TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
' የትምህር ቤት ክፍያ '

የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የ2015 የትምህርት ዘመንን የክፍያ ጭማሪ አስመልክቶ ከትምህርት ቤቶች ጋር ምክክር አድርጎ ነበር።

በዚህም ፥ በ2014 ዓ/ም ጭማሪ ያደረጉ ትምህርት ቤቶች በ2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ምንም አይነት ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ ተገልጿል።

ነገር ግን ላለፉት 2 እና 3 አመታት ጭማሪ ሳያደርጉ የቆዩ ትምህርት ቤቶች በሚያቀርቡት ፕሮፖዛል እና ከወላጅ ጋር በሚያደርጉት መግባባት መሰረት ጭማሪ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፎቻቸውን ጨምሮ 2 ሺህ ገደማ የግል ትምህርት ቤቶች አሉ፡፡ እነዚህ ትምህርት ቤቶች 400 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎችን ያስተናግዳሉ ፤ ይህም ከአጠቃላይ የአዲስ አበባ የተማሪ ሽፋን 43 በመቶውን ይይዛል፡፡

#AMN

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዮናስንጉሰ #ሔለንበርኸ👏 በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሀገሪቱ ከፍተኛውን ውጤት ያመጣው የትግራይ ፣ የቓላሚኖ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪው ዮናስ ንጉሰ ነው። በትግራይ ሀገር አቀፉ ፈተና ከ700 መሰጠቱ ይታወሳል። ተማሪ ዮናስ ንጉሰ ከ700ው 675 በማምጣት በሀገር ደረጃ ታሪካዊ ነው የተባለውን ውጤት አስመዝግቧል። ከዚህ ቀደም ከ700 በተሰጠ ፈተና ይሄን ያህል ከፍተኛ ውጤት (675)…
👏 #ሲፈን_ተክሉ

የአዲስ አበባዋ ተማሪ ሲፈን ተክሉ በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600ው 575 በማምጣት ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች።

ሲፈን የኦግዝሌየም ካቶሊክ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት።

ተማሪዋ " ጌዜን ትምህርት ላይ ማሳለፌ ፣በቡድን ማጥናቴ ፣ የቤተሰብና የመምህራኖቼ ድጋፍ ለዚህ ስኬት አብቅቶኛል " ብላለች።

ለቤተሰቦቿ 2ኛ ልጅ የሆነችው ሲፈን የስርዓተ ምግብ ባለሙያ የመሆኑ ዝንባሌ እንዳላትም ተናግራለች። #AMN

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia

አትሌት መሠረት ደፋር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ አባል ሆና ተመርጣለች።

አዳዲሶቹ የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚዎች እነማን ናቸው ?

1. አትሌት ስለሺ ስህን -ፕሬዚዳንት
2. አትሌት መሠረት ደፋር -ስራ አስፈጻሚ አባል
3. ወይዘሮ ሳራ ሐሰን- ስራ አስፈጻሚ አባል
4. ወይዘሮ አበባ የሱፍ -ስራ አስፈጻሚ አባል
5. ዶክተር ኤፍረህ መሀመድ -ስራ አስፈጻሚ አባል
6. አቶ ጌቱ ገረመው -ስራ አስፈጻሚ አባል
7. አቶ አድማሱ ሳጂ -ስራ አስፈጻሚ አባል
8. አቶ ቢኒያም ምሩጽ -ስራ አስፈጻሚ አባል እንዲሁም
9. ትዕዛዙ ሞሴ (ዶ/ር) ለመጪዎቹ 4 ዓመታት ብሄራዊ ፌዴሬሽኑን እንዲመሩ ተመርጠዋል።

ስራ አስፈጻሚ አባላቱ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንትና አቃቤ ንዋይ ይመርጣሉ።

#AMN

@tikvahethiopia