TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት #ተሰረዘ። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ምክር ቤቱ ዛሬ ባሄደው ልዩ ስብሰባ ህወሓትን ከሽብርተኛ መዝገብ ለማንሳት በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔውን አፅድቋል። #ኤፍቢሲ @tikvahethiopia
#Tigray

" በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ስራ እየገባ ነው " - ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል

ዛሬ የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በትግራይ ክልል ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫቸው በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ስራ እየገባ መሆኑን አሳውቀዋል።

ዶ/ር ደብረፅዮን ፤ የፌዴራል መንግስት ህወሓትን ከሽብርተኝነት ፍረጃ መሰረዙ በህወሓት ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ፕሬዜዳንትነት የሚመራ ጊዜያዊ አስተዳደር ወደ ትግበራ ለመግባት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ስለመግለፃቸው ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዶ/ር ደብረፅዮን ህወሓት ከሽብርተኝነት መዝገብ ስለመሰረዙ ምን አሉ ?

" በዛሬው ዕለት ህወሓት ከሽብር መዝገብ ተሰርዟል። ስለሆነም ጊዜያዊ አስተዳደራችን ስራው የሚጀምርበት ሁኔታ ተሟልቷል።

#በጀት የማዘጋጀትም ይሁን ሌሎች #ከእስረኞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የወንጀል ክሶችን በማንሳት እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ በሁለቱም ወገን በኩል ግኝኑነት ተጀምሯል።

በመሆኑም በበኩላችን በጓድ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደራችን ስራዎቹ እንዲሳኩ ለማድረግ ሁሉንም አቅማችንን በማቀናጀት ከፍተኛ ርብርብ እናደርጋለን።

የትግራይ ህዝብም በሁሉም አቅሙ የጊዜያዊ አስተዳደራችን ደግፎ እንዲሰማራ ጥሪ እናቀርባለን። "

ዶ/ር ደብረፅዮን ስለ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ምን አሉ ?

" የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማፋጠን አሸባሪነት የሚለው ሳይነሳ ቀድመን ነው እየሰራን የመጣነው። ጊዜያዊ መንግስቱን ለማቋቋም በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መምጣታቸውን ሁሉም ሲከታተለው የነበረ ጉዳይ ነው።

ኮሚቴ ከማቋቋም ጀምሮ ሁሉም ጊዜያዊ አስተዳደሩን በተመለከተ አጀንዳው አድርጎ እንዲሰራ በውስጥም በውጭም መድረኮችን በማዘጋጀት ተሰርቷል።

ኮንፈረንስ በማዘጋጀት እና ከኮንፈረስን በኃላ ምርጫዎችን በማካሄድ ሊያካትታቸው የሚገባ ፈፃሚ አካላት እንዲመረጡ ተደርጓል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ #ህወሓት እና #ባይቶና ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የትግራይ ሰራዊት ፣ የትግራይ ምሁራን ተሳታፊ ሆነዋል። በጊዜያዊ አስተዳደሩ የሚሳተፉ አካላት ተሟልተን ለማዕከላዊ መንግስቱ አሳውቀናል። "

ዶ/ር ደብረፅዮን #ህወሓትን በተመለከተ ምን አሉ ?

" ድርጅታችን ህወሓት የትግራይ ግዛታዊ አንድነትን ለማረጋገጥ ሰላም የሰፈነባትና ብሔራዊ ክብሯ የተጠበቀች ትግራይን ለመገንባት ሁሉንም አቅሙን በማቀናጀት የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚታገልበት ማረጋገጥ እፈልጋለሁ። ዘላለማዊ ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት!! "

@tikvahethiopia
👎1.96K👍1.57K181🕊92🤔25🙏23😢22😱14🥰13
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኡጋንዳ ፓርላማ በአገሪቱ ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ #ወንጀል እንዲሆን የሚያደርገውን ረቂቅ ሕግ አጸደቀ። ሕጉ ምን ይዟል ? - ማንኛውንም ራሱን በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪነት የመደበ፣ ወይም የጾታ ለውጥ ያስደረገ እንዲሁም በእንግሊዝኛ ምሕጻራቸው ኤል-ጂ-ቢ-ቲ-ኪው ዝርዝር ውስጥ የሚካተት የጾታ ዝንባሌ ያለው ዜጋን ሁሉ ወንጀለኛ ያደርጋል። - በጸደቀው…
#ኡጋንዳ

ምዕራባውያኑ በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ጉዳይ የኡጋንዳ ፓርላማ ያሳለፈውን ውሳኔ #እየተቃወሙ ናቸው።

የኡጋንዳ ፓርላማ ትላንት ከተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ጋር በተገናኘ አዲስ ህግ አውጥቷል።

ይኸው ህግ በኡጋንዳ ምንድር ማንም ሰው የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ነኝ በሚል ማንነቱን ቢገልፅ ህይወቱን ሙሉ / ለበርካታ አመታ እስር ቤት ውስጥ እንዲያሳልፍ የሚያደርግ ነው።

በአንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ #ሞትም ያስፈርዳል።

ይህ ህግ ትላንት ማክሰኞ በፓርላማ በከፍተኛ ድምፅ ነው የፀደቀው።

ይህንን ተከትሎ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ምዕራባውያኑ ውሳኔውን መቃወም ጀምረዋል።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ህጉን " #አፋኝ " ሲል ነው የተቃወመው። ተቋሙ ህጉን " አደንጋጭ ህግ " ሲልም ገልጾ " መድሎ እና ጥላቻን ያበረታታል ስለሆነም ሀገሪቱ እንደገና ህጉን ትፈትሽ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር #አንቶኒ_ብሊንከን እንዲሁም የዩናይትድ ኪንግደም የአፍሪካ ሚኒስትር #አንድሪው_ሚቼል አዲሱን ህግ ስለማውገዛቸው ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

አዲሱ ህግ የኡጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በፈረሙ ቅፅበት ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ከቀናት በፊት ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ተናግረው ነበር።

ፕሬዝዳንቱ በአገሪቱ ፓርላማ ቀርበው ንግግር ሲያደርጉ " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ብለዋል።

" ምዕራባውያን የራሳቸውን አሠራር በሌሎች ላይ ለመጫን የሚያባክኑትን ጊዜ ማቆም አለባቸው "  ሲሉም ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ አሳስበው ነበር።

@tikvahethiopia
👍5.96K430🙏121👎111🕊59🥰40😱25🤔14😢11
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ: የመጀመሪያው ምሽት ተራዊህ ሶላት በሳዑዲ አረቢያ - #RAMADAN #ታላቁ_የረመዷን_ወር

Photo Credit : Haramain

@tikvahethiopia
3.55K👍774👎216🥰151🕊120🤔27😱24😢13🙏2
TIKVAH-ETHIOPIA
#ረመዷን የረመዷን ወር መግቢያ ጨረቃ ዛሬ ባለመታየቷ ምክንያት ታላቁ የረመዷን ጾም ሀሙስ መጋቢት 14 ይጀምራል። እንኳን ለታላቁ የረመዷን ጾም በሰላም አድረሳችሁ። ረመዷን የፍቅር፣ የአንድነት፣ የሰላም፣ የመተሳሰብ እና የአብሮነት ወር እንዲሆንልን ከልብ እንመኛለን። #TikvahFamily @tikvahethiopia
#ረመዷን

የታላቁ የረመዷን ወር ጾም ዛሬ መጋቢት 14 አንድ ብሎ ጀምሯል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የ1444/2015 ዓ.ል የረመዷን ፆም ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ የአንድነት ፣ የራህመት ፣ የመተዛዘና የበረከት እንዲሆን ልባዊ ምኞታቸውን ገለፀዋል።

@tikvahethiopia
👍897190👎114🕊25🙏22🥰8😱1
#ረመዷን

በመላው ዓለም ላይ የሚታወቁት የዝምባብዌ ዜግነት ያላቸው የእስልምና መሁር ሙፍቲ  ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ስለ ቅዱሱ የረመዷን ወር እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ፦

ሙፍቲ  ኢስማኤል ሜንክ (ዶ/ር) ፦

" ረመዷን ምንድን ነው ? ሰዎች እየፆምን ነው ይላሉ ይህ ግን የረመዷን አንዱ ክፍል ብቻ ነው።

ረመዷን ፦
🤲 #የሰላም ወር ነው፤
🤲 #የመረጋጋት ወር ነው፤
🤲 #የመፈወሻ ወር ነው፤
🤲 #የቸርነት ወር ነው፤
🤲 #የምህረት ወር ነው፤
🤲 #የይቅርታ ወር ነው፤
🤲 #ጀነትን የምናገኝበት ወር ነው፤
🤲 ይህ ወር #ሙስሊም መሆናችንን የምናከብረበት ነው ፤ ሙስሊም በመሆናችን #ራስን_መግዛትን የምንለማመድበት የፈለግነውን ብቻ ሳይሆን ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ የወሰነውን የምናደርግበት ወር ነው ፤  ሱብሃንአላህ ! ስለዚህ ለአላህ ቃል ጥረት ማድረግ ግዴታችን ነው። "

መልካም #የረመዷን_ጾም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲሆን እንመኛለን።

#TikvahFamily

@tikvahethiopia
👍24.5K639👎131🥰65🙏64🕊62🤔14😱4
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት #ተሰረዘ። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ምክር ቤቱ ዛሬ ባሄደው ልዩ ስብሰባ ህወሓትን ከሽብርተኛ መዝገብ ለማንሳት በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔውን አፅድቋል። #ኤፍቢሲ @tikvahethiopia
" ውሳኔውን እንቃወማለን " - አብን

አብን የ " ህወሓት "ን ከሽብር መዝገብ መሰረዝ እንደሚቃወም ገለፀ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) ትላንት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሓትን ከአሸባሪ ድርጅትነት መዝገብ መሰረዙን እንደሚቃወም ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ፓርቲው በመግለጫው ፤ ዘላቂ ሰላም ያመጣል ተብሎ የተፈረመው የፕሪቶሪያው ሥምምነት አንኳር ጉዳዮች አልተተገበሩም ከዚህም በላይ የጦርነት ቀጠና ሆነው የቆዩትን አካባቢዎች ለ4ኛ ዙር የጦርነት አደጋ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች እየተከሰቱ ነው ብሏል።

አብን ፤ " በፕሪቶሪያው ሥምምነት አንቀጽ 6(F) መሰረት ትሕነግ (የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጪ ግንባር) በ30 ቀናት ውስጥ የቀላል መሳሪያ ትጥቅ ጨመሮ ጠቅላላ ትጥቅ እንዲፈታ እና በሥምምነቱ አንቀጽ 3(5) መሰረት ደግሞ የሀገር የመከላከያ ሠራዊት ወደ ትግራይ ገብቶ ጸጥታ የማስከበሩን ሥራ በተሟላ ሁኔታ እንደሚረከብ ሥምምነት የተደረሰ ቢሆንም ቡድኑም ትጥቅ ሳይፈታ የሀገር መከላከያ ሠራዊትም ወደ ትግራይ ገብቶ ጸጥታ የማስከበር ሥራውን ሳይረከብ ቡድኑ የገንዘብ እና የማቴሪያል ድጋፍ ሲደረግለት ቆይቷል " ብሏል።

አክሎም ፤ " ከጠቅላለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ብዛት ያላቸው የምክር ቤት አባላት ባልተገኙበት እና ከተገኙትም ውስጥ ከ60 በላይ ተወካዮች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ባሉበት ሁኔታ ቡድኑ ከሽብርተኝነት መዝገብ እንዲፋቅ ተደርጓል " ሲል አስረድቷል።

በአጀንዳው ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ በተጠራው ስብሰባ ላይ ብዛት ያላቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት አልተገኙም ያለው ፓርቲው ከተገኙትም ውስጥም ከ60 በላይ የሆኑት አባላት የውሳኔ ሃሳቡን በመቃወም እና ድምጸ ተዐቅቦ በማድረግ ድጋፋቸውን ነፍገዋል ይህ የሚያሳየው የሚበዙት የምክር ቤቱ አባላት የቡድኑን ከሽብርተኝት መዝገብ መፋቅ የማይደግፉ መሆኑን ነው ፤ ውሳኔው ሕጋዊ ነው ቢባል እንኳ ቅቡል (Legitimate) እንዳይሆን የሚያደርገው ነው ብሏል።

አብን ፦

- በጉዳዩ ላይ የጋራ መግባባት ባልተደረሰበት ፣

- የሚበዙት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የውሳኔው አካል ባልሆኑበት ፣

- ህወሓት ትጥቅ ባልፈታበት እና ይልቁንም ቡድኑ የፕቶሪያውን የሰላም የሥምምነት አንቀጽ 7(1)(D) በመጣስ በተለያዩ አካባቢዎች አዲስ የታጣቂዎች ምልመላ ፣ ስልጠና እና የጦርነት ዝግጅት እያደረገ ባለበት ሁኔታ ቡድኑን ከሽብርተኝነት መዝገብ መሰረዝ ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው ሲል ተቃውሟል።

ውሳኔው ተገማች በሆነ ጊዜ ውስጥ ለሌላ ዙር ግጭት እና ጦርነት የሚያጋልጥ በመሆኑ ፓርቲው ውሳኔውን በፅኑ እንደሚቃወም ገልጿል።

በመሰል አግባብነት በሌላቸው ውሳኔዎች በሕዝቡ እና በሀገር ላይ ለሚደርሰው በደል ሁሉ የፌዴራሉ መንግስት ሙሉ ኃላፊነቱን ይወስዳል ሲል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ አስገንዝቧል።

(አብን ያወጣው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
👍1.82K👎60874🤔28😢14🙏14🕊13🥰3😱1
#ድሬ

በድሬዳዋ ከተማ ትላንት በደረሰ የእሳት አደጋ የዋጋ ግምቱ 46 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ።

" ለጊዜው  ምክንያቱ ባልታወቀ  ሁኔታ  በተነሳ የእሳት ቃጠሎ የዋጋ ግምቱ አርባ ስድስት (46) ሚሊዬን ብር የሚገመት ንብረት ውድሟል " ሲል የድሬድዋ ፖሊስ አሳውቋል።

ፖሊስ እንደገለፀው አደጋው የደረሰው ትላንት መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ንብረትነቱ " የሮያል ፎም ፍራሽ እና ፕላስቲክ ፋብሪካ " ላይ ነው፡፡

ከቀኑ 5 ሰአት ገደማ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ የፋብሪካው ንብረት የሆኑ ፦

👉 አንድ ትልቅ የምርት ማከማቻ መጋዘን፤
👉 አንድ  ቦንድድ ማሽን፤
👉 በርካታ የተጠናቀቁ የስፖንጅ ፍራሽ ምርቶች እንዲሁም ሁለት ሆዝ የእሳት ማጥፊያ በአጠቃላይ የዋጋ ግምቱ አርባ ስድስት (46) ሚሊዬን ብር ንብረት ወድሟል።

አደጋው እንደደረሰ የድሬዳዋ ፖሊስ የእሳት እና ድንገተኛ ዲቪዥን እና የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የእሳት አደጋ ተከላካይ ቡድን በቦታው ላይ በመድረስ እሳቱ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይዛመት ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። አደጋውን ለመከላከል አርባ ስምንት ሺ ሊትር ውሃ እና አንድ መቶ ሊትር ፎም መጠቀማቸው ተገልጿል።

በደረሰው የእሳት አደጋ ከንብረት ጉዳት ውጪ በሰው ላይ ምንም አይነት አደጋ ያልደረሰ መሆኑን የገለፀው የድሬዳዋ ፖሊስ በአሁኑ ወቅት የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ምንጭ፡ #ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia
😢370👍30047😱34👎17🕊10🤔6🙏5🥰2