TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በመታወቂያ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ እንደተወሰነላቸው ጠበቃቸው ተናግሩ። በ2013 በተካሄደው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በባህርዳር ከተማ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፓርቲን ወክለው ተወዳድረው የተመረጡት እና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጥር 22 ቀን 2016 ዓ/ም ምሽት በጸጥታ ኃይሎች ከቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ ታስረው ቆይተዋል።…
አብዲ ኢሌ ከእስር ተፈቱ።

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) ከእስር መፈታታቸውን ጠበቃቸው ተናገሩ።

ከ6 ዓመት በፊት ነሐሴ 21/2010 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለው አስካሁን በእስር ላይ የቆዩት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር ከእስር የተለቀቁት ዐቃቤ ሕግ ክሱን በማንሳቱ መሆኑን ጠበቃቸው ገልጸዋል።

ጠበቃ እና የሕግ አማካሪው እስክንድር ገዛኸኝ ፤ የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክሳቸው ተነስቶ የተለቀቁት ዛሬ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም. መሆኑን አመልክተዋል።

ከአቶ አብዲ በተጨማሪም በተመሳሳይ በእሳቸው የክስ መዝገብ ጉዳያቸው ሲታይ የነበሩ የሌሎችም ተከሳሾች ክስ ተቋርጦ መለቀቃቸውን ጠበቃው ተናግረዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው ከዓመታት በፊት ጀምሮ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ሲመሩ የነበሩት አቶ አብዲ፣ በክልሉ ውስጥ ከተፈጸሙ በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ግድያዎች እና የመንግሥት ሀብት ብክነት ጋር በተያያዘ ክስ ይቀርብባቸዋል።

በቀድሞው ርዕሰ መስተዳደር ላይ ከቀረቡባቸው ክሶች መካከልም በ2010 ሰኔ እና ሐምሌ ወራት ውስጥ “በሶማሌ ክልል የእርስ በርስ ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ በማሰብ ‘ሄጎ’ በሚል ስያሜ የሚታወቅ ወጣቶች ቡድን አደራጅተዋል” የሚል ይገኝበታል።

በወቅቱ ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸው፣ ንብረት እና አብያተ ክርስቲያናት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል።

ዐቃቤ ሕግም ባቀረበው የክስ ዝርዝር በተከሰተው ግጭት ምክንያት ፦
* 59 ሰዎች #መገደላቸውን
* ከ250 በላይ መቁሰላቸውን
* በመንግሥት፣ በግል እና በሃይማኖት ተቋማት ንብረት ላይ ውድመት መድረሱን ገልጾ ነበር።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ነው።

ፎቶ፦ ፋይል

@tikvahethiopia