TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ረመዷን

በመላው ዓለም ላይ የሚታወቁት የዝምባብዌ ዜግነት ያላቸው የእስልምና መሁር ሙፍቲ  ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ስለ ቅዱሱ የረመዷን ወር እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ፦

ሙፍቲ  ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር) ፦

" ረመዷን ምንድን ነው ? ሰዎች እየፆምን ነው ይላሉ ይህ ግን የረመዷን አንዱ ክፍል ብቻ ነው።

ረመዷን ፦
🤲 #የሰላም ወር ነው፤
🤲 #የመረጋጋት ወር ነው፤
🤲 #የመፈወሻ ወር ነው፤
🤲 #የቸርነት ወር ነው፤
🤲 #የምህረት ወር ነው፤
🤲 #የይቅርታ ወር ነው፤
🤲 #ጀነትን የምናገኝበት ወር ነው፤
🤲 ይህ ወር #ሙስሊም መሆናችንን የምናከብረበት ነው ፤ ሙስሊም በመሆናችን #ራስን_መግዛትን የምንለማመድበት የፈለግነውን ብቻ ሳይሆን ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ የወሰነውን የምናደርግበት ወር ነው ፤  ሱብሃንአላህ ! ስለዚህ ለአላህ ቃል ጥረት ማድረግ ግዴታችን ነው። "

መልካም #የረመዷን_ጾም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲሆን እንመኛለን።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት #ተሰረዘ። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ምክር ቤቱ ዛሬ ባሄደው ልዩ ስብሰባ ህወሓትን ከሽብርተኛ መዝገብ ለማንሳት በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔውን አፅድቋል። #ኤፍቢሲ @tikvahethiopia
" ውሳኔውን እንቃወማለን " - አብን

አብን የ " ህወሓት "ን ከሽብር መዝገብ መሰረዝ እንደሚቃወም ገለፀ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) ትላንት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሓትን ከአሸባሪ ድርጅትነት መዝገብ መሰረዙን እንደሚቃወም ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ፓርቲው በመግለጫው ፤ ዘላቂ ሰላም ያመጣል ተብሎ የተፈረመው የፕሪቶሪያው ሥምምነት አንኳር ጉዳዮች አልተተገበሩም ከዚህም በላይ የጦርነት ቀጠና ሆነው የቆዩትን አካባቢዎች ለ4ኛ ዙር የጦርነት አደጋ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች እየተከሰቱ ነው ብሏል።

አብን ፤ " በፕሪቶሪያው ሥምምነት አንቀጽ 6(F) መሰረት ትሕነግ (የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር) በ30 ቀናት ውስጥ የቀላል መሳሪያ ትጥቅ ጨመሮ ጠቅላላ ትጥቅ እንዲፈታ እና በሥምምነቱ አንቀጽ 3(5) መሰረት ደግሞ የሀገር የመከላከያ ሠራዊት ወደ ትግራይ ገብቶ ጸጥታ የማስከበሩን ሥራ በተሟላ ሁኔታ እንደሚረከብ ሥምምነት የተደረሰ ቢሆንም ቡድኑም ትጥቅ ሳይፈታ የሀገር መከላከያ ሠራዊትም ወደ ትግራይ ገብቶ ጸጥታ የማስከበር ሥራውን ሳይረከብ ቡድኑ የገንዘብ እና የማቴሪያል ድጋፍ ሲደረግለት ቆይቷል " ብሏል።

አክሎም ፤ " ከጠቅላለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ብዛት ያላቸው የምክር ቤት አባላት ባልተገኙበት እና ከተገኙትም ውስጥ ከ60 በላይ ተወካዮች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ባሉበት ሁኔታ ቡድኑ ከሽብርተኝነት መዝገብ እንዲፋቅ ተደርጓል " ሲል አስረድቷል።

በአጀንዳው ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ በተጠራው ስብሰባ ላይ ብዛት ያላቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አልተገኙም ያለው ፓርቲው ከተገኙትም ውስጥም ከ60 በላይ የሆኑት አባላት የውሳኔ ሃሳቡን በመቃወም እና ድምጸ ተዐቅቦ በማድረግ ድጋፋቸውን ነፍገዋል ይህ የሚያሳየው የሚበዙት የምክር ቤቱ አባላት የቡድኑን ከሽብርተኝት መዝገብ መፋቅ የማይደግፉ መሆኑን ነው ፤ ውሳኔው ሕጋዊ ነው ቢባል እንኳ ቅቡል (Legitimate) እንዳይሆን የሚያደርገው ነው ብሏል።

አብን ፦

- በጉዳዩ ላይ የጋራ መግባባት ባልተደረሰበት ፣

- የሚበዙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የውሳኔው አካል ባልሆኑበት ፣

- ህወሓት ትጥቅ ባልፈታበት እና ይልቁንም ቡድኑ የፕቶሪያውን የሰላም የሥምምነት አንቀጽ 7(1)(D) በመጣስ በተለያዩ አካባቢዎች አዲስ የታጣቂዎች ምልመላ ፣ ስልጠና እና የጦርነት ዝግጅት እያደረገ ባለበት ሁኔታ ቡድኑን ከሽብርተኝነት መዝገብ መሰረዝ ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው ሲል ተቃውሟል።

ውሳኔው ተገማች በሆነ ጊዜ ውስጥ ለሌላ ዙር ግጭት እና ጦርነት የሚያጋልጥ በመሆኑ ፓርቲው ውሳኔውን በፅኑ እንደሚቃወም ገልጿል።

በመሰል አግባብነት በሌላቸው ውሳኔዎች በሕዝቡ እና በሀገር ላይ ለሚደርሰው በደል ሁሉ የፌዴራሉ መንግስት ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳል ሲል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ አስገንዝቧል።

(አብን ያወጣው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ድሬ

በድሬዳዋ ከተማ ትላንት በደረሰ የእሳት አደጋ የዋጋ ግምቱ 46 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ።

" ለጊዜው  ምክንያቱ ባልታወቀ  ሁኔታ  በተነሳ የእሳት ቃጠሎ የዋጋ ግምቱ አርባ ስድስት (46) ሚሊዬን ብር የሚገመት ንብረት ውድሟል " ሲል የድሬድዋ ፖሊስ አሳውቋል።

ፖሊስ እንደገለፀው አደጋው የደረሰው ትላንት መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ንብረትነቱ " የሮያል ፎም ፍራሽ እና ፕላስቲክ ፋብሪካ " ላይ ነው፡፡

ከቀኑ 5 ሰአት ገደማ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ የፋብሪካው ንብረት የሆኑ ፦

👉 አንድ ትልቅ የምርት ማከማቻ መጋዘን፤
👉 አንድ  ቦንድድ ማሽን፤
👉 በርካታ የተጠናቀቁ የስፖንጅ ፍራሽ ምርቶች እንዲሁም ሁለት ሆዝ የእሳት ማጥፊያ በአጠቃላይ የዋጋ ግምቱ አርባ ስድስት (46) ሚሊዬን ብር ንብረት ወድሟል።

አደጋው እንደደረሰ የድሬዳዋ ፖሊስ የእሳት እና ድንገተኛ ዲቪዥን እና የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የእሳት አደጋ ተከላካይ ቡድን በቦታው ላይ በመድረስ እሳቱ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይዛመት ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። አደጋውን ለመከላከል አርባ ስምንት ሺ ሊትር ውሃ እና አንድ መቶ ሊትር ፎም መጠቀማቸው ተገልጿል።

በደረሰው የእሳት አደጋ ከንብረት ጉዳት ውጪ በሰው ላይ ምንም አይነት አደጋ ያልደረሰ መሆኑን የገለፀው የድሬዳዋ ፖሊስ በአሁኑ ወቅት የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ምንጭ፡ #ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#NewsAlert

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ አቶ ጌታቸው ረዳን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳደር አድርገው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አሳውቋል።

ርዕሰ መስተዳደሩ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ሃይሎችን ውክልና የሚያረጋገጥና አካታች የሆነ አስተዳደር በማዋቀር የክልሉን አስፈፃሚ አካል የመምራትና የማስተባበር ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ወላይታሶዶ_ዩኒቨርሲቲ

• " ለጉልበት ሰራተኞች 4 ሚሊዮን ብር ተከፍሏል ቢባልም ገንዘብ መውጣቱን እንጂ #የት_እንደገባ ማረጋገጥ አልተቻለም " - የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን የ2013 በጀት ዓመት የሒሳብ ህጋዊነት ኦዲት ሪፖርትን ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል።

በዚህ ግምገማ ምን ተባለ ?

- ዩኒቨርሲቲው የኦዲት ግኝቱን የማስተካከያ እርምጃ እየወሰደ ባለመሆኑ ባለፉት አራት ዓመታት ተቀባይነት የሚያሳጣ የኦዲት አስተያየት ውስጥ ያለፈ ተቋም እንደሆነና በትኩረት መስራት እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አስገንዝቧል።

- ዩኒቨርሲቲው ማስመለስ ከነበረበት የገንዘብ ምጣኔ 99.95% እንዳላስመለሰ እና የኦዲት ግኝት መስተካከል ከነበረበት 11 ጉልህ  የኦዲት ግኝቶች 1 ብቻ ምላሽ እንዳገኘ ኮሚቴው ገልጿል።

- የዩኒቨርሲቲው አመራር የፋይናንስ ህግጋትን እና አሰራሮችን ተከትሎ ከመስራት አኳያ ሰፊ ክፍተት በመኖሩ በትኩረት መስራት አለበት ተብሏል።

- ዩኒቨርሲቲው ባልተሰጠው ስልጣን አዳዲስ ደንቦችን እና መመሪያዎችን እያዘጋጀ ክፍያ ሲፈፅም የነበረ ሲሆን #ለጉልበት_ሰራተኞች አራት (4) ሚሊዮን ብር ተከፍሏል ቢባልም ገንዘብ መውጣቱን እንጂ የት እንደገባ ማረጋገጥ እንዳልተቻለ ኮሚቴው ገልጿል።

የኦዲት ግኝቶችን በተመለከተ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ክርስትያን ታደለ ምን አሉ ?

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተሻሻለ የኦዲት ግኝት ማሻሻያ መርሃ-ግብሩን እስከ መጋቢት 23/2015 ዓ.ም እንዲያቀርብ እና መርሃ-ግብሩም ፦
- ለገንዘብ ሚኒስቴር፣
- ለፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት እና ለሰው ኃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ግልባጭ ሪፖርት ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ተቋሙ የኦዲት ግኝቶችን ትኩረት ሰጥቶ ተገቢውን የእርምት ዕርምጃዎችን እየወሰደ በየ 3 ወሩ ለቋሚ ኮሚቴው ሪፖርት ማቅረብ አለበት ብለዋል።

አያይዘውም ገንዘብ ሚኒስቴር ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባልተወጡ የዩኒቨርሲቲው #አመራሮች እና የሥራ ኃላፊዎች ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃዎችን ወስዶ ሪፖርቱን በ10 ቀናት ውስጥ ማሳወቅ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

የፍትህ ሚኒስቴር #በወንጀለኛ እና #በፍትሃብሄር ተጠያቂነት የሚያስከትሉ ጉዳዮች ካሉ መርምሮ ክስ መመስረት እንዳለበት አቶ ክርስቲያን ታደለ አስረድተዋል።

አቶ ክርስትያን የሰው ኃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኦዲት ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ተገቢውን የቁጥጥር ስራ እንዲሰራ እና የኦዲት ግኝቶች ዩኒቨርሲቲው የእቅድ አካል አድርጎ እንዲያካትታቸው ተገቢውን አመራር  እንዲሰጥ አሳስበዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከስልጣኑ ውጪ ባወጣቸው ደንቦች እና መመሪያዎች የሚያደርጋቸውን ክፍያዎች እንዲያቆም እና በቀጣይም በመንግስት የፋይናንስ ህግጋት እና መመሪያዎች ተንተርሶ ብቻ መስራት እንዳለበት፤ ያለ አግባብ የተከፈሉ ክፍያዎችም ተመላሽ እንዲሆኑ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

#FDRE_HoPR

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሐጅ " በዘንድሮ አመት ሐጅ ለማድረግ ዕቅድ ያላችሁ ቀድማችሁ የጉዞ ሰነዳችሁን (ፓስፖርታችሁን) ከወዲሁ ዝግጁ አድርጉ " - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2015/1444 አሂ የሃጅ መስተንግዶ በተሻለ መልኩ ለመስጠት ከክልልና ከተማ አስተዳደር የመጂሊስ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት መደረጉን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳውቋል። የ2015/1444 የተከበሩ የአሏህ…
#Update

• የዘንድሮ የሐጅ አድራጊ ክፍያ 👉 315,000 ብር እንዲሆን ተወስኗል።

የ1444/2015 የሁጃጆች ምዝገባ በ16 የምዝገባ ጣቢያዎች እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን የአንድ ሐጅ አድራጊ ክፍያ ብር 315,000 (ሶስት መቶ አስራ አምስት ሺህ) እንደሚሆን ይፋ ተደርጓል።

ይህ የተሰማው በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ1444/2015 ዓ.ል የሐጅ ምዝገባ በተመለከተ እየሰጠ በሚገኘው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

በመግለጫው የሐጅ ተጓዥ ለምዝገባ በአካል መቅረብ ይኖርበታል የተባለ ሲሆን ማንኛዉም ተመዝጋቢ የሚከተሉትንን መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅበታል ፦

1. የታደስ የነዋሪነት መታወቂያ/ መንጃ ፈቃድ
2. የጉዞ ሰነድ (ፖስፖርት ) የመጠቀሚያ ጊዜው ለመጠናቀቅ ከ9 ወራት በላይ የቀረው መሆን ይኖርበታል፡፡
3. አንድ ጉርድ ፍቶ ግራፍ
4. የኮቪድ ክትባት የወሠደበት ማስረጃ እንዲሁም የቢጫ ወባ ክትባት ካርድ (ቢጫ ካርድ) ማቅረብ ይጠበቅበታል።
5. እራሳቸዉን ችለው የሐጅ ስርዓቱን መፈፀም የሚችሉ ወይም አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተዉና ክፍያ ከፍለው ሊያግዛቸው የሚችል ሰው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ከእስልምና መሰረቶች ውስጥ አንዱ የሆነዉና አቅሙ ለፈቀደት ሙስሊም ወንድም ሆነ ሴት በዕድሜ ዘመኑ ቢያንስ አንድ ጊዜ ሐጅ የማድረግ ግዴታ እንዳለበት መሆኑ ይታወቃል።

(ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

@tikvahethiopia
#ኢትዮ_ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም “የቴሌብር ሱፐርአፕ” በማለት የሰየመውን ማዘመኛ በዛሬው ዕለት አስተዋውቋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በ " ቴሌብር " መተግበሪያው ቀደም ሲል ለደንበኞቹ ሲያቀርብ ከነበረው አገልግሎት በተጨማሪ ተጨማሪ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችለውን “የቴሌብር ሱፐርአፕ” በማለት የሰየመውን ማዘመኛ በቴሌብር መተግበሪያው ላይ ተግባራዊ አድርጎ በዛሬው ዕለት አስተዋውቋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፋጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት፤ ተቋሙ የተለያዩ አካላትን (የቢዝነስ ተቋማትን፣ ሶፍትዌር አበልጻጊዎችን፣ Solution partner, Content provider) በማካተት የዲጂታል ኢኮኖሚን እየገነባ ነው።

ኃላፊዋ ተቋሙ የሞባይል መተግበሪያው ከገንዘብ አገልግሎቶች በተጨማሪ የተለያዩ መተግበሪያዎችን በውስጡ በመያዝ ለተገልጋዩ እንደሚያደርስ ነው የገለፁት።

በ " ቴሌብር ሱፐርአፕ " የተጨመሩ አዳዲስ አገልግሎቶች ምን ምን ናቸው ?

- የታቀደ ክፍያ፦ የገንዘብ እና የአየር ሰዓት ለመላክ እንዲሁም ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያዎችን በቀኑ ለመክፈል ቀድሞ ማቀድ የሚያስችል አገልግሎት

- የድል ጨዋታ፦ አጠቃቀምን መሰረት ያደረ፣ የአጓጊ ሽልማቶች ባለቤት የሚኮንበት ልዩ ጨዋታ ነው

- ለቡድን ገንዘብ መላክ፦ ከአንድ በላይ ለሆኑ ተቀባዮች አስቀድመው በሚሞሉት መስፈርት መሰረት በአንዴ መላክ የሚያስችል አገልግሎት ነው።

- የተለያዩ መተግበሪያዎችን በአንድ ቦታ፦ የተለያዩ የአገልግሎት መተግበሪያዎችን መጫን ሳያስፈልግ በአንድ ቦታ ማግኘት የሚያስችል ነው። (ለምሳሌ:- የትራንስፖርት፣ እቁብ፣ ዴሊቨሪ፣ ኢ-ኮሜርስ፣ የትምህርት ወ.ዘ.ተ)

- የተለያዩ ዝግጅቶች/የበረራ ትኬቶችን መግዛት

መተግበሪያው የፋይናንስ እና መሰል አገልግሎቶችን በቀላሉ ለማግኘት፣ ለቢዝነስ ተቋማት ደግሞ ተጨማሪ የስራ እድልን ይፈጥራል፣ ተቋማት ከደንበኞቻቸው ጋር በቀላሉ እንዲገናኙ ያስችላል ተብሏል።

" ቴሌብር ሱፕርአፕ " መተግበሪያ በሁለተኛው ምዕራፍ የተለያዩ አዳዲስ አገልግሌቶችን ይዞ እንደሚመጣ ተጠቁሟል። " ቴሌብር ሱፐርአፕ "ን ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይስቶር በማዘመን/በማውረድ መጠቀም ይችላሉ።

ቴሌብር ሁለት አመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ 30 ሚሊዮን ደንበኞችን ማፍራቱን ገልጿል።

ባለፉት 22 ወራት ብቻ ከ101 ሺ በላይ ወኪሎች፣ ከ28 ሺህ ነጋዴዎች እንዲሁም ከ19 ባንኮች ጋር ትስስርን የፈጠረ ሲሆን ከ44 አገራት ከ1.95 ሚሊዮን ገቢ አድርጓል፡፡

በተጨማሪም በቅርቡ ባስጀመረው የዲጂታል ፋይናንስ የብድርና የቁጠባ አገልግሎቱ በቴሌብር መላ የብድር አገልግሎት ለ1.4 ሚሊዮን ተጠቃሚዎቹ 2.1 ቢሊዮን ብር ያበደረ ሲሆን 400 ሺ የቴሌብር ሳንዱቅ የቁጠባ አገልግሎት ተጠቃሚዎቹ 1.7 ቢሊዮን ብር እንዲቆጥቡ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል፡፡

@tikvahethiopia