TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ተጠርጣሪው ከፀጥታ ሀይል ለማምለጥ ሲል በሻፋሞ ጫካ ለጫካ ሲዘዋወር ነበር " - የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ
ፀጋ በላቸውን በማፈን የተጠረጠረውና በፖሊስ ሲፈለግ የነበረው ዋና ሳጂን የኋላ መብራት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።
የሲዳማ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ፤ በወ/ሪት ፀጋ በላቸው የጠለፋ ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ሲፈለግ የነበረው ተጠርጣሪ የጸጥታ ሀይሉ ባደረገው ክትትል በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር የዋለው በሀገረ ሰላም ወረዳ መሆኑ ተገልጿል።
ተጠርጣሪው ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ከፀጥታ ሀይል ለማምለጥ ሲል በሻፋሞ ጫካ ለጫካ ሲዘዋወር እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን የፀጥታ ኃይል አባላት ከበባ ውስጥ በማስገባት ለመያዝ መቻሉ ተመላክቷል።
ተጠርጣሪው አከባቢ በመቀየር ፍለጋውን አስቸጋሪ ቢያደርግ ማህበረሰቡን በማሳተፍ በተደረገው አሰሳ በዛሬው ዕለት ከቀኑ 10 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ላይ በሀገረ ሰላም ወረዳ በቁጥጥር ስር መዋሉን የፀጥታ ቢሮው አሳውቋል።
ተጠርጣሪው ግለሰብ ወንጀሉን ለመፈጸም ሲጠቀምባቸው ከነበሩ አንድ ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያና ሽጉጥ ጋር መያዙም ተገልጿል።
#ኢብኮ
@tikvahethiopia

የንብረት ግብር . . .
" ግብር ከፋዮች የሚከፍሉት የንብረት ግብር ተከራይን የማይመለከትና ወደ ተከራይ መተላለፍ የሌለበት መሆኑን ማወቅ አለባቸው " - የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ
ነዋሪዎች ስለ ንብረት ግብር ምን አሉ ?
" የኑሮ ውድነቱ ከብዶ ባለበት ሁኔታ ግብሩ መሻሻሉ የመጨረሻ ጫናው ተከራዮች ላይ እንዳያርፍ ያደርጋል።
መንግሥት ገበያውን መቆጣጣር አለበት።
ግብርን መክፈል የሥልጣኔ መገለጫ ቢሆንም፣ የከፋዮች የገቢ መጠንና ሌሎች ጫናዎችን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለበት "
የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ፤ የንብረት ግብር ማስተግበሪያ ጊዜያዊ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስማማው ሙልጌታ ፦
" የንብረት ግብር አሁን እንደ አዲስ እንዲታይ የሆነው በየወቅቱ ዓመታዊ የኪራይ ዋጋን መሰረት በማድረግ ሊሻሻል ሲገባ ለረጅም ጊዜ ሳይሻሻል ቆይቶ ዘንድሮ በመሻሻሉ ነው።
የንብረት ግብር በሀገራችን የተጀመረው በ1937 ዓ.ም በወጣው አዋጅ ሲሆን፣ አዋጁ በ1968 ዓ.ም አዋጅ ቁጥር 80/1968 ተብሎ ተሻሽሎ እስካሁን እየተጠቀምንበት ነው፡፡
መንግሥት በየዓመቱ ለሚያወጣው የመሰረተ ልማት ወጪ በጀት የሚሸፍነው በሚሰበስበው ገቢ ነው። አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ግን ይህ አልተቻለም።
ከዚህ ቀደም ሲከፈል የነበረው የንብረት ግብር ዝቅተኛ ነበር።
ለማሳያም አዲስ አበባ ውስጥ ፦
👉 ወደ 2 ሺህ 500 የቤት ባለቤቶች ከአንድ ብር በታች፤
👉 23 ሺህ 421 ግብር ከፋዮች ከ10 ብር በታች፤
👉 ወደ 84 ሺህ የሚሆኑት እስከ መቶ ብር ብቻ ሲከፍሉ ነበር።
96 በመቶ የሚሆኑት የንብረት ግብር ከፋዮችን ከ5 መቶ ብር በታች ይከፍሉ ነበር ፤ ይህ ደግሞ አዲስ አበባ ካለው ንብረት አንጻር በጣም ዝቅተኛ ነው።
የግብር ግመታው የተደረገው አዋጁ ዓመታዊ የኪራይ ግብርን መሰረት በማድረግ ከአንድ እስከ አራት በመቶ የግብር ጭማሪ ማድረግ እንደሚቻል ባስቀመጠው መሰረት ተሰልቶ ነው።
ግምቱ ንብረቱ አሁን ባለው ዋጋ ላይ ተመስርቶ የሚሰራ ሲሆን፣ የቦታ ደረጃ፣ የቤቱ ዓይነት እና የአገልግሎት ዓይነትን መሰረት በማድረግ ነው።
የግብር ግመታ ከመደረጉ በፊት ጥናት ተደርጎ ንብረቶቹ ወደ ተመሳሳይ ደረጃ በማምጣት ምደባ ተደርጓል፤ ግብር ከፋዮች በሚሞሉት የመሬት ስፋት መሰረት ግምቱ ይሰራል።
መንግሥት ግብርን መሰብሰቡ አንዱ የዋጋ ግሽበትን መከላከያ መንገድ ነው፤ ገቢ በሥርዓት ከተሰበሰበ የልማት ጥያቄዎች በትክክል መመለስ ስለሚቻል በቀጣይነት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ይቻላል።
ግብር ከፋዮች የሚከፍሉት የንብረት ግብር ተከራይን የማይመለከትና ወደ ተከራይ መተላለፍ የሌለበት መሆኑን ማወቅ አለባቸው፤ መንግሥትም የተከራዮችን ጫና ለመቀነስ ቋሚ ሥርዓት ለማበጀት እየሰራ ነው።
አቅመ ደካማ የሆኑ እና ገቢ የሌላቸው ሰዎች ካሉ በታክስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት የግብር ምህረት ስላለ በወረዳ ደረጃ ተጣርቶ የምህረቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ። "

" የሽብር ወንጀል ምርመራ ጀምሪያለሁ " - ፌዴራል ፖሊስ
ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መቐለ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን የፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።
ተጠርጣሪዎቹ ፦
👉 ዮሀንስ ዳንኤል
👉 አማኑኤል መውጫ
👉 ናትናኤል ወንድወሰን
👉 ኤልያስ ድሪባ
👉 ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ ናቸው።
የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው፥ " እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል " ብሏል።
" የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ከተጀመረው ምርመራ ባሻገር፣ ከጸረሰላም ሃይሎች ተልእኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ነው " የገለጸው።
የምርመራ መዝገቡ ፥ " በወቅቱ የአየር መንገዱ ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በትዕግስት ቢማጸናቸውም፣ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ በመሆናቸው አሻፈረን ብለዋል " ሲል ገልጿል።
" ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር መጠቀም ሲገባቸው፣ የሀገር ኩራት እና የራሳቸው ንብረት የሆነውን አየር መንገድ ማንቋሸሻቸው አሳዛኝ ተግባር ነው " ብሏል
" እነዚህ በቁጥጥር ስር የሚገኙ 6 ተጠርጣሪዎች በተላለፉት የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የበረራ አሰራር ጥሰት ብሎም በሽብር ወንጀሎች የምርመራ መዝገብ ነገ ነሀሴ 20/2016 ፍርድ ቤት ይቀርባሉ " ሲል ፌዴራል ፖሊስ አሳውቋል። #ኢብኮ

#Ethiopia የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሲቪል አቪዬሽን ሕግና አሠራር ጥሰዋል በማለት በቁጥጥር ስር አውሎ የሽብር ወንጀል ምርመራ የከፈተባቸውን 6 ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ማንነት የሚያሳይ ፎቶ ይፋ አድርጓል። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ያዋልኳቸው በሀገራችን ካለው የክረምት ወቅት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት " ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ አውሮፕላን…
#Update
የአቪዬሽን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ ፈጥረዋል የተባሉት 6 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የፌዴራል ፖሊስ በእነ ዮሐንስ ዳንኤል ላይ በጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ላይ የግራቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ብይን ለመስጠት ለነገ ነሐሴ 21ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል።
ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል። #ኢብኮ
@tikvahethiopia
የአቪዬሽን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ ፈጥረዋል የተባሉት 6 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የፌዴራል ፖሊስ በእነ ዮሐንስ ዳንኤል ላይ በጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ላይ የግራቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ብይን ለመስጠት ለነገ ነሐሴ 21ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል።
ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል። #ኢብኮ
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጥንቃቄ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፥ " ዜጎች በሕገ ወጥ ደላሎች ማታለያ ወደ ማይናማር እና ታይላንድ ከመጓዝ ሊታቀቡ ይገባል " ሲል አሳስቧል።
ሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች በይነ መረብን በመጠቀም በርካታ ዜጎች ችግር ላይ እንዲወድቁ ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ተናግረዋል።
" ዜጎች ባልተረጋገጡ አማላይ ማስታወቂያዎች ጉዳት እየደረሰባቸው ነው " ብለዋል።
" በጃፓን የሚገኘው የኢትዮጵያ ሚሲዮን የዜጎችን ችግር ለመፍታት ጥረት እያደርገ ነው " ብለው ሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎቹ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከተለያዩ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ተናግረዋል። #ኢብኮ