TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሶማሊያ #ኢትዮጵያ #ኤርትራ

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ መሐሙድ " የሶማልያ እና የኢትዮጵያን የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ስልታዊ አጋርነት ለማጠናከር ቁርጠኛ ነኝ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ፕሬዝደንቱ ይህን የገለጹት ዛሬ በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙክታር ሞሐመድ ዋሬ የሹመት ደብዳቤ በተቀበሉበት ወቅት እንደሆነ የሶማሊያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

ፕሬዝደንት ሐሰን ሼይክ መሐሙድ ዛሬ የአምባሳደሩን የሹመት ደብዳቤ የተቀበሉት ለሥራ ጉብኝት ከተጓዙበት አስመራ ወደ ሞቃዲሾ ከተመለሱ በኃላ ነው።

ፕሬዝደንቱ በአስመራ ከኤርትራው አቻቸው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተገናኝተው መወያየታቸው ታውቋል።

ውይይቱ " የጋራ ጠቀሜታ ባላቸው የቀጠናዊ ጉዳዮች " ላይ እንደነበረ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ወደ ስልጣን ከመጡ በኃላ ለስራ ጉብኝት ወደ ኤርትራ በተደጋጋሚ ጊዜ መጓዛቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ " ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ አቤቱታ ቀረበ። የኬንያ ፓርላማ " #ቲክቶክ " የተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ እንዲያግድ አቤቱታ እንደቀረበለት የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። " ወጣቶች ትምህርታቸውን ትተው የ 'ቲክቶክ' ቁራኛና የአዕምሮ ህመምተኛ እየሆኑ ነው " የሚለው አቤቱታው ፓርላማው አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል። የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዋታንጉላ፣ " ሁከትን እና የጥላቻ ንግግርን…
#ሶማሊያ

ሶማሊያ ቲክቶክ እና ቴሌግራም እንዲሁም 1ኤክስቤት (1XBet) የተባለውን የስፖርት ውርርድ ገጽን እንዲዘጉ አዘዘች።

" ቲክቶክ " እና " ቴሌግራም " የአሸባሪዎች መረጃ ማስተላለፊያ ሆነዋል ብሏል የሶማሊያ መንግሥት።

መተግበሪያዎቹ " አሸባሪ ድርጅቶች እና ቡድኖች አሰቃቂ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እንዲሁም ፎቶግራፎችን በማሰራጨት ሕብረተሰቡን ለማሳሳት ጥቅም ላይ ውለዋል " ሲል ገልጿል።

የሀገሪቱ መንግሥት የኢንተርኔት አግልግሎት አቅራቢዎች እስከ ሐሙስ ነሐሴ 18/2015 ዓ.ም. ድረስ  " እንዲዘጉ " የሚለውን ትዕዛዝ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ፤ የማያደርጉ ከሆነ ግን ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቋል።

ይህ ውሳኔ የተሰማው የሶማሊያ መንግሥት አልሸባብን ለማጥፋት ዘመቻ ከጀመረ በኃላ ነው።

በቅርቡ በሞቃዲሹ ኢንተርኔት እና ማኅበራዊ ሚዲያን በተመለከተ በተካሄደ ኮንፈረንስ ላይ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እና ኢንተርኔት በአጠቃላይ በተለይ በወጣቱ ላይ " ሕይወት እስከ ማሳጣት " የሚደርስ ጉዳት እያደረሰ ነው የሚል ሃሳብ በስፋት ተንጸባርቆ ነበር ተብሏል።

በኬንያም እንዲሁ በተለይም በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ ተጠቃሚ ያለውን " ቲክቶክ "ን ለማገድ የሚያስችል ሃሳብ ለምክር ቤት ከሰሞኑም መቅረቡ ይታወሳል።

ቲክቶክ እንዲታገድ የተጠየቀው ፤ ኬንያ ቲክቶክን ለመቆጣጠር የሚያስችል ጠንካራ ሕግ ስለሌላት ጉዳት የሚያስከትሉ እና ተገቢ ያልሆኑ ይዘቶች በመድረኩ ላይ በስፋት እንዲቀርቡ ምክንያት ሆኗል በሚል ነው።

የምክር ቤቱ አፈጉባኤ ሞሰስ ዊታንጉላ ፤ " ቲክቶክ በኬንያውያን በወጣቶች ዘንድ ተዘውታሪ በመሆኑ ፦
- ግጭቶችን በማባባስ፣
- ልቅ ወሲብን በማስፋፋት፣
- የጥላቻ ንግግሮችን በማስፋፋት፣
- የብልግና ቃላትን በማስፋፋት፣
- አደገኛ ባሕሪያትን በማስፋፋት ለአገሪቱ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ጠንቅ እየሆነ ነው " ብለዋል።

ቲክቶክ እንዲታገድ ጥያቄ ያቀረቡት ግለሰብ ምክር ቤቱ ቲክቶክን የሚያግደው ከሆነ፣ በወጣቶች ዘንድ እየተስፋፋ ያለውን ሱሰኝነት እና የአእምሮ ጤና ችግርን ለመከላከል ይቻላል ብለዋል።

የቲክቶክ መተግበሪያ በሕገወጥ መንገድ የኬንያውያንን ግላዊ መረጃ በመሰብሰብ እና በማጋራት ተጠያቂ ነውም ብለዋል።

የቀረበውን ሃሳብ አንዳንድ የምክር ቤት አባላት የደገፉት ሲሆን ሌሎች ደግሞ እገዳው ኬንያውያንን ከቴክኖሎጂ የሚያርቅ እና በቲክቶክ ላይ ይዘቶችን በማቅረብ ገቢ የሚያገኙ ወጣቶችን የሚጎዳ ነው በማለት ተቃውመውታል።

ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸውን የምክር ቤቱ አባላትን ጨምሮ አንዳንድ እንደራሴዎች ደግሞ ተክቶክን ሙሉ ለሙሉ ከማገድ ይልቅ በይዘቶቹ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ ደንብ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

#BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አውሮፓ ህብረት ምን አለ ? የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ እና በራዝ ገዟ ሶማሊላንድ መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት በተመለከተ አጭር መግለጫን ትላንት ምሽት አውጥቶ ነበር። በዚህ መግለጫው፤ እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የኢትዮጵያ  የባህር በር አገልግሎት (በሊዝ) ማግኘት የሚያችላትን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል…
#ኢጋድ #ሶማሊያ

ዛሬ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዲላፕሎማሲው መስክ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት መካከል እያታየ ያለው ሁኔታ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ኢጋድ ሁኔታውን በንቃት እየተከታተለ መሆኑን እና በቀጠናው መረጋጋት ላይ ያለውን ተፅእኖ እንደሚገነዘብ አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሁኔታዎችን በሰላማዊ እና በመግባባት መንፈስ ለመፍታት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ዶክተር ወርቅነህ በመግለጫቸው በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ መካከል ስለተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ያነሱት ነገር የለም።

የሶማሊያ መንግሥት የዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ መግለጫ እንዳበሳጨው ለመረዳት ተችሏል።

የሶማሊያ መንግሥት " የመግለጫው ሃሳብ ለኢትዮጵያ ያደላ ነው " በማለት ዶ/ር ወርቅነህ በአስቸኳይ ይቅርታ እንዲጠይቁ፣ የይቅርታ መግለጫም በማውጣት አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስዱ ብሏል።

ሶማሊያ ፤ የኔ አንድ ግዛት ናት በምትላት ሶማሊላንድ እና ኢትዮጵያ መካከል የተረፈመው ስምምነት ያበሳጫት ሲሆን ስምምነቱ የግዛት አንድነቴን እና ሉዓላዊነትን የጣሰ ነው በማለት እየተቃወመች ትገኛለች።

(የሁለቱም መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ቱርክ #ሶማሊያ

ሶማሊያ እና ቱርክ የካቲት 1/2016 በተለያዩ ወታደራዊ ዘርፎች ትብብር ለማድረግ ስምምነት መፈራረማቸውን ይታወሳል።

ይህንን ስምምነት ተከትሎ የቱርክ ባሕር ኃይል የጦር መርከብ ሞቃዲሾ ወደብ መድረሷን ቢቢሲ ዘግቧል።

የሁለቱ ሀገራት ስምምነት ዝርዝር ይፋ ባይሆንም ቱርክ የሶማሊያን ባሕር ኃይልን #ለማሠልጣን እና #ለማስታጠቅ እንዲሁም በአካባቢው ያለውን የባሕር ላይ ደኅንነት ለማስጠበቅ ተስማምታለች ተብሏል።

በአንጻሩ ቱርክ ከሶማሊያ የባሕር የተፈጥሮ ሃብት ተጠቃሚ እንደምትሆን ሪፖርቶች ይጠቁማሉ።

@tikvahethiopia