TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#የዩኒቨርሲቲ_መምህራን ! በዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበራት በኩል የቀረቡ ጥያቄዎች ፦ • መንግሥትን የደመወዝ ጭማሪ እና የዕርከን ዕድገት እንዲያደርግ ጠይቀዋል። • ለዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ እና ቴክኒካል ረዳቶች የተሰራውን አዲሱን የስራ ደረጃ ማሻሻያ JEG በተመለከተ ቅሬታ አላቸው። • የመምህራን የቤት አበልን በተመለከተ በፍጥነት አሁን ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ ከግምት አስገብቶ ተሻሽሎ ተግባራዊ እንዲደረገ…
የዩኒቨርሲቲ መምህራን ጥያቄ !

የዩኒቨርሲቲ መምህራን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠት ሒደቱ አሁን ምን ይመስላል ?  

የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ፦

" በሲቪል ሰርቪስ ባለሙያዎች የሥራ መዘርዝር በድጋሚ ታይቶ ሌላ የደረጃ ምዘና ተዘጋጅቷል፡፡ በዚህም ረዳት ምሩቅ ሁለት፣ ረዳት ሌክቸረር፣ ሌክቸረር፣ ተባባሪ ፕሮፌሰርና ረዳት ፕሮፌሰር ደረጃዎች ተሻሸለዋል፡፡

የረዳት ምሩቅ አንድና የፕሮፌሰር ግን ከነበረበት ደረጃ አልተሻሻለም፡፡ ለፕሮፌሰር ደረጃ ቀድሞም በ2011 ዓ.ም. ላይ ማሻሻያ ሲደረግ ደመወዝ የተጨመረው 233 ብር ገደማ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ዕድሜ ልካቸውን በትምህርት ላይ ያሳለፉ፣ እዚህ ለመድረስ ብዙ ጥናት ያሳተሙና ያማከሩ ናቸው፡፡

ውሳኔዎች ሲተላለፉ የአገር አቅም ከግምት ውስጥ የሚገባ ቢሆንም፣ እነዚህ ሰዎች ከዚህ ሌላ የገቢ ምንጭ የላቸውም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ ቀደም ማስተርስ ያላቸው ሆነው በታወቁ ጆርናሎች ላይ ጥናታቸውን ያሳተሙ መምህራን ረዳት ፕሮፌሰር መሆን ይችሉ ነበር፡፡

አሁን በወጣው ደረጃ ግን ረዳት ፕሮፌሰር ለመሆን ሦስተኛ ዲግሪ ስለሚያስፈልግ፣ ማስተርስ ኖሯቸው ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑ መምህራን በአዲሱ ደረጃ የተቀመጠውን የደመወዝ ጭማሪ አያገኙም፡፡

ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ስናነጋግር የሚያነሱ ጉዳዮች አሉ፡፡ አንደኛው ሰዎች በማስተርስ ደረጃ ረዳት ፕሮፌሰር የሚሆኑ ከሆነ ዶክትሬት ለመማር አይበረታቱም የሚል ነው፡፡

የትምህርት ዕድል ሲሰጣቸው ባለንበት ረዳት ፕሮፌሰር መሆን እንችላለን የሚሉ እንዳሉ ይነገራል፡፡

ይህንንና የረዳት ምሩቅ አንድና የፕሮፌሰር ደረጃ አለመሻሻሉን ጉዳይ ገና እየተወያየንበት ነው፡፡ "

ያንብቡ : telegra.ph/RE-08-14-3

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የሚገኙ 4 ወረዳዎች እና 1 ከተማ አስተዳደር የ "ክላስተር" አደረጃጀትን በየም/ቤቶቻቸው ባካሄዱት አስቸኳይ ጉባኤ አፅድቀዋል። የመስቃን እና ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እና የቡታጅራ ከተማ ማዕከሉን ቡታጅራ ያደረገ አዲስ ዞን ለመመስረት በተጨማሪነት የወሰኑ ሲሆን የማረቆ እና ቀቤና ወረዳዎች ደግሞ ወደ ልዩ ወረዳነት ለማደግ ውሳኔ አሳልፈዋል። የማረቆ፣ ቀቤና፣…
የደቡብ ክልል ዕጣፋንታ ምን ይሆን ?

መንግስት ክልሉ በክላስተር ተከፍሎ በአጎራባች ያሉ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች አንድ ላይ በመሆን ሁለት አዲስ ክልል እንዲመሰርቱ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ይህን አቅጣጫ ከተትሎም የዞን እና ልዩ ወረዳ ም/ቤቶች በየም/ቤቶቻቸው በመሰባሰብ በቀረቡላቸው የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ውሳኔ አሳልፈዋል፤ ውሳኔያቸውንም ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት አስገብተዋል።

አዎ! በመንግስት አቅጣጫ መሰረት በአንድ ላይ ሆነን በአዲስ 2 ክልል እንደራጃለን ብለው በምክር ቤት ያፀደቁ አጠቃላይ 10 ዞኖች እና 6 ልዩ ወረዳዎች ናቸው።

ከእነዚህ መካከል ግን በብቸኝነት የጉራጌ ዞን " ክላስተር አልደግፍም ፤ የህዝቡም ፍላጎት አይደለም ፤ እኛ የምንፈልገው በክልል መደራጀት ነው ፤ ይህም በህጋዊ መንገድ ምላሽ ሊሰጥበት ይገባል " ሲል የክላስተር አደረጃጀትን በምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ ውድቅ አድርጎታል።

ከዚህ በኃላ ግን በዛው በዞኑ ውስጥ ያሉ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት በዞናቸው ም/ ቤት በአብላጫ ድምፅ የተላለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበሉ በመግለፅ " ክላስተር እንደግፋለን " የሚል ውሳኔ አሳልፈዋል።

ውሳኔ ያሳለፉ (ትላንት) የማረቆ፣ ቀቤና፣ የመስቃን፣ ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እንዲሁም የቡታጅራ ከተማ ም/ ቤቶች ሲሆኑ #ዛሬ ደግሞ የቡኢ ከተማ፣ የደቡብ ሶዶ ወረዳ እና የሶዶ ወረዳ ምክር ቤቶች "ክላስተር እንደግፋለን " በሚል ውሳኔ አሳልፈዋል።

" ፌዴሬሽን ም/ቤት ስብሰባ ይቀመጣል "

የፌዴሬሽን ም/ቤት በ " ደቡብ ክልል " አደረጃጀት ጉዳይ ላይ ነሃሴ 12 #አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያደርግ እና ከክልሉ ጋር ተያይዞ የሚወስናቸው ውሳኔዎች እንደሚኖሩ የም/ቤቱን ህዝብ ግንኙነት ዋቢ አድርጎ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ዛሬ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነፃ የንግድ ቀጠና በድሬዳዋ በጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተመርቋል።

Photo Credit : PMOEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ዛሬ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነፃ የንግድ ቀጠና በድሬዳዋ በጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተመርቋል። Photo Credit : PMOEthiopia @tikvahethiopia
#FreeTradeZone

ነፃ የንግድ ቀጠና (Free-trade zone) ማለት ምን ማለት ነው ? ፋይዳውስ ?

ዛሬ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ነፃ የንግድ ቀጠና (Free-trade Zone) በድሬዳዋ ከተማ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተመርቋል።

ነፃ የንግድ ቀጠና ምንድነው ?

ነፃ የንግድ ቀጠና ልዩ ኢኮኖሚ ቀጠና አካል ሲሆን በውስጡ እሴትን የሚጨምሩ ፣ የሎጅስቲክስ አገልግሎቶችን፣ የማምረት ስራዎች እንዲሁም ንግድ የሚከናወኑባቸው ናቸው።

በዓለም ላይ በርካታ ሀገራት የነፃ የንግድ ቀጠና ያላቸው ሲሆን ጎረቤቶቻችን ጅቡቲ ፣ ኬንያ ፣ ሱዳን ነፃ የንግድ ቀጠና አላቸው።

በነፃ የንግድ ቀጠና ከቀረጥና ታክስ ነፃ ከሆኑ ዓለም አቀፍ የውጭ ኢቨስትመንት መሳብ ስለሚያስችል እንዲሁም ገንዝብ ያላቸው በነፃ ንግድ ታክስ ሳይከፍሉ ስለሚገቡ ብዙ ምርቶችን ማስገባት እና ለገበያ ማቅረብ ይቻላል።

በሀገራችን የነፃ ንግድ ቀጠና መቋቋሙ ፤ ወደ ውጭ የሚልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ መጥተው አምርተው እሴት ጨምረው ፣ መልሰው ብራንድ አድርገው ኤክስፖርት ሊያደርጉም ያስችላቸዋል።

ሀገራችን እስከዛሬ የነፃ ንግድ ቀጣና ስላልነበራት ምን አጣች ?

➤ የገቢ እና ወጪ እቃዎች በጎረቤት ሀገር ነፃ የንግድ ቀጠናዎች ስታስተላልፍ ነበር። ገቢ ወጪ እቃዎች ወደ ሀገር እስኪገቡ ድረስ ረጅም ጊዜ ይወስዳል። በጎረቤት ሀገር ረጅም ጊዜ ሲቀመጥም በእቃዎች ላይ #የጥራት_መጓደል እና #መበላሸት ይፈጠራል።

➤ እቃዎች በሚፈለገው ጊዜ ወደ ሀገር ስለማይገቡና ወደ ተጠቃሚው እንዲደርስ ስለማይደረግ ለአቅርቦት እጥረት እና ለኑሮ ውድነት መንስኤ ይሆናል።

➤ እቃዎች ፈጥነው ስለማይገቡ ዋጋዎች ይጨምራሉ ፣ አምራች ድርጅቶች ጥሬ እቃ በቶሎ ስለማይገባላቸው በምርት ላይ ዋጋ ይጨምራሉ ፣ አንዳንዴ በጥሬ እቃ ማጣት ምርት ያቆማሉ ሰራተኞችን እከመበተን ድረስ ይደርሳሉ።

ነፃ የንግድ ቀጠና ምን ፋይዳ ይኖረዋል ?

▪️ገቢ እቃዎች በጊዜ እንዲደርሱ ያደርጋል።

▪️የታሪፍ ጫናና የጉምሩክ ታክስን በማስቀረት ተገቢ ያልሆነ የንግድ ስርዓትን ይቀይራል።

▪️የሎጅስቲክስ ስርዓቱን በእጅጉ ያሻሽላል። ለዓለም አቀፍ ንግድ ቅልጥፍና ለኢንዱስትሪ እና ከተሞች እድገት ፣ ለስራ እድሎች መፈጠር ፣ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ትልቅ ጥቅም አለው።

▪️ምርቶች በቀጥታ ወደ ሀገር እንዲደርስ በማድረግ የወደብ ወጪ ያስቀራል።

▪️በነፃ የንግድ ቀጠና የሚገቡ ነጋዴዎች ከታክስ ነፃ የሚንቀሳቀሱ እና የታሪፍም ጫና የሚቀነስላቸው በመሆኑ ለራሳቸውም ለሀገርም ትልቅ ጥቅም አለው። ነጋዴዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ያደርጋቸዋል።

ነፃ የንግድ ቀጣና በድሬዳዋ መመስረቱ ምን ተጨማሪ ጥቅም ያስገኛል ?

በድሬዳዋ ብዙ የመሰረተ ልማት በመሟላቱ ፣ የሀገር ውስጥ ወደብ በድሬዳዋ በመኖሩ፣ ኤርፖርት የባቡር መስመር በመኖሩ፣ ኢንዱስትሪ ፓርክ በመኖሩ እንዲሁም ከጅቡቲ ወደብ ያለው ርቀት አጭር በመሆኑ ለሁሉ ነገር የተመቻቸ ነው ይህ አጠቀላይ ስራዎች እንዲፋጠኑ ያደርጋል።

©እነዚህ መረጀዎች የተሰባሰቡት ፦ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሎጅስቲክስ ማኔጅመንት ተባባሪ ፕሮፌሰር ማቲዮስ ኢንሳርሞ፣ ሀሪሽ ኮተሪ የሞሃ ስራ አኪያጅ - ከፋና ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
' አዲሱ የትምህርት ስርዓት ' በዘንድሮ 2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን በሙከራ ደረጃ እንዲሁም በ2015 ዓ/ም ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ የሚገባው አዲሱ የኢትዮጵያ 🇪🇹 የትምህርት ስርዓት ምን ምን ጉዳዮችን አካቷል ? - አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ለሀገር በቀል እውቀት ትኩረት የሰጠ ነው። - ከመዋለ ህፃናት አንስቶ የግብረገብ ትምህርት መስጠት የሚያስገድድ ነው። - በብቃት ላይ የተመሰረተ ፣ የሞያ እና የቀለም…
" አዲሱ ስርዓተ ትምህርት "

የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ የተጠናቀቀ ሲሆን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ክልሎች አስፈላጊ መፅሀፍትና ቋንቋ የመተርጎም ስራ እየሰሩ ሲሆን በፍጥነት ወደ መፅሀፍ የማሳተም ስራ እንዲገባ እየተሰራ ነው ተብሏል።

በዚህም ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት (ኤለመንተሪ) ካሪኩለም ስራ ላይ ይውላል።

በተመሳሳይ በቀጣይ ዓመት የሁለተኛ ደረጃ ካሪኩለም የሙከራ ስራ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚሞከር ሲሆን 2016 ዓ/ም ላይ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ስለ ሀገራችን የአዲሱ ትምህርት ስርዓት ከዚህ በፊት በዝርዝር ተፅፎ የተቀመጠ መረጃ በዚህ ሊንክ ማግኘት ይችላል👇
https://t.iss.one/tikvahethiopia/63595

@tikvahethiopia
ፎቶ ፦ ዛሬ በአዲስ አበባ የተመረቀው የሳርቤት – ጎፋ ማዞርያ – የፑሽኪን -ጎተራ ማሳለጫ ዘመናዊ የመንገድ ፕሮጀክት።

• ግንባታው የተጀመረው ፦ በ2012 ዓ.ም

• ርዝመት እና ስፋት ፦ 3 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና ከ30 እስከ 45 ሜትር የጎን ስፋት

• ፕሮጀክቱ ፈጣን የአውቶብስ መንገድን ጨምሮ በአንድ ጊዜ በርካታ ተሽከርካሪዎችን ሊያስተናግድ የሚያስችል 320 ሜትር ርዝመት ያለው ዋሻ እና ከመሬት ከፍ ብሎ የተገነባ ረጅም መሳለጫ ድልድይ ያካተተ ነው፡፡

• ከቂርቆስ፣ ከጎተራ፣ ከጎፋ ፣ ከሳር ቤት ፣ ከሜክሲኮ እና ከቄራ የሚመጡ ተሽከርካሪዎችን ያሳልጣል።

• የወጣበት ገንዘብ እና ምንጩ ፦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አማካኝነት ከቻይና መንግሥት በተገኘ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ብድር የተገነባ ነው፡፡

#ኤፍቢሲ

Photo Credit : Mayor Office AA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#US #SOMALIA አሜሪካ ትላንትና ማክሰኞ ፤ ከሶማሊያ መንግስት ጋር በመተባበር በፈፀመችው የአየር ድብደባ 4 የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላትን መግደሏን አሳውቃለች። የአልሸባብ ታጣቂዎች የሶማሊያ ጦር ላይ በቤልድዌይኔ ጥቃት የከፈቱ ሲሆን ይህን ተከትሎ የአሜሪካ ጦር በአየር በፈፀመው ድብደባ 4 የቡድኑን አባላት መግደሉ ተገልጿል። አሜሪካ እርምጃው በሶማሊያ መንግስት በኩል ፍቃድ ኖሮት መፈፀሙን…
#Somalia

የጎረቤት ሶማሊያ ብሄራዊ ጦር በሂራን ክልል እያካሄደ ባለው የፀረ ሽብር ዘመቻ ትላንት በማሃስ አውራጃ መሀመድ ወህሊዬ ዋሱጌን የተባለ የአልሸባብ ቡድን ቀደኛ ሰው ጨምሮ 14 ታጣቂዎችን መግደሉን የሶማሊያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።

በተጨማሪ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች በጦሩ ተይዘዋል።

አሜሪካ ደግሞ የአየር ላይ ጥቃት በመፈፀም የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎችን መደበቂያ ማውደሟ ተገልጿል።

አሜሪካ የአየር ድብደባ የፈፀመችው የፀረሽብር ኦፕሬሽን እያካሄደ የሚገኘውን የሶማሊያ ብሄራዊ ጦርን ለመደገፍ ነው።

ከቀናት በፊት አሜሪካ በሶማሊያ መንግስት ጥያቄ የአየር ጥቃት መፈፀም መጀመሯን መነገሩ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia