TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ልክ ጎንደር እንደተደረገው በደብረብርሃን ከተማም ክልከላዎች ተጣሉ። ደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ #ህጋዊ_መታወቂያ ሳይዙ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ህጋዊ መታወቂያ ሳይዝ የተንቀሳቀሰ ግለሰብም ሆነ ቡድን በህግ ቁጥጥር ስር ይውላል ተብሏል። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት " የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ " እንዲቻል በሚል ክልከላዎችን መጣሉን…
#ደሴ
የአማራ ክልል ከተሞች ተመሳሳይ / #አንድአይነት ይዘት ያላቸው ክልከላዎችን እየጣሉ ይገኛሉ።
ማምሻውን የደሴ ከተማ ኮማንድ ፖስት በጎንደር እና ደብረብርሃን የተጣሉትን አይነት ተመሳሳይ ክልከላዎች መጣሉን ገልጿል።
ኮማንድ ፖስቱ የጣላቸው ክልከላዎች ከላይ ተያይዘዋል።
በሌላ በኩል ፤ የፀጥታ ኮማንድ ፖስቱ ለከተማው ነዋሪዎች ባሰራጨው መልዕክት " በከተማው እየተሰራ ያለው ልማት ለደቂቃም ሊስተጓጎል አይገባም። " ብሏል።
" ህዝባችን ሰላም ፣ ልማት እንደሚፈልግ ጠንቅቀን እንረዳለን። " ያለው ኮማንድ ፖስቱ " የደሴ ህዝብ ከእንግዳህ በሴራ እየተጎዳ መቀጠል የለበትም " ሲል ገልጿል።
" ወጣቶቻችን በሆደ ሰፊነት በትዕግስት በስክነት ነገሮች እንዲፈቱ እንደሚፈልጉና ልማቱን ምንም እንቅፋት እንዲፈጠርበት እንደማይፈልጉ ጠንቅቀን እናውቃለን " ሲል የገለፀው ኮማንድ ፖስቱ " መንግስት ህግ ለማስከበር የተደራጀ ኃይል እና ዝግጅት ቢኖረውም ከተማችን ነገሮች በሰከነ መንገድ በውይይት እንደፈቱ ከመፈለግ ታግሰናል። " ብሏል።
የፀጥታ ኮማንድ ፖስቱ " ዋናው ችግር ከሌላ ቦታ በመጡ ኃይሎች አስተባባሪነት እንጂ በከተማው ህዝብ እንዳልሆነ ህዝባችን ልብ ሊል ይገባል " ብሏል።
የደሴ ከተማ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት " ከሌላ ቦታ መጡ " ያላቸው ኃይሎች እነማን እነድሆኑና ከየት እንደመጡ ባወጣው መግለጫ ያለው ነገር የለም / ማብራሪያም አልሰጠም።
@tikvahethiopia

የደሴ ፖሊስ መምሪያ ፤ በውሸት " ታግቻለሁ " በማለት ቤተሰቦቹን 500 መቶ ሺህ ብር የጠየቀ ግለሰብ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
ሳይታገት ታግቻለሁ በማለት ቤተሰቦቹን 500 መቶ ሽ ብር የጠየቀው ግለሰብ አልጋ ቤት ውስጥ ነው በቁጥጥር ስር የዋለው።
ተጠርጣሪው ግለሰብ ከደቡብ ወሎ ዞን ከመካነሰላም ወደ ደሴ በመምጣት ደሴ ከተማ ቧንቧ ውሀ ክፍለ ከተማ በ " ካራ ጉቱ " ከሚባለው አካባቢ ጫካ ውስጥ በመግባት ከጓደኛው ጋር በመመካከር ጓደኛው የታገተ በማስመሰል እራሱን በገመድ ዛፍ ጋር በማሰር ፎቶውን ለቤተሰቦቹ በመላክና በስልክ 500 መቶ ሽ ብር ላኩልኝ በማለት ይነግራቸዋል።
ቤተሰቦቹም ደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ 2ኛ/ዋ/ፖ/ጣቢያ ያመለክታሉ።
ፖሊስ ባደረገው ክትትል ግለሰቡ ታግቻለሁ እያለ ሲያወራና ቤተሰቦቹንና የአካባቢውን ሰው እያስጨነቀ እያለ ከሌሊቱ 07:00 ስዓት በህብረተሰቡ ጥቆማ መነኸሪያ አካባቢ አልጋ ቤት ውስጥ ከወንጀል ተባባሪዎቹ ጋር በቁጥጥር ስር ሊያውለው ችሏል።
መረጃው የደሴ ኮሚኒኬሽን ነው።

ከደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ህዝብ መኃል በሚገኘው በሆስፒታሉ የቆሻሻ ማስወገጃ ምክንያት እየተሰቃቁ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ቆሻሻው በሚወገድበት ጊዜ እስከ ቤታቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ይህ ሁኔታ የህፃናት ልጆቻቸውን ጤና እንዲሁም የራሳቸውን ጤና አደጋ ላይ እንደጣለውና እስከ ዛሬ ድረስ በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ለሆስፒታሉ ቢያቀርቡም መፍትሄ እንዳላገኙ ገልጸዋል።
ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪዎች ከህፃናት ልጆቻቸው ጤና የሚበልጥ ነገር ባለመኖሩ ላሉበት ቦታ የሚመጥናቸውን ካሳ ካገኙ ቦታውን ለመልቀቅ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

#ደሴ ከደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ህዝብ መኃል በሚገኘው በሆስፒታሉ የቆሻሻ ማስወገጃ ምክንያት እየተሰቃቁ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ቆሻሻው በሚወገድበት ጊዜ እስከ ቤታቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል። ይህ ሁኔታ የህፃናት ልጆቻቸውን ጤና እንዲሁም የራሳቸውን ጤና አደጋ ላይ እንደጣለውና እስከ ዛሬ ድረስ በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ለሆስፒታሉ ቢያቀርቡም መፍትሄ እንዳላገኙ ገልጸዋል።…
#ደሴ
“ አንድ ቀን ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ከአካባቢ ብክለት ነጻ እንዲሆኑ ፣ ከቦታው እንዲነሱ የከተማ አስተዳደርን ውሳኔ ነው የምንጠብቀው ” - ደሴ ሆስፒታል
በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ፣ በሆስፒታሉ በኩል የሚቃጠለው ቆሻሻ ወደ ቤታቸው እየገባ እንደተቸገሩ ፣ መጀመሪያ ዝም ብሎ ሜዳ ላይ ሲቃጠል እንደነበር ፣ ዘመናዊ ማስወገጃ ከተሰራ በኋላ ግን ሙሉ ወደ ግቢዎች ውስጥ እንደሚገባ ፣ በተደጋጋሚ ለችግሩ መፍትሄ ቢጠይቁም መፍትሄ እንዳላገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል።
መንደሮቹ በተለይም ህፃናት ልጆች ያሉባቸው እንደሆኑ የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ፣ አሁን ባሉበት ሁኔታ ከመኖር ለቤታቸው የሚመጥን ካሳ ከተከፈላቸው ቦታውን ለቀው መሄድም እንደሚሻላቸው ገልጸዋል።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት #ቪዲዮም በቃጠሎው ወቅት ቆሻሻው ወደ ቤት እንደሚገባ ያስገነዝባል።
ነዋሪዎቹ ላነሱት ቅሬታ ምን ምላሽ እንዳላቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የሆስፒታሉ ባለስልጣን ፤ “ አሁን ያ ሁሉ አልፎ በዘመናዊ መንገድ ተሰርቶ፣ ሕጋዊ ማስወገጃ ተሰርቶለት፣ ድሮ ከነበረው ችግር የወጣበት ቀን ነው ” ብለው፣ “ ከነበረው ችግር ወጣ ነው እንጂ ችግሩ ብሶ ቀጥሏል አልልም ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
“ በእርግጥ #ከሕዝብ_መኖሪያ ሊወጣ ተቋሙ ግድ ነው። አሁን ግን ያለው የቆሻሻ አወጋገድ በአዎሮፓ ህብረት እና በፈረንሳይ መንግሥት ተደግፎ Almost ሰባት ወሩ ከነሐሴ መጨረሻ ጀምሮ ዘመናዊ የሆነ፣ ስታንዳርዱን የጠበቀ ማቃጠያ ተሰርቶለታል ” ነው ያሉት።
እኚሁ ባለስልጣን አክለውም ፣ “ ግን ከሰው መሀል ነው። ያ በሕጋዊ መንገድ ሲቃጠል እንደድሮው እንኳ ብናኝ እንኳ አያርፍባቸውም። ጭሱ ግን ሊሸት ይችላል ” ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ዘመናዊ ማቀጠያ ቢሰራም ቆሻሻው እየገባ መሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ባቀረቡት መሠረት ማብራሪያ እንዲሰጡ ለባለስልጣኗ ጥያቄ አቅርቧል።
እሳቸውም ፤ “ ጭሱ ታካሚንም ይረብሻል፣ ከሕዝብ መሀል መሆናችን ነውና ዋናው ትልቁ ችግር። ጭሱማ እንዴት ይቀራል ? ተኔሬተር ነውኮ ግን የሚጨሰው ” ነው ያሉት።
“ እነዚህ አሁን የሚጨስባቸው ጠቅላላ በካዳስከርና በከተማ ማስተር ፕላን የሆስፒታሉ ቦታዎች ናቸው ” ብለው ፣ “ አንድ ቀን ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ከአካባቢ ብክለት ነጻ እንዲሆኑ፣ ከቦታው እንዲነሱ የከተማ አስተዳደርን ውሳኔ ነው የምንጠብቀው ፣ እንጂ አሁን ላይ እጅግ የተሻለ ነገር ነው ያለው ” ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም፣ “ ለምን ብትል በጣም ብዙ ተሰቃይተው አልፈዋል፣ ከዚህ አሁን ካለው በላይ። ግን ከጎኑ ያለው ሰው አይሸተውም አልልህም። ግን ከፍታው ከአራት ሜትር በላይ ሆኖ፣ ከአምስት፣ ከስድስት ሜትር በላይ ከፍ ብሎ የሚጨስ የተሰራበት ዘመን ላይ ነው ያለነው ” ብለዋል።
“ አሁን ላይ ራሱ ሞዲፋይ አለው ተነሬተሩ። የተሰራው ማቃጠያ #ሞዲፋይ አድርገው አሁንም እዛው ላይ የሰሩት ከፍታውን ካለው ጨምረው ሊሰሩት እያሰቡ ነው። በቅርብ ቀንም ይሰራል። ሁለተኛ ደግሞ ከውጪ ያልገባ ጭስ አልባ ማቃጠያ ማሽን አለን። በቅርብ ጊዜ (ከወር በኋላ) ይደርሳል። ብዙ ነገሮችን የሚቀንስልን ” ሲሉም ተናግረዋል።
ደሴ ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ በርካታ ነዋሪዎች ግን ፤ በሆስፒታሉ የቆሻሻ ማስወገጃ በየዕለቱ ስቃያቸውን እያዩ እንደሆነ ፣ ከምንም በላይ ደግሞ የትንንሽ ልጆቻቸው ጤና አደጋ ላይ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርቧል።
#TikvahFamilyAddisAbaba