TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#DigitalLottery

አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ጥር 25 ቀን 2015 በብሄራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በህዝብ ፊት ወጥቷል።

1.5 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 007235088931 ሆኖ ወጥቷል።

👉 1.5 ሚሊዮን ብር - 007235088931
👉 800 ሺህ ብር - 007311229183
👉 350 ሺህ ብር - 007308618207
👉 200 ሺህ ብር - 007209120515
👉 160 ሺህ ብር - 007304282769
👉 120 ሺህ ብር - 007293769171

(ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮች ከላይ ተያይዘዋል)

ምንጭ፦ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር

@tikvahethiopia
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጾመ ነነዌን በማስመልከት ጾምና ጸሎት አወጀ።

ቅዱስ ሲኖዶስ አዋጁን ያስተላለፈው ዛሬ ከደቂቃዎች በፊት በሰጠው መግለጫ ነው።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ በቤተክርስቲያኗ በተከሰተው ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮች በጣሰ ሁኔታ መፈንቅለ ሲኖዶስ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶስነት ሢመት በሰጡትና በተሾመ ግለሰቦች ላይ ጥር 18 ቃለ ውግዘት ታላልፎ እንደነበር ገልጿል።

" ይሁን እንጂ እነዚህ ሕገወጥ ቡድኖች ከድርጊታቸው ሊታቀቡ አልቻሉም " ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ ከዚህም በላይ በመንግሥት ኃይሎች በመታገዝ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተዳድራቸውን መንበረ ጵጵስናዎችንና ቢሮዎችን በኃይል በመውረርና በመስበር ከፍተኛ ጥፋት እያደረጉ ነው ብሏል።

እንዲሁም የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ፣ ሠራተኞች ካህናትና ምእመናን በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛሉ ሲል ገልጿል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ መንግሥት ሕግ ከማስከበር ይልቅ ለሕገ ወጥ ቡድኖች ድጋፍ በመስጠት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግና መብት ሊያስከብር አልቻለም ያለ ሲሆን " ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው አምላካችን በመማፀን ጸሎትና ምሕላ ማድረጉ አስፈላጊ መሆኑን ተረድተናል " ሲል አሳውቋል።

በዚህም " ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን #ጥቁር_ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንድታቀርቡ " ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አስተላልፏል።

" ጥቁር ልብስ  የምንለብሰው በመከራ መጽናት ለመግለጽ ነው " ሲልም አክሏል።

(ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ማስታወሻ

የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ዛሬ አርብ ጥር 26/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ያበቃል።

@tikvahethiopia
#SomaliRegion

የሶማሊ ክልል ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ፤ የሶማሊኛ ቋንቋን ያሳድጋል ፤ ይጠብቃል የተባለውን በሶማሊኛ የተዘጋጁ የወራት ስያሜዎች ስራ ላይ እንዲውሉ ወስኗል።

የክልሉና ሌሎች ባለሞያዎች በሶማለኛ የወር ስያሜዎች ላይ ያካሄዷቸው ጥናቶች ላይ ትላንት ውይይት ተካሂዶ ነበር።

በውይይቱ ላይ ባለሞያዎቹ በሶማሊኛ ቋንቋ በቀን ፤ በወርና በአመት ላይ የተከናወነውን ጥናት የሚያሳይ ጥናታዊ ጽሑፍ አቅርበዋል።

የክልሉ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ፤ በሶማሊኛ ቋንቋ የተዘጋጀው የወራት ስያሜዎችን እንዳደነቀና ይህም የሶማለኛ ቋንቋን ለማሳደግና ለመጠበቅ ጠቀሜታ እንዳለው መግለፁ ተመላክቷል።

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ከታች የተዘረዘሩትን የሶማሊኛ ቋንቋ የወር ስያሜዎች ከትላንት ጀምሮ የክልሉ መንግስት ስራ ላይ እንዲውል ውሳኔ አሳልፏል።

1. ኮድሂን / መስከረም / September
2. ዲሪር / ጥቀምት / October
3. ጉድባ / ህዳር / November
4. ሆሬይ / ታህሳስ / December
5. ደርበለይ / ጥር / January
6. አሪር / የካቲት / February
7. ኡር / መጋቢት / March
8. ዱጋቶ / ሚያዚያ / April
9. ሚአድ / ግንቦት / May
10. አጋሊ / ሰኔ / June
11. አፍጋል / ሀምሌ / July
12. ነፍ / ነሀሴ / August

#SRTVAmharic

@tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ጦርነት ምክንያት ክፉኛ ከተጎዱት መካከል #ተማሪዎች ዋነኛዎቹ እንደሆኑ ይታወቃል።

በጦርነት ምክንያት በክልሉ ያሉት ተማሪዎች ለበርካታ ወራት ከትምህርት ርቀው ይገኛሉ።

የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኃላም ተማሪዎችን በፍጥነት ወደ ቀደመው የትምህርት ህይወታቸው እንዲመለሱ የማድረጉ እንቅስቃሴ እጅግ በጣም ዘግይቷል።

ከሰሞኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ መደበኛ ትምህርት እስኪጀመር #በሬድዮ እና #ቴሌቪዥን ትምህርት እንዲጀመር ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ስለማሳወቁ ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ቅድሚያ ትንንሽ ህፃናት ላይ ትኩረት እንዳደረገ የገለፀው ቢሮው ይህም በአቅም ውስንነት እና በጀት ስለሌለው መሆኑን አመልክቷል። በሚዲያ ትምህርቱን ከመዋለህፃናት እስከ 4ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልጿል።

የሬድዮ ትምህርት በድምፂ ወያነ፣ የቴሌቪዥን ትምህርት በትግራይ ቴሌቪዥን ይተላለፋል ተብሏል።

ትምህርቱ ፤ የትግራይ ህፃናት በጦርነት ከደረሰባቸው ጫና እንዲወጡ ለማድረግና ለመደበኛው ትምህርት እንዲዘጋጁ የሚያደርግ እንጂ ከክፍል ወደ ክፍል የሚያሻግራቸው እንዳልሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ በሬድዮ እና ቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ትምህርት በተመለከተ በሰጠው ማብራሪያ ፤ ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል በሬድዮ የሚሰጠው ትምህርት ትግርኛ ፣ እንግሊዘኛ እና አካባቢ ሳይንስ ሲሆን በቴሌቪዥን ሒሳብን እንደሚያካትት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የሀገራችን እና የመላው አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በቅርቡ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ታስተናግዳለች።

በቅርቡ የሚካሄደው 36ኛው የመሪዎች ጉባኤ እና 42ኛው የህብረቱ የስራ አስፈፃሚዎች ጉባኤ ሲሆን በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑ ተሰምቷል።

የዘንድሮው የህብረቱ ስብሰባ የንግድ ግንኙነት እና ኢኮሮሚያዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል።

ይኸው ጉባኤ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሰላም መቋጫ እንዲያገኝ ከተደረገ በኃላ በአዲስ አበባ የሚካሄድ መሆኑን ተከትሎ በቱሪዝሙ ዘርፍ እየታየ የመጣውን ከፍተኛ መነቃቃት ያሳድገዋል ተብሎ ይታመናል።

በአዲስ አበባ የሚገኙ ሆቴሎች ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ እንግዶችን በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና በመልካም መስተንግዶ ለመቀበል ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን እያሳውቁ ይገኛሉ።

Photo Credit ፦ Abel Gashaw

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ የፌዴራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መገናኘታቸው ተሰማ።

የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በ " ሐላላ ኬላ " እንደሆነ ተነግሯል።

NB. ሐላል ኬላ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል ነው።

ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ #ለመጀመሪያ ጊዜ ከሰላም ስምምነት ትግበራ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ምክክር አድርገዋል ተብሏል።

በውይይታቸው እስካሁን በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራት መገምገሙና በቀጣይ ትኩረት በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ መቀመጡን ብሔራዊው የቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia