“ሹፌሩን፣ ጋቢና የነበሩ 2 ሰዎችን ጭንቅላታቸውን በሰደፍ መቷቸው። በገመድ አስረው፣ አፋቸውን በፕላስተር አስይዘው መኪናውን ይዘው ሄዱ ” - የተሽከርካሪው ባለቤት
“ እንዲህ አይነት ወንጀሎች ከዕለት ዕለት እየጨመሩ ነው ” - የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር
#ከአዲስ_አበባ ተነስቶ ወደ #ወላይታ_ሶዶ 70 ኩንታል ዱቄት ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ በሻሸመኔ እና ሀዋሳ መካከል ከቶጋ ካምፕ አለፍ ብሎ ቢሻን ጉራቻ (ጥቁር ውሃ) መግቢያ ላይ በሚገኝ ቦታ ማክሰኞ መጋቢት 3 ቀን 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ገደማ ላይ በታጠቁ ኃይሎች እንደተወሰደና እንዳልተመለሰላቸው የተሽከርካሪው ባለቤት፣ ሌላ እማኝና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የተሽከርካሪው ባለቤት በሰጡት ቃል፣ “ ሹፌሩን፣ ጋቢና የነበሩ 2 ሰዎችን ጭንቅላታቸውን በሰደፍ መቷቸው። በገመድ አስረው፣ አፋቸውን በፕላስተር አስይዘው መኪናውን ይዘው ሄዱ ” ሲሉ ገልጸዋል።
እንዲህ ያደረጉ አካላት ማን እንደሆኑ ሲያስረዱ ፣ “ ደብል ጋቢና በሆነ መኪና (አሮጌ ነገር ነው) እርሱ ላይ ሰዎች ነበሩ፣ 3 ክላሽ 1 ሽጉጥ የያዙ። ‘ኬላ ጥሳችሁ ነው የመጣችሁት አሉ’። ኬላ አልጣስንም ያው ደረሰኙ ቢላቸውም ‘አይ ውረድ ውረድ’ ብለው ሹፌሩን በሰደፍ መቱት ጭንቅላቱ ላይ፣ ጋቢና ላይ የነበሩ ሁለት ሰዎችንም አስወረዱ እነርሱንም ጭንቅላታቸውን በሰደፍ መቷቸው ” ነው ያሉት።
በገመድ አስረው ፣ አፋቸውንም በፕላስተር አስይዘው እንደነበር በኃላም አላሙዲን እርሻ ፊት ለፊት ባለው አቅጣጫ መኪናውን ይዘው እንደሄዱ ተናግረዋል።
የተሽከርካሪው ባለቤት ፤ በሰደፍ ተመቱ የተባሉት ሰዎች ቢለቀቁም ቁስሉ እንዳልተሻላቸው ገልጸዋል።
“ ዱቄቱ 70 ኩንታል ነው። 210 ሺሕ ብር ይገመታል። መኪናው አዲስ ነው 2022 ሞዴል ቢ 24 ነው። መኪናውን ይመልሱልኝ ” ሲሉ የመኪናው ባለቤት ተማጽነዋል።
ሌላኛው ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አካል በበኩላቸው፣ “ ሹፌሩንና ረዳቱን ደበደቡ። የኤሌክትሪክ ፓል ጋ ሹፌሩን አሰሩ። ከዚያ መኪናውን ይዘው ሄዱ። እስከዛሬ ፋይዳ የለም ” ሲሉ አረጋግጠዋል።
ተፈፀመ የተባለውን ድርጊት አስመልክቶ ምላሽ እንዲሰጥ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበለት ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ቡኩሉ ፣ 70 ኩንታል ዱቄት ጭኖ የነበረው ተሽከርካሪ በሻሸመኔ ቢሻን ጉራቻ (ጥቁር ውሃ) መግቢያ ላይ እንዲቆም ተደርጎ እንደተወሰደ፣ ሰዎቹ ተደብደብዋል መባሉም እውነት ነው እንደሆነ ገልጿል።
አንድ የማኀበሩ ኃላፊ ፤ ሌላም እዚህም ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ ከድሬዳዋ ዘይት ጭኖ የቆመ መኪና ሰሞኑን ጠፍቶ እንደነበር፣ መጨረሻም ጭነቱ ተራግፎ ቆሞ እንደተገኘ አስታውሰው፣ " ትክክል ነው የሻሸመኔውም። እንዲህ አይነት ወንጀሎች ከዕለት ዕለት እየጨመሩ ነው " ብለዋል።
" ምክያቱም በአሽከርካሪዎችና በተሽከርካሪዎች ላይ የሚደርስን ወንጀል በወንጀልነት ቆጥሮ በጸጥታ አካል አድኖ የመያዝ ሂደት አናሳ ሆኗል። አይደለም እቃውን የሰውን ሕይወት መጥፋትም በተለይ በመንግሥት ሚዲያዎች ሲዘገብ አናይም " ሲሉ አክለዋል።
" እገታና ዝርፊያ በጣም ተበራክቷል። " ያሉት እኚህ ኃላፊ " ሜዳ ላይ አስቁመው ደብድበው የሚፈልጉትን ይዘው ነው የሚሄዱት " ሲሉ የሁኔታውን አስከፊነት አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለጉዳዩ ምላሽ ለማግኘት ወደ ሻሸመኔ ከተማ ፓሊስ ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም። #TikvahFamilyAddisAbaba
@tikvahethiopia