TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
አንድ ዓመት ስለደፈነው የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፣ ህወሓት እና ሀገራት ምን አሉ ? የኢትዮጵያ መንግሥት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ የፕሪቶሪያው ግጭት የማስቆም ስምምነት ዋና ዉጤት " የጦር መሣሪያ ላንቃ መዘጋቱ " እንደሆነ አሳውቋል። ሚኒስቴር ከግጭት ማቆሙ ስምምነት በኋላ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች የምትጠቀስበት…
#Update

የኢትዮጵያ መንግሥት የኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት አንደኛ ዓመት በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህም መግለጫ የሰላም ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ እንዲከበር ቁርጠኛ መሆኑን አሳውቋል።

በአከራካሪ ቦታዎች ተፈናቃዮች እንዲመለሱና በህገመንግቱ መሰረት ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ አቋም ይዞ ተግባር ላይ እንዳለ አመልክቷል።

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ፤ መንግሥት በጦርነቱ የመጨረሻ ወቅት ምንም እንኳን ሁሉን ነገር በኃይል ለመፈፀም የሚያስችል ወታደራዊ ቁመና የነበረው ቢሆንም ጦርነቱ በሰላም ስምምነት ቢቋጭ ሀገርን አትራፊ የሚያደርግ መሆኑ ስለታመነበት የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እንዲፈረም መደረጉን አስታውሷል።

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ውሳኔ " ሀገርን ለመገንባትና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለመገንባት ሲባል የተከፈለ መሥዋዕትነት ነው " ብሎታል።

ከሰላም ስምምነቱ በኋላ መንግሥት በሆደ ሰፊነትና ቁስሉ እንዲሽር ካለው ፍላጎት ረጅም ርቀት መጓዙን ገልጿል። ወደ ትግራይ በአፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የተመራ ልዑክ መላኩ ፤ በፍጥነት የቴሌኮሚኒኬሽን፣ የባንክ ፣ የአውሮፕላን አገልግሎት መጀመሩን በማሳያነት አንስቷል።

በተጨማሪም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በተመሠረተ ጊዜ መሳሳብና መጓተትን ለማስቀረት ሲባል የአመራሩን ድርሻ ክልሉ እንዲወስድ ተደርጎ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፋታ አግኝቶ ፊቱን ወደ ሰላምና ልማት እንዲያዞር ተደርጓል ብሏል።

የኮሚኒኬሽን አገልግሎቱ በዚህ መግለጫው ፤ የፌዴራል መንግሥት አንዳንድ ነገሮችን እያገዘ ፤ አንዳንድ ነገሮችን ችሎ እያለፈ፣  አንዳንድ ነገሮችን እየመከረ አንዳንድ ነገሮችንም ራሱ እየሠራ የሰላም ስምምነቱ በተሟላ መልኩ በሂደት እንዲፈጸም ለማድረግ መሞከሩን አመልክቷል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአንዳንድ ነገሮች ወደኋላ እየቀረና ስምምነቱን በተሟላ ሁኔታ ሳይፈጽም እያነከሰ ለክልሉ የሚደረገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ የፌዴራል መንግሥቱ እንዳላቋረጠ በመግለጫው ተገልጿል።

መግለጫው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በምን በምን ጉዳዮች ወደኃላ እንደቀረ በግልፅና በዝርዝር አልገለጸም።

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ፤ አከራካሪ የሚባሉ አካባቢዎችን በተመለከተ የፌዴራል መንግሥቱ አቋም ወስዶ እንደሰራ እንደሆነም ይፋ አድርጓል።

" የፌዴራል መንግሥት በዚህ ረገድ ያለው አቋም ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጥ፣ ሁሉንም ወገን በሚጠቅም መንገድ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትና ብልጽግና በሚያረጋግጥ መንገድ መፍትሔ መሰጠት አለበት " የሚል እንደሆነ አመላክቷል።

🔹ክረምት ደርሶ የእርሻ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ተፈናቃዮች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ፤

🔹የአካባቢ ነዋሪዎች #በመረጧቸው አካላት እንዲተዳደሩ፤

🔹በመጨረሻም ደረጃ በደረጃ በሕገ መንግሥቱ መሠረት #ሕዝበ_ውሳኔ እንዲደረግ አቅጣጫ መቀመጡንና ይሄንንም ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ አሳውቋል።

" ይህ ሁሉ ቢደረግም እንኳን በዚያኛው ወገን እግር የመጎተት አዝማሚያ ይታያል፡፡ " ያለው መግለጫ " ይህ ግን ዘላቂ ሰላምን፣ ብልጽግናንና የሕዝቦችን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት አያረጋግጥም ብሏል።

የፌዴራል መንግሥት የፕሪቶርያውን ስምምነት በተመለከተ ከሚጠበቅበት በላይ መጓዙን፤ በዚህም ለሰላም ያለውን ጽኑ አቋም ደጋግሞ ማሳየቱን የኮሚኒኬሽን አገልግሎት አመልክቷል።

የፕሪቶርያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲከበር መንግሥት አሁንም ቁርጠኛ አቋም እንዳለው
ሁሉም አካላት ተመሳሳይ ቁርጠኝት በማሳየት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia