TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA #PEACE

በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት ትግበራ " ተስፋ ሰጪ ነው " ሲሉ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የገለፁት የናይሮቢ ሁለተኛውን ውይይት ተከትሎ የሰላም ሂደቱ በተገመገመበት ወቅት ነው።

ዛሬ የናይሮቢውን ውይይት ተከትሎ የሰላም ሂደቱ የተገመገመ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግምገማውን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው  " የሰላም ስምምነቱ የትግበራ ሂደት ተስፋ ሰጪ ነው። " ብለዋል።

" አሁንም ለሰላም ባለን ቁርጠኝነት ጸንተናል " ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray #Mekelle ዛሬ በአፈ ጉባኤ ታገሠ ጫፎ የሚመራ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን የትግራይ መዲና መቐለ አቅንቷል። የልኡካን ቡድኑ ወደ መቐለ ያቀናው የሰላም ስምምነቱን የትግበራ ሂደት ለመቃኘትና በስምምነቱ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች በታቀደው መሠረት እንዲፈጸሙ ለማድረግ ነው ተብሏል። የልኡካን ቡድኑ ከሁለት ዓመት በኋላ ወደ መቐለ የተጓዘ የመጀመሪያው የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ…
ፎቶ ፦ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የተመራው የፌደራል መንግስት ልኡካን ቡድን የትግራይ ክልል መዲና መቐለ ገብቷል።

ቡድኑ መቐለ ሲደረስ የሃይማኖት አባቶች ፣ እነ አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ ዶ/ር ሀጎስ ጎደፋይን ጨምሮ ክልሉን እያስተዳደሩ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገዋል።

#Peace #Ethiopia

Photo Credit : Demtsi Weyane / ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia
#Update

መቐለ ከተማ የስልክ አገልግሎት ማግኘቷን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።

በመቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፤ " በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የስልክ አገልግሎት በዛሬው ዕለት መቐለ ላይ የተሳካ ጥሪ ማድረግ ተችሏል " ሲሉ ገልጸዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም 981 ኪሎ ሜትር የፋይበር ጥገና ተከናውኖ በ27 ከተሞች የስልክና ሌሎች የቴሌኮም አገልግሎቶችን ማስጀመር ተችሏል ብለዋል።

የቴሌኮም አገልግሎቱ ዳግም መጀመር በመቻሉ 61 የባንክ ቅርንጫፎችም ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግ እንደተቻለ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ መናገራቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

#Peace #ETHIOPIA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update መቐለ ከተማ የስልክ አገልግሎት ማግኘቷን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ። በመቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል። ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፤ " በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የስልክ አገልግሎት በዛሬው ዕለት መቐለ ላይ የተሳካ ጥሪ ማድረግ ተችሏል " ሲሉ ገልጸዋል። ኢትዮ ቴሌኮም 981 ኪሎ ሜትር የፋይበር…
በአንድ ቀን ብቻ ከ200 ሺህ በላይ የስልክ ጥሪ 📞

• በመቐለ የኢትዮ ቴሌኮም መደብሮች በቀጣይ ቀናት ሥራ ይጀምራሉ።

በትግራይ ክልል፣ መቐለ ለሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ተቋርጦ የነበረው የስልክ አገልግሎት መሥራት ከጀመረ በኃላ እጅግ ከፍተኛ የስልክ ጥሪ ተደርጓል።

ለረጅም ጊዜ ከቤተሰብ ጋር ሳይገናኝ በርቀት የቆየው ሕዝብ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የስልክ ጥሪ ወደ መቐለ ማድረጉን ቢቢሲ ኢትዮ ቴሌኮም ዋቢ በማድረግ በድረገፁ አስነብቧል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና የኮምዩኒኬሽን ኃላፊ መሳይ ውብሸት ለቢቢሲ ከሰጡት ቃል ፦

" ወደ መቐለ ረቡዕ ከሰዓት በኋላ የመጀመሪያው የሙከራ ጥሪ በስኬት ከተደረገ በኋላ አመሻሽ ላይ አገልግሎቱ መጀመሩን ተከትሎ እስከ ሐሙስ አስር ሰዓት ድረስ ከ220 ሺህ በላይ የስልክ ጥሪ ወደ ከተማዋ ተደርጓል።

አገለግሎቱ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ተቋርጦ በመቆየቱ በርካቶቹ ሲም ካርዶች ላይሰሩ ከሚችሉበት ደረጃ ላይ ሊሆኑ ይችላሉ።

በኢትዮ ቴሌኮም አሰራር መሠረት ሲም ካርዶች አገልግሎት ላይ ሳይውሉ ለረጅም ጊዜ ካርድ ሳይሞሉ እና ጥሪ ሳያደርጉ በሚቆዩበት ጊዜ ሥርዓቱ ቁጥሮቹን ጥሪ ብቻ ወደ መቀበል ሲቆይ ደግሞ ከአገልግሎት ወደ ማገድ ደረጃ ውስጥ ያስገባቸዌ።

ደንበኞች የገጠማቸውን ችግር ለመቅረፍ የማስተካከል ሥራ እየተሰራ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ ውስጥ የኢትዮ ቴሌኮም መደብሮች በቀጣይ ቀናት ሥራ ስለሚጀምሩ የበለጠ ችግሩ ይቀረፋል ። "

Credit : BBC AMHARIC

#Peace #ETHIOPIA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OROMIA #Peace

" . . . እርቁ በምንፈልገው ፍጥነት አለመምጣቱ ቢያሳዝንም ተስፋ መቁረጥ ግን አያስፈልግም " - አቶ ጃዋር መሀመድ

አቶ ጃዋር መሀመድ የኢፌዴሪ መንግሥትና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA) በታንዛኒያ ዳሬሰላም ያደረጉት የሁለተኛው ዙር ድርድር ያለ ስምምነት ከተበተነ በኃላ ድርድሩን በተመለከተ ሰፋ ያለ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አቶ ጃዋር መሀመድ ምን አሉ ?

- መንግስትንና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (WBO-OLA) ለማስታረቅ የተደረገው 2ኛው ዙር ሙከራ አለመሳካቱ በህዝቡ ዘንድ ትልቅ ሀዘን የፈጠረ ነው።

- በሕዝቡ በኩል ቢያንስ ሁለቱም ወገኖች በዚህ ዙር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንደሚደርሱ ተስፋ ተደርጎ ነበር። በተለይ የጦር አዛዦች ከጦር ሜዳ ለውይይት መምጣታቸው እርቀ ሰላሙን ያሳካል የሚል ተስፋ ፈጥሮ ነበር።

- ድርድሩ አለመሳካት እንደ ትልቅ ውድቀት ሲቀርብ እናያለን ነገር ግን ውይይቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ብዙ ርቀት ተጉዟል። እርቅ ከማያስፈልግበት ወይም ከማይቻልበት ደረጃ ተነስተን የሁለቱም ወገን አመራሮች ፊት ለፊት ተገናኝተው መወያየት ደረጃ ደርሰናል።

- ይህ እርቅ በምንፈልገው ፍጥነት አለመምጣቱ ቢያሳዝንም ተስፋ መቁረጥ ግን አያስፈልግም። ተስፋ ልንቆርጥም አንችልም። ሌላ መፍትሄ የለንምና። ስለዚህ የሰላም ድርድሩ እንደሚቀጥል ተስፋ እናደርጋለን።

🕊አቶ ጃዋር መሀመድ በሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር ላይ ከተሳተፉት አካላት እና ከተለያዩ ምንጮች ተረዳሁት ያሉትንና ለቀጣይ ዙር የሰላም ድርድር ያግዛሉ ያሏቸውን ሃሳባችን በዝርዝር አቅርበዋል።

➜ በሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር ሁለቱም ወገኖች በእውነት #እርቅ/#ሰላም ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ።

በዚህ የተነሳ ሁለቱም ወገኖች ልክ እንደ ህዝቡ ይህ ምዕራፍ በእርቅ ስምምነቱ ይጠናቀቃል የሚል ተስፋ (expectation) ይዘው ነበር የቀረቡት።

ሁሉም ተሳታፊዎች (WBO / የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ፣ መንግስት እና አሸማጋዮች) በሰላም፣ በእርቅ ይጠናቀቃል የሚል ተስፋ ይዘው ስለሄዱ ግባቸው ላይ ባለመድረሳቸው የመናደድ ስሜት ውስጥ ገብተዋል። በዚህ ምክንያት ለቀጣዩ የሰላም ውይይት በር ከመክፈታቸው በፊት ተለያይተዋል።

➜ ሁለቱም ወገኖች በቅን ልቦና ለመታረቅ ቢሄዱም፣ አንዱ ከአንዱ የሚፈልገውን (demands/concessions) ለመስጠት እና ለመቀበል ሙሉ በሙሉ የተዘጋጁ አይመስሉም።

በመጀመሪያው ዙር እርስ በርሳቸው የሚፈልጉትን ነገር ተረድተው ተለያይተዋል። በሁለተኛው ዙር ደግሞ አንዳቸው ለሌላው መስጠት የማይችሉትን ያወቁ ይመስለኛል።

አሁንም ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኝነት ካላቸው፣ ቀጣዩ እርምጃ ሁለቱም ወገኖች ጥያቄዎቻቸውን ለማስተካከል (modifying demands) መዘጋጀት አለባቸው። ይህ ማለት እንዱ መቀበል የማይችላቸው ነገሮች ላይ በመግፋት መጋጨት መተው አለባቸው።

በሰላም ድርድር ውስጥ የሚፈልጉትን እና ይገባኛል ብለው የሚያስቡትን ሁሉ ማግኘት አይቻልም። ይገባኛል ብለው የሚያስቡትን ሁሉ ማጣትም አይቻልም። ሁለቱም ወገኖች ወደ መካከለኛው አቋም መምጣት ይጠበቅባቸዋል።

➜ የሰላም ድርድሩ ዋነኛው #እንቅፋት እየሆነ ያለው ዋና ምክንያት አንዱ ከአንዱ የሚፈልገው ነገር ላይ ተራርቀው ነው ብዬ አላስብም። ትልቁ እንቅፋት #አለመተማመን ነው። በሁለቱ ወገኖች በታሪክ ካለው ግንኙነት እና ከአገራችን የፖለቲካ ባህል አንፃር አለመተማመናቸው ይጠበቃል። የውጪው አካል ያስፈለገበትም ምክንያት ይሄ ችግር ስለተረዳ ነው። እነዚህ አስታራቂዎች የእርቅ ስምምነት ላይ መድረስ ብቻ ሳይሆን የስምምነቱ አፈጻጸምን ለማረጋገጥ ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ይህንን አሻሚ የሆነ ችግር ለማሻሻል ይጠቅማል።

➜ ከውስጥ ከውጭ " እርቅ ሊመጣ ነው " ብለው እያዘኑ የነበሩት ወገኖች አሁን በመፍረሱ በደስታ እየፈነደቁ ነው። ሌላ ዙር ድርድር እንዳይደረግም እያሴሩ ነው። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA) እና የመንግስት አመራሮች አሁንም ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል አቋም ካላቸው እነዚህ ፀረ-ሰላም ኃይሎች ወደ ውስጥ እንዳይገቡ ሁሉንም ክፍተቶች መዝጋት አለባቸው። በተጨማሪም የሚቀጥለውን ዙር እድሎች ከሚያጠብ ወይም ከሚያርቁ ድርጊቶች እና ቃላት መቆጠብ አለባቸው። ይህም የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ እና የመስክ ውጊያን አለማባባስን ያካትታል።

➜ እኔ እስከተረዳሁት ድረስ ከ2ቱም ወገን ደጋፊዎች በኩል የነበረው የ " #ምታ - #ስበር - #አጥፋ " ዘመቻ ባለፉት አመታት በጣም መቀነሱን ነው። የእርቅ ሀሳብ መደገፍ እና ሰላም እንዲወርድ ያላቸው ምኞትም ከየትኛውም ጊዜ በላይ እያደገ መጥቷል።

➜ አሁንም የሁለተኛው ዙር ሙከራ ስላልተሳካ እርስ በርስ ጣት መቀሳሰር እና መደማማት ምንም ፋይዳ እንደሌለው መረዳት ያስፈልጋል። የሚጠቅመው የሚደግፉትን ወገኖች ወደ ድርድሩ እንዲመለሱ እና የሚጠበቅባቸውን እንዲሰጡ ማበረታታት እና ጫና ማድረግ ነው።

➜ በመጨረሻም ፤ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ይሄ የሰላም ድርድር የጦር ሜዳ ውጤቶች አይደለም።

ሁለት የሚዋጉ ወገኖች ለእርቅ ድርድር የሚቀመጡት በሁለት ሁኔታዎች ውስጥ ነው።

የመጀመሪያው ፦ በጦር ሜዳ ላይ አንደኛው የበለጠ የበላይነት አግኝቶ ወደ ድል ሲቃረብ እና ሌላኛው ወገን ሙሉ በሙሉ ከመሸነፉ በፊት ለመታረቅ ሲወስን ነው።

ሁለተኛው ፦ ከረዥም ጊዜ ጦርነት በኋላ ሁለቱም ወገኖች መሸናነፍ ካልቻሉ ነው። በWBO-OLA እና በመንግስት መካከል ያለው ጦርነት የመሸናነፍ ወይም የመድከም ደረጃ ላይ አልደረሰም። በአጭር ጊዜ ውስጥም እዚህ ደረጃ ላይ ይደርሳል ብዬ አላስብም። ይህ ውይይት የመጣው በህዝብ እና በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ግፊት ነው።

በተለይም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሀገራችን ሰላም እንዲሰፍን ያሳየው ትኩረት ያልተጠበቀ እና ትልቅ እድል ነው።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትኩረት በፍጥነት እየተቀየረ ነው። ስለዚህ ፤ ጉዳያችን ትኩረት ባገኘበት በዚህ ወቅት በፍጥነትና በብልሃት መጠቀም አስፈላጊ ነው። ይህንን እድል መጠቀም ካልቻልንና የሚባክን ከሆነ ለረጅም ጊዜ እንቆጫለን።

#JawarMohammed

Via https://t.iss.one/tikvahethAFAANOROMOO

#TikvahEthiopiaAFAANOROMOO

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Peace #GoE #OLA

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (OLA መካከል ከዚህ ቀደም ታንዛኒያ ላይ ሁለት ጊዜ የሰላም ድርድር ተደርጎ ያለ ስምምነት / ወጤት መበተኑ ይታወሳል።

አሁንም ሌላ #ሶስተኛ_ዙር የሰላም ውይይት/ድርድር ሊኖር የሚችልበት ዕድል መኖሩን የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናግረዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ምን አሉ ?

- የመጀመሪያው ንግግር በጣም ጥሩ ርቀት ሄዶ ነበር ፤ በዚህም ብዙ መካሰስ ቀርቶ ለሚቀጥለው ዙር ለመነጋገር እናመቻች በሚል ነው የተጠናቀቀው።

- ሁለተኛው የሰላም ድርድር መጀመሪያ ላይ ከሁለቱም ወገን አግባቢዎች ሄደው ከሳምንት በላይ ፈጅተዋል። አዝማሚያው ጥሩ ነበር።  መጨረሻ የማያግባቡ ነጥቦች መጡ። በዚህም ትንሽ የተሻለ ኃይል ያለው ሰው ይምጣ ተብሎ ከመንግሥትም ከነሱም ሄዷል። በዚህም ጊዜ ጥሩ ሂደት ነበር።

- በህገ-መንግስት ጥላ ስር "የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ፣ አንድነት መቀበል ላይ ፤ የኢትዮጵያን ሀገረ መንግስት በምርጫ የመጣ Legitimacy ያለው መሆኑ ላይ መግባባት ተደርሶ ነበር። ወደ ዝርዝር ሲመጣ ግን እነዚህን መግባባቶች የሚሸረሽር ነገር ነው የመጣው።

- ስምምነቱ በመጨረሻ ለህዝብ ይፋ የሚሆን ደረጃ / ወደ ሰነድ ደረጃ ሲደርስ ያልተጠበቁ ጥያቄዎች ተነስትዋል።

ምንድናቸው ?

* አንደኛው --- ' #ስልጣን_አካፍሉኝ ' ነው እያንዳንዱን ጠብመንጃ የያዘ፣ ጫካ የገባ ሁሉ ስልጣን ለማግኘት ከሆነ የሚደራደረው ይሄ ለሀገር ሰላም አይሰጥም።

ጫካ እየገቡ ፣ ግጭት የፈጠሩ ፣ ህዝቡን እያበሳሰቡ ከዛ እንነጋገር እያሉ " እሺ " ሲባል ስልጣን አካፍሉኝ የሚባል ነገር ካለ መቼም ስርዓት አይመጣም። ሀገር ሰላም አይሆንም።

ምሳሌ ብንወድስ ፦ ከአማራ፣  ከቤንሻንጉል ጉምዝም ከሌላውም የታጣቁ ኃይሎች ስልጣን አካፍሉኝ ካሉ ስንት የታጠቀ ኃይል ስልጣን ሲካፈል ይኖራል ? ይሄ ኢትዮጵያን ይጎዳል።

እንዲህ አይነት ጥያቄ ነው ይዘው የቀረቡት (OLAን ማለታቸው ነው)።

መንግሥት ስልጣን ላካልፍ ቢልም ፍፁም አይችልም ፤ መብትም የለውም። #ማሳተፍ ግን ይችላል። ሸኔን ጭምር ማሳተፍ ይችላል።

ዋናው መሰረታዊ ልዩነት ይሄ ነው። ስልጣን አካፍሉኝ ስሉም እራሳቸው ፕሮፖዛል አስቀምጠው ፤ እዚህ ላይ ስልጣን ስጡኝ የሚል ነበር።

* ሁለተኛው --- ወደ ' DDR ' አልገባም ነው።

በሰላም ለመታገል ፣ ፓርቲ አቋቁሞ ለመታገል ፣ ወደ ህዝብ ምርጫ ለመቅረብ የገጠር ትጥቅ ትግል ትቶ በሰላም ወደ ህዝብ መመለስ ነው። ለዚህ ደግሞ ትጥቅ መፍታት አለባቸው።

DDR / Disarm, Demobilized , Reintegrate መሆን አለባቸው። ይሄ ዓለም የሚሰራበት ነው። ማንኛውም ግጭት የተፈታውም በዚህ ነው። ይሄን ለመቀበል የመቸገር ነገር ተከስቷል።

ትጥቅ ሳይፈታ ፦
° እንዴት እንደራደራለን?
° እንዴት Demobilize ይሆናሉ?
° እንዴት ወደ ህብረተሰቡ ይቀላቀላሉ ?

መንግስት በግልፅ DDR ፕሮግራም ውስጥ መግባት አለብን ብሏል። በአንድ ሀገር በፍፁም ሁለት የታጠቀ ኃይል ሊኖር አይችልም። ትጥቅ የመያዝ መብት ያለው መንግስት ብቻ ነው።

ይሄንን #መቀበል_ነበረባቸው። በዓለም ላይ ይሄን ሳይቀበሉ ስምምነት የለም። ድርድር ብሎ ነገር የለም።

ንግግሩ ጥሩ ሄዱ ከላይ ባሉት ሁለት ምክንያት ነው መጨረሻ ላይ የቆመው።

- ሶስተኛ ዕድል ይኖራል ? እኔ የሚኖር ይመስለኛል።

- ሁለቱን #ያልተስማማንባቸው_ነጥቦችን በተሳሳተ መንገድ እንዲወስዱ በማድረግ ሌሎች ኃይሎች እጅ አላቸው። OLA ላይ ታዝሎ የሚሄዱ ኃይሎች አሉ። ከሀገር ውስጥም ከሀገ ውጭም አሉ። ባዕዳንም ዜጎችም እነዚህ ኃይሎች OLA በሰከነ መንገድ አይቶ ስምምነቱን እንዳይቀበል አድርገውታል። OLA ሌላ መስማት አልነበረባቸውም፤ ችግር ውስጥ ያሉት እራሳቸው ስለሆኑ እራሳቸው መወሰን ነበረባቸው።

(ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ እነዚ ኃይሎች እነማን እንደሆኑ በግልፅ አልተናገሩም)

- ሌላው ኃይል ጣልቃ ስለገባ በዓለም experience ታይቶ የማይታወቅ ቅድመ ሁኔታ በማቅረብ መንግሥትን አስቸግረዋል (OLA ማለታቸው ነው)።

- ሶስተኛ ዕድል ሊኖር ይችላል። ሰከን ብለው አስበው አደራዳሪዎች ጭምር የሚያምኑበት የመጨረሻው ወረቀት / ዶክመንት / የቀበል ደረጃ ከደረሱ ሶስተኛ ውይይት ሊኖር ይችላል።

- ምናልባት ሶስተኛ ውይይት እንደሁለተኛው ውይይት ሰፊ ላይሆን ይችላል እስካሁን የተደከመበት ሰነድን መቀበል ላይ ከተደረሰ ሶስተኛው ውይይት ሊኖር ይችላል፤ ሶስተኛው ውይይት የመጨረሻም ይሆናልም ብዬ ገምታለሁ ወደሰላም ለመምጣት ወይም እስከመጨረሻው ሁለተኛ ላለመነጋገር የመጨረሻ ሊሆን ይችላል።

🕊 የኢጋድ ዋና ፀሀፊ የሆኑት ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከሳምንታት በፊት ያለ ስምምነት የተጠናቀቀውን 2ኛው ዙር የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሰላም ድርድርን በተመለከተ ሰጥተው በነበረው መግለጫ ሌላ አዲስ ዙር ውይይት ይጀመራል ብለው #ተስፋ እንደሚያደርጉ መግለፃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#Axum #Tigray

" በጦርነቱ ጊዜ እኮ #መከራው ከባድ ነበር !! "

ወ/ሮ በላይነሽ መኣሾ (የአክሱም ነዋሪ ለድምጺ ወያነ) ፦

" ሰላም በመሆኑ ጥሩ ነው ያለው።  ብርሃን አየን።

በሰላም እየተንቀሳቀስን ነው። #ሕጻናት እየተጫወቱ ነው።

ብዙ ለውጥ ነው ያለው።

በጦርነቱ ጊዜ እኮ #መከራው እጅግ ከባድ ነበር። አሁን በጣም በጣም ይሻላል ፤ ቢያንስ #እፎይ ብለን  መተኛት እንችላለን።

ቢሆንም ግን #የከፋው_ሰው_አለ ፤ ሰው የሚበላው የሚጠጣውን አጥቶ በጣም ከፍቶታል ፣ የመንግስት ሰራተኛውም ያለፉት ዓመታት ደመወዝ ባለመከፈሉ ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጦ ነው ያለው ፣ የተፈናቃዮች ነገርማ #አይወራም ፣ ሕጻናት ልጆች የሚበሉትን አጥተው በየከተማው #በልመና ነው ተሰማርተው ያሉት። "

#Ethiopia #TigrayRegion #Peace

@tikvahethiopia
#OROMIA #PEACE

" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ... ለሰላም ክፍት ነን ድርድሮችም እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም ቢሆን ያሉ ችግሮች #በሰላም እንዲፈቱ መንግሥት #ለድርድር ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።

የክልሉ መንግሥት አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በአዲስ አበባ እንደመከሩ ተነግሯል።

በምክክሩ ላይ የተገኙት የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈሰ ውይይቱ ልማትና ጸጥታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

በውይይቱ ፦

- የልማት ስራ ያለ ሰላም ውጤት አልባ እንደሆነ / ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነ ፤

- ሰው ሰርቶ የሚበላው ፣ ወልዶ የሚስመው ሰላም ሲኖር እንደሆነ አጽንኦተ ተሰጥቶበታል ብለዋል።

" ሰላም ለመንግሥት ብቻ የተተወ ስላልሆነ እንዴት ነው አብሮ መስራት የሚቻለው ? " የሚለውም መነሳቱን አስረድተዋል።

" መንግሥት እና ሸኔ የጀመሩት ድርድር ፤ በተለያየ ምክንያት አኩርፈው ጫካ የገቡ ነፍጥ ያነገቡ ጓዶች አሉ ፤ መንግሥት በሆደ ሰፊነት ዛሬ ነገ ሳይል እነዚህን አካላት ጠርቶ በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር አለበት ይህ ሲደረግ ደግሞ ለሰዎቹ እውቅና ተሰጥቶ የህግ ከለላ ተሰጥቶ ነው ውይይት መደረግ ያለበት " የሚለውም መነሳቱን ገልጸዋል።

" በመንግሥት በኩል ' ዛሬም ቢሆን ክፍት ነው እንነጋገራለን ፣ ችግሮችን በጋራ ተነጋግረን እንፈታለን ' የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን " ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ አሁንም ቢሆን የክልሉ መንግሥት በውይይት ያምናል ብለዋል።

" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ሙሉ ትኩረታችን ወደ ሰላም ማምጣት ነው ያለብን። የፈለግነውን ነገር በአዳራሽ መወያይት ይቻላል። ጥረቶች ብዙ ነው ያደረግነው አሁንም ለሰላም ክፍት ነን እኛ 3ኛ ዙር ይሁን፣ 5ኛ ዙር ይሁን ፣ 10ኛ ዙር ድርድሮች እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " ብለዋል።

#Ethiopia
#Oromia #VOA

@tikvahethiopia