TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#በወንጀል_ይፈለጋሉ #Wanted የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከላይ በፎቶ የሚታዩትን ተጠርጣሪዎች በወንጀል እየፈለጋቸው ይገኛል። የተጠርጣሪዎቹን አድራሻቸውን የሚያውቅ አልያም በአጋጣሚ የተመለከተ ማንኛውም ገለሰብ በስልክ ቁጥር ፦ 👉 0115309139 ዘውትር (በስራ ሰዓት ከ2:30 - 11:30) 👉 በ0111119475 / 0111711012 በማንኛውም ሰዓት ደውሎ እንዲያሳውቅ ተጠይቋል። ነፃ የስልክ…
#ምስጋና🙏

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ለህብረተሰቡ ምስጋና አቅርቧል !

ተደራጅተው ከወርቅ መሸጫ ጌጣጌጦች የዘረፉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከዚህ ቀደም በማህበራዊ ሚዲያዎች በተሰራጨ ቪድዮን ተከትሎ ተጠርጣሪዎች እንዲያዙ ትብብር እንዲደረግ ጥሪ አቅርቦ ነበር።

እንደ ፌዴራል ፖሊስ መረጃ በቡድን ተደራጅተው ዝርፊያውን የፈፀሙት ግለሰቦች በሞጆ ከተማ ሲሆን በቲክቶክ ላይ የአዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ የተባለው ስህተት እንደነበር ገልጿል።

ግለሰቦቹ ከወርቅ መሸጫው ሱቅ 49 ግራም የሚመዝኑ የወርቅ ጌጣጌጦችን ዘርፈው ከአካባቢው ተሰውረው የነበር ቢሆንም በህብረተሰቡ ጥቆማና በፖሊስ ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ስር ሊውሉ እንደቻሉ ተገልጿል።

የዘረፋ በድኑ አባላት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ህብረተሰቡ ላሳየው ትብብር እና ፈጣን ምላሽ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ምክትል ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ብርሃኑ አበበ  ፥ " በቡድን ተደራጅተው በተለያየ ጊዜ የፖሊስን የደንብ ልብስ በመልበስ ዘረፋ የሚያካሄዱ ግለሰቦች እየተበራከቱ መጥተዋል " ያሉ " ይህ ተግባር የፀጥታ ኃይሉን ስም ለማጠልሸትና የጠላትን ዓላማ ለማሳካት ሆን ተብሎ የተፈፀመ ነው " ብለዋል።

ረዳት ኮሚሽነር ብርሃኑ ፤ ፖሊስ ከህዝብ አብራክ የወጣና የህዝብ አገልጋይ በመሆኑ ለደንብ ልብሱና ለዓላማው ልዩ ክብርና ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ መሆኑን ገልፀው የማዕረግ የደንብ ልብሱን ለብሶ ማንም ሰው ስሙን ማጠልሸትና ማጉደፍ እንደሌለበት አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ነገ የሚከበረውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ 21 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* Update የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ከኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጋር መነጋገራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳውቋል። ሐመር በዚሁ ወቅት ጦርነት በአስቸኳይ ቆሞ ፤ በአፍሪካ ህብረት (AU) መሪነት ወደ ሰላም ድርድር ማምራት…
#AU #ETHIOPIA

የኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ኃላፊነት ተራዝሟል።

ለሰሜን ኢትዮጵያ ችግር ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያፈላልጉ እና ችግሩ በሰላም መቋጫ እንዲያገኝ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ስልጣን / ኃላፊነት መራዘሙን ለመስማት ተችሏል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛን ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ ኦባሳንጆ የተሰጣቸው ኃላፊነት መራዘሙንም አመልክተዋል። በእሳቸው (በኦባሳንጆ) ላይ ያላቸው እምነት ሙሉ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪ ፤ በኢትዮጵያ እና በቀጠናው ሰላም እና እርቅ እንዲመጣ ከሁለቱም ወገኖች እና ከዓለም አቀፍ ተዋናዮች ጋር የቀጠሉትን ግንኙነት አበረታታለሁ ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ጋር ትላንት እዚሁ አዲስ አበባ ላይ መመካከራቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ትኩረቱን ያደረገው በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር በተመለከተ ሲሆን ይህንን ንግግር አሜሪካ እንዴት በተሻለ ሁኔታ መደገፍ እንደምትችል ምክክር መደረጉን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AU #ETHIOPIA የኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ኃላፊነት ተራዝሟል። ለሰሜን ኢትዮጵያ ችግር ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያፈላልጉ እና ችግሩ በሰላም መቋጫ እንዲያገኝ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተሾሙት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ስልጣን / ኃላፊነት መራዘሙን ለመስማት ተችሏል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ…
#UpdateAU

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመርን ዛሬ ተቀብለው ማነጋገራቸውን በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አሳውቀዋል።

ሊቀመንበሩ አምባሳደር ማይክ ሐመርን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማስቆም #በአፍሪካ_ኅብረት_የሚመራውን የሰላም ሂደት ዓለም አቀፍ አጋሮች እንዲደግፉ መስማማታቸውን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዕጣ ወጣ !

የብሄራዊ ሌተሪ አስተዳደር የእንቁጣጣሽ ሌተሪ ትላንት ጳጉሜ 5 ቀን 2014 ዓ/ም በብሄራዊ ሎተሪ ዕጣ ማውጫ አዳራሽ በህዝብ ፊት መውጣቱን አሳውቋል።

የአሸናፊ ቁጥሮች ከላይ ተያይዘዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
እንኳን አደረሰን ፤ አደረሳችሁ !

ሀገራችን #ኢትዮጵያ በራሷ አቆጣጠር ዛሬ ያለፈውን 2014 ዓ/ም ሸኝታ አዲሱን 2015 ዓ/ም ተቀብላለች።

መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን እንኳን ይህችን ቀን ለማየት አበቃን ፤ እንኳን አደረሰን ፤ አደረሳችሁ !!

2014 ዓ/ም ሸኝተን 2015 ዓ/ምን ስንቀበል ደስታችን ሙሉ ሆኖ አይደለም፤ ልክ 2013 ዓ/ምን ሸኝተን 2014 ዓ/ምን እንደተቀበልነው ጊዜ ሁሉ ዛሬም ከጦርነት እና ከግጭት ቀጠና ያልወጡ ብዙ ወገኖቻችን አሉ።

በ2014 ዓ/ም ብዙ ወገኖቻችን በሀገራችን የተለያዩ ክፍሎች በነበሩ ግጭቶች እንዲሁም ጦርነት አጥተናል ፤ ብዙዎች ተጎድተውብናል፣ በርካታ ወገኖቻችን በደረሰባቸው ችግር ሰው ጠባቂ ሆነዋል። በተፈጥሮም አደጋ ያጣናቸው ወገኖቻችን ብዙ ናቸው።

በዓመቱ ችግር የደረሰባችሁ፣ የምትወዷቸውን ከአጠገባችሁ ያጣችሁ፣ ልጆቻችሁን የተነጠቃችሁ ወላጆች፣ ወላጆቻችሁን እና ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ ሁሉ ፈጣሪ መፅናናት እና ብርታትን ይሰጥልን ዘንድ እንማፀናለን። የተጎዱ ወገኖቻችንም ፈጥነው እንዲያገግሙ እንማፀናለን።

ዛሬ የተቀበልነው 2015 አዲስ ዓመት ከምንም ነገር በላይ ወገኖቻችንን ችግር የማንሰማበት ፣ የሰላም ፣ የደስታ ፣ መልካም መልካሙን ምንሰማበት ፣ ከችግሮቻችን ሁሉ ተቃላቀን ደስ የምንሰኝበት ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

የአዲስ ዓመት በዓልን ስናከበር በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በማሰብ፣ የታመሙትን በመጠየቅ፣ ፈጣሪ ለሀገራችን አስተማማኝ የሆነ ሰላምን እንዲሰጠን በመማፀን ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።

ፈጣሪ ሀገራችንን #ኢትዮጵያን ይጠብቅልን!
Tikvah Family ❤️

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UpdateAU የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመርን ዛሬ ተቀብለው ማነጋገራቸውን በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አሳውቀዋል። ሊቀመንበሩ አምባሳደር ማይክ ሐመርን ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለማስቆም #በአፍሪካ_ኅብረት_የሚመራውን የሰላም ሂደት ዓለም አቀፍ አጋሮች እንዲደግፉ መስማማታቸውን…
#ETHIOPIA

ዛሬ እና ባለፉት ቀናት ምን ሆነ ?

- የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረዋል በተጨማሪ ከህወሓት መሪ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋርም በምን አይነት መልኩ  እንደተነጋገሩ ባይታወቅም ተነጋግረዋል (እንደ አሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መረጃ)። ሐመር ዛሬም እዚሁ አዲስ አበባ ናቸው።

- አምባሳደር ሐመር ከአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ እና ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ጋር ተወያይተዋል።

- የአፍሪካ ህብረት በኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ላይ " ሙሉ እምነት " እንዳለው ገልጾ ኃላፊነታቸውን አራዝሟል።

- ኦባሳንጆ እና ሙሳ ፋኪ ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

- ዛሬ  በአዲሱ ዓመት ደግሞ ከዚህ ቀደም በኦባሳንጆ ላይ እምነት የለኝም ያለው ህወሓት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ከፌዴራል መንግስት ጋር እደራደራለሁኝ ሲል መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው ፦

• በአፍሪካ ኅብረት የሚመራ ተዓማኒ የሰላም ሒደት እንጠብቃለን ብሏል።

• በ " አፍሪካ ህብረት መሪነት " ለመደራደር ዝግጁ ነኝ ፤ ለድርድሩ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ፣ ለአፋጣኝ እና በሁለቱም ወገኖች ስምምነት ተግባራዊ ለሚደረግ የተኩስ አቁም ዝግጁ ነኝ ብሏል።

• በ2ቱ ወገኖች ተቀባይነት የሚኖራቸው አደራዳሪዎች ፣ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች እና ዓለም አቀፍ ባለሞያዎች በሰላም ሂደቱ ሊሳተፉ ይገባል ብሏል።

• ተደራዳሪዎቹ አቶ ጌታቸው ረዳ እና ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳይ እንደሆኑ ገልጾ በፍጥነት ተደራዳሪዎቹን ለመላክ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

• ለዚህ አሳዛኝ ግጭት ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ማምጣት የምንችለው #በሰላማዊ_ውይይት_ብቻ እንደሆነ እርግጠኞች ነን ብሏል።

➣ ዛሬ በ "ህወሓት" በኩል በወጣው መግለጫ ላይ ቅድመ ሁኔታዎች ተብለው የተዘረዘሩ ነጥቦች የሉም።

የ " ህወሓት " ን የዛሬ መግለጫ በተመለከተ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ መንግስት የተባለ ነገር የለም። ነገር ግን ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላማዊ መፍትሄ ዝግጁ መሆኑን በማረጋገጥ ፤ የሰላም ድርድር ኮሚቴውን አባላት በዝርዝር ማሳወቁ አይዘነጋም።

የሰላም ሂደቱ ተፈፃሚ የሚሆነው #በአፍሪካ_ህብረት ጥላ ስር ብቻ እና ብቻ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለፁ ይታወሳል።

በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግስት ህወሓት ዳግም ጥቃት መክፈቱን ካሳወቀ በኃላም በተደጋጋሚ ባወጣቸው መግለጫዎች ለሰላም የዘረጋው እጅ እንዳልታጠፈና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ " ህወሓት " ወደ ተከፈተው የሰላም በር እንዲመለስ ግፊት እንዲያደርግ ጥሪ ሲያቀርብ ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ዛሬ እና ባለፉት ቀናት ምን ሆነ ? - የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከፌዴራል መንግስት ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረዋል በተጨማሪ ከህወሓት መሪ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋርም በምን አይነት መልኩ  እንደተነጋገሩ ባይታወቅም ተነጋግረዋል (እንደ አሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መረጃ)። ሐመር ዛሬም እዚሁ አዲስ አበባ ናቸው። …
#UpdateAU #ETHIOPIA

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ፤ የትግራይ ክልል መንግስት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት መሪነት በሚካሄደው የሰላም ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ፍቃደኝነቱን መግለፁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል።

ይህን የገለፁት የትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው ህወሓት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ከፌዴራል መንግስት ጋር እደራደራለሁ ካለ በኃላ ባወጡት መግለጫ ነው።

ሊቀመንበሩ ይህ አዎንታዊ የሆነ እድገት በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላምን ወደነበረበት ለመመለስ ልዩ አጋጣሚ ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የትግራይ ክልል መንግስት ለድርድር ዝግጁ መሆኑን በመግለፁም ሊቀመንበሩ አመስግነዋል።

ከዚህ ባለፈ ሁለቱም ወገኖች (የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል መንግስት) በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ለማድረግ እንዲሰሩ እና የፊት ለፊት ንግግር እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ሊቀመንበሩ በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሰላም ሂደት ላይ ሁለቱም ወገኖች የሚስማሙባቸው ዓለም አቀፍ አጋሮች እንደሚካተቱ ጠቁመዋል።

ሙሳ ፋኪ መሀመት በመግለጫቸው ላይ በዚህ ወሳኝ ወቅት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአፍሪካ ኅብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ድጋፉን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UpdateAU #ETHIOPIA የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ፤ የትግራይ ክልል መንግስት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት መሪነት በሚካሄደው የሰላም ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ፍቃደኝነቱን መግለፁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል። ይህን የገለፁት የትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው ህወሓት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ከፌዴራል መንግስት…
#USA #ETHIOPIA

" አሜሪካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ትቆማለች ፤ የአፍሪካ ህብረትን (AU) ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን ትደግፋለች " - አንቶኒ ብሊንከን

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ #ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንደምትቆም እና በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት #እንደምትደግፍ ገልፀዋል።

ይህን የገለፁት ለሊት ባወጡት መግለጫ ነው።

ብሊንከን ፤ የአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ላለው ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ለማበጀት የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት (TPLF) በተቻለ ፍጥነት ወደ ውይይት እንዲመጡ ለማድረግ እየሰራ ላለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ሲባል ከህወሓት ጋር " በየትኛውም ስፍራ፣ በማንኛውም ጊዜ "  ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን እንደገለፀ ያስታወሱት ብሊንከን ለዚህ የመንግስት ዝግጁነት የሚሰጥ ምላሽን እናበረታታለን ብለዋል። ህወሓት (TPLF) ግጭት ለማቆም እና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ያወጣውን መግለጫ እናበረታታለን ሲሉም አክለዋል።

ዓለም አቀፍ አጋሮች የሰላም ሂደቱን ለማገዝ ዝግጁ ናቸውም ብለዋል።

ኤርትራ እና ሌሎችም ግጭቱን ማቀጣጠል ማቆም አለባቸውም ሲሉ ገልፀዋል።

አሜሪካ የኢትዮጵያን #አንድነት#ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት እንደምትደግፍ የገለፁት አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ወደ #ጠንካራ_አጋርነት መመለስ ትፈልጋለች ሲሉ ገልፀዋል።

" የአዲስ ዓመት መንፈስን ታሳቢ በማድረግ የአገሪቱ መሪዎች አገሪቱ መከራዋ ወደሚያበቃበት እና ዘላቂ ሰላም ሊያስገኝ ወደሚያስችል መንገድ እንደሚሯት ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #ETHIOPIA " አሜሪካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ትቆማለች ፤ የአፍሪካ ህብረትን (AU) ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን ትደግፋለች " - አንቶኒ ብሊንከን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ #ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንደምትቆም እና በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት #እንደምትደግፍ ገልፀዋል። ይህን የገለፁት ለሊት ባወጡት መግለጫ ነው። ብሊንከን ፤…
#UN #EU

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የትግራይ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት በአስቸኳይ ለማቆም እና በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት መዘጋጀቱን ማሳወቁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል።

በተጨማሪ የትግራይ ክልላዊ መንግስት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር ለሚደረገው የሰላም ሂደት ፍቃደኛ መሆኑን አበረታተዋል።

ጉተሬዝ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልላዊ መንግስት ይህንን እድል ለሰላም እንዲጠቀሙበት እና ግጭት እንዲቆም እርምጃዎችን እንዲወስዱ እንዲሁም ለውይይት አማራጭ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

ሁለቱም በቅን ልቦና ሳይዘገዩ እንዲሁም ለውይይቱ መካሄድ ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሰላም ሂደት ላይ በንቃት እንዲሳተፉ አበረታተዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ለመደገፍ ያለውን ዝግጁነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ዋና ፀሀፊው በመጨረሻም አዲሱ ዓመት ለመላው ኢትዮጵያውያን የደስታ እና የሰላም እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ፤ የአውሮፓ ህብረት የትግራይ ክልላዊ መንግስት በአስቸኳይ ግጭት ለማቆም እና በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሰላም ሂደት ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን መግለፁን ተከትሎ " አሁን ፤ ይህንን እድል ሁሉም ሊጠቀምበት ይገባል " ብሏል።

የአውሮፓ ህብረት፤ የአፍሪካ ህብረትን የሰላም ሂደት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑንም አሳውቋል።

@tikvahethiopia