉ ደረቅ ምግቦችን ይዞ መግባት የሚፈቀድ ሲሆን የቴክኖሎጂ ውጤቶች፣ ሞባይል፣ አይፓድ፣ ላፕቶፕ የመሳሰሉ እንዲሁም ማንኛውም ጌጣጌጥ ይዞ መግባት ፈፅሞ የተከለከለ ነው።

ተማሪዎቹ ከቤታቸው ሲወጡ፦
- መታወቂያ ፣
- አድሚሽን ካርድ
- የት/ቤት ዩኒፎርም መያዛቸውን እንዳይረሱ ፤ ወላጆችም ይህንን እንዲያስታውሷቸው ጥሪ ቀርቧል።

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በከፍተኛ የመንግሥት የትምህርት ተቋማት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ይሰጣል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#CBE

ግብርዎን በሲቢኢ ብር እንዴት ይከፍላሉ?
================================
ለአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ እና ሶማሌ ክልል ግብር ከፋዮች

ከግብር ሰብሳቢው ተቋም
• የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
• የገንዘብ መጠን እና
• የክፍያ ማዘዣ ቁጥር የያዘ መልእክት ሲደርስዎት

ወደ *847# በመደወል ቅደም ተከተሉን ጠብቀው ግብርዎን በቀላሉ ይክፈሉ፡፡
#MyWish

አስተማማኝ የሆነውንና ቱርክ ሰራሹን ኢሳን ሲልድ ባትሪን በተለያዩ አማራጮች ማለትም በ12V35AH፣ በ12V45AH፣ በ12V55AH፣ በ12V60AH፣ በ12V70AH፣ በ12V90AH፣ በ12V100AH፣በ12V120AH እና በ12V150AH በጅምላና በችርቻሮ በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡
0910041280  0911135133  0921612272  0911159234   0984733988  0941473413
ዋና መስሪያ ቤት፡ ሀይሌ ጋርመንት ወደለቡ መብራት በሚወስደው መንገድ ቅርንጫፍ፡ ወሎ ሰፈር ጎርጎሪዮስ አደባባይ አጠገብ
ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ 
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ: https://t.iss.one/MYWISHENT
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ወደየተመደቡበት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዛሬ መግባት ጀምረዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች እስከ ነገ ሐምሌ 17/2015 ዓ.ም ወደተመደቡበት ተቋም ተጠቃለው ይገባሉ።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ 21/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

@tikvahuniversity