TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle በዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራ ልዑክ መቐለ ገባ። በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራው የጤና ሚኒስቴር ልዑካን ቡድን ዛሬ መቐለ ገብቷል። ልዑኩ ከክልሉ አስተዳደር ጋር በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነጋገር ይጠበቃል። ፎቶ ፦ ድምፂ ወያነ @tikvahethiopia
" ጉዳቱ የሚያሳምም ቢሆንም ተባብረን ወደነበረበት እንመልሰዋለን " - ዶ/ር ሊያ ታደሰ
በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራው ልዑክ በትግራይ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
በትግራይ ያሉ የጤና ተቋማት የሰረሰባቸው ጉዳት እጅግ በጣም የሚያሳዝን እና ከፍተኛ ነው።
ዶ/ር ሊያ ፤ ጉዳቱ የሚያሳምም ቢሆንም ተባብረን ወደነበረበት እንመልሰዋለን። መመለስም ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።
ዶ/ር ሊያ እና የመሩት ልዑክ በመቐለ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታልም ጉብኝት ማድረጉና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መነጋገሩ ተሰምቷል።
ፎቶ ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን
@tikvahethiopia

#ብርሃን_ባንክ
ለግብይትዎ የብርሃን ኤቲኤም ካርድን በመጠቀም ጊዜዎን ይቆጥቡ፤ ድካምዎን ያቅልሉ!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ

#Oromia
" የልዩ ኃይል ስምሪት አቁመናል ፤ ... በክልሉ ያለውን የፀጥታ ማስከበር ሥራ የአገር መከላከያ ሠራዊት ተረክቧል " - የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የልዩ ኃይል አደረጃጀት ስምሪት ማቆሙን አስታወቀ።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ነው ይህንን ያሳውቁት።
ዋና ኮሚሽነሩ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤ የፌዴራሉ መንግሥት ባስተላለፈው መሠረት የልዩ ኃይል አደረጃጀት መዋቅርን በተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮች መልሶ የማደራጀቱ ተግባር እየተከናወነ ነው ብለዋል።
በክልሉ ያለውን የፀጥታ ማስከበር ሥራንም #የአገር_መከላከያ_ሠራዊት መረከቡን ገልጸዋል።
" የልዩ ኃይል አደረጃጀት ቀድሞውኑም ለጊዜያዊ የፀጥታ ችግር ያለ ሕገ መንግስታዊ መርህ ነው " የተመሰረተው የሚሉት ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ለሁሉም ክልሎች በወጥነት ተላልፏል ያሉትን መዋቅሩን በሌላ ፀጥታ ተቋማት የማደራጀቱ ሥራ እየተተገበረ ነው ብለዋል።
" ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት የሚፈርስ የሚለው መልሶ ለመገንባት በሚል መወሰድ አለበት። እንደ ወንጀለኛ ፈርሶ የሚሳደድ አካል የለም። አደረጃጀቱ ስህተት ስለነበረበት በዚህ መደራጀት አለበት የሚል ነው መወሰድ ያለበት። አንድ ሕጋዊ ክፍተት መኖሩ ሲሆን ሌላው የሚገዳደር የተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮች በአንድ አገር ውስጥ አያስፈልግም በሚል የፀጥታ ችግሮች በመከላከያ፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በክልሎች መደበኛ ፖሊስ በየደረጃው እንዲሠራ በሁሉም ውይይት ተደርጎበት የተወሰነው። " ሲሉ ተናግረዋል።
ውሳኔው ሁሉንም ክልሎች የሚመለከት እንደሆነ የገለፁት ኮሚሽነር አራርሳ በተደረገው ውይይትና በተደረሰበት ስምምነትም አተገባበሩም በአንድ ላይ እየተከናወነ ነው ብለዋል።
ሂደቱን የአገር መከላከያ እንደሚያስፈጽም መወሰኑንም አመልክተዋል።
" የፌዴራል መንግሥት ውሳኔውን ያስተላለፈው ሁሉም ክልሎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ነው። ከዚያ ውስጥ ኦሮሚያ አንዱ እንደመሆኑ መመሪያውን ተቀብለን በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እያደራጀን ነው። ኦሮሚያ አላፈረሰም ለአንዳንድ ክልል ብቻ የተላለፈ ነው ሚለው እውነት አይደለም ብቻ ሳይሆን በሬ ወለደ እንደ ማለት ነው። ይሄ የሚደበቅም ስላልሆነ ምንም የተለየ ማብራሪያ አያሻውም። ንጹሑ ህዝብ ግን እንዳይደናገር ውሳኔው ማንንም የሚመለከት መሆኑን ቢገነዘሙ መልካም ነው። " ብለዋል።
አሁን በክልሉ የሚሰማራ የልዩ ኃይል አደረጃጀት የለም ያሉት ኮሚሽነር አራርሳ በመከላከያ፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በክልል መደበኛ ፖሊስ እንደየሚያስፈልገው መስፈርት እየተደራጁ ለስልጠና እየተሰማሩመሆኑንም ተናግረዋል።
" በሁሉም የፀጥታ መዋቅሮች አልደራጅም ያለ አሊያም በጡረታ መገለልም ያለበት በደንቡ መሰረት የመሸኘቱ ሥራ እየተተገበረ " ነው ብለዋል።
#ዶቼቨለ_ሬድዮ

#Oromia " የልዩ ኃይል ስምሪት አቁመናል ፤ ... በክልሉ ያለውን የፀጥታ ማስከበር ሥራ የአገር መከላከያ ሠራዊት ተረክቧል " - የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የልዩ ኃይል አደረጃጀት ስምሪት ማቆሙን አስታወቀ። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ነው ይህንን ያሳውቁት። ዋና ኮሚሽነሩ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤ የፌዴራሉ…
#Oromia
የክልል ልዩ ኃይሎችን መልሶ የማደራጀት ተግባር መጀመሩን ተከትሎ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ኃይል ስምሪት #ማቆሙን ገልጿል።
በክልሉ ያለውን የፀጥታ ማስከበር ስራ የአገር መከላከያ ሰራዊት መረከቡንም አሳውቋል።
የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ጄነራል አራርሳ መርዳሳ ፤ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ነው ይህን ያሉህ።
ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው መንግሥት " ሸኔ " እያለ የሚጠራውና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን የመንግሥትን ጥሪ በመቀበል እንቅስቃሴውን የሚያቆም ከሆነ በክልል ሌሎች የፀጥታ ሥራዎች #በመደበኛ_ፖሊስ እንደሚከወኑ ያሳወቁት ጄነራል አራርሳ ለጊዜው ግን የዜጎች ደህንነት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ የመከላከያ መከላከያ ሰራዊት ኃላፊነቱን ተረክቧል ብለዋል።
በኦሮሚያ ላይ አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታው #አስተማማኝ_እንዳልሆነ ያልሸሸጉት ኮሚሽነሩ በተለያየ ስያሜ በመንቀሳቀስ ኅብረተሰቡን የሚያፈናቅሉ መኖራቸውን ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃለምልልስ ገልጸዋል።

#Amhara
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን በፌዴራልና በክልል መደበኛ የጸጥታ ኃይሎች ውስጥ እንዲካተቱ በማድረግ መልሶ ለማደራጀት ያሳለፈውን ውሳኔና ትግበራ መጀመሩን ተከትሎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ ተቃውሞዎች፣ የጸጥታ መደፍረስ እና በአንዳንድ አካባቢዎች የደረሱ ግጭቶችንና ጉዳቶችን በተመለከተ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።
በተለይም፦
- በቆቦ፣
- በባሕር ዳር፣
- በወረታ፣
- በኮምቦልቻ፣
- በደብረ ብርሃን እና በመራዊ የተቃውሞ ሰልፎች፣ መንገድ መዘጋት፣ የአገልግሎት መቋረጥ እንዲሁም በጸጥታ ኃይሎች መካከል ፍጥጫዎች የተከሰቱ ሲሆን፤ በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች በጸጥታ ኃይሎች በተወሰዱ እርምጃዎችና ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የተፈጸሙ ጥቃቶች የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች ሠራተኞችን ጨምሮ የሲቪል ሰዎች ሞት እና የአካል ጉዳት ማስከተሉን ኢሰመኮ አሳውቋል።
በሌላ በኩል በእነዚህ ከተሞችና ሌሎችም አካባቢዎች በተፈጠረው ውጥረት፣ አለመረጋጋት፣ የአገልግሎት መቋረጥ እና የእንቅስቃሴ እገዳዎች ምክንያት በነዋሪዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ እና ሥራ ላይ እንቅፋት መፈጠሩን አመልክቷል።
አጠቃላይ ችግሩና የጸጥታው ሁኔታ አስቸኳይ እልባት ካላገኘ ለከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ሥጋት በመሆኑ ፦
➤ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ጉዳዩን በምክክርና በመግባባት እንዲፈቱ፣
➤ በተለይም አጠቃላይ የፖለቲካ ነባራዊ ሁኔታው የፈጠረውን ሥጋትና የአለመተማመን ስሜት ከግምት በማስገባት መንግሥት የፖሊሲ ውሳኔውን አስፈላጊነትና ጠቀሜታ ለሚመለከታቸው ሁሉ በትዕግሥትና በጽሞና የሚያስረዳበትን ሁኔታ እንዲያመቻች፣
➤ የጸጥታ አካላት ያልተመጣጠነ እና ሕይወት የሚያጠፋ ኃይል ከመጠቀም እንዲቆጠቡ፣
➤ መንግሥት ስለደረሰው ጉዳት ሁሉ አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት እንዲያረጋግጥ እንዲሁም ሁሉም ሰው ሐሳቡን በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲገልጽ ኢሰመኮ ጥሪውን አቅርቧል።
ኢሰመኮ ከመደበኛው የክትትል እና ምርመራ ሥራው ጎን ለጎን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በሙሉ በማነጋገር እና ምክረ ሐሳቦችን በመስጠት የተፈጠረው ችግር በውይይት እንዲፈታ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጿል።
ምንጭ፦ ኢሰመኮ

" የተከሰተው ችግር #በውይይት_ተፈቷል ፤... የሰላም #ስምምነትም ተደርጓል " - የሰ/ ወሎ ዞን አስተዳደር
የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ፤ ከሰሞኑን ከክልል ልዩ ሀይል መልሶ ማደራጀት ጋር ተያይዞ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር በውይይት መፈታቱን ዛሬ ምሽት አሳውቋል።
የፀጥታ ችግሩን ለመፍታት በሐይማኖት አባቶች፣ በአገር ሽማግሌዎችና በዘወልድ ሽምግልና ስርዓት የሠላም ስምምነት ተደረጓል ብሏል።
በሰላም ስምምነት ስነስርዓቱ ላይ ፦
- የአገር መከላከያ ሠራዊት ፣
- የክልል ፣ የዞን ፣ አመራሮች
- የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራሮች
- የአገር ሽማግሌዎች የሰላም ስምምነቱን አስመልክተው መግለጫ መስጠታቸውንም የዞን አስተዳደሩ አመልክቷል።
ስምምነቱን በተመለከተ የሰ/ወሎ ዞን አስተዳደር ለህዝብ ያሰራጨው መረጃ #ከላይ ተያይዟል።
NB. ውድ ቤተሰቦቻችን በዚህ የሰ/ወሎ ዞን አስተዳደር መግለጫ ዙሪያና ስምምነቱ ዙሪያ ከፋኖ አደረጃጀት አመራሮች ዘንድ የሚሰጥ አስተያየት ካለ ተከታትለን የምናሳውቅ ይሆናል።