TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቴሌብር #ኢትዮቴሌኮም

ገና በአጭር እድሜው 30 ሚሊየን ተጠቃሚ ያፈራ ፤ 370 ቢሊየን ብር በገበያ ያዘዋወረ ፤ ከ18 ባንኮች ጋር የተጣመረ ፡ እነሆ ቴሌብር ሱፐርአፕን አበሰረ!!!

ከእንግዲህ ለተለያዩ አገልግሎቶች በርካታ መተግበሪያዎችን አይጭኑም፦

በቴሌብር ሱፐርአፕ ሁሉም ስለተጣመሩ
ጊዜና ጉልበት ሳይባክኑ እልፍ ጉዳይዎን እዛው ይከውናሉ።

የትራንስፖርት፣ የመዝናኛ፣ ኢ-ኮሜርስ፣ የመሠረታዊ አገልግሎቶች፣ የምግብ እና ዴሊቨሪ አገልግሎት ሰጪዎች ኧረ ማን የቀረ አለ በቴሌብር ሱፐርአፕ ሁሉም በአንድ ተሰብስበዋል።

የስራ ውጥረት ሲበዛ የክፍያዎች ቀን ይረሳል ፤ ሱፐርአፕ አያንቀላፋም ቀደም ብሎ ያስታውሳል።

የደህንነት አጥሩ አስተማማኝ እና ጠንካራ ፤ ከይለፍ ቃል በተጨማሪ በፊት ገፅና በአሻራ

እልፍ ጉዳይ በአንድ መተግበሪያ
onelink.to/75zfa5 አውርደው ይሞክሩት

(ኢትዮ ቴሌኮም)
#አቢሲንያ_ባንክ

ጊዜ ገና ብዙ ያሳየናል!

አፖሎን ይበልጥ ተመራጭ የሚያደርገው የጣት አሻራዎን በመጠቀም የባንክ ሒሳብዎን ደህንነት አስተማማኝ ማድረግ ማስቻሉ ነው።
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollodigitalproduct #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ Telegram: https://t.iss.one/apollodigitalproduct
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በውግዘት የተለዩ 17 "የቀድሞ" አባቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በተደረሰው ስምምነት መሰረት 10ሩን የስምምነት ነጥቦች መቀበልላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) አስገብተዋል ሲል የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታውቋል።

ደብዳቤውን ያስገቡት 17 ሲሆኑ አንዱ ወደ ጸበል መሄዳቸውን ገልጸው ደብዳቤአቸውን በተወካይ አስገብተዋል።

በጥቅሉ ደብዳቤ ያስገቡት18 ሲሆኑ ቀሪዎቹ  6 የቀድሞ አባቶች በህመም ምክንያት እንዳልተገኙ በዛሬው ዕለት የተገኙት የቀድሞ አባቶች ገልጸው በቅርብ ጊዜ ቀሪዎቹ ግለሰቦች ማመልከቻቸውን ይዘው እንደሚመጡ አስረድተዋል ነው ያለው።

መምሪያው ፥ " በቪዲዮ የይቅርታ መልዕክት እንዲያስተላልፉ እድል እንዲሰጣቸው የተደረገ ቢሆንም ግለሰቦቹ አልተቀበሉትም " ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

" #አስቸኳይ የፓስፖርት አገልግሎት ለጊዜው ተቋርጧል " - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና መሥሪያ ቤት እንዲሁም በ11ዱ የክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ሲሰጥ የነበረው “ አስቸኳይ ” የፓስፖርት አገልግሎት ለጊዜው መቋረጡን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎቱ ለምን ተቋረጠ ?

አገልግሎቱ የተቋረጠው #ከአቅም_በላይ የባለ ጉዳይ ፍሰት ከመፈጠሩ ጋር ተያይዞ መጠነ ሰፊ #የሠነድ_ማጭበርበሮች በመስተዋላቸው ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ተገልጋዮች ሊገለገሉ ሌሊት ላይ በሚመጡበት ወቅት በተለያዩ ህገ-ወጥ ግለሰቦች የሚደርስባቸው እንግልትና ጉዳት በአገልግሎት አሰጣጥና በተገልጋዩ ላይ ተግዳሮት በመፍጠሩ ነው።

ስለሆነም የማስተናገድ አቅም እና ሌሎች ክፍተቶች እስከሚስተካከሉ ድረስ ይሰጥ የነበረው የ “ አስቸኳይ ” ፓስፖርት አገልግሎት ለጊዜው ተቋርጧል።

አስቸኳይ ጉዞ ያላቸው በምን ይስተናገዳሉ ?

ቀድሞ ይሰራበት በነበረው አሰራር መሰረት #አስቸኳይ_ጉዞ ያላቸው አገልግሎት ጠያቂዎች ማስረጃዎቻቸውን አቅርበው #በዋና_መስሪያ ቤት ብቻ ከመጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ይስተናገዳሉ።

ማሳሰቢያ ፦ ተገልጋዮች ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከህገወጥ ደላሎች እንዲጠነቀቁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የመደበኛ ፓስፖርትን በተመለከተስ ?

የመደበኛ ፓስፖርት ተገልጋዮች ቀድሞ በነበረው ሂደት መስተናገድ #ይቀጥላሉ

ምንጭ፦ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

@tikvahethiopia
የIMF ሰዎች እዚህ ኢትዮጵያ ናቸው።

ብሉምበርግ የዜና ወኪል ፤ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ለኢትዮጵያ ሊሰጥ በሚችለው ድጋፍ አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግ የድርጅቱ ባለሥልጣናት አዲስ አበባ ይገኛሉ ብሏል።

በእርስ በርስ ጦርነቱ ሳቢያ ኢትዮጵያ ከIMF ጨምሮ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር የነበራት ግንኙነት ተቀዛቅዞ መቆየቱ ይታወሳል።

እንደ ብሉምበርግ ዘገባ የተቋሙ የባለሙያዎች ቡድን ኢትዮጵያ ከIMF ሊደረግላት ስለሚችለው ድጋፍ አስፈላጊውን “ቴክኒካዊ ሥራ ለማከናወን” ነው አዲስ አበባ የሚገኘው።

ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ በተመለከተ ውይይት እና አስፈላጊውን ሁኔታ እንዲያመቻቹ የተላኩት የIMF ባለሥልጣናት ለ10 ቀናት ያህል ይቆያሉ።

ቃላቸውን ለሮይተር የዜና ወኪል የሰጡ የIMF ቃል አቀባይ በበኩላቸው ፤ ኢትዮጵያ ለምታካሂደው ምጣኔ ሀብታዊ ለውጥ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግላት ተቋሙን እንደጠየቀች ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ ፤ " ሊሰጥ የሚችለው ድጋፍ አገሪቱ ለምታካሂደው አገር በቀል የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ እና ምጣኔ ሀብቷን በማረጋጋት ለሰብአዊ ድጋፍ፣ ለሥራ ፈጠራ እና ለድህነት ቅነሳ የሚውል ይሆናል " ብለዋል።

የIMF ባለሥልጣናት በዚህ ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ የሚያደርጉት ቴክኒካዊ ውይይት ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እና በተቋሙ መካከል ሰብአዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ችግሮችን ለማሻሻል የተደረገ ንግግር ተከታይ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እና በዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም መካከል ሲካሄድ የነበረው የድጋፍ፣ የብድር ስረዛ እና ሽግሽግ ንግግር በከፊል በትግራይ ሲካሄድ ከነበረው ጦርነት ጋር ተያይዞ ምላሽ ሳያገኝ ቆይቶ ነበር።

ብሉምበርግ እንደዘገበው ኢትዮጵያ ጦርነቱ ያስከተለውን ውድመት መልሶ ለመገንባትና የገጠማትን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመሸፈን አስፈላጊ ለሆኑ የገቢ ምርቶች ክፍያ ለመፈጸም ድጋፍ ያስፈልጋታል።

ጦርነቱ ካስከተለው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ውድመት ባሻገር በአፍሪካ ካሉ የመዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች መዳረሻ ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን እና ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የተነሳ ከዓለም ባንክ (World Bank) አንዲሁም ከIMF የምታገኘውን ድጋፍ ገትቶት መቆየቱን አስታውሷል።

በጦርነቱ እና በዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ምክንያት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ችግር የገጠማት ሲሆን ባለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ከመመዝገቡ በላይ እጥረትም ተከስቷል።

#ቢቢሲ #ብሉምበርግ #ሮይተርስ

@tikvahethiopia
" ከአፍጥርና ከፆም ሰዓታት በኋላ ደም በመለገስ የደም ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች እንታደግ " - ደም ባንክ

በተያዘው የጾም ወቅት በቂ ደም ከማግኘት አንፃር ውስነነት መኖሩን የኢትዮጵያ ደም እና ኅብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡ ባንኩ በዚህ ወቅት በቂ ደም እያገኘ አለመሆኑን ነው ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ታዬ ለፋብኮ ተናግረዋል።

#ሕይወትን_ማትረፍ ከፆሙ ዓላማ አንፃር ያለው ፋይዳ ትልቅ ስለሆነ ከአፍጥር እንዲሁም ከፆም ሰዓታት በኋላ ደም በመለገስ የደም ሕክምና የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች ለመታደግ ሕብረተሰቡ በንቃት ደም እንዲለግስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ደም የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ሕይወት ለመታደግ በተንቀሳቃሽ እና በቋሚ ቦታዎች እንዲሁም በሥራ ቀናት በትምህርት ቤቶች፣ መንግሥታዊ እና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት በመዘዋወር የደም ማሰባሰብ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ቅዳሜ ቅዳሜ አደባባይ ላይ ድንኳን በመትከል የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾችን በመቀስቀስ እና እሁድ በቤተ እምነቶች የደም ማሰባሰብ ሥራ እየተከናነ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

#ኤፍቢሲ

More : @tikvahethmagazine
#ድሬ

ትላንት ምሽቱን በድሬዳዋ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በጎርፍ የአንድ ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን በንብረትም ላይ ጉዳት ደርሷል።

የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ እንዳሳወቀው ፤ በቀበሌ 07 አፈተ-ኢሳ / አሸዋ ሰልባጅ ተራ / ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በጎርፍ መውረጃ አሸዋ ውስጥ ተኝቶ የነበረው የ55 አመት ጎልማሳ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ በተኛበት ህይወቱ አልፎ የተገኘ ሲሆን የሰልባጅ ልብስ መሸጫ ቦታው ላይ ጉዳት ደርሷል።

የ55 አመቱ ጎልማሳ በአካባቢው ላይ የቀን ስራ እየሰራ ራሱን እና ቤተሰቡን የሚያስተዳድር ግለሰብ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ አስክሬኑ ወደ ድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ተልኳል ብሏል።

ከመጋቢት 7 - መጋቢት መጨረሻ ድረስ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል የሜትዮሮሎጂ ትንበያ መረጃ የሚያመለክት ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የድሬዳዋ የአደጋ ስጋት ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳሬክቶሬት መረጃ ሲሰጥ ቆይቷል ተብሏል።

በሌላ ዜና ፦ መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ገደማ ቀበሌ 09 " ገንደ ገመቹ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት የገባ #ከርከሮ በቤቱ ባለቤት ላይ ከባድ የአካል ጉዳት አድርሷል።

በአሁኑ ወቅት ግለሰቡ በድልጮራ ሪፈራ ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኝ ሲሆን በድሬዳዋ ከተማ ዳርቻ የሚኖሩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተገቢውን #ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ፖሊስ አሳስቧል፡፡

#ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

ለግብይትዎ የብርሃን ኤቲኤም ካርድን በመጠቀም ጊዜዎን ይቆጥቡ፤ ድካምዎን ያቅልሉ!

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !

Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://t.iss.one/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
#AddisAbaba

ዛሬ ከሠዓት ላይ በአዲስ አበባ፣ አዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 1 መርካቶ በተለምዶ " ማር ተራ " ተብሎ በሚጠራው ቦታ የእሳት አደጋ ደርሶ ነበር።

የእሳት አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

የእሳት አደጋው የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር የተቻለው በእሳት አደጋ ሰራተኞች፣ የፖሊስ አባላት እና በአካባቢው #ወጣቶች ከፍተኛ ርብርብ መሆኑ ተመላክቷል።

የእሳት አደጋው መንስኤ እንዲሁም ያስከተለው የጉዳት መጠን በቀጣይ ተጣርቶ ይገለፃል ተብሏል

መረጃው የክ/ከተማው ኮምንኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#Tigray

“ በጀት ተፈቅዷል። ትክክለኛ ቁጥሩን በሚመለከት ግን ገና እንነጋገራለን ” - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የፌደራል መንግስት፤ ለትግራይ ክልል የበጀት ድጎማ ለመልቀቅ መስማማቱ ገለፁ።

አቶ ጌታቸው ፤ የፌደራል መንግስት ለትግራይ ክልል በጀት ለማስተላለፍ ከስምምነት ላይ መድረሱን የገለፁት ለ “ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ” ድረገፅ በሰጡት ቃል ነው።

ምንም እንኳን በጀት ለማስተላለፍ ስምምነት ላይ ቢደረስም የሚለቀቀውን የገንዘብ መጠን በተመለከተ ግን ገና ውይይት እንደሚካሄድ አቶ ጌታቸው ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

“ በጀት ተፈቅዷል። [ትክክለኛ] ቁጥሩን በሚመለከት ግን ገና እንነጋገራለን ”

NB. ከተሾሙ በነገው ዕለት አንድ ሳምንት የሚሞላቸው አቶ ጌታቸው ረዳ 11 የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላትን ይዘው ከፌደራል መንግስት ጋር ለመነጋገር በአዲስ አበባ ከተማ ይገኛሉ።

የትግራይ ክልል የበጀት ድጎማ መቼ እና ለምን ነበር የተቋረጠው ?

የፌዴሬሽን ምክር ቤት በመስከረም 2013 ባስተላለፈው ውሳኔ ነው የትግራይ ክልል የበጀት ድጎማ የተቋረጠው።

የበጀት ድጋፍ እንዲቋረጥ የተደረገው፤ ክልሉ ከፌደራል መንግስት እውቅና ውጭ “ኢ-ህገ መንግስታዊ ምርጫ አካሄዷል” በሚል ነው።

Credit - ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@tikvahethiopia