#OFC #OLF
ቀጣይ በሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ላይ የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከእያንዳንዳቸው 50 በመቶ ተወካዮችን ይዘው ለመቅረብ እየሰሩ መሆኑ ተሰምቷል።
የኦፌኮ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከሰሞኑን ከ " ሪፖርተር ጋዜጣ " ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።
በዚህ ቃለ ምልልስ ፓርቲያቸው በቀጣይ ለሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ ምን አይነት ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።
ፕ/ር መረራ ፤ መንግሥት አሁን ላይ እየሄደበት ባለው መንገድ ወደፊት ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ በኢትዮጵያ ይደረጋል የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልጻዋል።
ያም ሆኖ ግን ለምርጫው ከኦነግ ጋር ስምምነት እንዳላቸው ጠቁመዋል።
፣ ከእኛ ሃምሳ በመቶ ከእነሱ ሃምሳ በመቶ ተወካዮችን አዘጋጅተን በምርጫ ለመምጣት ዕቅድ አለን፡፡ " ያሉት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲያ " ከኦነግ ጋር በትብብር ለመሥራት ተስማምተናል " ሲሉ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ፤ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ እንዲሁም የኢህአዴግን ስርዓት በመጣል ውስጥ ከፍተኛ ተፅእኖ ያላቸው የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ በምን ምክንያት እንደጠፉ የተጠየቁት ፕ/ር መረራ ምላሽ ሰጥተዋል።
" እኔ እንደምገምተው የፖለቲካ ምኅዳሩ አልተመቸውም፡፡ " ያሉት ፕ/ር መረራ " የፖለቲካው ምኅዳር ጠቦበታል፣ በዚህ በኩልም እሳት ነው ፤ በዛም እሳት ነው መንግሥትም እሳት ሆነበት " ሲሉ መልሰዋል።
ከዚህ በተጨማሪ አቶ ጃዋርን ጨምሮ እሳቸው እና የሚመሩት ፓርቲ ከመንግሥት ጋር አብሮ እየሰራ ነው የሚባለው ወሬ ሀሰት መሆኑና ከመንግሥት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ፕ/ር መረራ ጉዲና ለጋዜጣው ተናግረዋል።
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ፦
- አሁን ላይ ዝምታ መርጠው ስለጠፉበት ሁኔታ፤
- ስለ ኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ፤
- በኦሮሚያ ክልል ስላለው ቀውስ እና ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ቀውስ መፍትሄ፤
- ስለ ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እና የመንግስት ድርድር፤
- ስለ ህገመንግስት መሻሻል ፤
- በኦሮሞ እና በአማራ ፖለቲካ ስላለው ሁኔታ፤
- ስለ ሀገሪቱ ኢኮኖሚ እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ተጠይቀው ምላሽ የሰጡበት የ " ሪፖርተር ጋዜጣ " ቃለ ምልልስ በዚህ ይገኛል ፦ https://www.ethiopianreporter.com/
@tikvahethiopia

#OFC
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና አሜሪካ መግባታቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ፕሮፌሰሩ በአሜሪካ ለአንድ ወር እንደሚቆዩ የፓርቲው ዓለም አቀፍ ድጋፍ ቡድን አሳውቋል።
በአሜሪካ ቆይታቸው ፦
- ወደ ተለያዩ ግዛቶች በማቅናት ከኦሮሞ ተወላጅ ዳያስፖራዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ።
- ይፋዊ / መደበኛ ባልሆኑ የተለያዩ ግብዣዎች ላይ በመገኘት ከወዳጆቻቸው እና ከፓርቲው ደጋፊዎች ጋር ይነጋገራሉ።
- በኦፌኮ-ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን አዘጋጅትነት የሚካሄድ ቨርቹዋል ኮንፈረንስ በመምራት ከዓለም አቀፍ የኦሮሞ ተወላጅ ዲያስፖራዎች ጋር በመገናኘት በወቅታዊ ክልላዊ ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ፤ በወቅታዊ የኢትዮጵያ አሳሳቢ ችግሮች ላይ እንዲሁም የኦሮሞ ህዝብ ትግል አሁናዊና ቀጣይ ሁኔታን በተመለከተ ይመክራሉ።
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ወደ አሜሪካ ሀገር ያቀኑት የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ " በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ሆነ በግል በነጻነት ለመኖር " አሳሳቢ በመሆኑ በሄዱበት አሜሪካ ሀገር ጥገኝነት መጠየቃቸውን ካሳወቁ ከ12 ቀናት በኃላ ነው።
ፎቶ - ፋይል

TIKVAH-ETHIOPIA
#OROMIA #PEACE " የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ... ለሰላም ክፍት ነን ድርድሮችም እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም ቢሆን ያሉ ችግሮች #በሰላም እንዲፈቱ መንግሥት #ለድርድር ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል። የክልሉ መንግሥት አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በአዲስ አበባ…
ኦነግ እና ኦፌኮ በውይይቱ ተገኝተው ነበር ?
#አልተገኙም
" ውይይት መደረጉን የሰማነው እራሱ በሚዲያ ነው " - ኦፌኮ
በኦሮሚያ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ከተባሉ ፓርቲዎች ጋር የክልሉ መንግሥት አድርጎታል በተባለው ውይይት ላይ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) #አልተሳተፉም።
የኦፌኮ ዋና ፀሀፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ ለቪኦኤ ሬድዮ ፥ " ውይይቱ መደረጉን የሰማነው ከብዙሃን መገናኛ ነው። እንደ ግለሰብ ይሁን እንደ ተቋም የደረሰን ጥሪ የለም የኮሚኒኬሽን ክፍተቱ ከማን በኩል እንደሆነ አላውቅም " ብለዋል።
ኦፌኮ የክልሉ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ቢሆንም ባለው ቅሬታ ሙሉ ተሳትፎ እያደረገ እንዳልሆነ ገልጸዋል።
አቶ ጥሩነህ ፤ ለውይይት በም/ቤት ይሁን በመንግስት ጥሪ አልደረሰንም ብለዋል።
የኦነግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለሚ ገመቹ በበኩላቸው ፤ ፓርቲያቸው በውይይቱ #እንዳልተሳተፈ ገልጸዋል።
" ለውይይቱ ጥሪ ሊደረግ ይችላል እኛ ግን የምንፈልገው በአንድ አካል አቅራቢነት የሚደረገውን ውይይት ሳይሆን ሁሉም በእኩልነት የሚሳተፍበትን ውይይት ነው። " ብለዋል።
" የምንፈልገው አንድ ሀገርን የሚያስተዳደር መንግሥት በሚሰጥህ ቦታ ተወስኖ መወያየት ሳይሆን እራሳችንን የመፍትሄ አካል ነን ብለን የምናይ አካላት በአንድ ላይ ሆነን በተመሳሳይ ድምጽ ተወያይተን ዘላቂ መፍትሄ የምናስቀምጥበት ካልሆነ ኦነግ በአንድ አካል ጥሪ የሚሳተፍበት መድረክ አይኖርም " ሲሉ ተናግረዋል።
የኦሮሞን ችግር የሚፈተው በእውነታ ላይ የተሰመሰረተ አካታች ውይይት እንደሆነ የገለጹት አቶ ለሚ ፤ ውይይት ሂደቱን ጠብቆ አካታች በሆነ መልኩ መከናወን አለበት አሁን ያለው አካሄድ ሂደቱን ያልጠበቀ ቅንነት የሌለው በአንድ አካል ብቻ ተጎትቶ እየሄደ ያለ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ም/ቤት ሰብሳቢ እና የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት አቶ ሰለሞን ታፈሰ ኦነግ እና ኦፌኮ ከውይይት መቅረታቸውን አረጋግጠዋል።
" በድረገጻችን ላይ ለቀናል፣ በዋትስአፕ ላይ ተለቋል። እንደምንሄድ ኮሚቴው ሲወስን ተለቋል። በአካል አነጋሬያለሁ የሚመለከታቸውን ኦሮሚያ የኢትዮጵያ እምብርት ናት እናተ ስለሚመለከታችሁ ለምን አብረን አንሄድም? ብዬ ነግሬያቸዋለሁ። ተጋብዘዋልም " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
#Ethiopia
#Oromia #VOA

#OFC #Ethiopia
" በአንድ ፓርቲ ፍላጎትና ሙሉ ቁጥጥር በሚመራ መንገድ የ120 ሚሊዮን ህዝብ ቁመት የሚሆን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በፍጹም አይፈጠርም !! " - ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና (ለቪኦኤ ሬድዮ ከሰጡት ቃል) ፦
" ዋና የኢትዮጵያ ችግር ፈጣሪ መንግሥት ነው። ይሄ ምንም ጥያቄ የለውም።
ከፖለቲካ ኃይሎች ጋር ሆነን ፣ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡም ጋር ሆነን ሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያላደረግነው ነገር የለም።
ዋናው ጉዳይ ስልጣን የያዘው ቡድን ሀቀኛ ፍትሃዊ የሚባለውን ነገር በጭራሽ አይፈልገውም።
' ስልጣን እኛ እጅ ነው ' ተንበርከኩና እኛ ጋር ግቡ ወይም የስልጣን ፍርፋሪ ኑና ውሰዱ ካልሆነ በስተቀር የኢትዮጵያ ህዝብ ከመገዳደል ፖለቲካ ወደ መደራደር ፖለቲካ እንዲገባ አይፈልግም።
ችግሩ ይሄ ነው በአንድ እጅ ማጨብጨብ አይቻልም።
እኛ የምንችለውን ያክል ይሄ ሀገር መሸጋገር የሚችለው ፣ የተሳካ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር መምጣት የሚችለው ፣ የተሳካ ሰላም እና መረጋጋት መምጣት የሚችለው ሁሉም የኢትዮጵያ ኃይሎች የተሳተፉበት ፦
- ብሔራዊ እርቅ
- ብሔራዊ ድርድር
- ብሔራዊ ምክክር ሲደረግ ነው እያልን ስንጠይቅ ነበር።
ፖለቲካ እስከሚገባን ድረስ አሁን እየተገፋ ባለበት መንገድ 3 ነገሮች በኢትዮጵያ ምድር መሆን አይችሉም።
1ኛ. ሀቀኛ ሰላምና መረጋጋት አይመጣም ፥ ሰላምና መረጋጋት አሁን እየገፉ ባሉበት መንገድ መምጣት አይችልም። እኛም ኖርን አልኖርን !
2ኛ. በኢትዮጵያ ምድር ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ፣ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር ፣ ሀቀኛ ፌዴራላዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ፣ በነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ስልጣን ላይ የሚወጣ መንግሥት ፣ የህዝቡን ይሁንታ ካጣ ከስልጣን የሚወርድ መንግሥት መፍጠር አይቻልም።
3ኛ. በአንድ ፓርቲ ፍላጎት ፣ ሙሉ ቁጥጥር በሚመራ መንገድ የ120 ሚሊዮን ህዝብ ቁመት የሚሆን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በፍጹም አይፈጠርም።
አንድ ቀን እነሱም ሰምተው ፤ ችግሩም ደግሞ አስተምሯቸው መስመር ሊይዝ ይችላል።
እኛ እንሞክር ነበር አሁንም ያንኑ ህጋዊ እና ሰላማዊ ትግላችንን እንቀጥላለን።
በሀገሪቱ ግጭት ያባባሰው ስር የሰደደው የፖለቲካ ችግር የሚፈታው በፖለቲካዊ ንግግር ብቻ ነው። "
#OromoFederalistCongress

#OLF " ለ4 ዓመታት ያህል በግፍ ታስረው የቆዩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራሮች ከእስር መለቀቃቸውን " የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራር አቶ ጃዋር መሀመድ አወደሱ። ፖለቲከኛው ፥ በአመራሮቹ መፈታት እጅጉን እንደተደሰቱ ገልጸዋል። " መንግስት የቀሩትን የፖለቲካ እስረኞች በመፍታት የትጥቅ ግጭቶችን ሁሉ በውይይት እንዲቆሙ በማድረግ ይህንን በጎ እርምጃ ማሳደግ ይኖርበታል " ብለዋል።…
#OLF #OFC
የኦፌኮ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጡሩነህ ገምታ ከእስር የተፈቱትን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራሮች በአካል በማግኘት " እንኳን በሰላም ከእስር ተፈታችሁ ! " በማለት በኦፌኮ ስም ደስታቸውን ገልፀዋል።
አቶ ጥሩነህ " በተለያዩ እስር ቤቶች በህገ ወጥ መንገድ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ደጋግመን እየጠየቅን ነበር " ብለዋል።
" የኦሮሞ ታጋዮች አቋምና ድጋፍ እንዲሁም በኦፌኮ እና በOLF ድርጅቶች መካከል ያለው ትብብር ለአገር ድል ወሳኝ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

“ አሁንም ቢሆን ሀገራዊ ምክክሩ በሚሄድበት አቅጣጫ እርካታ የለንም ” - ኦፌኮ
ከዚህ ቀደም በምክክሩ እንደማይሳተው ገልጾ የነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ (ኦፌኮ) አሁንም እየተሳተፈ እንዳልሆነ፣ ኮሚሽኑ በሚሄድበት አቅጣጫ እርካታ እንደሌለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል።
ፓርቲው ከዚህ ቀደም በሀገራዊ ምክክሩ እንዲሳተፍ ቢጋበዝም በምክክሩ እንዳልተገኘ አስታውሷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሥራውን መቀጠሉን እየገለጸ ነው፤ አሁንስ ፓርቲው ከኮሚሽኑ ጋር ተቀራርቦ ለመስራት አላሰበም ? ከምክክሩ የወጣበት ምክንያትስ ምንድን ነው ? ምላሽስ አላገኘም ? ሲል ጥያቄ አቅቧል።
ፓርቲው ምን ምላሽ ሰጠ ?
“ በእርግጥ ከዚህ ቀደምም ጥሪ ተደርጎልን ነበር። ችግሩ ከዝግጅት ጀምሮ ያለው እንቅስቀሴ አሳታፊ አልነበረም።
ሲጀመር የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ተጠሪነቱ 'ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ይሆናል’ ተባለ፣ ከዚያ ተመልሶ ‘ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሆናል’ ተባለ።
ይሄ ልዩነቱም አልታየንም። ምክንያቱም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም በገዢው ፓርቲ የተሞላ ስለሆነ ገልተኛነቱ ያን ያክል አስተማማኝ እንዳልሆነ ነው የምንረዳው።
ምክንያቱም የሌሎች ተሳትፎ ወይ የለም ወይ በጣም አናሳ ነው፤ ኢንሲግኒፊካንት የሚባል ደረጃ ማለት ነው።
የኛ ሀሳብ ፓለቲካዊ ውይይቶች በፓለቲካ ኃይሎች መካከል መካሄድ ይኖርባቸዋል፣ ሁሉንም ኃይሎች አካታች መሆን አለበት የሚል ነው።
እኛ ሕዝብ ማወያየትን አንጠላም ወይም አናናንቅም ነገር ግን ከሕዝብ ጋር ከመድረሱ በፊት ወይም እየደረሰም እያለ ሌሎች የፓለቲካ ኃይሎች ሊነጋገሩበትና ሊፈቷቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ።
ለምሳሌ በተለያዩ አካባቢዎች የኛ ፅሕፈት ቤቶች ተዘግተው ባሉበት፣ አባሎቻችንን ሰብስበን ማነጋገር ባልቻልንበት ሁኔታ፣ ለሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ መፍጠር የሚባለው ነገር ውስጥ መሳተፍ አስፈላጊ አይደለም።
እንደገናም ጦርነት እየተካሄደ ሀገራዊ ምክክር ብሎ ነገር ምንድን ነው? ይሄ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነገር ነው።
ይሄን እርስ በእርስ የሚጋጨውን ነገር የሆነ ጋፕ ስጡት፣ ለመነጋገር፣ ለመወያየት እድል ይሰጠው አገር እየተጠበቀ አገር ቢነጋገርበት ጥሩ ይሆናል በሚል ጥያቄ አቅርበን ነበር።
ይሄን የኛን ሀሳብና ጥያቄ ምንም ከዚህ ግባ አላሉትም። ምናልበት የተሻለ ነገር ቢያመጡ እኛም አጨብጭበን እንቀበላቸዋለንና እንዲሄዱ ነው የተውናቸው።
ኦፌኮ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ፓርቲዎች አሉ እንደዚህ ያደረጉ። ጊዜና መነጋገር የሚፈልጉ፣ አንድ ወገንን ብቻ ተጠያቂ ከማድረግ እንድንቆጠብ የሚያደርጉ ነገሮች አሉ።
ስለዚህ ነገሮቹ መፍትሄ ካላገኙና የተወሰነ አቅጣጫ ካልተቀመጠላቸው እንዲያው ለመሳተፍ ተብሎ የምንሳተፍበት ምክንያት አይኖርም።
አሁንም ቢሆን ሀገራዊ ምክክሩ በሚሄድበት አቅጣጫ እርካታ የለንም። እርካታ ቢኖረንና ብንሳተፍበት ጥሩ ነበር ” ብሏል።
ለቀረበበት ትችት ምላሽ እንዲሰጥ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ ለጊዜው በተደጋጋሚ ስብሰባ ላይ መሆኑን በመግለጹ ምላሹን እንደሰጠ የሚቀርብ ይሆናል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA