TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ይነበብ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመራቸው ስራዎች አንዱ የሆነ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከነገ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ/ም ይጀምራል። በዚህ ፈተና ወቅት ከተማሪዎች እና ከፈታኞች ምን እጠበቃል ? [ ከተፈታኞች የሚጠበቅ ] - ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍላቸው ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ…
#ይነበብ2

የመውጫ ፈተና በሚሰጥባቸው ቀናት ከሚኖሩ ዲስፕሊንና እና ፕሮቶኮል መካከል ፦

- ከተፈቀደላቸው የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ለእለቱና ለዛ ፈተና ከተመደቡ አስተባባሪዎች፣ ለፈተናው ከተመደቡ ፈታኞች ውጭ የትኛውም አካል ወደ መፈተኛ ክፍል መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው።

- ፈተናው በኦንላይን ስለሚሰጥ የአይሲቲ ሙያተኞች በመፈተኛ ክፍሎች አቅራቢያ በመሆን ድጋፍ ይሰጣሉ፡፡

- የፀጥታ ሃይል ወደ መፈተኛ ክፍል እንዲገባ አስገዳጅ ሁኔታ ከተፈጠረ በማንኛውም ጊዜ ሊገባ ይችላል፡፡

- የዩኒቨርስቲ የበላይ ኃላፊዎችን ጨምሮ የትኛውም አካል በምንም ሁኔታ ስልክ፣ ስማርት ዋች፣ ታብሌት እና ተመሳሳይ ቁሶችን ይዞ ወደ መፈተኛ ክፍል መግባት አይችልም፡፡

- የአይሲቲ ሙያተኞች በመፈተኛ ክፍሎች የሚስጡት ድጋፍ ከትምህርት ሚኒስቴር ባልደረቦች ወይም ከዩኒቨርስቲው አመራር ድጋፍና አመራር ማግኘትን ስለሚያካትት በልዩ ሁኔታ በዩኒቨርስቲው ተመዝግቦ የሚያዝና የሚታወቅ ቁጥር ያለው ስልክ ይዘው ወደ መፈተኛ አዳራሽ እንዲገቡ ሊፈቀድ ይችላል፡፡

- በአንዳንድ ፕሮግራሞች #ካልኩሌተር ማምጣት ይፈቀዳል፡፡ በተጨማሪም በአንዳንድ ፕሮግራሞች ለማስልያ የሚረዳ ንፁህ ወረቀት በዩኒቨርሰቲዎች በኩል ሊፈቀድ ይችላል፡፡ ይህም ሆኖ ስልክ፣ ስማርት ዋች፤ ታብሌት እና ተመሳሳይ ቁሶችን እንደ ካልኩሌተር መጠቀም ፈፅሞ አይፈቀደም፡፡ ሥራ ላይ የሚውሉ ካልኩሌተሮች የተራቀቁና ፕሮግራ መብል እንዳይሆነ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡

- በማንኛውም ወቅት ከተፈቀደላቸውና ለድጋፍ ከተመደቡ የአይ.ሲ.ቲ ባለሙያዎች በስተቀር የተፈታኙን መፈተኛ ኮምፒውተር መንካት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

(ተጨማሪ ከላይ ያንብቡ)

በድጋሚ መልካም ፈተና !

@tikvahethiopia
#coop

👉🏼 @coopbankoromia
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክን የቴሌግራም ቻነል በመቀላቀል የሚከተሉትን ያግኙ!
- የባንክ መረጃዎች
- የፋይናንስ ግንዛቤ
- የባንኩን የሥራ ማስታወቂያዎች 🔎
- የውድድር ተሳትፎና ስጦታዎች 🎁
t.iss.one/coopbankoromia
#ኤክሶደስ

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦
- ለአንገት፣ ለትክሻ፣ ለወገብ ህመም ፣ ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ   ችግር
- ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል
- ለስፖርታዊ ጉዳቶች፣ ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች
- በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ!

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት፤ አድራሻችን 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን። ስልክ ቁጥር 0979099909/ 0911039377
  √በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ 13 አባላት ያሉት የልዑካን ቡድን ሐምሌ…
#መቐለ

በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ ልዑካን ቡድን መቐለ ገብቷል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለክልል ትግራይ የሰብዐዊ ድጋፍ እንዲደረግና ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በትግራይ ክልል ከሚገኙ ብፁዓን አባቶች ጋር የሰላም ውይይት እንዲያደረጉ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል።

በዚህ መሰረት የልዑካን ቡድን ዛሬ ክልል ትግራይ መቐለ ከተማ ገብቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መቐለ በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ ልዑካን ቡድን መቐለ ገብቷል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለክልል ትግራይ የሰብዐዊ ድጋፍ እንዲደረግና ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በትግራይ ክልል ከሚገኙ ብፁዓን አባቶች ጋር የሰላም ውይይት እንዲያደረጉ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። በዚህ መሰረት የልዑካን ቡድን ዛሬ ክልል ትግራይ መቐለ ከተማ ገብቷል። @tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሰላም ልኡካኑ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በመቐለ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት ተገናኝተዋል።

Credit : EOTC TV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሰላም ልኡካኑ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ከአቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በመቐለ አሉላ አባ ነጋ ኤርፖርት ተገናኝተዋል። Credit : EOTC TV @tikvahethiopia
ልዑካን ቡድኑ በመቐለ የሚኖረው ቆይታ ምን ይመስላል ?

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክሳዊት ቤተክርስትያን ሲኖዶስ ልኡክ ዛሬ ጥዋት መቐለ ገብቷል።

ቆይታው ለሁለት ቀን ይሆናል። 

ለልዑኩ በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ አቀባበል ተደርጓል።

ቀጥሎ በመቐለ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራ ፀሎት ይከናወናል።

በመቀጠል ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅህፈት ቤት በመጓዝ ከሲኖዶስ የተላከ ሰብአዊ እርዳታ ካስረከቡ በኋላ አጭር ውይይት ይካሄዳል።

ውይይቱ በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ እና የትግራይ አብያተ ክርስትያናት አባቶች አንድነት መቀጠልና ማጠናከር ላይ ያተኩራል።

ከውይይቱ በኋላ በጦትነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች በተጠለሉበት በተለምዶ በመቐለ 70 ካሬ ተብሎ የሚጠራው ቦታ ጉብኝት ይካሄዳል።

ጉብኝቱ ተፈናቃዮቹ በቀጣይ እንዲቋቋሙ የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስትያን አስተዋፅኦ ምን መሆን እንዳለበት የሚያመላክት ሆኖ አጭር ቡራኬና መግለጫ በቅዱስ ፓትርያርኩ ይቀርባል።

ቀጥሎ ከትግራይ ብፁአን አበውና የኦርቶዶክሳዊ ቤተክርስተያን አመራሮች ግንኙነትና ውይይት ይካሄዳል።

በቦታው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ሃይማኖታዊ አስተምህሮና ምክር ይሰጣል።

የዛሬ የሰኞ ሃምሌ 3 /2015 ዓ.ም ጉብኝት ማጠቃለያ በዚህ ይሆናል።

ነገ ማክሰኞ ሃምሌ 4 /2015 ዓ.ም ጥዋት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የጉብኝቱ ዓላማና ቆይታ የሚመለከት ለጊዚያዊ አስተዳደሩ አመራሮችና ለብፁአን አበው መግለጫ ያቀርባሉ።

መግለጫው ተከትሎ ውይይት ከተካሄደ በኋላ ጉብኝቱ ይጠናቀቃል።

ከጉብኝቱ ማጠቃለያ በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራው ልኡክ ወደ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ሽኝት ይደረግለታል።

መረጃው የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE አገር አቀፍ ፈተናዎች የሚሰጡባቸው እና የምረቃ ቀናት እንዲሁም የሬሜዲያ ፈተና ወጤት አያያዝ ላይ ቅያሪ ተደርጓል። ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ/ም ያስተላለፈውን ሴርኩላር በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልል ት/ቢሮ አመራሮች ጋር በድጋሚ ግንቦት 22 ቀን 2015 በበይነ-መረብ ውይይት አድርጓል። በውይይቱ መሰረትም ፦ - ፈተናዎች የሚሰጡባቸው ቀናት፣ - የተማሪዎች ምረቃ…
" . . . ሁሉም ለምረቃ ብቁ የሆነ ዕጩ ተመራቂ ተማሪ በምርቃት መርሃ ግብር ላይ ይሳተፋል " - የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት

' ሁሉም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ' በተቋማቸው የምርቃት መርሃ ግብር ላይ እንደሚሳተፉ ተገለጸ።

መንግሥት ከዚህ ቀደም ወስዶት በነበረው ውሳኔ ላይ ማሻሻያ በማድረግ፤ “የመውጫ ፈተናን #ያላለፉ ተማሪዎችም በተቋማቸው የምርቃት ፕሮግራም ላይ እንደሚሳተፉ” የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም ከግማሽ በላይ ጠቅላላ ድምር ውጤት (CGPA 2.00>) ያላቸው ተማሪዎች የምርቃት መርሃ ግብር ላይ ይሳተፉ የነበረ መሆኑን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት አስታውሷል።

አሁንም በተመሳሳይ የመውጫ ፈተናውን የማያልፉ ተማሪዎች የምርቃት መርሃ ግብር ላይ የሚሳተፉ ሲሆን ዲግሪ ለመውሰድ መሟላት የሚገባቸውን እንዲያሟሉ ይጠበቃል ብሏል።

የመውጫ ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች ለምዘና ብቁ ሲሆኑ በየሦስት ወሩ መፈተን እንደሚችሉም ህብረቱ ገልጿል።

ድጋሚ የመፈተን ፍላጎት የሌለው እጩ ምሩቅ በደረጃ ዝቅ ያለ የት/ት ማስረጃ መውሰድ እንደሚችል በመመሪያ መቀመጡንም አሳውቋል።

ያለገደብ ድጋሚ የመፈተን ፍላጎት የሌላቸው ዕጩ ምሩቃን በደረጃ ዝቅ ያለ የትምህርት ማስረጃ መውሰድ እንደሚችሉ በመመሪያ መቀመጡን ህብረቱ የላከልን መግለጫ ያሳያል።

የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች በትምህርት ማስረጃቸው ላይ ከ100 ያመጡት ውጤት የሚገለፀው በጊዜያዊው ማስረጃቸው ላይ ሳይሆን በትራንስክሪፕት / የወጪ መጋራታቸውን ከፍለው ሲያጠናቅቁ በሚሰጣቸው፤ የወሰዱትን የትምህርት አይነቶች ከነውጤታቸው በሚያሳየው ማስረጃ ላይ መሆኑን ህብረቱ ጠቁሟል።

በሌላ በኩል ዕጩ ተመራቂ ተፈታኞች በመውጫ ፈተና ወቅት ተከታዮቹን ጥንቃቄዎች እንዲያደርጉ አሳስቧል።

- የሚፈተኑበትን ኮምፒውተር ፈተና ከመጀመሩ በፊት ሙሉ አገልግሎት እንደሚሰጥ ፈትሸው እንዲጠቀሙ።

- ፈተናውን በሚሰሩበት ወቅት የኮምፒውተር ገመዶች በሰውነታቸውም ሆነ በሌላ ነገሮች እንዳይነኩ እና እንዳይቋረጡ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ።

- ወደ መፈተኛ ክፍሎች ሲገቡና እና ፈተናው በሚሰጥበት ጊዜ መመሪያዎችን እንዲያከብሩ።

- ምዘናው በበይነመረብ የሚሰጥ እንደመሆኑ በፈተናው ወቅት ችግሮች ካጋጠሙም ወድያው መፍታት ስለሚቻል እንከን ሲያጋጥማቸው በየመፈተኛ አዳራሹ ለተመደቡ የICT ባለሙያዎች በፍጥነት እንዲያሳውቁ፤

- የሚያጋጥሟቸው የትኛውም ተግዳሮቶች በግቢያቸው ላለው ህብረት በማመልከት ከግቢው አቅም በላይ ከሆነ በሚመለከተው አካል እንዲፈታ የሚደረግ መሆኑን አስገንዝቧል።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" . . . ሁሉም ለምረቃ ብቁ የሆነ ዕጩ ተመራቂ ተማሪ በምርቃት መርሃ ግብር ላይ ይሳተፋል " - የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ' ሁሉም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች ' በተቋማቸው የምርቃት መርሃ ግብር ላይ እንደሚሳተፉ ተገለጸ። መንግሥት ከዚህ ቀደም ወስዶት በነበረው ውሳኔ ላይ ማሻሻያ በማድረግ፤ “የመውጫ ፈተናን #ያላለፉ ተማሪዎችም በተቋማቸው የምርቃት ፕሮግራም ላይ እንደሚሳተፉ”…
ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም ዕጩ ምሩቃን ላይ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው ይህ የመውጫ ፈተና ከቀናት በፊት ለጤና ተማሪዎች መሰጠቱ ይታወሳል።

ዛሬ ደግሞ በተለያዩ የትምህርት መርሀግብሮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ዕጩ ምሩቃን ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ።

የመውጫ ፈተናው እስከ ሐምሌ 8 /2015 ድረስ መሰጠቱን የሚቀጥል ሲሆን የፈተናው ውጤት በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ምናልባትም ፤ ዕጩ ምሩቃን ይህንን ፈተና ባያልፉ ያለገደብ ደጋግመው ፈተናውን ወውሰድ ይችላሉ።

አሁን ባለው ሁኔታ ትምህርት ሚኒስቴር ይህን ፈተና በዓመት ሁለት ጊዜ ለመስጠት ያቀደ ሲሆን ቀጣዩ ፈተና ጥር / የካቲት ወር ለመስጠት ታስቧል።

ተፈታኞች ዳግም ፈተና ለመውሰድ መጀመሪያ ሲማሩበት ወደነበረበት ተቋም መሄድ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት አካባቢ ባሉ ተቋማት ፈተናውን እንደሚወስዱ የሚደረግበት ሁኔታ ይኖራል።

በሌላ በኩል ዕጩ ምሩቃን ይህን ፈተና ቢየልፉም ባያልፉም በተቋማቸውን የሴኔት አሰራር መሰረት ለምረቃ ብቁ ሆነው ከተገኙ በምረቃ መርሀግብር ላይ መሳተፍ ይችላሉ።

ፎቶ ፦ ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እና ከደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተላከ

@tikvahethiopia