TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#SNNPRS #SouthWestEthiopia

የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የደቡብ ክልል እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑ ዛሬ ተገልጿል።

በሁለቱ ክልሎች ውሳኔ መሰረት የማለፊያ ነጥብ ፦

👉 ለወንዶች 41፣
👉 ለሴቶች 40 እና
👉 ለአይነ ስውራን 39 ሆኖ ተወስኗል።

በዚህ መሰረት ፦ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁለቱም ክልሎች ለፈተና ከተቀመጡ ከ257 ሺህ በላይ ተማሪዎች 187 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል የሚያሳልፋቸውን ውጤት አምጥተዋል።

ለፈተና ከተቀመጠው አጠቃላይ ተማሪ ቁጥር ሲታይ ከ73 በመቶ በላይ ተማሪዎች አልፈዋል።

በተለየ መልኩ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በአሉታዊ ጫና ውስጥ ሆነው የተማሩና ለፈተና የተቀመጡ የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎችን ውጤት በተለየ መልኩ ታይቷታ።

በዚህም መሰረት ፦

👉 ለወንዶች 39፣
👉 ለሴቶች 38 እና
👉 ለአይነ ስውራን 37 ሆኖ ተወስኗል።

የሁለቱ ክልሎች ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጀምሮ መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።

የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎች ግን ውጤታቸው በእጅ የሚሰራ በመሆኑ የ1 ሳምንት ጊዜ ዘግይቶ ይደርሳል እስከዛው በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት ተላልፏል።

#ENA

@tikvahethiopia
ሰሞነኛው ዝናብ ...

በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ከሰሞኑን እየጣለ ያለው ዝናብ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ፥ ጎፋ ዞን ዑባ-ደብረፀሃይ ወረዳ ዛባ ቀበሌ በጣለው ከባድ ዝናብ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ 21 ሰዎች መሞታቸውን ለማወቅ ተችሏል። በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

በህይወት የተረፉ ዜጎ በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲጠለሉ የተደረገ ሲሆን ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማፈላለግ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መገባቱ ተሰምቷል።

ተጎጂ ወገኖችን ለመደገፍም በዞኑ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ማቋቋሚያ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000511561276 ላይ ድጋፍ እንዲደረግ ተጠይቋል።

#Amhara

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ 02 አዋተል ቀበሌ ሚያዚያ 27/2015 ዓ.ም ምሽት ለተከታታይ 30 ደቂቃ የጣለው በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በእንስሳት፣ በሰብልና በመኖሪያ ቤቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ከ37 ሄክታር መሬት በላይ የደረሱ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል።

#Gambella

በጋምቤላ ክልል ፤ በዲማ ወረዳና አጎራባች ወረዳዎች ከሚያዝያ 25 /2015 ዓ.ም ጀምሮ እየጣለ ባለው ሃይለኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው ጎርፍ በሚሊየን የሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

የጎርፍ አደጋው እስካሁን ባለው መረጃ በወረዳው ከ70 በላይ መኖሪያ ቤቶች በውሃ ያጥለቀለቀ ሲሆን በሰብል ላይም ጉዳት አድርሷል።

ጎርፉ በዲማ ከተማ ወንዝ ዳር የነበረውን የከተማ ንፁህ መጠጥ ውሃ መሳቢያ ጀነሬተርና ፖምፕ ግንብ ቤቱን ጨምሮ በሚሊዮን በሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ታውቋል።

በዚህም ችግር ሳቢያ የከተማው ንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት መቆሙ ተነግሯል።

በተመሳሳይ በዲፕ (መርከስ) ቀበሌ የሚገኘው የእኩጉ ስደተኞች መጠለያ ጣብያና የአካባቢው ማህበረሰብ የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት የሚሰጡ ሁለት መሳቢያ ጀነሬተሮች በጎርፍ መወሰዱ ታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም የአኮቦ ወንዝ እስከጫፉ ድረስ በመሙላቱ ዲማ ወረዳን ጨምሮ ሁለት አጎራባች ወረዳዎች የሚያገናኝ የአኮቦ ብረት ድልድይ ላይ ጉዳት ደርሷል።

በደረሰው አደጋ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች ለማገዝ የክልሉ መንግሥትን ጨምሮ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃ ምንጮች ፦ የጎፋ ዞን ፣ የለገሂዳ እና የዲማ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ናቸው።

@tikvahethiopia