TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ከ / ወደ ትግራይ  የየብስ ትራንስፖርት መቼ ይጀምራል ? ከትግራይ ክልል ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች #በቅርቡ የየብስ ትራንስፖርት እንደሚጀምር ከሰሞኑን ተገልጿል። ከአየር ትራንስፖርት በተጨማሪ የየብስ ትራንስፖርት በቅርብ ቀን ለማስጀመር ከፌዴራል መንግስት ጋር በመነጋገር ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን የክልል የኮንድትራክሽንና መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል። ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በህጋዊ…
#Update

ከ/ወደ ትግራይ የየብስ ትራንስፖርት ለመጀመር የአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት ማመላለሻ ማህበራት ዝግጁ እንዲሆኑ መመሪያ መተላለፉ ተሰምቷል።

ሪፖርተር ጋዜጣ ከአገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ማኅበራት ያገኘሁት ባለው መረጀ ፤ የትራንስፖርት ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ወደ ትግራይ የተለያዩ ከተሞች የሕዝብ ማመላለሻ የትራንስፖርት አገልግሎትን ዳግም ለመጀመር ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ መመርያ ተላልፎላቸዋል፡፡

በዚሁ የሚኒስቴሩ መመርያ መሠረት ማኅበራቱ ለአባሎቻቸው አገልግሎቱን መልሶ ለማስቀጠል ዝግጁ እንዲሆኑ ያሳወቁ ሲሆን አሁን እየጠበቁ ያሉትም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን የመጨረሻ ውሳኔ እንደሆነ ለማወቅ መቻሉን #ሪፖርተር_ጋዜጣ ዘግቧል።

ከጥቂት ቀናት በፊት የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽንና መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ  ከትግራይ ክልል ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች #በቅርቡ የየብስ ትራንስፖርት እንደሚጀምር ማሳወቁ አይዘነጋም።

ቢሮው ከአየር ትራንስፖርት በተጨማሪ የየብስ ትራንስፖርት በቅርብ ቀን ለማስጀመር ከፌዴራል መንግስት ጋር በመነጋገር ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#EOTC

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፤ የ " ቤተክርስቲያን ችግሮች እና ዘለቄታዊ መፍትሔ ጥናትና ትግበራ ኮሚቴ " በሚል ስያሜ እንደተቋቋመ የገለፀችውና ከሁሉም የሞያ ዘርፎች የተውጣጡ የቤተክርስቲያኗን ልጆች ያቀፈው ቡድን ወደ ትግበራ ሊገባ መሆኑን አስታወቀች።

ኮሚቴው የጥናታዊ ጽሑፍ በማቅረብ አላማውን እና የአሰራር ሂደቱን ያብራራ ሲሆን ሰፊ ውይይት አካሂዷል ተባቧል።

በቅድስት ቤተክርስቲያኗ መዋቅር ውስጥ #ከዶግማ_በስተቀር ከላይ ጀምሮ እስከ ታች ድረስ ያሉ ችግሮችን ለማስተካከል እንደሠራም ተገልጿል።

ውጤቱን በተመለከተ ቤተክርስቲያን የራሷ #መንፈሳዊ_ፍርድ_ቤት እንዲኖራት ማድረግን ጨምሮ 25 ዝርዝር ነጥቦች ላይ ማተኮሩ ተመላክቷል።

#ከ90_በላይ አባላትን በጥናት ያሳተፈው ኮሚቴ በ14 ቡድኖች ተዋቅሮ ስራውን #በቅርቡ እንደሚጀምር ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።

#EOTC_TV

@tikvahethiopia
#Tigray

ትግራይ ውስጥ ተቀስቅሶ ወደሌሎች ክልሎች በተስፋፋው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት " በሺዎች የሚቆጠሩ " የትግራይ ተዋጊዎች መሞታቸው፣ ሌሎች በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውና ዘላቂ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸዉ የክልሉ ባለስልጣናት ማስታወቃቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዳስታወቀዉ በጦርነቱ ለሞቱ የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች አባላት፣ ቤተሰቦቻቸው #በቅርቡ በይፋ መርዶ ይነገራቸዋል።

ዛሬ በመቐለ ከተማ የትግራይ የጦር ጉዳተኞች ማእከል ስራ ባስጀመሩበት ወቅት ንግግር ያደረጉ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ፥ ቁጥሩን በትክክል ባይጠቅሱም " በሺዎች የሚቆጠሩ " ያልዋቸው የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች አባላት በሁለት ዓመቱ ጦርነት መሞታቸውን አረጋግጠዋል።

የሟች ቤተሰቦችን ከማርዳት በተጨማሪ መስተዳድራቸዉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአማራ ክልል የሚገኙ የ10 ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዜዳንቶች በቅርቡ ከክልሉ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ አኳያ የመማር ማስተማር ሂደትን ማስቀጠል ይቻል እንደሆነ ውይይት እንዳደረጉ ቪኦኤ ዘግቧል። የክልሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዋና ፀሀፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል፤ የዩኒቨርሲቲዎቹ ፕሬዜዳንቶች ባደረጉት ውይይት ወቅታዊው የክልሉ የፀጥታ ችግር በቅርቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ…
#Amhara

በአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዋና ጸሐፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን፤ የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎችን አቋም በተመለከተ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የነበረው መረጃ " #የተሳሳተ ነው " አሉ።

ከሰሞኑን በአማራ ክልል ስላሉ ዩኒቨርሲቲዎች ምንድነው የተባለው ?

ከቀናት በፊት ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ የፎረሙን ዋና ጸሐፊ የሆኑትን ዶ/ር አስማረ ደጀንን ዋቢ በማድረግ ባወጣውና ቲክቫህ ኢትዮጵያም ባጋራው ዘገባ ፤ በአማራ ክልል የሚገኙ የ10 ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች ከክልሉ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ አኳያ የመማር ማስተማር ሂደትን ማስቀጠል ይቻል እንደሆነ ውይይት ካደረጉ በኃላ ሁኔታው #በቅርቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማስቀጠል የሚያስችል እንዳልሆነ የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

በተጨማሪ ዶ/ር አስማረ ደጀን ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል፤
*  ተማሪዎች ገብተው ግጭቶች በሚመጡበት ጊዜ ዩኒቨርሲቲዎች ኃላፊነት እንደማይወስዱ፤

* ዩኒቨርሲቲዎች ለ2016 የሚሆን የምግብ አቅርቦት ማዘጋጀት የነበረባቸው ቢሆንም አቅራቢዎቹ ከቦታ ቦታ ፤ ምርት ካለበት ቦታ ሄደው ተዘዋውረው መግዛት ስላልቻሉ የምግብ ግብአቶች በጠቅላላው ተማሪን ሊያስጠራ የሚችል እንዳልሆነ ገልፀዋል።

ፎረሙ ትምህርት ሚኒስቴር " ለ2016 ትምህርት በአሁን ሰዓት ተማሪዎችን ጥሩ እያለ ነው " ብሎ ለፀጥታው ኃላፊነት የሚወስድ አካል ከሌለ ይህን ማድረግ #እንደሚያስቸግር ነው የገለፀው።

ከዚህ ባለፈ የፎረሙ አባልና የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ፤ በአካባቢው የቀጠለው አለመረጋጋት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ እንደማያስችል ከተስማሙት የፎረሙ አባላት እንደሆኑ ገልጸዋል።

ያለው ሁኔታ ካልተሻሻለ በስተቀር አሁን ባለው ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ግቢ ውስጥ ተማሪ ማስገባት በእጅጉ ፈታኝ እንደሚሆንና ለልጆችም ደህንነት በጣም አስጊ መሆኑን ፕሬዜዳንቱ ለጣቢያው ተናግረዋል።

ይህ መረጃ ከተሰራጨ ከቀናት በኃላ የፎረሙ ዋና ጸሐፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዛሬ በሰጡት ቃል " ሰሞኑን የተሰራጨው መረጃ በአማራ ክልል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ያልተባለና ስህተት ነው " ብለዋል።

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ለመቀበል አመች ሁኔታዎችን እየተጠባበቁ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በክልሉ የሚገኙ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን መጥራት መጀመራቸውንም ገልጸው፣ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች ጥሪ ማስተላለፉን ለአብነት አንስተዋል፡፡

"አብዛኞቹ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን እየጠሩ ነው" ያሉ ሲሆን " ብዙ ተማሪዎችን በአንድ ጊዜ ለመጥራት ግን የግብዓት ችግር ለተቋማቱ እንቅፋት ሆኗል " ብለዋል።

ዶ/ር አስማረ፤ በክልሉ በተፈጠረው የሰላም እጦት ግብዓት አቅራቢዎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ለማቅረብ የተቸገሩ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲዎች የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየሠሩ መሆኑን አሳውቀዋል። በየአካባቢው ያሉ አቅራቢዎች ግብዓት እንዲያቀርቡ እየተደረገ ነው ብለዋል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎችን ተቀበሉ በሚልበት ጊዜ የማይቀበሉበት ምክንያት እንደሌለም ገልጸዋል።

" ክልሉ ያጋጠመው የጸጥታ ችግር እየተሻሻለ ከመጣ ተቋማቱ ተማሪዎቻቸውን ወዲያው ይጠራሉ፤ ተማሪዎችን አይጠሩም የተባለው ስህተት ነው፤ አልተባለምም " ሲሉ ተናግረዋል።

አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ግብዓት ለማግኘት ከመቸገራቸው ውጭ የመማሪያ ክፍሎችን አጽድተዋል፣እድሳት የሚያስፈልጋቸውንም አድሰው ለትምህርት ዘመኑ የመማር ማስተማር ዝግጁ ሆነዋል ሲሉ ለክልሉ ሚዲያ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ራስ ገዟ ሶማሊላንድ የሶማሊያ መንግሥትን አስጠነቀቀች። ከኢትዮጵያ ጋር የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ለማደናቀፍም ይሁን ለመቃረን የሚሞክር ማንኛውም ግለሰብ ይሁን አካል ላይ እርምጃ ወስዳለሁ ብላለች። የራስ ገዟ ሶማሌላንድ" የሚኒስትሮች ምክር ቤት " ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ ነበር። ከስብሰባው በኃላ ባወጣው ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ ፦ - ምክር ቤቱ እ.ኤ.አ. ጥር 1/2024…
#ሀርጌሳ

" ሀገራችንን አልሸጥንም " - ሙሴ ባሂ አብዲ

ባለፉት ቀናት ኢትዮጵያ የነበሩት የራስ ገዟ ሶማሌላንድ ፕሬዝዳንት ዛሬ ሐሙስ ዕለት ወደ ሀርጌሳ ተመልሰዋል።

ፕሬዚዳንቱ ሀርጌሳ ሲገቡ ህዝቡ ወደ አደባባይ ወጥቶ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

አደባባይ ወጥቶ ለተቀበላቸው ህዝብ ባሰሙት ንግግር ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር የተፈራረሙት የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑ ገልጸዋል።

ፕሬዜዳንቱ " ሀገራችንን አልሸጥንም " ያሉ ሲሆን " ኢትዮጵያ የባህር ሃይል ጦር ሰፈር #በሊዝ ነው የምትከራየው " ብለዋል።

" ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ እውቅና ለመስጠትም ተስማምታለች " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ መቼ እንደሆነ ቀኑን በግልፅ ባይናገሩም የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት #በቅርቡ ለሶማሌላንድ እውቅና እንደሚሰጥ በድጋሚ ለህዝባቸው ገልጸዋል።

" ይህ የሶማሌላንድ ህዝብ ላለፉት ሶስት አስርት አመታት የደረሰበት ትልቅ ስኬት ነው " ሲሉም ገልጸዋል።

ስምምነቱ በሁለቱም ወገን በኩል ፍላጎትና ጥቅማቸውን መሰረት ያደረገ ነው ሲሉ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል ፤ ሶማሌላንድን እንደ ራሷ አንድ ግዛት የምትቆጥራትና የተፈረመው ስምምነት ሉዓላዊነቴን ጥሷል በሚል የተቃወመችው ሶማሊያ ውስጥ ዛሬ የተቃውሞ የአደባባይ ሰልፎች ሲደረጉ መዋሉን ለማወቅ ተችሏል።

ፎቶ / ቪድዮ ፦ ሶማሌላንድ፣ ሀርጌሳ (ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 206 ዓ/ም)

@tikvahethiopia