TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ለሰሜን ኢትዮጵያ ችግር ሰላማዊ የሆነ መፍትሄ ለመፈለግ እና ችግሩን በሰላማዊ ድርድር ለመቋጨት በፌዴራሉ መንግስት የተቋቋመው " የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ " ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር። በመግለጫው ላይ ከተጠቀሱ #ወሳኝ ነጥቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል ፦ • ኮሚቴው ባደረገው ውይይት የትግራይ፣ የአፋር፣ የአማራ ክልል አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑ ዜጎች በእለት ተእለት ኑሮዋችው ላይ…
#GoE

የጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢልለኔ ስዩም ዛሬ በሰጡት መግለጫ የተለያዩ ጉዳዮችን አስንተዋል።

ከካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ በሰላም አመራጭ ኮሚቴ በኩል ስለ ተዘጋጀው የሰላም ረቂቅ ሰነድ ነው።

በዚህም የሰላም ረቂቅ ሰነዱ በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ለተከሰተው ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ለመስጠት፤ በመጪዎቹ ሳምንታት የተኩስ አቁም እንዲደረስ፣ የሰላም ውይይት እንዲሁም ሌሎች በእንጥልጥል የቀሩ ጉዳዮች ደግሞ በብሄራዊ ምክክሩ እንዲዳሰሱ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል።

ሰነዱ መንግስት ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ በሚፈታበት ሁኔታ ላይ እያደረገ ያለውን ከፍተኛ ጥረት አመላካች ነው ሲሉ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል በትግራይ ክልል መላሶ ግንባታ እና መሰረታዊ ድጋፎች ላይ መንግስት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

መንግስት ባለሙያ በመላክም ሆነ እዛው ያለውን የሰው ኃይል በመጠቀም በክልሉ መሰረታዊ የህዝብ አገልግሎት ለመመለስ ፍላጎት እንዳለውና ለዚህም ደግሞ አንዳንድ በመሬት ላይ ያሉ ሁኔታዎች እንዲሻሻሉ እንደሚፈልግ ገልፀዋል፡፡

መንግስት በአፍሪካ ህብረት መሪነት በማንኛውም ጊዜና ቦታ የሰላም ድርድር ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ቢልለኔ በዛሬው መግለጫቸው ከአማራ ክልል ወደ አ/አ በሚደረገው ጉዞ ተጓዦች ላይ ስለሚደርስ እንግልት ተጠይቀው መልሰዋል።

በዚህም፤ "ህወሃት በአንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢዎች ወረራ በፈፀመበት ወቅት የዘረፋቸውን የመንግስት ማህተሞች በመጠቀም ሀሰተኛ መታወቂያ በማሳተም ለእኩይ ተግባሩ እያዋለ በመሆኑ ይህንን ድርጊቱን ለመግታትና ተከታትሎ ለመያዝ በተወሰደ እርምጃ የተፈጠረ ነው" ብለዋል።

አሁን ላይ ግን የትራንስፖርት አገልግሎቱ ወደ ቀድሞ ሁኔታው መመለሱን ለጋዜጠኞች መናገራቸውን ከኤፍ ቢ ሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#ፊንላንድ

ከወደ ፊንላንድ የተሰማ ...

በእድሜ ወጣት የሆኑት የ36 ዓመቷ የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በአንድ ፓርቲ ላይ ሲጨፍሩ የሚያሳይ ቪድዮ ሾልኮ ከተለቀቀባቸው በኃላ ከፍተኛ ትችት እየደረሰባቸው ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን ሾልኮ በወጣው ቪድዮ ከዝነኛ ፊላንዳውያን ጓደኞቻቸው ጋር ሲጨፍሩ እና ሲዘፍኑ ታይተዋል።

ከዚህም በኃላ የጠቅላይ ሚኒስትሯን ድርጊት በተለይ ከተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ዘንድ ከፍተኛ ትችት አስከትሎባቸዋል።

አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትሯ " የአደንዛዥ እጽ ምረመራ ይደረግላቸው " ሲሉ ጠይቀዋል። ሌሎች ደግሞ ብዙ ሀገራዊ ጉዳይ እያለ ስለጭፈራ ማውራቱ ጊዜው አይደለም ሲሉ ተችተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ግን " አደንዛዥ እጽ አልወሰድኩም " ያሉ ሲሆን አልኮል መጠጣታቸውን እና በሙሉ ኃይላቸው በፓርቲው ላይ መጨፈራቸውን ግን ተናግረዋል።

ቪዲዮ እየተቀረጹ መሆኑን እንደሚያውቁ የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሯ " ለሕዝብ ዕይታ መቅረቡ ግን ያበሳጫል " ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

" ደንሻለሁ፣ ዘፍኛለሁ እንዲሁም ፓርቲ አድርጊያለሁ ሁሉም ሕጋዊ ናቸው። እኔ ወይም በአካባቢዬ አደንዛዥ እጽ በሚወሰድበት ቦታ ሆኜ አላውቅም " ሲሉም አክለዋል።

በተጨማሪ " የቤተሰብ ሕይወት አለኝ፣ የሥራ ሕይወት አለኝ፣ እንዲሁም ከጓደኞቼ ጋር የማሳለፈው ነጻ የምሆንበት ጊዜ አለኝ። በእኔ የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ከሌሎች ሰዎች ጋር ተመሳሳይ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

መሪን ከእ.አ.አ. 2019 መጨረሻ ጀምሮ ፊንላንድን እየመሩ ሲሆን አሁንም ድረስ ከፓርቲያቸው ጠንካራ ድጋፍ እንዳላቸው ቢቢሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
ፍትሕን በገንዘብ ያልሸጣት ምስጉን ዳኛ!

በምእራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ነሐሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 1:40 ሰዓት ላይ አንዲት ህፃንን አስገድዶ በመድፈሩ ምክንያት ተከሳሽ ተይዞ ጉዳዩ በህግ ይታያል።

በዚህን ጊዜ የተከሳሽ ወንድምና ጓደኛ መዝገቡን የሚያየውን ዳኛ በከተማው በሚገኝ ፅናት ሆቴል ይቀጥሩታል። ኃሳባቸውም ለዳኛው 10 ሺህ ብር ጉቦ በመስጠት ተከሳሽ ነጻ እንዲወጣ ማድረግ ነበር።

ዳኛውም ቀጠሮዎን አክብሮ ከቦታው ይደርሳል፥ የተከሳሹ ተባባሪዎችም ገንዘቡን አውጥተው ለዳኛው ሊሰጡት ሲሉ ዳኛዉ አስቀድሞ ለፖሊስ አሳውቆ ነበርና እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸዉ እንደሚገኝ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ያገኘነው መረጃ ያሳል።

አንዳንድ ፍትሕን በገንዘብ የሚሸጡ፣ ያስተማራቸውን ያሳደጋቸውን ማህበረሰብ እና ሀገርን በገንዘብ የሚለውጡ የፍትህ አካላት እንዳሉ ሁሉ ከላይ መረጃውን እንዳነበብነው አይነት ምስጉን የፍትህ አካላት አሉ። ማህበረሰቡን እና ሀገርን በታማኝነት የሚያገለግሉ አካላት ሊመሰገኑ ይገባል።

በእርግጥ ሁላችንም ባለበት ቦታ ኃላፊነታችንን መወጣት ፤ ታማኝነታችንን ማሳየት ፣ ለማህበረሰባችን ፣ ለሀገራችን የገባነውን ቃል ማክበር ግዴታችን እና የሚጠበቅብን ቢሆንም እንዲህ ያሉ የሚያስመሰግኑ ተግባራትን ማበረታታና ማመስገን ይገባል።

@tikvahethmagazine
ፎቶ ፦ የደብረ ታቦር በዓል በደብረታቦር ከተማ !

በየዓመቱ ነሐሴ 13 ቀን የሚከበረው የደብረታቦር (የቡሄ ) በዓል በታላቁ ደብር ደብረታቦር እየሱስ ቤተክርስቲያን ባህላዊ እና ሐይማኖታዊ ትዉፊቱን ጠብቆ ተከብሯል።

Credit : ደብረታቦር ኮሙኒኬሽን

@tikvahethiopia @tikvahethmagazine
#ETHIOPIA

8 የስኳር ፋብሪካዎች ለጨረታ ቀረቡ።

የኢትዮጵያ መንግስት የስኳር ኢንተርፕራይዞችን ወደግል ለማዛወር በወጣው ጨረታ ባለሐብቶች እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረበ።

የሀገር ውስጥ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ባለሐብቶች የስኳር ፋብሪካዎችን ወደግሉ ዘርፍ ለማዛወር በወጣው ጨረታ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

ለጨረታ የቀረቡት ፦

👉 ኦሞ ኩራዝ 1፣
👉 ኦሞ ኩራዝ 2፣
👉 ኦሞ ኩራዝ 3 ፣
👉 ኦሞ ኩራዝ 5፣
👉 አርጆ ደዴሳ፣
👉 ከሰም፣
👉 ጣና በለስ እና ተንዳሆ የስኳር ፋብሪካዎች ናቸው።

(ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)

Via Ministry of Finance ፣ FBC

@tikvahethiopia
#Gondar

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጎንደር ሊያካሂድ የነበረውን የጠቅላላ ጉባኤ ወደ አዲስ አበባ ቀይሯል።

ይህ የሆነው ጎንደር ዝግጅቷን ጨርሳ ጉባኤውን ስትጠባበቅ ነው።

ፌዴሬሽኑ ቦታ ተመቀየር ለምን ፈለገ ?

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፤ የአማራ ክልል መንግስት የስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የጠቅላላ ጉባኤ ሥራ ወደሚያከናውኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸን ሰራተኞች ስልክ በመደወል ከክልሉ ክለቦች የተላኩ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ወኪሎች ስሞች መቀየር እንዳለባቸው እና ይህንን እንዲያደርጉ ፤ ካላደረጉ ግን ጉባኤው እንዲስተጓጎል እንደሚያደርጉ በማስፈራራት ጭምር ስሜታቸውን መግለፃቸው ማረጋገጡን ገልጿል።

ጠቅላላ ጉባኤው ከጉባኤው አባላት በተጨማሪ የፊፋ እና የካፍ ታዛቢዎች የሚታደሙበት ነው ያለው ፌዴሬሽኑ ነገር ግን የክልሉ ከፍተኛ አመራር ሆነው ጉባኤው የተሳካ እንዲሆን ከፍተኛ ሥራ መሥራት ሲገባቸው ችግር እንደሚፈጥሩ መግለፃቸው የጉባኤው ውጤታማነት ላይ ስጋት እንዲያድርብን ምክንያት ሆኗል ብሏል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር እያደረገ ያለው ተግባር ፍፁም የሚያስመሰግነው ቢሆንም ፤ የክልሉ አመራር በዚህ ደረጃ ችግር ለመፍጠር እየሞከሩ በመሆኑ እና ሌሎች የእርምት እርምጃዎችን ለመውሰድ ያለው ጊዜ አጭር በመሆኑ የጉባኤውን ቦታ መቀየር ማስፈለጉንዳማስፈለጉን ፌዴሬሽኑ ገልጿል።

በዚህም ጉባኤው አዲስ አበባ ከተማ እንዲሆን መወሰኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gondar የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጎንደር ሊያካሂድ የነበረውን የጠቅላላ ጉባኤ ወደ አዲስ አበባ ቀይሯል። ይህ የሆነው ጎንደር ዝግጅቷን ጨርሳ ጉባኤውን ስትጠባበቅ ነው። ፌዴሬሽኑ ቦታ ተመቀየር ለምን ፈለገ ? የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፤ የአማራ ክልል መንግስት የስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የጠቅላላ ጉባኤ ሥራ ወደሚያከናውኑ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሸን ሰራተኞች ስልክ በመደወል…
#Gondar

" ውሳኔያችሁን በድጋሜ አጢኑት " - ጎንደር

የጎንደር ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔን #ተገቢነት_የሌለው ነው አለ ፤ ውሳኔውንም ድጋሜ እንዲያጤነው ጠይቋል።

የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በጎንደር ከተማ የፌዱሬሽኑን የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ እንደተዘጋጀ ለከተማው አስተዳደር አሳውቆ ነበር።

ነገር ግን ፌዴሬሽኑ የጉባኤ ቦታው እንዲቀየር መወሰኑን የገለፀ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ይህ ውሳኔ ተገቢነት የለውም ብሏል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2014 ዓ.ም የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤውን ከነሀሴ 21-ነሀሴ 22/2014 ዓ.ም በጎንደር ከተማ እንደሚያካሂድ በቀን 22/11/2014 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ነበር ያሳወቀው።

ፌደሬሽኑ በከተማዋ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ ካሳወቀ በኃላ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ከፌዴሬሽኑ አብይ ኮሚቴ ጋር በቅንጅት በተሳካ ሁኔታ ማከናወን መቻሉን የጎንደር ከተማ አስተደር ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ገልጿል።

ይሁን እንጅ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀው ጉባኤውን በመጠበቅ ላይ እያለ አሳማኝ ባልሆነ ምክኒያት ፌደሬሽኑ ጉባኤውን ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድበትን ቦታ ቀይሬያለሁ ሲል በቀን 12/12/2014 ዓ.ም ማሳወቁን የከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።

ፌዴሬሽኑ የወሰነው ውሳኔ #ተገቢነት_የሌለው መሆኑን የገለፀው የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፌደሬሽኑ የወሰነው ውሳኔው ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ውሳኔውን በድጋሜ ሊጤን ይገባል ብሏል።

(ጎንደር ኮሚኒኬሽን)

@tikvahethiopia
#EthiopiaAirlines🇪🇹

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ፤ ከካርቱም ወደ አዲስ አበባ ሲበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET343 አውሮፕላን ነሀሴ 9 ቀን 2014 ዓ.ም ከአዲስ አበባ አየር ትራፊክ ቁጥጥር ጋር ያለው ግንኙነት ለጊዜው ተቋርጦ እንደነበር የሚጠቁም ሪፖርት እንደደረሰው አመልክቷል።

ሆኖም ግንኙነቱ ከተመለሰ በኋላ አውሮኘላኑ በሰላም እንዳረፈ ገልጿል።

ተጨማሪ #ምርመራ እስከሚያጠናቅቅ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የበረራ ሠራተኞች ከሥራ ታግደው ይቆያሉ ብሏል።

በምርመራው ውጤት መሰረት ተገቢው የእርምት እርምጃ ይወሰዳል ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነትን ማስጠበቅ  የሁልጊዜም የመጀመሪያው ተግባሩ ሆኖ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gondar " ውሳኔያችሁን በድጋሜ አጢኑት " - ጎንደር የጎንደር ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔን #ተገቢነት_የሌለው ነው አለ ፤ ውሳኔውንም ድጋሜ እንዲያጤነው ጠይቋል። የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን በጎንደር ከተማ የፌዱሬሽኑን የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ ለማካሄድ እንደተዘጋጀ ለከተማው አስተዳደር አሳውቆ ነበር። ነገር ግን ፌዴሬሽኑ የጉባኤ ቦታው እንዲቀየር መወሰኑን የገለፀ…
" ውሳኔውን አንቀበልም " - የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የአማራ ክልል እግር ኳስ ፌደሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የጠቅላላ ጉባኤ የቦታ (ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ) ለውጥ ማድረጉን የማይቀበል መሆኑን ገልጿል።

ፌደሬሽኑ ውሃ በማይቋጥር ምክንያት ጠቅላላ ጉባኤ የሚከናወንበትን ቦታ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ መቀየሩ እንዳሳዘነውም ለፌደሬሽኑ በላከው መግለጫ አሳውቋል።

የክልሉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ጉባኤው በተያዘለት መርሃ ግብር እና በተያዘለት ቦታ የማይካሄደ ከሆነ ጉዳዩን ወደ ካፍ እና ፊፋ እንደሚወስደው አሳውቋል።

Via Amhara Communication

@tikvahethiopia