TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት ሆነው ተሾሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንትነት በእጩነት ያቀረቧቸው ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ ሹመታቸው ፀድቋል። የህ/ተ/ም/ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሹመትን በሁለት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው ያፀደቀው። @tikvahethiopia
#NewsAlert
ወ/ሮ ዘሃራ ኡመር አሊ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተሾሙ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዜዳንትነት በእጩነት ያቀረቧቸው ወ/ሮ ዘሃራ ኡመር አሊ ሹመታቸው ፀድቋል።
የህ/ተ/ም/ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሹመትን በሁለት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው ያፀደቀው።
@tikvahethiopia

Photo
#Update
ዶ/ር ጫላ ዋታ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ተጠየቀ።
የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ የመንግስት ግዥ ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በሰሩት ስራ ነው ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የተጠየቀው።
ምክር ቤቱ ያለመከሰስ መብታቸው መነሳት ላይ ድምፅ ይሰጣል።
በአሁን ሰዓት ዶ/ር ጫላን ጨምሮ ሌሎች የምክር ቤት አባላት በጉዳዩ ዘሪያ አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ።

#Update ዶ/ር ጫላ ዋታ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ተጠየቀ። የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ የመንግስት ግዥ ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በሰሩት ስራ ነው ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ የተጠየቀው። ምክር ቤቱ ያለመከሰስ መብታቸው መነሳት ላይ ድምፅ ይሰጣል። በአሁን ሰዓት ዶ/ር ጫላን ጨምሮ ሌሎች የምክር ቤት አባላት በጉዳዩ ዘሪያ አስተያየት እየሰጡ ይገኛሉ። @tikvahethiopia
#NewsAlert
ዶ/ር ጫላ ዋታ ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ።
የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ የመንግስት ግዥ ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በሰሩት ስራ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል።
ምክር ቤቱ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው ያለመከሰስ መብታቸው የማንሳት ውሳኔን ያፀደቀው።
አንድ ድምፀ ተአቅቦ ያደረጉት እራሳቸው ዶ/ር ጫላ ዋታ ናቸው።
(ዝርዝር ይኖረናል)
@tikvahethiopia
ዶ/ር ጫላ ዋታ ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ።
የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ የመንግስት ግዥ ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በሰሩት ስራ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል።
ምክር ቤቱ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው ያለመከሰስ መብታቸው የማንሳት ውሳኔን ያፀደቀው።
አንድ ድምፀ ተአቅቦ ያደረጉት እራሳቸው ዶ/ር ጫላ ዋታ ናቸው።
(ዝርዝር ይኖረናል)
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ዶ/ር ጫላ ዋታ ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ። የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ የመንግስት ግዥ ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በሰሩት ስራ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቷል። ምክር ቤቱ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው ያለመከሰስ መብታቸው የማንሳት ውሳኔን ያፀደቀው። አንድ ድምፀ ተአቅቦ ያደረጉት እራሳቸው ዶ/ር ጫላ ዋታ ናቸው። (ዝርዝር ይኖረናል) …
#ዝርዝር
የቀድሞ የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ ዛሬ ያለመከሰስ መብታቸው ተገፏል።
የምክር ቤቱ የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስለ ዶ/ር ጫላ ዋታ ምን አለ ?
#የመንግስት_ግዥ_ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በመሄድ የውስጥ ገቢ ማስገኛ በሚል " ቢኤችዩ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነሪንግ ጄነራል ሌቭል 1 ፒኤልሲ " የተባለ አማካሪ ድርጅት በማቋቋም በስማቸው ንግድ ፍቃድ በማውጣት ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተለያዩ የግንባታ ስራዎችን የማማከር አገልግሎት ለመስጠት በቀጥታ ግዥ በመፈፀም መዋዋሉን ፣ ለአማካሪ ድርጅቱና ለአማካሪ ድርጅቱ ላፀደቃቸው ተቋራጮች ክፍያ በመፈፀም በመንግስት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ አድርገዋል በሚል ጥቆማ ደርሶ ዝርዝር ምርመራ ተደርጓል።
በዚህም በተደረገ የወንጀል ማጣራት ፦
- 195 ሚሊዮን 52 ሺህ 812 ብር ከ81 ሳንቲም የሚያወጡ የተገለያዩ የግንባታ ስራዎች ለዘጠኝ ተቋራጮች ከመንግስት የግዥ አዋጆች እና አፈፃፀም መመሪያ ውጭ በቀጥታ እንዲፈፀም አድርገዋል።
- ዩኒቨርሲቲው ለመሰረተ ልማት ግንባታ የተፈቀደለትን የካፒታል በጀት አላግባብ በመጠቀም የግዥ ህግ እና ደንብ ባልተከተለ መልኩ ዋጋቸው 116 ሚሊዮን ብር የሆኑ 14 ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች በግል ተቋራጭ ድርጅት ስም ግዥ ተፈፅሟል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተሽከርካሪዎቹ እና ማሽነሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው ገንዘብ የተገዙ ቢሆንም በግል ተቋራጮች ድርጅቶች ስም እንዲሆኑ ተደርጋል።
ተሽከርካሪዎቹ እንዲሁም ማሽነሪዎቹ የተገዙበት ዋጋ እጅግ የተጋነነ ሲሆን ለምሳሌ አንድ ደብል ጋቢና ፒካፕ ለተሽከርካሪ ተቋራጭ ድርጅቱ ከአስመጪ በብር 3 ሚሊዮን 300 ሺህ ግዥ የተፈፀመ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው በብር 6 ሚሊዮን 173 ሺህ 396 ብር ከ83 ሳንቲም እንደተገዛ ተቆጥሮ ክፍያ በመፈፀም ብር 2 ሚሊዮን 873 ሺህ 396 ብር እላፊ ተከፍሏል።
አንድ ሌላ ተሽከርካሪ ግዥ የተፈፀመው በብር 6.1 ሚሊዮን ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው በብር 6 ሚሊዮን 415 ሺህ 687 ብር ከ05 ሳንቲም በመግዛት ክፍያ የተፈፀመ በመሆኑ 315 ሺህ 687 ብር ከ05 ሳንቲም እላፊ እንዲከፈል ተደርጓል።
አጠቃላይ የ14ቱ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች ባለቤት የዩኒቨርሲቲው ሳይሆን የስራ ተቋራጭ ድርጅቶቹ እንዲሆኑ በማድረግ የተሰጣቸውን የመንግስት ኃላፊነትን ወደ ጎን በመተው ለራሳቸው የማይገባ ጥቅም በማግኘት እንዲሁም አማካሪ ድርጅት በሌለበት የተቋሙ የግንባታ ፅህፈት ቤት በፀደቁ የክፍያ የምስክር ወረቀት 11 ሚሊዮን 532 ሺህ 83 ብር ከ53 ሳንቲም ለተቋራጮች ክፍያ እንዲፈፀም በማድረግ የመንግሥት ሃብት እና ንብረት እንዲባክን አድርገዋል።
- በዶ/ር ጫላ እና ቢኤችዩ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነሪንግ ጄነራል ሌቭል 1 ፒኤልሲ በተባለው ድርጅት ላይ በተካሄደው የሃብት ምርመራ ስራ በተገኘው ውጤት ድርጅቱን የሚያንቀሳቅሱት ስራ አስኪያጅ እና የቦርድ ዳይሬክተር ዶ/ር ጫላ ዋታ መሆናቸው በዚህም ድርጅቱ ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ጋር በገባው ውል መሰረት በድምሩ 23 ሚሊዮን 135 ሺህ 433 ብር ከ27 ሳንቲም ያለአግባብ ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ የባንክ ሂሳብ ላይ ተቀንሶ ወደ ድርጅቱ ሂሳብ ቁጥር ገቢ መደረጉና ከዚህ በመቀጠል ከድርጅቱ ቢኤችዩ ኃ/የተ/የግል ማህበር የባንክ ሂሳን ተቀንሶ በ6 የተለያዩ ጊዜያት በድምሩ 2 ሚሊዮን 116 ሺህ 16 ብር ከ65 ሳንቲም ወደ ዶ/ር ጫላ ዋታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ የሂሳብ አካውንት ገቢ ተደርጓል።
- በዶ/ር ጫላ ዋታ ባለቤት ስም ወ/ሮ ፀሃይ ኃይሉ ተፈራ ስም 72 ካሬ ላይ ያረፈ በብር 10 ሚሊዮን የተገዛ ባለ 3 ወለል ህንፃ የተገኘ መሆኑና ህንፃው የተገዛበት ገንዘብ በተመለከተ የተደረገው የፋይናንስ ምርመራ ክፍያው የተፈፀመው " ቢዳሩ ኮንስትራክሽን " ከተባለ ድርጅት ብር 4 ሚሊዮን እንዲሁም ደግሞ አቶ ተስፋሁን ሌንጄቦ ሌካ ብር 3 ሚሊዮን 500 ሺህ በተጨማሪ በዚህ ተመሳሳይ ቀን ቦኩይ ኢታንሳ የተባሉ ብር 2 ሚሊዮን 500 ሺህ በዶ/ር ጫላ ዋታ ባለቤት ወ/ሮ ፃሃይ ኃይሉ ስም ወደ ተከፈተ የሂሳብ ቁጥር ገቢ ተደርጎ ይኸው ገንዘብ በቀጥታ ለህንፃው ግዥ መዋሉ ታውቋል።
ገንዘቡ ለባለቤታቸው ለወ/ሮ ፀሃይ ኃይሉ ተፈራ ገቢ አድራጊዎች ማንነት ለማጣራት በተደረገው ምርመራ መሰረት በ " ቢዳሩ ኮንስትራክሽን " በቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ገንዘብ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አአ 05069 የሆነ በብር 7 ሚሊዮን 785 ሺህ 157 ከ30 ሳንቲም የተገዛለት መሆኑና ተስፋሁን ሌንጄቦ የተባለው ደግሞ ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ለሚያሰራቸው ግንባታ መሰረተ ልማት እና ኢንፍራስትራክቸር ዝርጋታ ስራ በቀጥታ በደብዳቤ ትዕዛዝ 55 ሚሊዮን 133 ሺህ 893 ብር ስራ የተሠጠው ነው።
- በዶክተር ጫላ ዋታ ስማቸው የተመዘገበ አ/አ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ አንድ ሙሉ ክፍያው የተፈፀመ ኮንዶሚኒየም ቤት በልጃቸው ስም 200 ሺህ ብር በራሳቸው ስም የተገዛ የ1 ሚሊዮን ብር ሼር የተገኘ መሆኑ ተረጋግጧል።
ዶ/ር ጫላ ዋታ ምን አሉ ? ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-04-04

Telegraph
Tikvah Ethiopia
#ዝርዝር የቀድሞ የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት የነበሩት ዶ/ር ጫላ ዋታ ዛሬ ያለመከሰስ መብታቸው ተገፏል። የምክር ቤቱ የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስለ ዶ/ር ጫላ ዋታ ምን አለ ? የመንግስት ግዥ ህግ ከሚፈቅደው አሰራር ውጭ በመሄድ የውስጥ ገቢ ማስገኛ በሚል " ቢኤችዩ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነሪንግ ጄነራል ሌቭል 1 ፒኤልሲ " የተባለ አማካሪ ድርጅት በማቋቋም በስማቸው ንግድ ፍቃድ በማውጣት ከቡሌሆራ…
#ኢትዮ_ቴሌኮም
በቴሌብር ሱፐርአፕ በፊት ገፅታ ወይም በጣት አሻራ ደህንነቱ የተጠበቀ አስተማማኝ አገልግሎት ያግኙ!
አዲሱ የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ በፊት ገፅታዎ ወይም በጣት አሻራዎ የሚሰራ ባዮሜትሪክ የደህንነት ማረጋገጫ ስላለው ከመቼውም ጊዜ የበለጠ አካውንትዎ ከደህንነት ስጋት ነፃ ነው፡፡
መተግበሪያውን ከ onelink.to/75zfa5 አውርደው ይጠቀሙ
(ኢትዮ ቴሌኮም)

" እኛ እንዲህ ዓይነት ዘረፋ ይኖራል ብለንም አስበን አናውቅም " - የዘረፋው መርማሪ
ጠቅላላ ዘረፋውን ለመፈጸም የወሰደው 2 ሰዓት ከ13 ደቂቃ ነው።
ዘረፋው በተመሳሳይ ሰዓት፣ በ28 አገራት ውስጥ ነው የተፈፀመው።
ነገሩን በአጭሩ ለማስቀመጥ ተራ ግለሰቦች ወደ ባንክ ኤቲኤም ማሽን ሄደው ገንዘብ ያወጡበት ዘረፋ ነው።
ይህ እንዴት ሆነ ? የሚለውን እንመልከት።
በሕንድ የተወሰኑ ሰዎች ለአስተኔ ገጸባሕሪ (extra role) ፊልም ቀረጻ ተመለመሉ። ደስም አላቸው።
የተሰጣቸው ሚና ከኤቲኤም ማሽን ብር ማውጣት ነው።
ሕንድ ሀገር ማሃራሽትራ የሚገኙ ምልምል ተዋናዮች ድርጊቱን ሲፈጽሙ ለፊልም ቀረጻ መስሏቸዋል።
የታላቁ የገንዘብ ርቆት አካል እንደተደረጉ በፍጹም አያውቁም።
ይህ የሆነው በሐምሌ 2018 ሰንበት ነበር።
ኮስሞስ ይባላል የተዘረፈው ባንክ።
ጭር ባለው የሰንበት ዕለት ድንገት ዋናው የባንኩ መሥሪያ ቤት ያሉ ሠራተኞች መልዕክት ደረሳቸው። መልዕክቱ የሚመጣው ከአሜሪካ የቪዛ ካርድ ኩባንያ ነበር።
ቪዛ ኩባንያ ለኮስሞስ ባንክ ሰዎች በቀጣይ ደቂቃዎች በርካታ የገንዘብ ጥያቄዎች ሊቀርቡላችሁ ይችላል ሲሉ አስጠነቀቁ። ያልተለመዱ ነገሮች በኤቲኤም አካባቢ እየታዩ እንደሆነ አብራሩ።
ግን የኮስሞስ ባንክ ሰዎች ምንድነው የምታወሩት በሚል ቸል አሉት ማስጠንቀቂያውን ነገሩ ሊገባቸው አልቻለም። ምክንያቱም እነርሱ ሲስተም ላይ የሚታይ ምንም የተለየ ነገር የለም።
ከግማሽ ሰዓት በኋላ ቪዛ ኩባንያ በድጋሚ ወደ ኮስሞስ ደወለ።
" እኔ ጋ የሚታዩ ምልክቶች ጤናማ አይመስሉም፤ ለማንኛውም ሁሉምን ኤቲኤም ማሽኖቻችሁን ለጊዜው ከጥቅም ውጭ አድርጉ " አላቸው።
ይህ ለኮስሞስ ባንክ ብዙ ዋጋ የሚያስከፍል ውሳኔ ቢሆንም ምክሩን ተቀብለው ኤቲኤም ማሽኖቻቸውን ዘጉ።
እንዲያም ሆኖ ዘግይተዋል። ኮስሞስ ባንክ በዚያች ሁለት ሰዓት ብቻ 14 ሚሊዮን ዶላር ተዘርፈው ነበር።
ይህን ዘረፋ ማን አቀነባበረው ?
ይህ ዘረፋ በ28 አገሮች ውስጥ በሚገኙ ኤቲኤም ማሽኖች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት የተፈጸመ ነው።
- ሩሲያ፣
- አሜሪካ፣
- ካናዳ፣
- ዩናይትድ ኪንግደም፣
- ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ይገኙበታል።
ሂደቱ በሰሜን ኮሪያ ጠላፊዎች መመራቱ እንደተደረሰበት ተነግሯል።
የዝርፊያው አቀናባሪዎች ላይ ከመደረሱ በፊት የባንኩ ሰዎች ለምን በርካታ ሰዎች #በተመሳሳይ ሰዓት ወደ ኤቲኤም ማሽን ሄደው ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደሚወስዱ ግራ ገብቷቸው ነበር።
የዘረፋው መርማሪ፣ “እኛ እንዲህ ዓይነት ዘረፋ ይኖራል ብለንም አስበን አናውቅም” ይላሉ።
የደኅንነት ካሜራ (ሲሲቲቪ) ምስሎችን በመጠቀም የሕንድ መርማሪዎች ለጊዜው 18 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋል ቻሉ። እነዚህ ሰዎች ተራ ሰዎች ናቸው። ሾፌሮች፣ የቡና ቤት አስተናጋጆች፣ ጫማ ጠራጊዎች ይገኙበታል።
እነርሱ ለፊልም ቀረጻ መመልመላቸውን እንጂ ማን እየተጠቀመባቸውን እንደነሆ አያውቁም ነበር።
በመጨረሻ ከዚህ ጥንቅቅ ካለ ዘረፋ ጀርባ ያለው ‘አልአዛር’ የተሰኘው የሰሜን ኮሪያ ጠላፊዎች ቡድን እንደሆነ ተደረሰበት።
እንዴት ግን ቡድኑ በ28 አገራት ዘራፊ ሊያሰማራ ቻለ ?
ዘራፊና አዘራፊን አገናኝ ደላላ ፦
" አልአዛር " በሚል የሚጠራው የዘራፊዎች ቡድን የሰሜን ኮሪያ የወታደራዊ ደኅንነት መሥሪያ ቤት የሚመራው ነው ይባላል።
" አልአዛር " የሚለውን ስም ያገኘውም ከመጽሐፍ ቅዱስ ሞቶ ከተነሳው አልአዛር ነው።
የእነርሱ የኮምፒውተር ቫይረሶች አንዴ ከገቡ ሁሉን ነገር ይገድላሉ። ኮምፒውተር ሲስተሙን መልሰው መቀስቀስ የሚችሉት እነርሱ ብቻ ናቸው። ከእዚሁ ተግባራቸው ጋር ተያይዞ ነው አልአዛር የሚለው ስያሜ የተሰጣቸው።
ከዚህ ቀደም፦
- ሆሊውድን፣
- ሶኒ ፒክቸርስን እና ሌሎችንም ግዙፍ መሥሪያ ቤቶች መረጃ ዘርፈዋል።
ከባንግላዴሽ ባንክ አንድ ቢሊዮን ዶላር ለመዝረፍ ሞክረዋል።
ሰሜን ኮሪያ ይህ " አልአዛር " የተሰኘው ቡድን በአገሬ ስለመኖሩ አላውቅም ስትል ታስተባብላለች።
ቡድኑ (አልአዛር) ኮስሞስ ባንክ ላይ ለፈጸመው ዘረፋ የተጠቀመው " ጃክፖት " የሚባለውን ስልት ነው። ይህ ስም የተሰጠው ልክ እንደ መቆመሪያ ማሽን ኤቲኤም ገንዘብ እንዲተፋ ስለሚያደርግ ነው።
" አልአዛር " ቡድን ይህን ስልት በተግባር ከማዋሉ በፊት የተመሳሰለ ኢሜይል ወደ ባንኩ ሰዎች በመላክ እንዲከፍቱት ካደረገ በኋላ ወደ ባንኩ ሲስተም ሰርጎ መግባት ችሏል።
ከዚያም የባንኩን የቁጥጥር ሥርዓትን ካሉበት ሆነው ማዘዘ ቻሉ።
ይህ መቆጣጠሪያ ባንኩ የገንዘብ ወጪ ጥያቄ ሲቀርብለት ማሽኑ ገንዘብ እንዲተፋ የሚያዝ ሥርዓት ነው።
ማለትም ከየትኛውም የዓለም ክፍል ከሚገኝ ኤቲኤም የገንዘብ ትዕዛዝ ቢመጣ ሰርሳሪዎቹ ማሽኑ ገንዘቡን እንዲለቀው ማድረግ ያስችላቸዋል።
የማይችሉት አንድ ማሽን ምን ያህል ገንዘብ መልቀቅ እንዳለበት መወሰን ነበር። ብዙ ገንዘብ ለማውጣት ደግሞ የግድ ብዙ ካርድ ማተም ነበረባቸው።
የሚቀራቸው ተመሳሳይ #የኤቲኤም_ካርድ_ህትመት ነው። ይህን የሚሠራ ሌላ ድርጅት ተገኘ።
አስገራሚው እሱ አይደለም፤ ሰሜን ኮሪያዊያን እንዴት ከ28 አገር በተመሳሳይ ጊዜ ገንዘብ የሚያወጡላቸው ሰዎችን ማዘጋጀት ቻሉ ? ምክንያቱም ቪዛ ለማግኘት ራሱ ብዙ ችግር የሚያዩ ናቸው።
ይህን ሥራ ለሌላ ለሚተባበራቸው ድርጅት ኃላፊነት መስጠት ነበረባቸው።
በበይነ መረብ በተዘረጋው የጠላፊዎች ግንኙነት አንድ ሰው ይህን ሥራ እንደሚሠራ ገለጸ።
ይህ ቢግቦስ በሚል ስም የሚጠራው መረጃ ቦርቧሪ ግለሰብ ኤቲኤም ካርዶችን ማምረት እና ሰዎችንም ማዘጋጀት እንደሚችል ገለጸ።
በካናዳና አሜሪካ ተቀጣሪ ሊሆኑ የሚችሉ እንዲሁም ከኤቲኤም ማሽን ገንዘብ ማውጣት የሚቸሉ ግለሰቦችን እንደሚመለምል አስታወቀ።
ይህ በትክክል አልአዛር ቡድን የሚፈልገው አገልግሎት ነበር። ቢግቦስ እና አልአዛር አብረው ጥምረት ፈጠሩ።
ቢግቦስ ለ14 ዓመታት በስርቆት የተሰማራ ማንነቱ ሳይታወቅ የቆየ ግለሰብ ነበር። የሆነ ወቅት ላይ ማንነቱ ተደርሶበት አሜሪካ ውስጥ በመኖርያ ቤቱ ሳለ ተይዞ አሁን ዘብጥያ ወርዷል። የ35 ዓመት ካናዳዊ ነው።
እርሱን መያዝ ቢቻልም የባንኩ 14 ሚሊዮን ዶላር ግን እስከወዲያኛው ቀልጦ ቀርቷል። እነዚህ የሰሜን ኮሪያ ሰርሳሪዎች በፍጹም ዝቀተኛ ገንዘብ ላይ ጊዜያቸውን አያጠፉም። እንዲያውም አሁን አሁን ላይ ትኩረታቸውን ወደ ክሪፕቶከረንሲ አዞረው ወደ 3.2 ቢሊዮን ዶላር ዘርፈዋል።
የአሜሪካ ባለሥልጣናት አልአዛር የተባለውን የዓለም ግዙፍ የባንክ ዘራፊ ቡድን ብሎ ይጠራዋል ለዚያውም ያለ አንዳች የጦር መሣሪያ።
Credit : BBC AMHARIC

#ሊትል
መነሻውን ኬንያ ያደረገው ድርጅታችን ሊትል ሊሚትድ በዋነኝነት በመተግበሪያ የታገዘ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢ ሲሆን ፤ በአሁን ስአት ከ 5ዐዐዐ በላይ ድርጅቶች አለም ላይ አብረውን ይሰራሉ። ከ2016 EC ጀምሮ ላለፉት 7 አመታት አገልግሎት በመስጠት ላይ እንገኛለን ።
ይህን የዳበረ ልምድ ይዘን የሀገራችንን ህዝብ እና ድርጅቶች ለማገልገል ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) መግባታችንን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።
ለአጠቃቀም ምቹ እና ቀላል የሆነ መተግበሪያ አዘጋጅተን የአሽከርካሪውንም ሆነ የተሳፋሪውን ደህንነት በተጠበቀበት ሆኔታ አገልግሎት እየሰጠን እንገኛለን።
ሀበሻ ዊክሊ ያዘጋጀውን ባዛር በማስመልከት የኛን መተግበሪያ ተጠቅመው ሲጓዙ 35% ቅናሽ ያገኛሉ።
አጠቃቀም ፤ መተግበሪያችንን (Little Ride) ከ Play store/App store በማውረድ Promo Code የሚለውን አማራጭ በመጫን LITTLE EASTER በማስገባት አሽከርካሪ መጥራትና የ35% ቅናሽ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ለተጨማሪ መረጃ 7933 ይደውሉ።
(ሊትል ሊሚትድ)

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባላት እነማን ናቸው ?
በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር 27 አባላት ያሉትን ካቢኔ ዛሬ ይፋ አድርጓል።
አዲሱ ካቢኔ የተዋቀረው ከህወሓት፣ ከትግራይ ኃይሎች፣ ከምሁራን እና ከባይቶና ፖለቲካ ፓርቲ ነው።
የካቢኔው 51 በመቶ ቦታ የተያዘው በህወሓት ሲሆን፤ ተቃዋሚው ባይቶና ፓርቲ ሁለት ቢሮዎችን በኃላፊነት የመምራት ዕድል አግኝቷል።
የካቢኔው አባላት ፦
👉 ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ - ምክትል ፕሬዝዳንት እና የሰላምና ጸጥታ ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
👉 ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ - በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ ያልተማከለ አስተዳደር እና ዴሞክራታዜይሽን ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
👉 አቶ በየነ ምክሩ - የኢኮኖሚ ልማት ሽግግር ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
👉 ዶ/ር ሓጎስ ጎደፋይ - የእቅድ፣ ገቢና የሀብት አስተዳደር ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
👉 ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሂወት - የማህበራዊ ልማት ሽግግር ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
👉 ወ/ሮ ያለም ጸጋይ - የመሰረት ልማት ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
👉 ብ/ ጄነራል ተኽላይ አሸብር - የመልሶ ግንባታና ማቋቋም ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
👉 ዶ/ር አልጋነሽ ተሰማ - የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራና ስልጠና ካቢኔ ሴክሬተሪያት ኃላፊ
👉 አቶ አማኑኤል አሰፋ - ቺፍ ካቢኔ ሴክሬተሪያት
👉 ዶ/ር እያሱ አብርሃ – የእርሻ ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ
👉 ዶ/ር ገብረህይወት ዓገባ - የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ
👉 አቶ ሞገስ ገብረእግዚአብሄር - የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ
👉 አቶ ታደለ መንግስቱ - የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ
👉 ወ/ሮ ምሕረት በየነ – የፋይናንስና ሀብት ማስተባበር ቢሮ ኃላፊ
👉 ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ – የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
👉 ዶ/ር አማኑኤል ሃይለ – የጤና ቢሮ ኃላፊ
👉 አቶ ሓድሽ ተስፋ - የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ
👉 ሌ/ጄነራል ፍስሃ ኪዳኑ ፋንታ – የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ
👉 ዶ/ር ከላሊ አድሃና – የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ
👉 አቶ ሓይሽ ሱባጋዳስ - የወጣቶች ቢሮ ኃላፊ
👉 ወ/ሮ ገነት አረፈ – የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ
👉 ሜ/ጄነራል ዘውዱ ኪሮስ - የማህበራዊ ጉዳይ እና መልሶ ማቋቋም ቢሮ ኃላፊ
👉 ወ/ሮ አልማዝ ገብረጻድቅ – የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ
👉 ወ/ሮ ፈለጉሽ አሳምነው – የመሬት እና ማዕድን ቢሮ ኃላፊ
👉 ወ/ሮ ፍረወይኒ ገብረእግዚአብሄር – የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
👉 ዶ/ር አጽብሃ ገብረእግዚአብሄር - የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
በሌላ በኩል ፤ አዲሱ የጊዜያዊ አስተዳደር ከቀድሞው አስተዳደር ጋር ዛሬ መቐለ ውስጥ ርክክብ አድርጋል።
መረጃው የ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " እና " ትግራይ ቴሌቪዥን " ነው።
ፎቶ ፦ ትግራይ ኮሚኒኬሽን

" 1 ሚሊዮን ደንበኞቼን ሸልማለሁ " - ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ " በ14 ሳምንታት ውስጥ 1 ሚሊዮን ደንበኞቼን ሸልማለሁ " ብሏል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለአዳዲስ እና ነባር ለሆኑ ደንበኞቹ " ተረክ በጉርሻ " በሚል የሽልማት መርሐግብር መጀመሩን አስታውቋል። በዚህ መርሐግብር አንድ ሚሊዮን ደንበኞችን ሸልማለው ብሏል።
የሽልማት መርሐግብሩ በየሁለት ሳምንቱ እና በየወሩ የሚካሄድ ሆኖ ከመጋቢት 27 እስከ ሰኔ 27 እንደሚቆይ ተገልጿል።
ሽልማቱ ምንድን ነው ?
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አትዮጵያ 3 መኪኖች ፣ 7 ሞተር ሳይክሎች ፣ 7 ባጃጆች፣ ስማርት ስልኮችና ነጻ የአየር ሰዓት ለሽልማቱ ማዘጋጀቱን ገልጿል።
- መኪኖቹ በየወሩ ለባለ ዕድለኞች የሚተላለፉ ይሆናል።
- በየሁለት ሳምንቱ አንድ ባጃጅ እና አንድ ሞተር ሳይክል ለዕድለኞች ይደርሳል።
- በየሁለት ሳምንቱ 3 ሳምሰንግ S-21 እንዲሁም 3 ሳምሰንግ ታብ 8 ለባለ ዕድለኞች ይወጣል።
- ሳፋሪኮም በራሱ ብራንድ የሚያስመጣቸው " ቅመም " የተባሉ ስልኮችን ለሽልማቱ ያዘጋጀ ሲሆን ከቅመም ስልኮች ውስጥ " ቀረፋ " እና " ናና " የተባሉ ስልኮችን ለሽልማት አቅርቧል። እነዚህም በየሁለት ሳምንቱ ለ100 እድለኞች በሽልማትነት ይቀርባሉ፤
- በየቀኑ የ50 ብር፤ የ100 ብር፤ የ200 ብር የአየር ሰዓት ሽልማቶችም ተዘጋጅተዋል።
የዕጣው ዕድለኛ ለመሆን ምን ማድረግ ይጠበቃል ?
- በዕጣው ተሳታፊ ለመሆን ለአዲስ ደንበኞች ሲም ካርድ ገዝተው በ24 ሰዓት ውስጥ ካርድ የሚሞሉ ከሆነ 3 የዕጣ ቁጥሮችን ማግኘት ይችላሉ።
- የሳፋሪኮምን የ10 ብር አየር ሰዓት መሙላት አንድ የእጣ ቁጥር እንዲደርሶ ያስችላል። ይህም ደንበኞች በሚገዙት የአየር ሰዓት መጠን የዕጣ ቁጥሮቹ መጠን እየጨመረ ይሄዳል።
- የድምጽ፣ የአጭር መልዕክት፣ የዳታ፣ የሁሉም ኔትወርክ ወይንም የኮምቦ ጥቅሎችን መግዛት፤ በ1ዐ ብር ጥቅል አንድ ኮድ፤ በ20 ብር ሁለት ጥቅል ሁለት ኮድ ማገኘት ይቻላል ተብሏል። የአየር ሰዓት በስጦታ መልክ መላክም የዕጣ ቁጥር ያሰጣል።
በተጨማሪም ደንበኞች WhatsApp ላይ ብቻ የሚገለገሉበት የኢንተርኔት ጥቅል እያቀረበ መሆኑን የገለጸው ሳፋሪኮም የ 1GB ጥቅል ለሚገዙ ደንበኞቹ 3 የዕጣ ቁጥሮችን ማግኘት ይቻላል ተብሏል።
በየሁለት ሳምንቱ የሚወጣው ዕጣ በብሔራዊ ሎተሪ አማካኝነት የሚወጣ ሲሆን አሸናፊዎች እድለኛ መሆናቸውን በ0700 700 700 ተደውሎ የሚገለፅላቸው ይሆናል ተብሏል።
ቁጥራዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አሁን ላይ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቹ ቁጥር ከ2.8 ሚሊዮን መሻገሩን አስታውቋል።

#ብርሃን_ባንክ
የብርሃን ሞባይል ባንኪንግን (*881#) ተጠቅመው :-
- የዋይፋይና ሌሎችም የኢትዮ ቴሌኮም ክፍያዎችን በቀላሉ ያከናውኑ!
- የአየር ትኬትዎን ይቁረጡ!
- ቀሪ የብድር መጠንዎን ይወቁ
- ያለ ኢንተርኔት በቀላሉ ገንዘብ ያስተላልፉ!
- በሞባይልዎ የቼክ ደብተር ይዘዙ!
- የት/ቤት ክፍያዎን በቀላሉ ይክፈሉ!
- ከራስዎ የባንክ ሂሳብ ወደ ሌሎች ባንኮች ሂሳብ ገንዘብ ያስተላልፉ!
አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !
Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ

የነጻ ትምህርት ዕድል
በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ወይንም Menschen für Menschen Foundation ስር የሚተዳደረው የሐረር ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በ2015 የትምህርት ዘመን ብቁ የሆኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብር ሙሉ ወጪያቸውን ሸፍኖ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ተማሪዎች ከመጋቢተ 18 - 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ባሉት የስራ ቀናት በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
የመመዝገቢያ መስፈርቶች ፦ ትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም. ያወጣውን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርት የሚያሟሉ ወይንም በአገር አቀፍ ፈተና 50% እና ከዚያ በላይ ያመጡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች፡፡
የምዝገባ ቦታዎች በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ በሚገኘው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ዋና መ/ቤት፤ ሐረር በኮሌጁ ቅጥር ግቢ፤ የድርጅቱ ፕሮጄክት ጽ/ቤቶች በሚገኙባችው በተጨማሪም በድረ-ገጻችን https://www.mfmattc.edu.et ላይም መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0256663738/1139 ወይም 0114714579 ደውሎ ማንጋገር ይቻላል፡፡
(ሰዎች ለሰዎች ድርጅት Menschen für Menschen Foundation)