TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EthiomartShopping

ሴኩሪቲ ካሜራ ሽያጭና ነፃ ገጠማ : 0911582926

security camera CCTV (ባለ 4 አና ባ 8 ካሜራ) ለቤትዎ፤ ለድርጅት፤ ለሱቅ፤ ለፋርማሲ፤ ለዳቦ ቤት፤ ለቡቲክ፤ ለህንጻዎ ፤ ለመጋዘንዎ አና ለንብረትዎ የአመታት ልምድ ባለው ድርጅታችን ሴኩሪቲ ካሜራ ያስገጠሙ።

- 4 ካሜራዎች :- 4 ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች  35,000 ብር
-8 ካሜራዎች :- 8 ባለ 20 ሜትር ኦሪጂናል የካሜራ ኬብሎች 50,000 ብር

ቦሌ መድሀንያለም ቤዛ ህንጻ 208
#ነዳጅ

ለመጪው የ2016 ዓ/ም ወደ አገር ለማስገባት ለታቀደው 4.3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ 4.4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አስታውቋል።

ኢትዮጵያ በ2016 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋትን ነዳጅ ለማስገባት የወጣውን ዓለም አቀፍ ጨረታ፣ " ቪቶል " የተባለው የባህሬን ኩባንያ በድጋሚ በማሸነፉ የኮንትራት ውል ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በ2016 ዓ.ም. ለማስገባት ያቀደውን ሙሉ ለሙሉ ቤንዚን፣ እንዲሁም ከጠቅላላው የነጭ ናፍጣ ግዥ 40 በመቶውን " ቪቶል " ኩባንያ እንደሚያስገባ ታውቋል፡፡

በስምምነቱ መሠረት ለ1 ዓመት የሚያስፈልገውን 760 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ቤንዚንና 1.2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነጭ ናፍጣ ኩባንያው ያቀርባል፡፡

" ቪቶል " ጨረታውን ያሸነፈው ከሁለት ሌሎች ኩባንያዎች ጋር ተወዳድሮ እንደሆነ ተነግሯል።

" ቪቶል " እየተጠናቀቀ ላለፈው የበጀት ዓመት በተመሳሳይ የወጣውን ጨረታ አሸንፎ ሲያቀርብ ነበር።

ለ2016 በጀት ዓመት ያስፈልጋል ተብሎ የታቀደው ነዳጅ ከ2015 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በስምንት በመቶ ብልጫ አለው፡፡

በተናጠል ሲታይ ቤንዚን ስምንት በመቶና ነጭ ናፍጣ አምስት በመቶ ጭማሪ ይኖራቸዋል፡፡ 

Via Ethiopian Reporter

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ 2 ሺህ ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በመስጠት የተጠረጠረው ግለሰብ ተያዘ። እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ በነበረው የዘር ማጥፋት እልቂት፣ ከጥቃት ለማምለጥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ ሁለት ሺሕ #ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ አስተላልፏል በሚል የተጠረጠረው ግለሰብ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ መያዙን የሩዋንዳውን የዘር ማጥፋት የሚከታተለው፣ የተባበሩት…
" ከፍትሕ ማምለጥ እንደማይችሉ ማሳያ ነው "

ካለፉት 22 ዓመታ ጀምሮ ሽሽት ላይ የነበረውና በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወቅት ከዘር ማጥፋት እልቂት ለማምለጥ በቤተክርስቲያን የተሸሸጉ 2,000 (ሁለት ሺህ) ቱትሲዎች እንዲገደሉ ትዕዛዝ በማስተላለፍ የተጠረጠረው ፉልጌንሴ ካይሼማ መያዝ ምንም ያህል ጊዜ ቢወስድ እንዲህ አይነት ድርጊት የፈፀሙ ሰዎች #ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችሉ ማሳያ ነው ተብሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የግለሰቡን መታሰር መሰል ወንጀሎችን የፈፀሙ ከፍትህ ማምለጥ እንደማይችሉ ትልቅ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው ብለዋል።

ጉተሬዝ ፤ " እንዲህ አይነት ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ሰዎች ከፍትህ ሊያመልጡ እንደማይችሉ እና ከሩብ ምዕተ አመት በኋላም ቢሆን #ተጠያቂ እንደሚሆኑ የሚያሳይ ኃይለኛ መልእክት ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

እ.አ.አ በ1994 በሀገረ ሩዋንዳ በአክራሪ ሁቱዎች በተፈጸመ የዘር ማጥፋት፣ 800 ሺሕ የሚሆኑ ቱትሲዎች መገደላቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#Update

ዛሬ በቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሜ ህዝቡ ድምፁን ሲሰጥ ውሏል።

በአሁን ሰዓት የድምፅ ቆጠራው እየተካሄደ ይገኛል።

እስካሁን ባለው 96.01 በመቶ የድምፅ ሳጥን ተከፍቶ በተካሄደ ቆጠራ ፦

- ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን 52.28 % 
- የኤርዶጋን ዋነኛ ተቀናቃኝ ክሊክዳርጎሉ 47.72 % ድምፅ አግኝተዋል።

በቱርክ ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው ምርጫ ተወዳዳሪዎች የሚፈለገውን ያህል  ድምጽ (ከ50 በመቶ በላይ) ማግኘት ባለመቻላቸው ምርጫው በድጋሚ እንደሚደረግ መገለፁ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሜ ህዝቡ ድምፁን ሲሰጥ ውሏል። በአሁን ሰዓት የድምፅ ቆጠራው እየተካሄደ ይገኛል። እስካሁን ባለው 96.01 በመቶ የድምፅ ሳጥን ተከፍቶ በተካሄደ ቆጠራ ፦ - ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን 52.28 %  - የኤርዶጋን ዋነኛ ተቀናቃኝ ክሊክዳርጎሉ 47.72 % ድምፅ አግኝተዋል። በቱርክ ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው ምርጫ ተወዳዳሪዎች የሚፈለገውን ያህል …
#UPDATE

በቱርክ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ አሁናዊ የድምፅ ቆጠራው 97.94 በመቶ ደርሷል / የድምፅ ሳጥን ተከፍቶ ቆጠራ ተካሂዷል።

በዚህም የአሁኑ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን 52.14 % በመቶ ድምፅ ምርጫውን እየመሩ ሲሆን የኤርዶጋን ዋነኛ ተቀናቃኝ ክሊክዳርጎሉ 47.86 % ድምፅ በማግኘት እየተከተሏቸው ነው።

ከወዲሁ የሀገራት መሪዎች ለአሁኑ ፕሬዜዳንት የ " #እንኳን_ደስ_አልዎት " መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በቱርክ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ አሁናዊ የድምፅ ቆጠራው 97.94 በመቶ ደርሷል / የድምፅ ሳጥን ተከፍቶ ቆጠራ ተካሂዷል። በዚህም የአሁኑ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን 52.14 % በመቶ ድምፅ ምርጫውን እየመሩ ሲሆን የኤርዶጋን ዋነኛ ተቀናቃኝ ክሊክዳርጎሉ 47.86 % ድምፅ በማግኘት እየተከተሏቸው ነው። ከወዲሁ የሀገራት መሪዎች ለአሁኑ ፕሬዜዳንት የ " #እንኳን_ደስ_አልዎት " መልዕክት…
#UPDATE

በቱርክ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ #አሁናዊ የድምፅ ቆጠራው 99.20 በመቶ ደርሷል።

በዚህም የአሁኑ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን 52.08 % በመቶ ድምፅ ምርጫውን እየመሩ ሲሆን የኤርዶጋን ዋነኛ ተቀናቃኝ ክሊክዳርጎሉ 47.92 % ድምፅ በማግኘት እየተከተሏቸው ነው።

አሁናዊው ውጤት የኤርዶጋንን ማሸነፍ እና ለ5 ዓመታት የሀገሪቱ መሪ ሊያደርጋቸው የሚችል መሆኑን የሚያመላክት መሆኑን ተከትሎ ደጋፊዎቻቸው ደስታቸውን ለመግለፅ አደባባይ ወጥተዋል።

የሀገራት መሪዎች ለኤርዶጋን የ " እንኳን ደስ አልዎት " መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
#ExodusPhysiotherapy

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦
- ለአንገት፣ለትክሻ፣ለወገብ ህመም;ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ችግር፣ ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል፣ ለስፖርታዊ ጉዳቶች ፣ ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች ፣ በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ !

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ     #ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት
አድራሻችን ፦ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን።

ስልክ ፦ 0979099909/ 0911039377
በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ምዕራባውያን ሚዲያዎች ተሸንፈዋል " - ኤርዶጋን

የቱርክ ጠቅላይ ምርጫ ካውንስል የመጀመሪያ ደረጃ የምርጫ ውጤት የአሁኑ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ምርጫውን #ማሸነፋቸውን አመልክቷል።

ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ምርጫውን ማሸነፋቸውን ተከትሎ በአንካራ ለደጋፊዎቻቸው ንግግር አድርገዋል።

ምን አሉ ?

ፕሬዜዳንቱ በንግግራቸው " ዛሬ ማንም የተሸነፈ የለም ሁሉም 85 ሚሊዮን ህዝብ አሸንፏል። " ያሉ ሲሆን " አሁን ጊዜው የአንድነት፣ በአገራዊ ግቦቻችን እና ሀገራዊ ህልሞቻችን ዙሪያ መዋሃድ ነው " ብለዋል።

በንግግራቸው የምዕራባውያን ሚዲያዎች እሳቸውን " ለማጥፋት " ሲሰሩ እንደነበር በመጠቆም ፤ " የምዕራባውያን ሚዲያዎች ተሸንፈዋል " ሲሉ ተደምጠዋል።

ኤርዶጋን በቱርክ በዋጋ ንረት ምክንያት የተከሰቱ ችግሮችን መፍታት፣ ከምንም ነገር በላይ " በጣም አስቸኳይ " እና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን በንግግራቸው አንስተዋል።

@tikvahethiopia
#UNMAS

ፈንጂዎችን እና ሌሎች የጦር መሣሪያ ቅሪቶችን የማስወገድ ተልዕኮ የተሰጠው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) ፈንጂ ማስወገድ አገልግሎት (UNMAS) በዋናነት በትግራይ ክልል እንዲሁም ጦርነት በተካሄደባቸው አዋሳኝ የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች እንዲሰማራ የኢትዮጵያ መንግሥት ፈቅዷል።

ፈንጂዎችና ሌሎች ያልፈነዱ የጦር መሣሪያ ቅሪቶች ጦርነት በተካሄደባቸው የሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች፣ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት እያደረሱ በመሆኑ አካባቢዎችን ከፈንጂዎች ለማጽዳት እንዲቻል፣ የተመድ ፈንጂ ማስወገድ አገልግሎት እንዲሰማራ መፈቀዱን የአፍሪካ ኅብረት መረጃ ያመለክታል።

የተመድ ፈንጂ ማስወገድ አገልግሎት በቅርቡ በመቐለ ከተማ ቢሮውን እንደሚከፍትና ዋና መቀመጫውን በመቐለ አድርጎ በሁሉም ጦርነቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ኃላፊነቱን ለመወጣት እንደሚሰማራ ተነግሯል።

በዚህ ወር በአፋር ክልል በፈነዳ የወደቀ የሞርታር ጥይት የአራት ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን በትግራይ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል 300 በሚሆኑት ውስጥ በርካታ የጦር መሳሪያ ቅሪቶች ተገኝተዋል።

Via Ethiopian Reporter

@tikvahethiopia