TIKVAH-ETHIOPIA
#የኩላሊት_እጥበት_ማዕከል በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል በተመረቀበት ወቅት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተናገሩት ፦ " ሰው በሚያውቀው በተማረበት በርካታ ድንቅ ስራ ሊሰራ እንደሚችል ዛሬ አይቻለሁ፤ ባየሁትም ነገር ተደስቻለሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ ፕሮፌሽናሊዝም ጠፍቶ በመቆየቱ ምክንያት ማየት የሚገባንን ነገር ለብዙ ጊዜ ማየት ሳንችል ቆይተናል። በምንችለው በተማርነው…
#የኩላሊት_እጥበት_ማዕከል
በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል በተመረቀበት ወቅት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተናገሩት ፦
" የኩላሊት ህመም የጤና ስርዓቱን እየፈተነ ያለ ህመም በመሆኑ ምክንያት የከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ሁለት አመታት ምንም ገቢ የሌላቸውንና አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ነፃ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። በዚህም በሁለቱ አመታት 24 ሚሊየን ብር ያህል ድጎማ አድርጓል።
አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ በአጋርነት መስራት አስፈላጊነት ታምኖበት ህግ ማእቀፍ ወጥቶለት እየተተገበረ ነው። መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገውን የአብ ሜዲካል ሴንተር ላበረከተው አስተዋፅኤ አድናቆቴን እገልፃለሁ።
ይህ የኩላሊት መድከም ላለባቸው ዜጎች ትልቅ የምስራች ነው ፤ ሌሎችም ተጨማሪ አገልግሎቶችን እናሰፋለን።
በተጨማሪም ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል ትልቁና ዘመናዊ የአይን ህክምና ማእከል ሆኖ እንዲወጣ በአዲሱ አመት ለህዝባችን አዲስ ምስራች እናበስራለን።
በአጠቃላይ የከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባን የጤና ማእከል ለማድረግ 24 ቦታዎችን ለግል ዘርፉ የሰጠ ሲሆን አስተዳደሩ በራሱ አቅም ደግሞ ሶስት ሆስፒታሎችን በጀት መድቦ እየገነባ ነው።ነባር ሆስፒታሎችን የማደስም ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል። "
@tikvahethiopia