TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Oromia #ICRC

በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው የነበሩ እና በቅርቡ በምስራቅ ወለጋ፣ ጉቶ ጊዳ ወረዳ፣ አለልቱ ቀበሌ ወደሚገኘው መኖሪያ ስፍራቸው ለተመለሱ 800 ግለሰቦች መሰረታዊ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን የዓለም ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) አስታውቋል።

ድጋፍ ከተደረጉት ቁሳቁሶች መካከል ሶላር የእጅ ባትሪዎች ፣ ጀሪካኖች ፣ የማዕድ ቤት እቃዎች ፣ ምንጣፎች ፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና መጠለያ እንደሚገኙበት ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#ICRC

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚያካሂደውን የሰብል ምርጥ ዘር ስርጭት በመቀጠል በግጭቱ ለተጎዱ 15,000 አርሶ አደር አባወራዎች ድጋፍ አቅርቧል።

አርሶ አደሮቹ በላዕላይ ማይጨው ከሚገኙ 8 ቀበሌዎች እና በማዕከላዊ ትግራይ ዞን በአድዋ ወረዳ ከሚገኙ 4 ቀበሌዎች የመጡ ናቸው። ኮሚቴው ለእያንዳንዱ ቤተሰብ 10 ኪሎ ግራም የጤፍ ዘር እና 2.5 ኪሎ ግራም የማሽላ ዘር ድጋፍ አድርጓል።

#ICRCEthiopia

@tikvahethiopia
#ICRC

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፤ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ማግኘት ህይወታቸውን እንደሚታደግ ገልጾ ፦ በሐይቅ፣ ደሴ፣ ወልድያ፣ መርሳ፣ ኮምቦልቻ፣ አይደር፣ ማይጨው፣ ዓዲግራት፣ መሆኒ፣ ሽሬ፣ ኣክሱም፣ ላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ዋድላ፣ ባህር ዳር፣ ደባርቅ፣ ጎንደር፣ ነቀምት፣ ጊምቢ እና ደምቢዶሎ ሆስፒታሎች ያሉትን የአንድ መስኮት የአገልግሎት ማዕከላትን በመደገፍ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

በሌላ በኩል ኮሚቴው በጤና ድንገተኛ አደጋዎች ፈጣን እና ውጤታማ የሆነ ምላሽ ለመስጠት ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በቅርበት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጾ ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ 14 የክልል እና ዞን የኢቀመማ ቅርንጫፎች የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ መሳሪያዎችን እና የአምቡላንስ አቅርቦቶችን ድጋፍ ማድረጉ አሳውቋል።

ከዚህም በተጨማሪ ፤ ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች #ተቀብረው_ሳይፈነዱ_የሚቀሩ ፈንጂዎች በሰዎች አካል ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ የሚገልፀው የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ተጎጂዎችን ለመርዳት በኢትዮጵያ ውስጥ በባህር ዳር፣ ደሴ፣ አሶሳ፣ አሰላ፣ ነቀምት፣ አርባምንጭ፣ መናገሻ፣ ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ፣ መቐለ እና ኪዩር ሆስፒታል የአካል ማገገሚያ ማዕከላትን በማጠናከር ላይ እንደሆነ ገልጿል።

#ICRCEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ICRC የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፤ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ማግኘት ህይወታቸውን እንደሚታደግ ገልጾ ፦ በሐይቅ፣ ደሴ፣ ወልድያ፣ መርሳ፣ ኮምቦልቻ፣ አይደር፣ ማይጨው፣ ዓዲግራት፣ መሆኒ፣ ሽሬ፣ ኣክሱም፣ ላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ዋድላ፣ ባህር ዳር፣ ደባርቅ፣ ጎንደር፣ ነቀምት፣ ጊምቢ እና ደምቢዶሎ ሆስፒታሎች ያሉትን የአንድ መስኮት የአገልግሎት ማዕከላትን በመደገፍ…
#ICRC #Tigray

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) በተለያዩ ክልሎች በግጭት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን ቀጥሏል።

ኮሚቴው #በትግራይ_ክልል በግጭት የተጎዱ አርሶ አደሮችን ምርታማነት ለማሳደግ ፦

👉 በማዕከላዊ፣
👉 በምስራቅ ፣
👉 በደቡብ ምስራቅ እና በደቡብ ዞኖች ለሚገኙ ለ20,000 አባውራዎች (120,000 ግለሰቦች) የአፈር ማዳበሪያ በማከፋፈል ላይ እንደሚገኝ ዛሬ አሳውቋል።

ICRC ፤ ከሰሞኑን በትግራይ፣ አማራ እንዲሁም ኦሮሚያ ክልል ከተሞች ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ እና ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ተቀብረው ሳይፈነዱ ሚቀሩ ፈንጂዎች በሰዎች አካል ላይ የሚያደረሱትን ጉዳት ተንተርሶ ተጎጂዎችን ለመርዳት በተለያዩ ከተሞች የአካል ማገገሚያ ማዕከላትን በማጠናከር ላይ እንደሆነ መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ICRC #Tigray የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) በተለያዩ ክልሎች በግጭት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉን ቀጥሏል። ኮሚቴው #በትግራይ_ክልል በግጭት የተጎዱ አርሶ አደሮችን ምርታማነት ለማሳደግ ፦ 👉 በማዕከላዊ፣ 👉 በምስራቅ ፣ 👉 በደቡብ ምስራቅ እና በደቡብ ዞኖች ለሚገኙ ለ20,000 አባውራዎች (120,000 ግለሰቦች) የአፈር ማዳበሪያ በማከፋፈል ላይ እንደሚገኝ ዛሬ አሳውቋል።…
#ICRC

ICRC ለተፈናቃይ አባወራዎች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ በግጭት የተፈናቀሉ አብዛኛዎቹ ሰዎች በሕይወት ለመቆየት በሰብአዊ እርዳታ ላይ ጥገኛ መሆናቸውን አመልክቷል።

በመጠለያ ካምፖች ውስጥ ያሉ ተፈናቃይ ሰዎች ደግሞ ምንም አይነት አስተማማኝ የኢኮኖሚ ምንጭ የላቸውም ሲል ገልጿል።

በዚህም ምክንያት በአማራ ክልል ፦ ሰሜን ወሎ ዞን፣ ሃብሩ ወረዳ፣ ጃራ የተፈናቃዮች መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ 3,674 #ተፈናቃይ_አባወራዎች (22,044 ግለሰቦች) መሰረታዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን አሳውቋል።

@tikvahethiopia