TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ አይመን አል-ዛዋሂሪን ገደልኩኝ አለች። አሜሪካ የአልቃይዳውን መሪ አይማን አል-ዛዋሂሪን በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ባካሄደችው የድሮን ጥቃት መግደሏን ነው በፕሬዝዳንቷ ጆ ባይደን በኩል ያሳወቀችው። የአሜሪካ የደህንነት መስሪያ ቤት ሲአይኤ (CIA) ባሳለፍነው ዕሁድ ካቡል ውስጥ ባካሄደው የፀረ-ሽብር ዘመቻ ዛዋሂሪን መግደል መቻሉን ባይደን ገልፀዋል። ፕሬዘዳንት ባይደን " ዛዋሂሪ በአሜሪካ…
ስቴቨን ኩክ ስለ አልዛዋሂሪ ፦
" ዛዋሂሪ ከአልቃይዳ ጋር ወሳኝ ግንኙነት ከነበራቸው የግብፃውያን ቡድን አንዱ ነው። በአንዋር ሳዳት ግድያ ውስጥም እጁ ነበረበት።
በ1980ዎቹ ላይ ከግብፅ እስር ቤት ከተለቀቀ በኋላ በፔሻዋር ከኦሳማ ቢን ላደን ጋር ግንኙነት ነበረው። የቀረው ታሪክ ነው... "
@tikvahethiopia

Video
አልቃይዳ በቀጣይ በማን ይመራል ?
አሜሪካ አል-ዛዋሂሪን ገደልኩኝ ማለቷን ተከትሎ አልቃይዳ የቀድሞውን የግብፅ ወታደር መሪ ያደርጋል ተብሎ ተገምቷል።
በአልቃይዳ ውስጥ ሶስተኛው ሰው ነው ተብሎ የሚታሰበው ሳይፍ አልአድል ሲሆን የቀድሞ ግብፅ ኮሎኔል ፣ በወታደራዊ እና በደህንነት ጉዳዮች ጥልቅ እውቀት እንዳለው ይነገራል።
ከዓመታት በፊት አልአደል ፤ በአፍጋኒስታን፣ ፓኪስታን እና ሱዳን ላሉ የአልቃይዳ እና ሌሌች ቡድኖች አባላት እንዲሁም ፀረ-UN አቋም ላላቸው የሶማሊያ ጎሳዎች ወታደራዊ እና የስለላ ስልጠና መስጠቱ ይነገራል።
በሶማሊያ በኬንያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው በራስ ካምቦኒ የአልቃይዳን ማሰልጠኛ ተቋምም መስርቷል።
አል-አደል በ1987 የግብፅን መንግስት ለመጣል ሞክሯል በሚል ተከሶ የነበረ ሲሆን ክሱ ውድቅ ከተደረገ በኋላ በ1988 አገሩን ለቆ የሶቪየትን የአፍጋኒስታን ወረራ ለመመከት ወደ አፍጋኒስታን አቅንቶ ነበር።
አልአደል ከዓመታት በፊት በሱዳን መዲና ካርቱም ውስጥም ለተመለመሉ ታጣቂዎች ፈንጂዎችን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ትምህርት ሲሰጥ እንደነበር እሱን በተመለከተ የተፃፉት መረጃዎች ያሳያሉ።
ከ1998ቱ በኬንያ ከአሜሪካ ኤምባሲ የቦንብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ (ከ200 በላይ ሰዎች ተገድለዋል) አሜሪካ በጥብቅ ከምትፈልጋቸው ሰዎች አንዱ ነው።
አሁን ላይ ብዙም ስለእሱ የሚታወቅ ትክክለኛ መረጀ የለም። ነገር ግን አልቃይዳ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ሲሆን ቀጣዩ መሪም ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ሰው ነው።
መረጃው የተሰባሰበው ከአል ሲፋን የቀድሞ የFBI ኤጀንት ነው።

Photo
#ችሎት
• ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለነሐሴ 19/2014 ተቀጥሯል።
• የክስ መቃወሚያው ውድቅ ተደርጓል።
ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ሐምሌ 26 ቀን 2014 ዓ/ም የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 1ኛ ፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ችሎት አቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ ላይ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ካቀረበው መቃወሚያ ጋር አገናዝቦ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ጉዳዩ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ መሠረት የሚታይ ቢሆንም ይርጋ እንዴት መቆጠር አለበት የሚለው ጉዳይን በወንጀል ህጉ መሠረት ስናየው ክሱ በይርጋ ቀሪ የሚሆን አይደለም ብሎ የጋዜጠኛ ተመስገንን መቃወሚያ ውድቅ አድርጓል።
ክሱን ከቀረበው ማስረጃ አንፃር መርምሮ እንዲከላከል ወይም በነፃ ለመልቀቅ ለነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።
ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ከ24 ቀን በኋላ እንዲቀርብ እንደቀጠረ የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ አሳውቋል።

#እንድታውቁት
የፌደራል ፍ/ቤቶች በነሐሴ ወር መደበኛ የዳኝነት አገልግሎትታቸውን ይቀጥላሉ።
በፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/3 አንቀፅ 38(2) መሰረት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ባለው ጊዜ ዝግ እንደሚሆኑ ይደነግጋል፡፡
ሆኖም በዳኞች ፈቃደኝነት ላይ በመመስረት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ማለትም የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ፤ ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤትከነሐሴ 1 30/2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ መደበኛውን የዳኝነት አገልግሎት መስጠታቸውን እንደሚቀጥሉ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል።
ይህም ወደ 205 ዓ.ም የሚያልፉ መዝገቦችን ቁጥር ለመቀነስ፣ የበሰሉ መዝገቦችን እልባት ለመስጠት፣ እስረኛ ያለባቸውን መዝገቦች ቅድሚያ ሰጥቶ ለመስራት ያስችላል ተብሏል።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኞች ያላቸውን የዕረፍት ጊዜ መስዋዕት በማድረግ መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት ለመስጠት ፍቃደኛ በመሆናቸው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አመስግኗል።
@tikvahethmagazine

#Tigray , #Mekelle
የአሜሪካ ፣ የአውሮፓ እና የተመድ ባለስልጣናት ወደ ትግራይ ክልል ተጉዘው ክልሉን እያስተዳደሩ ካሉት የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ጋር ተወያዩ።
በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልእከተኛ ማይክ ሀመር፣ በአፍሪካ ቀንድ የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልእክተኛ አኔት ዌይበር፣ የተባበሩት መንግስታቱ ድርጅት ተወካይ ፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈፃሚ ፣ የካናዳ እና ጣልያን አምባሳደሮች እንዲሁም ተወካዮች ፣ ከፍተኛ ኃላፊዎች ናቸው ወደ ትግራይ በመጓዝ ከዶክተር ደብረፅዮን ገ/ ሚካኤል ጋር ተገናኝተው የመከሩት።
አሜሪካ፣ ተመድ ፣ የአውሮፓ ህብረት እንዲሁም የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በሰላማዊ ድርድር እንዲቋጭ ጥረት እያደረጉ እንዳሉ ይታወቃል።
የፌዴራል መንግስት እና ትግራይን እያስተዳደረ ያለው ህወሓት ሌላ ተጨማሪ እልቂት ሳይኖር ያሉ ችግሮች በሰላማዊ ድርድር እንዲፈቱ አቋም መያዛቸው ለሰላም ድርድር የተደራዳሪ አካላትን መሰየማቸው አይዘነጋም።

#Update
የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔት ዌበር ፣ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር ፣ የተመድ ተወካዮች ፣ የሀገራት አምባሳደሮች ከትግራይ ክልል ለፌዴራል መንግስት ደብዳቤ ይዘው ተመልሰዋል።
ከዚህ ቀደም መልዕክተኞቹ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባደረጉት ውይይት በትግራይ የመብራት፣ የቴሌኮም፣ የባንክ እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶችን #በፍጥነት ወደነበረበት መመለስ ለትግራይ ህዝብ አስፈላጊ መሆኑን ስምምነት ላይ ደርሰው ነበር።
በዚህም የትግራይ ክልልን እያስተዳደሩ ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በዓለማቀፍ ማህበረሰቡ ተወካዮች በኩል ለፌዴራል መንግስት ደብዳቤ ልከዋል።
ደብዳቤው ፤ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ስልክ ፣ ባንክ፣ መብራት እና የመሳሰሉትን ለመመለስ እና አገልግሎት እንዲጀምሩ ለማድረግ ወደ ክልሉ ገብተው ለሚሰሩ አካላት የደህንነት ማረጋገጫ የሚሰጥ ነው።
በዚህ #የደህንነት_ማረጋገጫ አገልግሎቶችን ወደነበረበት መመለስ ለማስጀመር ምንም አይነት መሰናክል ሊኖር አይገባም ተብሏል።
ተጨማሪ https://www.eeas.europa.eu/eeas/ethiopia-eu-and-us-special-envoys-visit-mekelle-tigray_en

የቤጂንግ እና የዋሽንግቶን ውጥረት ?
አሜሪካ እና ቻይናን ውጥረት ውስጥ የከተታቸው የታይዋን ጉዳይ ነው።
ቻይና ታይዋን #ወደ_እናት_አገሯ መመለስ ያለባት አፈንጋጭ ግዛቷ እንደሆነች ነው የምታስበው
ይህንንም ለማሳካት ወደፊት ቤይጂንግ ኃይል መጠቀምን እንደ አንድ አማራጭ ታየዋለች።
አሜሪካ ደግሞ ከቻይና ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላት ሲሆን፣ ከታይዋን ጋር ግን “ይፋዊ ያልሆ ጠንካራ” ዲፕሎማሲያዊ ግንኙት አላት ይባላል።
ረጅም ጊዜ ይሄ ጉዳይ ሲንከባለል እና በቻይና እና አሜሪካ መካከል ምልልስን ሲፈጥር ቆይቷል።
አሁን ግን የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋን እንደሚጎበኙ ማሳወቃቸው የለየት ውጥረትን ፈጥሯል።
ፔሎሲ በአገሪቱ የሥልጣን አርከን ውስጥ ከፕሬዝዳንቱ እና ከምክትላቸው ቀጥሎ ሦስተኛ ሰው ናቸው።
ቻይና ፔሎሲ ታይዋንን ከጎበኙ እስከ ወታደራዊ እርምጃ ድረስ ልትወስድ እንደምትችል ሲነገር ነበር።
ምንም እንኳን ቻይና የአሜሪካዋ 3ኛ ሰው ታይዋንን እንዳትጎበኝ ብታስጠነቅቅም ከጥቂት ሰዓት በፊት ታይዋን ደርሰዋል።
አቀባበልም ተደርጎላቸዋል።
የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉብኝቱን ለቻይና ክብር አለመስጠታቸው ማሳያ ነው ፤ ለቻይና ተገንጣይ ቡድኖች እውቅና መስጠት ነው ብሏል።
ሚኒስቴሩ በፔሎሲ ውሳኔ ማዘኑን አስታውቋል፡፡
ለሉአላዊነትና ደህንነትን ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
ለሚመጣው መዘዝ አሜሪካ እና ታይዋን ሃላፊነቱን ይወስዳሉ ብሏል።
#RT #CGTN #BBC

የቤጂንግ እና የዋሽንግቶን ውጥረት ? አሜሪካ እና ቻይናን ውጥረት ውስጥ የከተታቸው የታይዋን ጉዳይ ነው። ቻይና ታይዋን #ወደ_እናት_አገሯ መመለስ ያለባት አፈንጋጭ ግዛቷ እንደሆነች ነው የምታስበው ይህንንም ለማሳካት ወደፊት ቤይጂንግ ኃይል መጠቀምን እንደ አንድ አማራጭ ታየዋለች። አሜሪካ ደግሞ ከቻይና ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላት ሲሆን፣ ከታይዋን ጋር ግን “ይፋዊ ያልሆ ጠንካራ” ዲፕሎማሲያዊ…
" ሀሰተኛ ዜና ነው " - ታይዋን
የታይዋን መከላከያ የቻይና የጦር ጄቶች PLA Su-35 " የታይዋንን አየር ክልል ጥሰው ገቡ " ተብሎ በኦንላይን ሚዲያዎች የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰተኛ_ዜና ነው አለ።
በታይዋን ያለውን ጉዳይ የሚከታተሉ ትክክለኛው የመከላከያ ድረገፅ ብቻ እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተለልፏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ነዋሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩትን ሀሰተኛ መረጃዎች ለሌሎች እንዳያጋሩ አሳስቦ " ይህን እኩይ ተግባር በጽኑ እናወግዛለን " ብሏል።
CGTNን ጨምሮ ሌሎችም ሚዲያዎች የቻይና Su-35 ተዋጊ ጄቶች " የታይዋንን አየር ክልል ጥሰው ገቡ " ሲሉ ዘገባዎችን አውጥተው ነበር።
ቻይና " ታይዋን " #ወደ_እናት_ሀገሯ መመለስ አለባት ብላ ታምናለች ፤ ታይዋንን የሚደግፉ ሁሉ በሀገር አንድነት ላይ አደጋ ያመጡ አድርጋ ነው የምትወስዳቸው።
ለዛም ነው በአሜሪካ የስልጣን እርከን ሶስተኛዋ ሰው ፔሎሲ ታይዋን መግባታቸው ያስቆጣት እና እርምጃ እንደምትወስድ በተደጋጋሚ እየዛተች የምትገኘው።

ደቡብ ክልል ?
በደቡብ ክልል ስር ያሉ 10 የዞን እና 6 ልዩ ወረዳ ምክር ቤቶች ክልሉን በሁለት ክላስተር ለማደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አፅድቀዋል።
እስካሁን በአዲስ ክልል ለመደራጀት ስምምነት ላይ ደርሰዋል በም/ቤቶቻቸውም አፅድቀዋል የተባሉት ፦
- የወላይታ ዞን፣
- የጋሞ ዞን፣
- የጎፋ ዞን፣
- የደቡብ ኦሞ ዞን፣
- የኮንሶ ዞን
- የጌዲኦ ዞን
- የአማሮ ልዩ ወረዳ፣
- የቡርጂ ልዩ ወረዳ፣
- የባስኬቶ ልዩ ወረዳ፣
- የአሌ ልዩ ወረዳና የዲራሼ ልዩ ወረዳ ናቸው።
እነዚህ በአንድ ላይ በአዲስ ክልል ለመደራጀት የወሰኑ ናቸው።
በተመሳሳይ ፦
- የሀዲያ ዞን፣
- የስልጤ ዞን፣
- የከምባታ ጠምባሮ ዞን፣
- የሀላባ ዞን እና የየም ልዩ ወረዳ በምክር ቤቶቻቸው የአዲሱን የክልል አደረጃጀት አፅድቀዋል።
እነዚህም አንድ ላይ ሆነው የጉራጌ ዞንን አጠቃለው አንድ ክልል ለመመስረት የወሰኑ ናቸው።
እስካሁን ግን የጉራጌ ዞን በቀረበው የአዲስ የጋራ ክልል የውሳኔ ሀሳብ ላይ በምክር ቤት ተሰብስቦ አልወሰነም / አላፀደቀም።
ከዛሬ ከጥዋት አንስቶ በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያዎች የዞኑ ምክር ቤት ከትላንት ጀምሮ ጉባኤውን ጀምሯል በአዲሱ ክልል ዙርያም ውሳኔ ያሳልፋል እየተባለ ቢነገርም ይህን የሚያሳይ መረጃ ከዞኑ አልወጣም።
ጉባኤው መቼ ይደረጋል የሚለውም በግልፅ አልታወቀም።
የማህበራዊ ሚዲያዎቹ የጉባኤውን መረጃ ከዞኑ ኮሚኒኬሽን የማህበራዊ ትስስር ገፅ እንዳገኙት እየገለፁ ቢሆንም በትክክለኛው የዞኑ አድራሻ ባለፉት 24 ሰዓት ስለጉባኤው የተፃፈ ሆነ የተባለ ነገር የለም።

ደቡብ ክልል ? በደቡብ ክልል ስር ያሉ 10 የዞን እና 6 ልዩ ወረዳ ምክር ቤቶች ክልሉን በሁለት ክላስተር ለማደራጀት የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አፅድቀዋል። እስካሁን በአዲስ ክልል ለመደራጀት ስምምነት ላይ ደርሰዋል በም/ቤቶቻቸውም አፅድቀዋል የተባሉት ፦ - የወላይታ ዞን፣ - የጋሞ ዞን፣ - የጎፋ ዞን፣ - የደቡብ ኦሞ ዞን፣ - የኮንሶ ዞን - የጌዲኦ ዞን - የአማሮ ልዩ ወረዳ፣ - የቡርጂ…
#GurageZone
የጉራጌ ዞን መንግስት የኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ ቡድን መሪ አቶ ፈቃዱ ዘለቀ ለብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬድዮ ጣቢያ የተናገሩት ፦
" ... የጉራጌ ዞን በክልልነት ለመዋቀር ለፌደሬሽን ም/ቤት የቀረበውን ጥያቄ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ ነው።
የህዝቡ ጥያቄ በክልልነት ለመዋቀር ነዉ ይሄንንም ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቅርበናል ምላሹን እየጠበቅን ነው።
የዞኑ ም/ቤት እስካሁን በአዲሱ አደረጃጀት ዙሪያ አልተወያየም። በቀጣይ በጉዳዩ መቼ ውይይት እንደሚደግ አይታወቅም።
በማህበራዊ ሚዲያ ዞኑ የክላስተር መዋቅሩን አጽድቋል ፤ በሌላ በኩል አላጸደቀም ተብለዉ የሚሰራጩ መረጃዎች የተሳሳቱ ናቸው።
ይህ በዞኑ አመራሮች ላይ ጫናን ለማሳደር የታሰበ ነው። "