TIKVAH-ETHIOPIA
#HappeningNow ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌብር መላ፤ ቴሌብር እንደኪሴ እንዲሁም ቴሌብር ቁጠባ የተሰኙ የፋይናንሻል አገልግሎቶችን ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል። ቴሌ ብር መላ፦ የቴሌብር ደንበኞቹን ባንቀሳቀሱት የገንዘብ ዝውውር መሰረት ታይቶ እስከ በቀን እስከ 2,000 በወር ደግሞ እስከ 10,000 ብር የሚደርስ ብድር የሚያመቻች አገልግሎት ነው። ቴሌ ብር እንደኪሴ ፦ በቴሌብር አማካኝነት…
#ዝርዝር_ማብራሪያ
ኢትዮ ቴሌኮም ፦
• ቴሌብር መላ ፤
• ቴሌብር እንደኪሴ
• ቴሌብር ሳንዱቅ የተሰኙ የፋይናንሻል አገልግሎቶችን አስተዋውቋል።
ይህንን በሚመለከት ዝርዝር መረጃ አጠናቅረናል።
- " ቴሌብር መላ " አነስተኛ የብድር አገልግሎት ሲሆን ግለሰቦች እንዲሁም ነጋዴዎች እና ወኪሎች ያለየብድር ማስያዥያ ( Collateral ) ገንዘብ መበደር ያስችላቸዋል።
ምን ያህል መበደር እችላለሁ የአገልግሎት ክፍያውስ?
- " ቴሌብር እንደኪሴ " የክሬዲት ክፍያ/ኦቨርድራፍት ብድር አገልግሎት ሲሆን ገንዘብ በጎደሎት ጊዜ ሞልቶ ይከፍላል።
እንዴት መጠቀም እችላለሁ?
- " ቴሌብር ሳንዱቅ " የቁጠባ አገልግሎትን የሚሰጥ ሲሆን ከአንስተኛ ብር ጀምረው መቆጠብ ይችላሉ።
ወለዱ እንዴት ይሰላል ?
ያንብቡ : https://telegra.ph/telebirr-08-05

Telegraph
telebirr
ቴሌብር ስላስተዋወቃቸው ሦስቱ የፋይናንስ አገልግሎቶች፦ በአፍሪካ ቀደምትና ለ128 ዓመታት የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ተቋም የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌብር የተሰኘውን የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ካስተዋወቀ ከ15 ወራት በኋላ ትልቅ የሚባለውን የፋይናንስ አገልግሎት ከዳሽን ባንክ ጋር በመተባበር አስተዋውቋል። በዕለቱ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ በኢትዮጵያ 60…
#ሚኒስትሮች_ምክርቤት
ከ10ኛው የሚኒስትሮች ም/ቤት ውሳኔዎች መካከል ፦
" ወደ አገር በሚገቡ እቃዎች ላይ የማህበራዊ ልማት ቀረጥ ለማስከፈል የቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቷን።
ወደ አገር በሚገቡ በተወሰኑ ምርቶች ላይ አነስተኛ ቀረጥ በመጣል በሚገኘው ገቢ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በማስፋፋት በመጠገን እና በማሻሻል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችል ረቂቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡
ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡ "
(ሙሉ የሚኒስትሮች ም/ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

#Afar ⛈
ከትላንትና በስቲያ ፤ በአፋር ክልል ጭፍራ ወረዳ ከምሽት 1 ሰዓት አንስቶ ለሊቱን ሙሉ በጣለው ከፍተኛ ዝናብ በተለያዩ የቤት እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል።
የክልሉ አደጋ መከላከልና ስጋት አመራርና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን ለኢዜአ በሰጠው ቃል ፤ ሀሙስ ከምሽቱ 1 ሰአት ጀምሮ ሌሊቱን ሙሉ በጣለው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ምክንያት ፦
👉 13 ሺህ 834 ፍየል እና በግ፣
👉 180 የቀንድ ከብት፣
👉 20 ግመሎች እና 3 አህዮች ሞተዋል።
በክልሉ ባለዉ ድርቅ የቤት እንስሳዎቹ በመኖ እጥረት የተጎዱ በመሆናቸዉ ዝናቡን መቋቋም አለመቻላቸው አደጋውን የከፋ አድርጎታል ተብሏል።
በወረዳው ደርጌራ ፣ አፉማና ወአማ ቀበሌዎች በዝናቡ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።
የቤት እንስሳቶቻቸው ለሞቱባቸው ቤተሰቦች ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተገልጿል።
የጭፍራ ወረዳ አርብቶ አደር ጽ/ ቤት በበኩሉ ፤ ከወረዳዉ ስፋት ጋር በተያያዘ ገና መረጃ እየተሰበሰበ የሚገኝ በመሆኑ የሞቱ የቤት እንሰሳዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ለኢዜአ ገልጿል።

የካቢኔ አባል የተደረጉት የቀድሞ የአልሸባብ ከፍተኛ አመራር ማንናቸው ? በትላንትናው ዕለት የሶማሊያ ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ 26 አባላት ያሉትን ካቢኔ ይፋ አድርገዋል። ጠ/ሚስትሩ በጠ/ሚኒስትርነት ከተሾሙ በኃላ ካቢኔያቸውን የሚያሳውቁበት ቀን በሶማሊያውያን ዘንድ በብዙ ሲጠበቅ ነበር። ትላንት ይፋ ባደረጉት የካቤኔ አባላት ዝርዝር ግን አንድ የቀድሞ የአልሸባብ ከፍተኛ አመራርን ማካተታቸው የሚዲያዎችን…
#Update
የሶማሊያ ፓርላማ ነገ እሁድ ይሰበሰባል።
በነገው ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ ባሬ የቀረበውን የካቢኔ አባላት ላይ ድምፅ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ከቀናት በፊት ጠ/ሚኒስትሩ የቀድሞ " አልሸባብ " ምክትል መሪ ሙክታር ሮቦው የሀይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር ያደረጉበት 26 የካቢኔ አባላት ፓርላማው እንዲያፀድቅላቸው መጠየቃቸው ይታወሳል።

" ፍትህ ይሰጠኝ ፣ ህግ ይፍረደኝ " - ወላጅ አባት
ከሰሞኑን በአ/አ በአንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ አንድ ተማሪ እጅግ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተገድሏል። ጉዳዩ ምንም እንኳን በህግ ቢያዝም ቤተሰቦች ተገቢውን ፍትህ እንዲያገኙ ጠይቀዋል።
በሚማርበት ተቋም ውስጥ የተገደለው ተማሪ ዮሐንስ አሰፋ ይባላል።
ተማሪ ዮሐንስ እድሜው 20 እስከ 12ኛ ክፍልም በኮከበፅብአ ት/ቤት ትምህርቱን ተከታትሏል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውጤት አምጥቶም ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ቢመደብም አባት አቅም ስለሌላቸውና አጠገባቸው እንዲሆን ቅ/ማርያም ዩኒቨርሲቲ (ዋቢ ሸበሌ) ትምህርቱን እንዲጀምር ያደርጋሉ።
ዮሐንስን ትምህርቱን (በአካውንቲንግ) በከፍተኛ ውጤት እየተከታተለ 2 ዓመት ድረስ መድረስ ችሏል።
የተማሪውን ባህሪ የሚያውቁ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላትና የዮሐንስ ወላጅ አባት ልጃቸው ከሰው ጋር የማይጋጭ፣ በቤተክርስቲያን አስተምሮ ያደገ፣ የቤተክርስቲያን አገልጋይ፣ ጨዋና ሰዎችን ቀና ብሎ የማያይ እንደሆነ ገልፀዋል።
ነገር ግን ከሰሞኑን በትምህርት ተቋሙ ውስጥ በርካታ የሰውነቱ ቦታ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ተወጋግቶ ተገድሏል።
አባት፤ "ልጄ እንደበግ ነው የታረደው" ያሉ ሲሆን "ህግ ፍትህ ይስጠኝ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ ፣ የልጄ ደም ይውጣልኝ፤ ህግ ካለ መንግስት ካለ ፍትህ ይስጠኝ" ብለዋል።
ወላጅ አባት ጉዳዩ በህግ እንደተያዘ ገልፀው " ህግ ይፍረደኝ የልጄን ደም ይፈልግልኝ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ፤ ንፁህ ኢትዮጵያዊ በኤርትራ ምድር ደሜ ፈሷል ቆስያለሁ ቆስዬ ጡረታም የለኝ፣ የምሰራው በአትክልተኝነት ነው ልጄን በብዙ ችግር ነው ያሳደኩት የኢትዮጵያ ህዝብ ይሄን አይቶ ይፍረደኝ" ሲሉ ተማፅነዋል።
ያንብቡ telegra.ph/Yohannes-Asefa-08-06

#Reminder 🛎
#National_Exit_Exam
በመጪው 2015 ዓ/ም መጨረሻ ላይ የመውጫ ፈተና መሰጠት ይጀምራል።
በ2015 ዓ.ም መጨረሻ መተግበር በሚጀምረው የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዙሪያ ከሰሞኑን የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለአዲስ ዘመን ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።
ሚኒስትር ዴኤታው ካነሳሷቸው ሃሳቦች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው
• የመውጫ ፈተና ምዘና የሚሰጠው ለመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ብቻ ነው።
• በግልም ሆነ በመንግስት የትምህርት ተቋም የሚማር ተማሪ ዲግሪውን የሚያገኘው ምዘናውን ሲያልፍ ብቻ ነው፡፡
• የመውጫ ፈተናው የሚዘጋጅበት፣ የሚያዝበት እና የሚሰራጭበት ስርዓት ከሰው ንክኪ ነጻ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
• በየዓመቱ ከ150 እስከ 180 ሺህ በመጀመሪያ ዲግሪ የሚመረቁ ተማሪዎችን ምዘና ለመስጠት የሚያስችል አቅም አለ፡፡
• የሙያ ማኅበራት አቅማቸው ሲጎለብት የሙያ ፈተና ይሰጣሉ፤ የመውጫ ፈተና ሥራን ከመንግስት ይረከባሉ።
• ፈተናውን የሚያሰናዱ ተቋማትና መምህራን ዝግጅት ሥራዎች እስከ ግንቦት 2015 ዓ.ም ይሰራሉ፡፡
• የፈተና አሰጣጥ ሂደቱን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ግልጸኝነቱ የተጠበቀ ለማድረግ እየተሰራበት ነው።
@tikvahethiopia @tikvahuniversity

ዳግም የሀገራችንን ስም በዓለም ከፍ ያደሩጉት ወጣቶች !
ላለፉት 6 ተከታታይ ቀናት በኮሎምቢያ ካሊ የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሲካሄድ ሰንብቷል።
በዚችም ሀገራችን በ19 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ በ10 የውድድር ተግባራት ብቻ ተሳትፋለች።
የአትሌቲክስ ቡድናችን በሻምፒዮናው ፦
🥇6 ወርቅ፣
🥈5 ብር
🥉1 ነሃስ በድምሩ በ12 ሜዳልያዎች በማግኘት ከዓለም ሃገራት አሜሪካንን እና ጃማይካን በመከተል 3ኛ ደረጃን ይዘን አጠናቀናል።
የተመዘገበው ውጤት እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪካችን ዘንድሮ #ከፍተኛው ውጤት ነው።
ከተሳተፍንበት ውስን የውድድር ተግባራት አንፃር እጅግ የሚያኮራ ውጤት ነው።
ሜዳሊያ ያስመዘገቡ የነገዎቹ የሀገር ተስፋዎች እነማን ናቸው ?
#ወርቅ
🥇ኤርሚያስ ግርማ (800 ሜትር)
🥇መልክነህ አዘዘ (3000 ሜትር)
🥇አዲሱ ይሁኔ (5000 ሜትር)
🥇ሳሙኤል ዱጉና (3000 ሜትር መሰናክል)
🥇 ብርቄ ሀየሎም (1500 ሜትር)
🥇መዲና ኢሳ (5000 ሜትር)
#ብር
🥈ኤርሚያስ ግርማ (1500 ሜትር)
🥈ሳሙኤል ፍሬው (3000 ሜትር መሰናክል)
🥈ፅዮን አበበ (3000 ሜትር)
🥈መልክናት ውዱ (5000 ሜትር)
🥈ሲምቦ አለማየሁ (3000 ሜትር መሰናክል)
#ብር
🥉መሰረት የሻነህ (3000 ሜትር መሰናክል)
እንኳን ደስ አለን አላችሁ !
ይቀላቀሉ : @tikvahethsport
https: //t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

#ትምህርት_ሚኒስቴር የ2014 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው። የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል። ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ…
#NationalExam
የ12ኛ ክፍል ፈተና ከመስከረም 30 ቀን 2015 ጀምሮ ይሰጣል።
የ2014 የትምህርት ዘመን ብሔራዊ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ማጠቃለያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።
ፈተናው ከመስከረም 30/2015 ዓ/ም ጀምሮ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
የፈተና ደንብ ጥሰቶች #በህግ ያስጠይቃሉም ተብሏል።
የ2014 ዓ/ም ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በዩኒቨርሲቲዎች ከመስጠት ባለፈ የፈተና ኩረጀ እና ስርቆትን ለመከላከል በ12 ኮድ (በጥያቄ አቀማመጥ ስብጥር) ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ከቀናት በፊት መገለፁ ይታወሳል።
የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከዚህ በፊት እንደነበረው በ4 ኮድ (4 የተለያዩ ፈተናዎች/በጥያቄ አቀማመጥ) ሳይሆን እስከ 12 እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው እንደነበር አይዘነጋም።
ይህ የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ከሚሰሩት ስራዎች መካከል አንዱ ሲሆን ለጎን ያሉ ተማሪዎች እርስ በእርስ የሚፈተኑት ፈተና የጥያቄው ዝርዝር (order) በፍፁም የተገናኘ እንዳይሆን ለማድረግ የታሰበ ነው።