TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ExodusPhysiotherapy

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦
- ለአንገት፣ለትክሻ፣ለወገብ ህመም;ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ችግር፣ ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል፣ ለስፖርታዊ ጉዳቶች ፣ ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች ፣ በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ !

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ     #ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት
አድራሻችን ፦ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን።

ስልክ ፦ 0979099909/ 0911039377
በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ምዕራባውያን ሚዲያዎች ተሸንፈዋል " - ኤርዶጋን

የቱርክ ጠቅላይ ምርጫ ካውንስል የመጀመሪያ ደረጃ የምርጫ ውጤት የአሁኑ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ምርጫውን #ማሸነፋቸውን አመልክቷል።

ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ምርጫውን ማሸነፋቸውን ተከትሎ በአንካራ ለደጋፊዎቻቸው ንግግር አድርገዋል።

ምን አሉ ?

ፕሬዜዳንቱ በንግግራቸው " ዛሬ ማንም የተሸነፈ የለም ሁሉም 85 ሚሊዮን ህዝብ አሸንፏል። " ያሉ ሲሆን " አሁን ጊዜው የአንድነት፣ በአገራዊ ግቦቻችን እና ሀገራዊ ህልሞቻችን ዙሪያ መዋሃድ ነው " ብለዋል።

በንግግራቸው የምዕራባውያን ሚዲያዎች እሳቸውን " ለማጥፋት " ሲሰሩ እንደነበር በመጠቆም ፤ " የምዕራባውያን ሚዲያዎች ተሸንፈዋል " ሲሉ ተደምጠዋል።

ኤርዶጋን በቱርክ በዋጋ ንረት ምክንያት የተከሰቱ ችግሮችን መፍታት፣ ከምንም ነገር በላይ " በጣም አስቸኳይ " እና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን በንግግራቸው አንስተዋል።

@tikvahethiopia
#UNMAS

ፈንጂዎችን እና ሌሎች የጦር መሣሪያ ቅሪቶችን የማስወገድ ተልዕኮ የተሰጠው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) ፈንጂ ማስወገድ አገልግሎት (UNMAS) በዋናነት በትግራይ ክልል እንዲሁም ጦርነት በተካሄደባቸው አዋሳኝ የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች እንዲሰማራ የኢትዮጵያ መንግሥት ፈቅዷል።

ፈንጂዎችና ሌሎች ያልፈነዱ የጦር መሣሪያ ቅሪቶች ጦርነት በተካሄደባቸው የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች፣ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እያደረሱ በመሆኑ አካባቢዎችን ከፈንጂዎች ለማጽዳት እንዲቻል፣ የተመድ ፈንጂ ማስወገድ አገልግሎት እንዲሰማራ መፈቀዱን የአፍሪካ ኅብረት መረጃ ያመለክታል።

የተመድ ፈንጂ ማስወገድ አገልግሎት በቅርቡ በመቐለ ከተማ ቢሮውን እንደሚከፍትና ዋና መቀመጫውን በመቐለ አድርጎ በሁሉም ጦርነቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ኃላፊነቱን ለመወጣት እንደሚሰማራ ተነግሯል።

በዚህ ወር በአፋር ክልል በፈነዳ የወደቀ የሞርታር ጥይት የአራት ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን በትግራይ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል 300 በሚሆኑት ውስጥ በርካታ የጦር መሳሪያ ቅሪቶች ተገኝተዋል።

Via Ethiopian Reporter

@tikvahethiopia
" ... በከተማው የንጥቂያ እና ዝርፊያ ወንጀሎች #መባባስ በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ እያስነሳ ነው " - የጋምቤላ ፖሊስ

በጋምቤላ ከተማ በሞተር ሳይክሎች ላይ የሰዓት ገደብ ተጣለ።

በጋምቤላ ከተማ በተሽከርካሪ የሚፈፀም ስርቆትና ዝርፊያን ለመከላከል ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ድረስ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክሎች ላይ እገዳ መጣሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰናይ አኩዎር ፤ በከተማው የንጥቂያና ዝርፊያ ወንጀሎች #መባባስ በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ እያስነሳ ነው ብለዋል።

በከተማዋ እየተስፋፋ በመጣው የዝርፊያና መሰል ወንጀሎች በዋናነት ተጠቂዎቹ ሴቶችና አቅመ ደካሞች እንደሆኑ ገልፀው ወንጀሎቹን ለማስቀረት የፀጥታ ሀይሉ የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ ተናግረዋል።

በተለይም በከተማው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክሎችን በመጠቀም የተንቀሳቃሽ የእጅ ስልክ፣ ቦርሳና መሰል ንብረቶችን በመንጠቅና በመዝረፍ የተሰማሩ እንዳሉ በተደረገው ክትትል ለማወቅ መቻሉን አስረድተዋል።

በመሆኑም እነዚህንና መሰል ወንጀሎችን ለመከላከል ሲባል የፀጥታ ቴክኒክ ኮሚቴ በወሰነው ውሳኔ መሰረት ከግንቦት 20 /2015 ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክሎች እንዳይንቀሳቀሱ እገዳ መጣሉን ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

መረጃው የክልሉ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " አዲስ ተሽከርካሪዎች ገበያ ላይ የሚሸጡበት ዋጋ እና የሚቆርጡት ደረሰኝ ሰፊ ልዩነት እንዳለው በጥናት አረጋግጠናል " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጠን ጋር በመሆን በተሽከርካሪዎች ግብይትና አሰራር ዙሪያ ትላንት መግለጫ ሰጥቶ ነበር። በመግለጫው የተሽከርካሪዎች ግብይት መሬት ላይ ያለው…
#ይወረሳሉ !

" በሕገወጥ መንገድ የገቡ መኪናዎች #ይወረሳሉ " - የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን

ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ የገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ ርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታውቋል።

በሕገወጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉ መኪናዎችን የመለየት ሥራ መሰራት ከተጀመረ አንድ ወር ሆኖታል ተብሏል።

ባለሥልጣኑ ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ባደረገው ጥናት በባለሥልጣኑ የሚመዘገበው የገንዘብ መጠን እና ለገቢዎች ቢሮ የሚቆረጠው ደረሰኝ ተመሳሳይ ያለመሆን ሁኔታዎች መኖራቸው አመላክቷል።

በዚህም በተለይ የአዲስ ተሽከርካሪዎች ዋጋ የሚቆረጥበት ደረሰኝና ገዢዎች ለመኪናው የሚከፍሉት ዋጋ ሰፊ ልዩነት ያለው መሆኑ ተረጋግጧል።

መንግሥት ከተሽከርካሪዎች ግዥና ሽያጭ ማግኘት የሚገባውን የታክስ ገቢ እያገኘ አይደለም ያለው ባለስልጣን መ/ቤቱ ይህንን እና መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ በሕገወጥ መንገድ የገቡ መኪናዎችን የመለየት ሥራ ተጀምሯል ብሏል።

ተቋሙ በተለያዩ ጊዜያት ሁለት አይነት ሕገወጥ ተግባራት እንደሚያጋጥሙት ገልጿል እነዚህም ፦
- ከክልል በዝውውር የሚመጡ መኪናዎች ላይና
- በተጭበረበረ ሰነድ የተመዘገቡ መኪናዎች ናቸው።

ይህንን ለመከላከል የሚያግዝ ዘመናዊ ሥርዓት የመኪናዎቹን ሕጋዊነት የማጣራት ሥራ እየተሠራ መሆኑን አሳውቋል።

የማጣራት ሥራው የሚሠራው ካለፉት ዘጠኝ ዓመታት ጀምሮ ሲሆን ከዚህ በፊት አንድ የመኪና ሻጭ በስሙ የነበረውን መኪና ለሌላ ሰው ሲያስተላልፍ የማጣራት ሥራ እንዳልተሠራ እና በዚህም መንግሥት ማግኘት የሚገባውን ታክስ እንዳላገኘ ተገልጿል።

አሁን ግን ከጉሙሩክ ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን አዲስ ሥርዓት መዘርጋት ተችሏል ተብሏል።

ሥርዓቱም መንግሥት ከተሽከርካሪዎች ማግኘት የሚገባውን ታክስ እንዲያገኝ ከማድረግ ባለፈ መኪና ገዢዎች እንዳይጭበረበሩ እና መንግሥት ሕገወጥነትን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት የሚያጠናክር እንደሆነ ተገልጿል።

በሂደቱም በሕገወጥ መንገድ የገቡ መኪናዎች #እንደሚወረሱ ባለስልጣን መ/ቤቱ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ፤ የአዲስ መኪና ገዢዎች የሚከፍሉት ዋጋ በደረሰኙ ላይ መጠቀሱን በማረጋገጥ ሊገዙ ይገባል ብሏል።

ይህንን ማድረግ ለገዢው በርካታ ጠቀሜታ የሚያስገኝ ከመሆኑ ባለፈ የሚሰበሰበው ገቢ ለከተማዋ መሠረተ ልማት የሚውል በመሆኑ በኃላፊነት ሊታይ እንደሚገባ አሳስቧል።

#ኢፕድ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጋምቤላ 10 ሰዎች ሲገደሉ 12 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ቅዳሜ ዕለት ከደቡብ ሱዳን በመነሳት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ወደ ጋምቤላ ክልል ኑዌር ዞን የገቡ የ " ሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች " 10 ሰዎችን ገድለው 12 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ማድረሳቸውን ከጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል። ታጣቂዎቹ ቅዳሜ ምሽት 3 ሰዓት ተኩል ገደማ ድንበር ጥሰው በመግባት…
#Update

ምዕመናን ለተጎጂዎች ድጋፍ በማድረግ እንዲደርሱላቸው፤ በምልጃና በፀሎትም እንዲያስቧቸው ጥሪ ቀረበ።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በምዕራብ ጋምቤላ ቤቴል ሲኖዶስ አገልግሎት ክልል ውስጥ በሚገኘው " ማታራ " ቀበሌ፣ በሲኖዶሱ የሴቶች አገልግሎት በተዘጋጀ እና ከስድስት ፕርስፒቴሪ የመጡ ወጣት ሴቶች፣ እናቶችና ልጆቻቸው በተገኙበት መንፈሳዊ ኮንፍራስ ላይ ከደቡብ ሱዳን ዘልቀው በገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ በብዙዎች ላይ የሞትና ከባድ የመቁሰል አደጋ መድረሱን በመግለፅ ሀዘኗን ገልጻለች።

ቤተክርስቲያኗ ፤ ጥቃቱ የተፈፀመው ቅዳሜ ግንቦት 12፣ 2015 ዓ.ም 11 ሰዓት አከባቢ መሆኑን አስታውሳ ፤ የኮንፍረንሱ ተካፈይ የሆኑ ከ2,700 በላይ የሚሆኑ ሴቶች፣ እናቶችና ልጆቻቸው የቀኑን መርሀ ግብር አጠናቀው ለእራት በተቀመጡበት ወቅት ታጣቂዎቹ ልጆቻቸውን በጉልበት አፍነው ሊወስዱ ሲሞክሩ እናቶች በመከላከላቸው በከፈቱባቸው ተኩስ የተነሳ የሰው ህይወት መጥፋቱና ጉዳት መድረሱን አስረድታለች።

ከደረሰውም አሰቃቂ ጥቃት የተነሳ ማጣራቱ እስከተጠናቀቀበት ሰዓት ድረስ የሟች ምዕመናን ቁጥር 9 የደረሰ ሲሆን ከነዚያም ውስጥ የስድስት አመት ህፃን የሆነችው " ንያካካ ዊዩአል ኒኜት " እና አንዲት የምታጠባ እናት ይገኙበታል።

በተጨማሪም በጥቃቱ ቆስለው በጋምቤላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በህክምና እየተረዱ ያሉ በርካታ እናቶች ሲኖሩ ከነዚህም ውስጥ የሁለቱ ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነ ተገልጿል።

ቤተክርስትያኗ ፤ ለተጎጂች አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ እንዲደርሱላቸው በምልጃ ጸሎትም እንዲያስቧቸው ለምዕመናን ጥሪ አቅርባለች።

ጥቃቱ የደረሰበት ይህ አከባቢ የልጆች አፈናና የከብት ዝርፊያ በተደጋጋሚ የሚከሰትበት እንደመሆኑ በመንግሥትና በሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት እየተደረገ ያለው ክትትልና ትኩረት የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን አስተላልፋለች።

ከቀናት በፊት የጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዶች ድንበር ጥሰው በመግባት በማኩዌይ ወረዳ ቢልኬች ቀበሌ እንዲሁም በዋንቱዋ ወረዳ መተሀር ከተማ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን በፈፀሙት ጥቃት በአጠቃላይ 10 ሰዎችን ገድለው ፤ 12 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ማድረሳቸውን ማሳወቁ ይታወሳል።

ማስታወሻ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/78609?single

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
አፅድቀውታል ፤ ፈርመውበታል !

ዩጋንዳ የ " ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ን ወንጀል የሚያደርገውን ሕግ አፀደቀች።

ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ያፀደቁት / ፊርማቸውን ያኖሩበት የረቂቅ አዋጅ ሕግ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን ሁሉ በዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ነው።

በአንዳንድ ሁኔታዎች ዳግሞ #የሞት ቅጣትን የሚያስከትል ነዉ።

ረቂቅ ሕጉ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአገሪቱ ምክር ቤት አባላት ተቀባይንት ያገኘ ሲሆን፣ ማሻሻያ እንዲደረግበት ለፓርላማው ተመልሶ ቀርቦ ነበር።

ቀደም ሲል ቀርቦ በነበረው ረቂቅ ሕግ ላይ ማንኛውም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም ከዚሁ ጋር በተያያዘው ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ የሚያደርግ ነበር።

ሆኖም ግን ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ይህ ሰዎች እንዲታሰሩ እና በአካላዊ ገጽታቸው ብቻ እንዲከሰሱ ያደርጋል ሲሉ ሳይቀበሉት ቀርተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ረቂቅ ሕጉ እንዲሻሻል ወደ ፓርላማ መልሰውት ነበር።

በዚህ መሠረት ተሻሽሎ አሁን ላይ የቀረበው ረቂቅ ሕግ፣ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ወንጀልነት ወንድ ከወንድ ጋር በሚያደርገው ወሲባዊ ድርጊቶች ላይ የተወሰነ ሆኗል።

ይህንን ሕግ ተላልፈው የተገኙም እስከ እድሜ ልክ እስራት ይጠብቃቸዋል።

ለከባድ ወንጀሎች ማለትም ወሲባዊ ጥቃቱ #በሕጻናት_ላይ ፣ በአካል ጉዳተኛ እንዲሁም ተጋላጭ በሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ በሚፈፀምበት ጊዜ አሊያም የጥቃት ሰለባዎቹ ለዕድሜ ልክ ህመም የሚዳረጉ ከሆነ በድርጊቱ ፈፃሚ ላይ #የሞት ቅጣትን ይደነግጋል።

ማኅበረሰቡ #በሕጻናት ወይም በሌሎች ተጋላጭ በሆኑ የሕብረተሰቡ አባላት ላይ ማንኛውንም ዓይነት የተመሳሳይ ጾታ ጥቃት በሚያዩ አልያም በሚሰሙበት ጊዜ ለባለሥልጣናት ማሳወቅ እንደሚጠበቅባቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

በምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኡጋንዳ የተመሳሳይ ጾታ ቀድሞም ሕገ ወጥ ተደርጎ ነው የቆየው ፤ ይህ ሕግ ከሕገ ወጥነቱ አልፎ ነገሩን ወንጀልና በተራዘመ እስር የሚያስቀጣ ያደርገዋል።

#ምዕራባውያን ሀገራትና #ተቋማት በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ጉዳይ በዩጋንዳ ፓርላማ የተላለፈውን ውሳኔ ሲቃወሙና ፕሬዜዳንቱ #እንዳይፈርሙ ሲያሳስቡ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia