TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ካህኑን ማን ገደላቸው ? " ኃይሌ ጋርመንት " የሁርሲሳ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ቀዳሽ ካህን ቀሲስ ዐባይ መለስ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ አካላት በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። ካህኑን የሚያውቋቸው አገልጋዮች /ምዕመናን  ስለነበረው ሁኔታ / ስለጥቃቱ ምን አሉ ? (ለማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ከተናገሩት የተወሰደ) ቃላቸውን የሰጡ ምዕመን አንድ ፦ " ትላንት/መጋቢት…
#መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶኮስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ፤ መንግስት የቄስ ዓባይ መለሰን ገዳዮች ተከታትሎ ለፍርድ ያቅርብ አለ።

ሀገረ ስብከቱ በሰጠው መግለጫ ፤ " መንግሥት የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ በመሆናቸው ምክንያት በአሰቃቂ ሁኔታ በመንገድ ላይ ተደብድበው ሕይወታቸው እንዲያልፍ የተደረጉት የቄስ ዐባይ መለሰ ገዳዮችን ተከታትሎ ለፍርድ ያቅርብ " ብሏል።

አክሎም ፤ " ችግሩን ከሥር ከመሠረቱ በመፍታት የአገልጋዮችንና የምእመናን መብት እንዲያስከብር " ሲል ጠይቋል።

ከዚህ ባለፈ በሸገር ከተማ አስተዳደር አብያተ ክርስቲያናትን የማፍረስ ድርጊት እየተፈፀመ መሆኑን በመግለፅ ይህ ድርጊት በአስቸኴይ እንዲቆም እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

እስካሁን የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያናት ቦታ ተመላሽ እንዲያደርግ እና የፈረሰውን ቤተ ክርስቲያንም በራሱ ወጪ እንዲያሠራ እንዲደረግ ሀገረ ስብከቱ ጠይቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መግለጫ : " የአእላፋት ዝማሬ/The Melody of Myriads " ሰኞ በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ በተመሳሳይ ሰዓት ይካሄዳል።

ይህንን አስመልክቶ የተሰጠው
መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

የዘንድሮው የእላፋት ዝማሬ / The Melody of Myriads በአዲስ አበባ በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል (ቦሌ መድኃኔዓለም) ፤ በድሬዳዋ ደግሞ ለገሀር አደባባይ ብቻ ነው የሚካሄደው።

(መግለጫውን ያንብቡ)

@tikvahethiopia