#Oromia
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፤ " የሕገ-ወጥ ቤቶች ፈረሳ ሒደት መስጅድ ላይ ያተኮረ አይደለም " አለ።
ዛሬ የክልሉ ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በዚህም ወቅት እየተካሄደ ስላለው የቤቶች ፈረሳ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸው ፤ ምንም እንኳን እነማን እንደሆኑ በግልፅ ያልተናገሩት " አንዳንድ አካላት " ሲሉ የጠሯቸው በኦሮሚያ ክልል ህገ ወጥ ግንባታዎችን የማፍረሱን ሥራ በአንድ ሃይማኖት ላይ ያነጣጠረ ማስመሰላቸው ፈጽሞ ትክክል አይደለም ብለዋል።
" የሕገ-ወጥ ቤቶች ፈረሳ ሒደት መስጅድ ላይ ያተኮረ አይደለም " ያሉት ኃላፊው " በክልሉ 600 በሚሆኑ ከተሞች በህገ-ወጥ መንገድ የተገነቡ ቤቶችን የማፍረስ ሒደት እንደሚከናወን ገልፀዋል።
ሕግ የማስከበር ስራው በዋናነት ህገ-ወጥነትን በዘላቂነት ለመከላከል ያለመ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
ኃላፊው ይህ ስራ በሚሰራበት ወቅት የተለያየ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ፤ አካላት የአንድ ብሔርና ሃይማኖት እንደተጠቃ አድርገው በመገናኛ ብዙሃን የሚያራግቡት ትክክል አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።
ህገወጥ ግንባታ ሲካሄድ መንግሥት ለምን ዝምታን መረጠ በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄም ፤ " መንግስት ኃላፊዎቹን ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ እንደሆነ ለማረጋገጥ እንወዳለን " ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግስት በሃይማኖት ጉዳዮች ላይ ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ የተናገሩት አቶ ኃይሉ አዱኛ ፤ " የሃይማኖት ተቋማት እና የእምነቱ ተከታዮች እምነትን ተገን አድርገው ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር የሚሞክሩ አካላትን በጋራ ሊከላከሉ ይገባል " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በኦሮሚያ ክልል፣ ሸገር ከተማ በርካታ መስጅዶች እየፈረሱ መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በተደጋጋሚ ማሳወቁ እንዲሁም መፍትሄ እንዲፈለግ ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ መፃፉ የሚዘነጋ አይደለም።
ምክር ቤቱ ከቀናት በፊት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ላይም በ " ሸገር ከተማ " ኢስላምንና ሙስሊሞችን በናቀ መልኩ በመስጂዶች ላይ እየተደረገ ያለው የጅምላ ፈረሳ ሂደት በአስቸኳይ እንዲቆም፥ እንዲሁም ለፈረሱት መስጊዶች የክልሉ መንግስት #ምትክ_ቦታ በመስጠት በአስቸኳይ ተመልሰው እንዲገነቡ በማድረግ ሕዝበ ሙስሊሙን በይፋ ይቅርታ በመጠየቅ እንዲክስ ማሳሰቢያ መስጠቱ ይታወሳል።
የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፤ በሸገር ከተማ አስተዳደር እስካሁን ከ19 በላይ መስጂዶች ፈርሰዋል ሲል መግለጫ መስጠቱ የሚዘነጋ አይደለም።
@tikvahethiopia