TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OromiaRegion

የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል ሲካሄድ የነበረው የሰላም ንግግር ዛሬ መጠናቀቁ ይታወቃል።

ይህንን የሰላም ንግግር በተመለከተ ሁለቱም አካላት በተናጠል ባሰራጩት መግለጫ ውይይቱ አንውታዊ / በአንዳድን ጉዳዮች መግባባት ላይ የተደረሰበት እንደነበር እና በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ ሳይቻል መቅረቱን አመልክተዋል።

ተደራዳሪ አካላቱ ስለምን እንደተነጋገሩ፣ በምን ጉዳዮች ላይ እንደተግባቡ እና በምን ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳልተቻለ ምንም ያሉት ነገር የለም።

ቢቢሲ የሰላም ንግግሩ ተሳታፊዎችን ዋቢ በማድረግ ከዛው ዛንዚባር ባሰራጨው መረጀ ፤ መንግሥትን እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ካላስማሙ ጉዳዮች መካከል አንዱ " የጋራ የሽግግር መንግሥት ምሥረታ " ጉዳይ መሆኑ ታውቋል።

አንድ ስማቸው ይፋ እንዳይሆን የፈለጉ የውይይቱ ተሳታፊ ፥ " ተደራዳሪዎቹን ካላስማሟቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የጋራ የሽግግር መንግሥት መቋቋም ነው " ሲሉ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ፥ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱትን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር፣ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስን እና ብልጽግናን ጨምሮ ሌሎች ፓለቲካ ፓርቲዎችን ያካተተ የጋራ የሽግግር መንግሥት ይቋቋም ሲል መጠየቁን ከእኚሁ ተሳታፊ ማረጋገጡን ቢቢሲ አማክቷል።

የጋራ የሽግግር መንግሥት ምሥረታው በፌደራል መንግሥቱ ተደራዳሪዎች በኩል ተቀባይነት አለማግኘቱን ተነግሯል።

ተሳታፊዎቹ እንደገለጹት የሽግግር መንግሥት በዋነኝነት የሚቋቋመው በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል መተማመን እንዲኖር እና አገሪቱ ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ ማካሄድ እንድትችል የማሻገር ኃላፊነትን እንዲወጣ ለማድረግ ነበር።

መንግስት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የአሁኑ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሰላም ንግግር ቢጠናቀቅም የውይይቱ መቀጠል ላይ ስምምነት መደረሱንና ለችግሩ ሰላማዊ መፍትሄ ለማበጀት ቁርጠኛ መሆናቸውን በመግለጫ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#DigitalLottery

አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ሚያዚያ 25 ቀን 2015 በብሄራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በህዝብ ፊት ወጥቷል።

3 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 0102013522 ሆኖ ወጥቷል።

👉 3 ሚሊዮን ብር - 0102013522
👉 1,200,000 ብር - 0100663609
👉 800 ሺህ ብር - 0100706800
👉 400 ሺህ ብር - 0100750353

(ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮች ከላይ ተያይዘዋል)

ምንጭ፦ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ በትግራይ ክልል ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ተመለሱ። ላለፉት ዓመታት በትግራይ ክልል አንድም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኃላም በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ትምህርት ዛሬ ሚያዚያ 23 ቀን 2015 ዓ/ም በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተጀምሯል። የትግራይ ትምህርት ቢሮ ትምህርት የሚጀመረው ሁሉ ነገር ተሟልቶ ፤ ችግሮች ሁሉ ተፈተው ሳይሆን ትውልድን ለማስቀጠል ሲባል መሆኑን ከዚህ ቀደም አሳውቆ…
#Tigray

በትግራይ ተቋርጦ የነበረው መደበኛ ትምህርት ከሠኞ ጀምሮ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ተጀምሯል።

ትምህርት የተጀመረው አዳዲስ አሰራሮችን  ተግባራዊ በማድረግ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ ለኢቢሲ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ  ምን አሉ ?

" ትምህርቱ ከሚያዚያ 24 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 7 ቀን 2015 ድረስ ለ2 ወር ተኩል በማካሄድ  የመጀመሪያው መንፈቅ ይጠናቀቃል። ይህም እንደ አንድ ወሰነ ትምህርት ጊዜ ይይዛል።

እንዲህ ያለው የትምህርት ዘዴ ወይም (Accerated Learning Program) ተማሪዎች እድሜያቸው መድረስ በሚገባቸው የትምህርት እርከን ላይ እስኪደርሱ በዓመት ሁለት ደረጃ ትምህርቶችን እንዲያልፉ ተደርጎ ተሰርቷል።

በዚህም አንድ ዓመት 4 የወሰነ ትምህርት ጊዜ በማድረግ ሁለት ደረጃ ትምህርት በአንድ ዓመት እንዲጨርሱ ይደረጋል። "

በሌላ በኩል ቢሮው ፥ በጦርነቱ ምክንያት ብዙ ጉዳት በመድረሱ የልዩ ፍላጎት የሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ቁጥራቸው  በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨምር አሳውቋል።

የጉዳቱን መጠን በመረዳት የፌዴራል መንግስት፣ ትምህርት ሚኒስቴር ፣ ዓለም አቀፍ  የእርዳታ ድርጅቶች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት አስቸኳይ ድጋፍ  እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እርዳታው የተቋረጠው የተፈፀመውን ስርቆት ለማጣራት ውሳጣዊ ምርመራ ለማካሄድ ነው " - የረድኤት ሰራተኞች የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ውስጥ የሚያቀርበውን የምግብ እርዳታ ማቋረጡን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ 4 የረድኤት ሠራተኞች ለአሶሺየትድ ፕሬስ ተናግረዋል። እርዳታው ለምን ቆመ ? እንደ ረድኤት ሰራተኞቹ ቃል ፤ ድርጅቱ የእርዳታ አቅርቦት ያቋረጠው ከሳምንታት በፊት ለተረጂዎች በሚቀርብ…
#Tigray

የአሜሪካ መንግሥት የተራድኦ ድርጅት (USAID) በትግራይ ውስጥ ተከስቷል ከተባለው የእርዳታ ምግብ ስርቆት ጋር በተያያዘ በክልሉ ውስጥ የሚያካሂደውን የእርዳታ ሥራ ለጊዜው አቋርጧል።

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው " በትግራይ ውስጥ ረሃብ በሚመስል ሁኔታ እየተሰቃዩ ላሉ ሰዎች የታለመው የምግብ እርዳታ " ከታለመለት አላማ ውጪ ገበያ ላይ ለሽያጭ መቅረቡን በመረዳቱ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም ሳቢያ " አስቸጋሪ ያለውን ውሳኔ " ለማሳለፍ መገደዱን በማመልከት፣ ተጨማሪ መግለጫ እስኪሰጥ ድረስ፣ በትግራይ ክልል ውስጥ የሚካሄዱ በድርጅቱ የሚደገፉ የምግብ እርዳታ አቅርቦቶች እንዲቋረጥ መደረጉን አሳውቋል።

በተመሳሳይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለተረጂዎች በሚቀርብ የምግብ እርዳታ ላይ ተፈጸመ የተባለውን ስርቆት ለማጣራት ውስጣዊ ምርመራ ለማካሄድበ ትግራይ ክልል ውስጥ የሚያቀርበውን የምግብ እርዳታ ማቋረጡ ከቀናት በፊት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በትግራይ ክልል በስርቆት ምክንያት እርዳታ መቆሙን ተከትሎ ዓለም አቀፍ ተቋማት ያሳለፉትን ውሳኔ በተመለከተ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ  የእርዳታ ምግብ አቅርቦት ለሌላ አላማ መዋሉን በተመለከተ ከዲፕሎማቶች፣ ከእርዳታ ድርጅት ተወካዮች እና ከክልሉ ነዋሪዎች ጋር ሲነጋገሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

ከችግሩ ከፍተኛነት እና ባሉ በርካታ ማስረጃዎች መሠረትነት የድርጊቱን ፈጻሚዎችን ማንነት በመለየት ተጠያቂ ለማድረግ በከፍተኛ የክልሉ ኃላፊዎች የሚመራ ምርመራ መጀመሩን አስታውቀዋል።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Germany

ዛሬ የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ  አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ኦላፍ ሹልዝ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነው።

ከእሳቸው ጋር የጀርመን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ ባለሀብቶች ፣ የተቋማት መሪዎች እንዲሁም በርከት ያለ የልዑካን እንደሚመጡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ለጀርመኑን መራሄ መንግሥት አቀባበል ለማድረግ ከቦሌ ኤርፖርት ጀምሮ ያለው መንገድ ዝግጁ መደረጉን ተዘዋውረን ለመመልከተ ችለናል።

@tikvahethiopia
#Mekelle

የመቐለ ወደብና ተርሚናል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታውቋል።

በጦርነት ተቋርጦ የቆየው የመቐለ ወደብና ተርሚናል ወደ መደበኛ አገልግሎት መመለሱ ተገልጿል።

በዚህም መዳረሻቸው መቐለ ወደብና ተርሚናል ለሆኑ ገቢ ጭነቶችን  ከዛሬ ሚያዝያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከመነሻ የባሕር ወደብ ለመቐለ ኦፕሬሽን መክፈት የሚቻል መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#Big5Construction

አስደሳች ዜና !

በዓለማችን ላይ እጅግ ታዋቂ የሆነው ቢግ 5 የግንባታ ንግድ ትርዒት ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ ነው።

ኤግዚቢሽኑ ከግንቦት 10 እስከ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዲስ አበባ የሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።

በከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ዕውቅና እና ድጋፍ ያለው ብሎም ከ24 ሀገራት የተውጣጡ ከ100 በላይ የዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ ስመጥር የዘርፉ ባለሙያዎች እና ግብዓት አቅራቢዎች የሚሳተፉበት ይህ ታላቅ ዐውደ ርዕይ ሊያመልጥዎት አይገባም!

ምን ይሄ ብቻ! ቢግ 5 ኮንስትራክት ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ተከታታይ የሙያ ዕድገት (CPD) ፕሮግራምን በማቅረቡ ኩራት ይሰማዋል።

ከ20 በላይ የግንባታው ኢንደስትሪ ላይ ያተኮሩ ሙያዊ ንግግሮች በሚደረጉበት እና ዓለም አቀፋዊ የሙያ የምስክር ወረቀቶች  በሚሰጡበት ኢግዚቢሽን ላይ፤ የዘርፉ ባለሙያዎች በፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ ቴክኖሎጂ፣ ሕንጻ ንድፍ እና ዲዛይን፣ ምሕንድስና እና መሰል ሙያዎች ላይ የCPD ነጥባቸውን ማሳደግ የሚችሉበት ትልቅ ዕድል ተመቻችቷል።

በዘርፉ ያልዎትን ዕውቀት ለማሳደግ እና በዘርፉ ካሉ ባለሙያዎች ጋር ትውውቅዎን ለማስፋት ይህ ወርቃማ ዕድል አያምልጥዎ !

የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል መስፈንጠሪያውን ይከተሉ: https://t.iss.one/big5ethiopia
#AmharaRegion

በአማራ ክልል በሲቪል ሰዎች ላይ የሞት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት የደረሰ መሆኑን እንዲሁም ከደሴ - አ/አ መንገድ በተለያየ ጊዜ መዘጋቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለፀ።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአማራ ክልል የተወሰኑ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው “ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ” በሰብአዊ መብቶች ላይ ያለውን አንድምታና ተጽእኖ በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ኮሚሽኑ ፤ በሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት ያለ መሆኑን፤ በተለይም ሸዋ ሮቢት፣ አርማኒያ፣ አንጾኪያ፣ ገምዛ እና ማጀቴ በመከላከያ ሰራዊት እና በአካባቢው ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውውጥና በከባድ መሣሪያ ጭምር የታገዘ ጥቃት መኖሩን ገልጿል።

በዚህም ምክንያት በሲቪል ሰዎች ላይ የሞት፣ የአካልና የንብረት ጉዳት የደረሰ መሆኑን እንዲሁም ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ በተለያዩ ጊዜያት የተዘጋ መሆኑን ለማረጋገጥ መቻሉን ኢሰመኮ አሳውቋል።

በተጨማሪም በክልሉ ያሉ የተወሰኑ ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ የክልል ልዩ ኃይሎችን እንደገና የማዋቀር ውሳኔን በመቃወም የተካሄዱ ሰልፎችን መርተዋል/አስተባብረዋል የተባሉ የተወሰኑ ወጣቶች እና ከፋኖ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ የተወሰኑ ሰዎች እንደታሰሩ ኢሰመኮ ተረድቻለሁ ብሏል።

ኢሰመኮ ፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄደው ጦርነት በሲቪል ሰዎች ላይ መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰትና ጉዳት ማድረሱን በተደጋጋሚ መግለፁን ያስታወሰው ኢሰመኮ ፤  በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚፈጠሩ ተጨማሪ ግጭቶች ሰብአዊ መብቶች ላይ አስከፊ/ከባድ ጥሰቶች የሚያስከትሉ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም የሚመለከታቸው ወገኖች ችግሩን በሰላማዊ መንገድና በውይይት እንዲፈቱ፣ ግጭቱን ከሚያባብሱ ድርጊቶችና ንግግሮች እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርቧል።

ኮሚሽኑ ፤ ስለደረሰው ጉዳት ሁሉ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ፣ እንዲሁም በማናቸውም ሁኔታ የሚፈጸሙ እስራቶች ሕግን መሠረት ያደረጉ በተለይም “የጥብቅ አስፈላጊነት፣ ተመጣጣኝነትና ከመድልዎ ነጻ መሆን” የሚሉትን የሰብአዊ መብቶች መርሆችን ያከበሩ መሆናቸውን መንግሥት እንዲያረጋግጥ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
#ExodusPhysiotherapy

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦
- ለአንገት፣ለትክሻ፣ለወገብ ህመም;ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ችግር፣ ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል፣ ለስፖርታዊ ጉዳቶች ፣ ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች ፣ በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ !

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ     #ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት
አድራሻችን ፦ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን።

ስልክ ፦ 0979099909/ 0911039377
በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic